
አገዛዙ በግፍ አፍኖ ያሰራቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአራቱ ጉባኤ መምህር እና የሁለት ገዳማት አበ እምኔት የኔታ ይባቤ በላይ ጨምሮ በቤተክርቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃና ግፍ እንዲሁም የታሰሩ የሐይማኖት አባቶች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሰላማዊ ሰልፈኛው ጠይቋል።
በሰልፉ ላይ የተስተጋቡ መፈክሮች መሀልም
-ብልፅግና ከቤተክርቲያናችን ላይ እጁን ያንሳ!
-ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተክርስቲያንን እና መምህራኖቻችንን ያስከብር !

-የአብነት ተማሪዎችን እና መምህራንን በማሰር የሚገኝ ድል የለም።
-ፍትህ ለአባታችን
-ሀይማኖት እና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው እና ሌሎችም ይገኙበታል።
በመጨረሻም አባታችን እስካልተፈቱ ድረስ ሁሉን አቀፍ ትግል እንደሚደረግ ተስማምቶ በአባቶች ብራኬ እና ቃለ ምእዳን ተሰጥቶ ሰልፉ ተጠናቋል።