- ጦርነቱ ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ይሁን ?
🇮🇷” ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል (የሆርሙዝ መዘጋት) ” – ኢራን
- 🇺🇸” አራን ሰርጡን ብትዘጋ መጥፊያዋ ይሆናል ” – አሜሪካ
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት የደኅንነት ምክር ቤቱን ውሳኔ እየጠበቀች ነው።
የአለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚቀርብበትን የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲዘጋ የኢራን ፓርላማ ሲወስን የደኅንነት ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሚገኝ የኢራን የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የጦርነቱ ሂደት ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ሲሆን ስለ ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የተጠየቁት የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም ” ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል ” ብለው መልሰዋል።
የአያቶላህ አሊካሚኒ ከፍተኛ አማካሪም ሃገራቸው በአሜሪካ በተጠቃች በኋላ ኢራን ሰርጡን መዝጋት እንዳለባት እና የአሜሪካን መርከብ ማጥቃት እንዳለባት ሲገልፁ ነበር።
የምክር ቤቱ ውሳኔ የአለምን ኢኮኖሚ በተለየ ሁኔታ የነዳጅን ዋጋ ሊያሻቅብ የሚችል ሲሆን የሚሰጠው ውሳኔ ይጠበቃል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ምክትል ፕረዚዳንት ጄዲ ቫይንስ ፤ የኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋት መጥፊያዋ እንደሚሆን ገልየዋል።
ቫይንስ ሃገራቸው አሜሪካ ወደ ጦርነት ውስጥ የገባችው ከኢራን ጋር ሳይሆን ከኒውኪሊየር ፕሮግራሟ ጋር እንደሆነ ተናግረዋል።
በ100% መተማመን የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች አጥፍቷል ወይ ? በሚል ተጠይቀው “ወደ እንደዚህ አይነት የደህንነት መረጃዎች መግባት አልፈልግም፤ የአሜሪካ የምሽቱ ጥቃት ግን የኢራንን ኒውኪሊየር የመታጠቅ አቅም በእጅጉ አዘግይቶታል ” ብለዋል።
ጥቃቱን ተከትሎ ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ያለውን የመርከብ እንቅስቃሴ ልትረብሽ ትችላለች በሚል የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ “እሱ ለኢራን መጥፊያዋ ይሆናል” ሲሉ መልሰዋል።
ሆርሙዝ ቢረበሽ ምን ይፈጠራል ?
– ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣ ኩዌት ኢራቅ ፣ ኳታር አብዛኛውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋር ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩት በሆርሙዝ ሰርጥ ነው።
– ነዳጅ ላኪዎች የሚጠቀሙበት ሰርጥ ስለሆነ የነዳጅ እጥረት ይከሰታል በመሆኑም ዋጋው ይወደዳል።
– ብዙ ሀገራት በዚህ ሰርጥ በሚመጣው ነዳጅ ነው ኢኮኖሚያቸው የሚንቀሳቀሰው በመሆኑም ሰርጡ ቢረበሽ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ይፈጠራል።
– የተለያዩ ሸቀጦችም፣ የኢንዱስትሪ እቃዎች፣ ምርቶች በመርከብ በዚህ ሰርጥ ያልፋሉ ይህ ሰርጥ ቢረበሽ የሎጂስቲክስ ስራዎች ችግር ይገጥማቸዋል የዓለም የንግድ ስርዓት ላይም ትልቅ ችግር ይፈጠራል። ዋጋም ይወደዳል።
መረጃው ከተለያዩ የውጭ ሀገራት መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰበ ነው።