የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የዕለቱ ሁነቶች !

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ስር የተከወኑ የሀምሌ 15/2017 ዓ.ም የዕለቱ ሁነቶች !

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🔸ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ወረዳ ከ18 በላይ የብልፅግና አድማ ብተና አባላት በመደምሰስ ከ16 በላይ በማቁሰልና 15 ፈቅዶ እንዲቀላቀል በማድረግ አንፀባራቂ ተጋድሎ ፈፅመዋል።
🔸የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳምነው ኮር የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ወረዳ የሚገኘው የብልፅግና ወንበር አስከባሪ አድማ ብተና አባላት ላይ ጥቃት በመፈፀም 18ቱ ሲደመሰሱ 16ቱ ቆስለዋል።
በዚህ አውደ ውጊያ የውባንተ አባተ ክፍለ ጦር አራት ሻለቃዎች መቶ አለቃ ዳንዔል መለሰ፣ኮሎኔል ሰሎሞን አሻግሬ፣አይሻ ሙሀመድ እና ዋግሹም አድማሱ ሻለቃዎች ላይ የተውጣጡ ፋኖዎች የተሳተፉበት ሲሆን ደብረ ዘቢጥ፣ኮኪት፣አግሪት፣ጫት ውኃ፣ፍላቂትና ገረገራ መሽጎ በነበረው የአገዛዙ ሎሌ በሆነው አድማ ብተናና ፖሊስ አባላት ላይ ሐምሌ 14 / 2017 ዓ.ም ጥቃት አድርሰውበታል።

በዚህ ኦፕሬሽን 18 የተሰዋ፣16 የቆሰለ፣ 18 ክላሽ፣አምስት የወገብ ትጥቅ፣450 ተተኳሽ የተማረከ ሲሆን 11 ሚሊሻዎች እና አራት አድማ ብተና አባላትም የአገዛዙን ግፍና መከራ በመቃወም ወደ አድማ ብተና አባላት አፈሙዝ አዙረው እየተኮሱ የውባንተ አባተ ክፍለ ጦር ፋኖዎችን ተቀላቅለዋል።

🔸ተጠናክሮ በቀጠለው የምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር የራያ ቆቦ ዞብልና ቀዩ ጋሪያ ተጋድሎ ትናንት ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም ከሰዓትና ማምሻውን 1ኛ ሻለቃ ዞብል ተሮ በር ላይ የተረፈውን የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት መንገድ ላይ ደፈጣ ጥሎ በመጠበቅ ኦራል ላይ እንዳለ ሙሉ ለሙሉ ደምስሰውታል::

ራያ ቆቦ ዞብል ተሮ በር ላይ በዞብል አምባ 3ኛ (ራያ ሻለቃ) በርካታ ሃይሉ ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ ሆኖ ከባድ ኪሳራ የደረሰበት የጠላት 49ኛ ክፍለጦር በተመሳሳይ ሰራዊቱን ወደ ቆቦ ከተማ እያሸሸ ባለበት የአፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ ዞብል አምባ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ መንገድ ላይ በደፈጣ ጥቃት ኦራል ተሽከርካሪ ላይ ባለበት በርካታ ሃይሉን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ዙ23ቱን ይዞ እርሻ ለርሻ እንዲፈረጥጥ አድርጋዋለች::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል !

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም