ኢሠማኮ፣ ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8 ሺሕ 384 ብር የኾኑ ሠራተኞች ከደመወዝ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ ኢሠማኮ፣ በወር ከ8 ሺሕ 384 ብር እስከ 22 ሺሕ 974 ብር የሚያገኙ ሠራተኞች 10 በመቶ፣ ከ22 ሺሕ 975 እስከ 44 ሺሕ 530 ብር የሚከፈላቸው 15 በመቶ፣ ከ44 ሺሕ 531 እስከ 72 ሺሕ 336 ብር የሚከፈላቸው 20 በመቶ እንዲኹም ከ72 ሺሕ 337 እስከ 107 ሺሕ 449 ብር የሚከፈላቸእ የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መጠየቁን ዘገባው ጠቅሷል። ከ107 ሺሕ 450 እስከ 150 ሺሕ 107 ብር ባለው ደመወዝ ላይ 30 በመቶ ግብር እና ከ150 ሺሕ 108 ብር በላይ ደሞዝ ላይ ደሞ 35 በመቶ ግብር እንዲጣል ኢሠመኮ ጠይቋል ተብሏል።
አዲሱ ግብር የሚከፈልበት የደሞዝ መጠን! የኢሠማኮ አማራጭ ቁጥሮች!
በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የሰራተኞች የደሞዝ ግብር መጠን በገንዘብ ሚኒስትር ረቂቁ ቀርቦ ውይይት ላይ ነው!
ነገር ግን በመንግስት እየቀረበ ያለው የደሞዝ ግብር መጠን (ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ደሞዝ) እና የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ያቀረቡት መነሻ የሰማይ እና የምድር ያህል ልዩነት አለው!
የተቀመጠውን የደሞዝ እና የግብር መጠን በዝርዝር ከነምክንያቱ እንመልከተው…. https://youtu.be/dAydraFIzwk