የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ለመኖር የሚያስችል ፈቃድ በ5 ሚሊየን ዶላር ለሽያጭ አቀረቡ።
ከዚህ ቀደም ከሚታወቀው አረንጓዴ ካርድ (የመኖሪያ ፈቃድ) ጋር የሚስተካከለውና 5 ሚሊየን ዶላር የመክፈል አቅም ላላቸው የሚቀርበው ወርቃማው ካርድ በቀጣዮቹ ቀናት ለገዥዎች ክፍት ይሆናል።
ወርቃማው ካርድ በሂደት የአሜሪካ ዜግነትንም ያስገኛል ተብሏል።
የአረንጓዴ ካርድ ዕጣ ፈንታን በተመለከተ ፕሬዝዳንቱ አስተያየት አልሰጡም።
ስለጉዳዩ የሚያውቁ ግን ፕሬዝዳንቱ አረንጓዴ ካርድን የመገደብ ፍላጎት አላቸው። አዲሱ ወርቃማ ካርድ ተሽጦ የሚገኘው ገንዘብ የአሜሪካን የበጀት ጉድለት ለሟሟላት ይውላል።