የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጦራቸው ከካርቱም መውጣቱን አመኑ።

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጦራቸው ከካርቱም መውጣቱን አመኑ።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ የሆኑት መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሱዳን ጦር ካርቱምን ከተቆጣጠረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ከጦሩ ጋር የሚያደርጉት ውጊያ እንዳላበቃና ወደ ካርቱም ዳግም እንደሚመለሱ ተናግረዋል።

ዳጋሎ አክለውም ጦራቸው ከዋና ከተማዋ መውጣቱን ያመኑ ሲሆን የወጣነው ግን በአመራሮቻችን በተወሰነ ታክቲካዊ ውሳኔ ራሳችንን በኦምዱርማን ለማደራጀት ነው ብለዋል።

የጦር መሪው አክለውም ጠንክረን እንመለሳለን ያሉ ሲሆን ድርድር እና ስምምነት አለ ብላችሁ የምታስቡምም ከጦር ውጪ ቋንቋ እንደሌለ እወቁት ብለዋል።

የሱዳን ጦር ዋና ከተማዋን ካርቱምን የያዘ ሲሆን ትናንት በኦምዱርማን የሚገኘውን ቁልፍ የገበያ ቦታ መያዙም መነገሩ ይታወሳል።

የጦሩ መሪ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃንም ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ይቅርታ እንደማይኖር ሲናገሩ ቡድኑን ከማጥፋት ውጪ ምንም ድርድርም የለም ብለዋል።

በሱዳን ላለፉት ሁለት አመታት የቀጠለው የእርስ በእርስ ጦርነት የቀጠለ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ቀውስም የተመዘገበበት ጦርነት ሆኖ ቀጥሏል።