አሜሪካ በሕወሓትና በትግራይ ጸጥታ ኃይሎች ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ልትጥል ነው

አሜሪካ በሕወሓትና በትግራይ ጸጥታ ኃይሎች ውስጥ ሥልጣን ባላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ልትጥል እንደምትችል አንድ የአገሪቱ ባለሥልጣን እንደነገሩት ጠቅሶ ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ አስነብቧል።

አሜሪካ ማዕቀብ ለመጣል እያሰላሰለች ያለችው፣ ትግራይ እንዳትረጋጋ እንቅፋት በኾኑና ክልሉ በድጋሚ ጦርነት እንዲያመራ እያደረጉ ይገኛሉ በምትላቸው ግለሰቦች ላይ እንደኾነ ባለሥልጣኑ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

አሜሪካ ማዕቀብ መጣልን እንደ አማራጭ ያየችው፣ የተወሰኑ የትግራይ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ወታደራዊ አዛዦች ጌታቸው ረዳ በሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ ከሳምንታት በፊት የመፈንቅለ ሥልጣን ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።