DW Amharic : የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) በኤርትራ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ በኤርትራ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና በሌሎች የሲቪክ ማህበራት አዘጋጅነት ኢትዮጵያ ውስጥ ትናንት እሁድ ተዘጋጀ በተባለው የቀይ ባሕር አፋር ጉባኤ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተገኝተዋል፡፡
የቀይ ባሕር አፋር በኢትዮጵያ ያካሄደው ሕዝባዊ ጉባኤ
የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) በኤርትራ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ በኤርትራ በተቃዋሚነት የምንቀሳቀሰው የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና በሌሎች የሲቪክ ማህበራት አዘጋጅነት ኢትዮጵያ ውስጥ ትናንት እሁድ ተዘጋጀ በተባለው የቀይ ባሕር አፋር ህዝባዊ ጉባኤ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የማህበረሰቡ አካላት ታዳሚ ነበሩም ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሽኩቻ መሰል ዉጥረት በጎላበት ባሁን ወቅት በኤርትራ መንግስት በቀይ ባህር አፋር ህዝብ ላይ ይፈጸማል የተባለው ሰቆቃ መጉላቱን ያሳወቀው ጉባኤው ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ የትኩረት ጥሪ አሰምቷልም።ትግራይ ክልል የእርስበርስ ግጭት እንዳይከሰት ሥጋት መፈጠሩን የሲቪክ ተቋማት ገለጹ
የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ ድርጅት አመራሮች፣ የስደተኞች ተወካዮች፣ የጎሳ መሪዎች እና የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት ተሳትፈውበታል የተባለው ትናንት በአፋር ክልል ሰመራ-ሎጊያ ከተማ ላይ የተካሄደው ህዝባዊ ኮንፌረንስ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለስልጣናት መካከል የቃላት ጦርነትን ተከትለሎ ባሁኑ ወቅት በድንበር አከባቢዎች ላይ ውጥረት መንገሱን ያመለከተው አንዱና ዋነኛው የጉባኤው ተሳታፊና አዘጋጅ የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ድርጅት ((RSADO) የቀይ ባሕር አፋር ህዝብ የጦርነት ሜዳ እንዳይሆን አስግቶናል ይላል፡፡ ከአከባቢው ድንበር ዙሪያ የህዝብ ማፈናቀል ብሎም እሰከ 60 ዓመት አዛውንት ወደ ጦር ካምፕ ስልጠና ማስገባት ብሎም ህዝቡ ወደ አጎራባች አገራት እንዳይወጡ ድንበርችን በመዝጋት ሰቆቃዎች ይፈጸማልም ይላል።

ወቅታዊውን የኤርትራ መንግስትን “አምባገነን” ሲል የጠራው የጉባኤው መግለጫ “የቀይ ባህር ህዝብ የራሱን እጣ በራሱ ለመወሰን” እንደምንቀሳቀስና የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ በዓላማው ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡ አስተያየታቸውን ለ ዶይቼ ቬለ የሰጡ የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሀሩን የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት በሻከረበት ባሁን ወቅት በተለይም አዋሳኙ አከባቢ ያለው ህዝብ ከፍተኛ ፈተና ያለበትን ጊዜ እያሳለፈ ነው በማለት የህዝባዊ ጉባኤውን ዓላማ አብራርተዋል፡፡ “ህዝባችን የከፋ ችግር ውስጥ ይገኛል፤ በድንበር አከባቢ ያለው ህዝብ የጦርነት ምሽግ ቁፋሮን በመሸሽ ይሰደዳል” ያሉት አቶ ኢብራሂም ተማሪና አዛውንቶችም ጭምር ወደ ጦር ካምፕ በግድ እየተጋዙ ነው ብለዋል፡፡ “የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ላይ እልቂት ይፈጸማልም” የሚሉት የድርጅቱ ኃላፊ የአከባቢው አገራት እና ዓለማቀፉ ማህበረሰብ ህዝቡ ላይ ይፈጸማል ያሉትን ሰቆቃ ለማስቆም እንዲተባበሩም ጉባኤው መጠየቁን አስረድተወዋልም፡፡ በጉባኤው በሁሉም አገራት ውስጥ ያሉ የአፋር ህዝብ መብት እንዲከበርና በተለይም የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይላት የጋራ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪም የቀረበበት ነው ብለዋል፡፡በትግራይ ክልል የተከፋፈሉት ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ያስከተለው ስጋት
በጎርጎሳውያኑ 1999 የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚገለልጸው የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት 600 ሺህ ግድም የሚገመተውን የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለማጎናጸም ላለፉት 26 ዓመታት ትግሉን አንዴ በህቡዕ ሌላም ጊዜ በግልጽ መቀጠሉን ያስረዳል፡፡ አሁን ላይ በኢትዮጵያ አፋር ክልል ላከናወነው በሺዎች የምቆጠሩ የተለያዩ የማህበረሰቡ አካላት የተሳተፉበት ኮንፈረንስ ሲካሄድ በተለያዩ መንገዶች አንድነቱን የሚሳይ በተለያዩ አገራት ውስጥ ያለው የአፋር ህዝብ አጋርነቱን ያሳየበት ነው ብለዋል፡፡ የቀኝ ግዛት የአፋር ህዝብን በተለያዩ ሶስት አገራት ከፍሎታልም ያሉት አቶ ኢብራሂም ይህ የህዝቡ ፍላጎት እንዳልነበር በአስተያየታቸው ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ በኤርትራ ያለው መንግስት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ እንድትጠቀም ፍላጎት የለውም በማለት ስርዓቱን በመታገል የህዝባቸውንም ሆነ የኢትዮጵያን ፍላጎት ማስከበር ለነሱ በጎ አጋጣሚ መሆኑንም በአስተያየታቸው አስረድተዋል፡፡

ሌላው ከአውሮጳ መጥተው መታደማቸውን የገለጹት ጉባኤተኛ የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅ ከፍተኛ አመራር እና የኤርትራ ፖለቲካ ኃይሎች ምክትል ሊቀመንበር ያሲን መሀመድ አብደላ ትናንት በአፋር ክልል ክልል የተካሄደው በቀይባህር አፋር ህዝብ ላይ ያተኮረው ህዝባዊ ጉባኤ ትብብርን ያጠናከረ ብለውታል፡፡ “የትኛውም የማህበረሰብ አካላት ከወጣቶች፣ ሴቶች፣ ስደተኞች እና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ አካላት ተሰባስበው የተወያዩበት ነው” በማለት በጉባኤው ቀደምት የአፋር ህዝብ ትብብር የታየበትም ነው ብለዋል፡፡
ዶይቼ ቬለ ኢትዮጵያ ውስጥ በአፋር ክልል ተካሄደ ስለተባለው የኤርትራ ተቃዋሚዎቹ ጉባኤ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በተለይም ከአፋር ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልሰመረም፡፡ https://www.dw.com/am/