ምዕራባዊያን ዱፕሎማቶች በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጥረቱ መባባሱን ተከትሎ በመካከላቸው ወታደራዊ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው አፍሪካ ኢንተለጀንስ ድረገጽ ዘግቧል።
በተለይ የአንዱ የሕወሓት ቡድን አመራሮች ከኤርትራ መንግሥት ጋር ቅርርቦሽ መፍጠሩ፣ ለግጭቱ መቀስቀስ ምክንያት ሊኾን ይችላል የሚል ስጋት በዲፕሎማቶቹ ዘንድ እንዳለ ዘገባው ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ በቅርቡ በትግራይ ጉብኝት ያደረጉ ጊዜ፣ ሕወሓት ከአስመራ ጋር የጀመረውን “አደገኛ ቅርርቦሽ” ለሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል አንስተውላቸው እንደነበር ዘገባው አመልክቷል። https://www.africaintelligence.com/eastern-africa-and-the-horn/2025/02/24/tigray-leaders-dangerously-torn-between-addis-ababa-and-asmara,110378687-eve