የጮቄው በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ አዲስ የድሮን መቆጣጠሪያ ተተከለ

የብልጽግናው መንግስት ንጹሃን እየተገደሉ ለሚገኙበት የድሮን ጥቃት ማስፈጸሚያ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ዮፍታሔ ንጉሴ አዳራሽ ጎን የድሮን መቆጣጠሪያ አንቴና መትኩሉ ታውቋል።

ብልጽግና በደ/ማርቆስ ከተማ የድሮን መቆጣጠሪያውን የተከለው ከዚህ በፊት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በቀጠናው ጮቄ ተራራማ አካባቢ ተክሎ ሲጠቀሙበት የቆየውን አንቴና መቆጣጠር ባለመቻሉ ነው።

የጮቄው መቆጣጠሪያቸው በፋኖ ቁጥጥር ስር ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ከስራ ውጭም ስለተደረገ አዲስ መቆጣጠሪያ በደብረ ማርቆስ ተክለዋል።