በኢትዮጵያ እና በኬንያ አሳ አጥማጆች መካከል በተፈጠረ የድንበር ግጭት 13 ኢትዮጵውያን ሲገደሉ፣ ሶስቱ ቆሥለዋል፤ በተጨማሪም ሁለት ዜጎች የገቡበት አልታወቀም፣ በአንፃሩ 22 ኬንያውያን የገቡበት መጥፋቱን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡ ዓለም አቀፍ የመገናኛ አውታሩ መረጃውን የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት አረጋግጠውልኛል ብሏል።
ግጭቱ ቅዳሜ አመሻሽ ላይ በኦሞ ወንዝ አካባቢ በሁለቱ ሀገሮች ድንበር ላይ መከሰቱን የኬንያ ቱርካና ካውንቲ አስተዳዳሪ ኤርሚያስ ሎሞሩካይ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ስየስ ቀበሌ ነዋሪዎች ነገሩኝ ብሎ አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው፣ የኬንያ ታጣቂዎች “ስድስት ጀልባዎችን ጨምሮ 130 የሚደረሱ የአሣ ማጥመጃ መረቦች፣ እስከ 500 ሺህ የሚደርሱ ደረቅ አሣዎች እና በርካታ ንብረቶችን” መወሰዳቸውን ጽፏል።
በደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ዋና የመንግሥት ተጠሪ የሆኑት መሳይ ሊበን፤ “የኬንያ መንግሥት የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ለሚመጡ ታጣቂዎቹ ከተሽከርካሪ አንስቶ እስከ ተተኳሽ የጦር መሣሪያዎች ድጋፍ ማድረጉን” ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኪፕቹምባ ሙርኮመን እሁድ ዕለት በኤክስ ገፃቸው ላይ እንደፃፉት፣ መንግሥት በድንበሩ ላይ ተጨማሪ ጥበቃ ማሰማራቱን እና “በሁለቱ ማኅበረሰቦች መካከል ሰላም ለመፍጠር” ከአዲስ አበባ ጋር እየተገናኘ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
ኢትዮጵያ አንፃራዊ ሰላም ያለው የድንበር ግንኙነት ከኬንያ ጋር ያላት ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኬንያ በኩል የእርሻ እና ግጦሽ መሬትን በሃይል ለመንጠቅ እንደዚሁም ውሃ ፍለጋ የሚደረጉ መተናኮሶች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ እንደሆነ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ እነዚህ ግጭቶቹ በአካባው ሽማግሌዎች፣ አለፍ ሲልም የአካባቢ የመንግሥት አስተዳደሮች እልባት ሲሰጡት መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይ በቅርቡ ከጅቡቲ የተነሳ ድሮን በኢትዮጵያ አፋር ክልል ጥቃት ማድረሱ በሃገር ውስጥ የተለያዩ አካላት ዘንድ ቁጣ የቀሰሰ ክስተት እንደነበር ይታወሳል፡፡ በደቡብ ሱዳን የሙርሌ ብሄር ጥቃት እና ተደጋጋሚ ትንኮሳም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን፣ አልፋሽጋን እንደምክንያት በመጥቀስ የሱዳን ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ወደኢትዮጵያ ድ