ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንዲሁም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተው ነበር።

ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያን መስጠታቸው ታውቋል።

ምን ተባለ?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፦

” ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዳይተገበር እንቅፋት ሆኗል።

በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ የሰጠውን መመሪያ አልተቀበለም።

የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር እየሰራ ሲሆን መንግስት የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በጥሞና እየተከታተለ ነው።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት አስፈላጊውን እገዛ ሊያደርግ ይገባል ” ብለዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የዕለት ተለት ተግባራት ላይ እክል እየፈጠረ መጥቷል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የፌደራል መንግሥት በክልሉ ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ” ብለዋል።