ኢንተርናሽናል ሜዲያ ሳፖርት የተሰኘው ዓለማቀፍ ተቋም፣ በኢትዮጵያ ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት የጋዜጠኞች ደኅንነት እጅግ አሳሳቢ ኾኖ መዝለቁን አዲስ ባወጣው ሪፖርት ገልጧል።
በዓመቱ 43 ጋዜጠኞቹ እንደታሠሩ ወይም እንደታገቱና ከታገቱት ሦስቱ መካከል ኹለቱ እስካሁን የደረሱበት እንዳልታወቀ ሪፖርቱ ጠቅሷል።
በጋዜጠኞች ላይ በጣም አሳሳቢ ጥሰቶች የተፈጸሙት፣ የግጭት ተጋላጭ በኾኑና በድኅረ-ግጭት የማገገም ሂደት ላይ ባሉ ክልሎች ውስጥ ነው ተብሏል።
መንግሥት ጋዜጠኞች መረጃ የማግኘትና የመረጃ ምንጫቸውን በሚስጢር የመያዝ መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ሙሉ ፖለቲካዊ ድጋፍ እንዲሠጥ የጠየቀው ተቋሙ፣ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኀን ተቋማት ለፍርድ ቤት የጠበቃ አገልግሎት የገንዘብ ድጋፍና ለሕክምና ወጪዎች የገንዘብ ዕርዳታ የሚያስገኝ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ መስጫ ሥርዓት እንዲቋቋም ጠይቋል።