ኬንያ፣ የኢትዮጵያው የዳሰነች ጎሳ ታጣቂዎች በኬንያ ቱርካና አሳ አስጋሪዎች ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት ከጠፉ ከ20 በላይ ኬንያዊያን መካከል የኹለቱን አስከሬን በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ትናንት ማግኘታቸውን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
የኹለቱ ኬንያዊያን አስከሬኖች የተገኙት፣ የኬንያ ባለሥልጣናት በጥቃቱ ወቅት የደረሱበት ያልታወቁ ኬንያዊያን ዜጎችን በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዲያፈላልጉ የኢትዮጵያ መንግሥት ፍቃድ መስጠቱን ተከትሎ እንደኾነ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።
የዳሰነች ጎሳ ታጣቂዎች በቱርካና አሳ አስጋሪዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት፣ በርካታ ኬንያዊያን የደረሱበት እንዳልታወቀ ዘገባዎች አመልክተዋል።
የዳሰነች ታጣቂዎች በቱርካና አሳ አስጋሪዎች ላይ ጥቃት የፈጸሙት፣ የኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች ከቀናት በፊት ዳሰነች ወረዳ ውስጥ ላደረሱት ጥቃት አጸፋ እንደኾነ ተነግሯል።