አሜሪካ በየመን በአፍሪካዊያን ፍልሰተኞች ማዕከል ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በትንሹ 68 ሰዎች መገደላቸውን ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች የሁቲዎችን ቴሌቪዥን ጠቅሰው ዘግበዋል። በጥቃቱ ሌሎች 47 ሰዎች መቁሰላቸውን የጠቀሱት ዘገባዎቹ፣ አንዱ ኢትዮጵያዊ እንደኾነ አመልክተዋል። ፔንታጎን ፍልሰተኞች የጥቃቱ ሰለባ በመኾናቸው ዙሪያ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው ነገር የለም። በየመን ጊዜያዊ የፍልሰተኞች ማቆያ ማዕከላት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ መሻገር የሚፈልጉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች ይገኛሉ።