5 የፖለቲካ ድርጅቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ላይ ያነሱት ቅሬታ
በማርክሲስት ሌኒኒስት ርዕዮተ ዓለም ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት አልሞ የተቋቋመው ኢሕአፓ ከደርግ ጋር ባካሄደው የከተማና የገጠር ውጊያ በርካታ አባላትና ደጋፊዎቹ ተገድለዋል፤ ታስረዋል የደረሱበት ያልታወቀም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተወያዩ

አወዛጋቢ ታሪክ ያለው ፓርቲው ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ የተለያዩ አንጃዎች ተፈጥረዋል። ከመካከላቸው በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ሀገር ቤት የገባው የኢሕአፓ ቡድን፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ከዛሬ ስድስት ዓመት አንስቶ እየተንቀሳቀሰ ነው ። የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቤ ብሊይ አብርሀም ሃይማኖት የዛሬው አንድ-ለ-አንድ ዝግጅታችን እንግዳ ናቸው ። ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከድምጽ ማዕቀፉ ማዳመጥ ይቻላል።