የመንግሥት ሠራተኞች “የፖለቲካ ቁማር መያዣ” ተደርገዋል

እናት ፓርቲ፣ የመንግሥት ሠራተኞች “የፖለቲካ ቁማር መያዣ” ተደርገዋል ብሎ እንደሚያምን ባወጣው መግለጫ ገልጧል። ፓርቲው፣ ኑሮ የከበዳቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ለመብታቸው በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ጥሪ አድርጓል። ከወቅታዊው የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅ አኳያ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ባስቸኳይ እንዲታይና መንግሥት የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን እንዲቀይስም ፓርቲው ጠይቋል። ፓርቲው፣ የፌደራል ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን ሊተገብረው አስቧል ያለው የሠራተኛ ቅነሳ “ከጅምላ ፍጅት” ተነጥሎ አይታይም በማለትም ቅነሳ እንዳይካሄድ አሳስቧል።