በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጥቃት የደረሰባቸው የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ሕይወታቸው አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ ረቡዕ’ለት በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው ፍቼ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ የነበሩት የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዝናቡ በለጠ፣ ሐሙስ ሌሊት ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል።

የጽሕፈት ቤት ኃላፊው ከታጣቂ ቡድኑ ጥቃት ለማምለጥ ሲሞክሩ ድንጋያማ ገደል ውስጥ ገብተው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸውና፣ አብረዋቸው የነበሩት የወረዳው የጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ታደሠ ተፈሪ ደሞ ወዲያው ሕይወታቸው ማለፉን ይታወሳል።

የወረዳው የኮምኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ትናንት ባወጣው መግለጫም፣ ኹለቱም የወረዳው አመራሮች ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጧል።

የኮምኒኬሽን ጽሕፈት ቤቱ በመግለጫው፣ “በአመራሮቹ ላይ የተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ልብ ይሰብራል” በማለት ድርጊቱን አውግዟል።