በሙስና ተጀምሮ በሙስና ተደግፎ በአብይ አሕመድ የተመረቀው የጅግጅጋ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከአገልግሎት ውጪ መሆኑ እያነጋገረ ነው።

የጅግጅጋ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ገና በስምንት ወራት ውስጥ ከአገልግሎት ውጭ እየኾነ መኾኑንና በነባሩ የውሃ መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረሱን በምርመራ ማረጋገጡን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል።

የፕሮጀክቱ ተቋራጭ የቻይናው ኩባንያ፣ ሪፖርተር ካሁን ቀደም በፕሮጀክቱ ችግሮች ዙሪያ ያተማቸውን ዘገባዎች እንዲያስተባብል በጠበቃዎቹ በኩል ተደጋጋሚ ግፊት ማድረጉን ዘገባው ጠቅሷል።

በስምምነቱ መሠረት ፕሮጀክቱ በተጠናቀቀ ባንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ችግር ቢያጋጥመው ተቋራጩ በራሱ ወጪ ማስተካከል እንዳለበት በፕሮጀክቱ ስምምነት ላይ የተቀመጠ መኾኑን የጠቀሰ ጋዜጣው፣ ኾኖም ተቋራጩ ከቀነ ገደቡ በፊት የምስክር ወረቀት እንደተሠጠው ምንጮች እንደነገሩት ገልጧል።

የክልሉ የውሃ ቢሮ በፕሮጀክት ስምምነቱ መሠረት አንድ ዓመት ሳይሞላው ገና በአምስተኛው ወር ላይ በተቋራጩ ጥያቄ መሠረት የዋጋ ክለሳ በማድረግ፣ የፕሮጀክቱን 20 በመቶ ማለትም 150 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ክፍያ ለተቋራጩ መክፈሉንም የምርምራ ዘገባው ያሳያል።

ፕሮጀክቱን ከተቋራጩ ጋር የተፈራረመው የክልሉ ውሃ ልማት ቢሮ፣ ባለፉት ስድስት ዓመታት ግልጽ ባልኾኑ ምክንያቶች ሦስት ጊዜ ሹሞች እንደተቀያየሩበትም ዘገባው ጠቅሷል።