የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱ ታወቀ

የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ብቻ ሲካሄድ የቆየው የባንክ ስራ አገልግሎት፤ ከዛሬ ጀምሮ ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ የውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ከዛሬ ጀምሮ ማመልከቻዎቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማስገባት እንደሚችሉም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

አቶ ማሞ ምህረቱ በገዢነት የሚመሩት ብሔራዊ ባንክ ይህን ያስታወቀው፤ የውጭ ባለሃብቶች የባንክ ስራ ፈቃድ ለማግኘት እና ለማሳደስ የሚያስችላቸውን መመሪያ ይፋ ባደረገበት መግለጫ ነው። አዲሱ መመሪያ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የውክልና ጽህፈት ቤት ለመክፈት ማሟላት የሚያስፈልጋቸውን ቅድመ-ሁኔታዎችም ይዘረዝራል።

መመሪያው ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ዓመት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገው “ሰፊ ምክክር” ውጤት እንደሆነ የመስሪያ ቤቱ መግለጫ አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ለውጪ ባንኮች እና ለኢንቨስተሮች ተዘግቶ የቆየውን የባንክ ስራ ዘርፍ ለመክፈት ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ወደ ተግባር የገባው ከሶስት ዓመት በፊት ነበር።

🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16188/