Blog Archives

የ2012ቱ ምርጫ እና የየፖለቲካ ቡድኑ ፍላጎት

በመጪው የኢትዮጵያ ዓመት - በ2012 ኢትዮጵያ መደበኛ አገር ዐቀፍ የሕዝብ እንደራሴዎች ምርጫ ታካሒዳለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምርጫውን አጓጊ የሚያደርገው ላለፉት አራት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲንጣት ከቆየው ሕዝባዊ አመፅ ቀጥሎ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የመስቀል በዓል በአዲግራት ከኤርትራዉያን ጋር

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዝያ ባሻገር ኢትዮጵያዊ እሴቶችን የያዘ ብዙ ሊባልለት የሚችል ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢ ሰዎች ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር የሚቀራረቡበት ፤ ከበአሉ ጋር ተያይዞ የተጣሉ የሚታረቁበት፤ ብዙ ልንዘረዝራቸዉ የምንችል መገለጫዎች ያሉት ክብረ በዓል ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ከብአዴን እና ከህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ ምን ይጠበቃል?

12 ኛዉ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጉባኤ ዛሬ ከቀትር በኃላ ባህርዳር ላይ ተጀምሮአል።ትናንት በመቐለ ከተማ በይፋ የተጀመረዉ 13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ/ህወሓት/  ድርጅታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ የተጀመረዉን የለዉጥ ሂደት ለማስቀጠል በሚያስችል ሁኔታ እንደሚወያይ ተገለጿል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ደቡብ ሱዳናዊዉ የሰብዓዊ ጉዳዮች ተሸላሚ

የደቡብ ሱዳን የሕክምና ዶክተር ኤቫን አታር አደሃ ፤ ስደተኞችን በመርዳት ላሳዩት የላቀ አስተዋፅኦ የ2018 የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት « UNHCR» ን ናንስን ሽልማትን አገኙ። ከጎርጎረሳዊዉ 1954 ጀምሮ የሚበረከተዉ ናንሰን ሽልማት ፤ ለስደተኞች ከፍተኛ ግልጋሎትን ባበረከቱት የኖርዌ ዜጋ በፍሪድጆፍ ናንሰን የተሰየመ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በተ.ዐ.ኤሚሬትስ ያሉ የኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች እጣ ፈንታ

የተባበሩት ዐረብ ኤሚሬትስ መንግሥት በሀገሩ የሚኖሩ፣ግን በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰሩ አሁን በሕጋዊነት መኖር ወይም ወደ ሀገራቸው መግባት ለሚፈልጉት የውጭ ዜጎች ከጎርጎሪዮሳዊው ነሃሴ አንድ  እስከ ጥቅምት 30፣ 2018 ዓም፣  ለሶስት ወራት የሚቆይ የምህረት አዋጅ አውጥቷል። የበርካታ ሀገር ዜጎች በዚሁ እድል በመጠቀም ላይ ናቸው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዓለም የቱሪዝም ቀን በጋምቤላ ተከበረ

የዓለም የቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያ ዘንድሮ በርካታ የተፈጥሮ ሐብት በሚገኝበት የጋምቤላ ክልል ላለፉት ሶስት ቀናት ተከብሯል። በክልሉ የአገር ጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ በርካታ መዳረሻዎች ቢኖሩም የመሰረተ-ልማት እጥረትን የመሰሉ ችግሮች ለዘርፉ ፈተና ሆነዋል። ነጃት ኢብራሒም የክልሉን ኃላፊ በበዓሉ አከባበር ላይ አነጋግራቸዋለች። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስደተኞች እና የአውሮጳ የፍልሰት ፖሊሲ

ሰሞኑን ከሊቢያ የባህር ጠረፍ የታደገቻቸውን 58 ስደተኞች ያሳፈረችው አኳሪየስ የተባለችው የነፍስ አድን መርከብ ማረፊያ ፍለጋ ቆይታ ወደ ፈረንሳይ ማርሴይ ወደብ ብታቀናም ለጊዜው ተቀባይነት ሳታገን መቅረቷ ይታወሳል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የደመራ በዓል በአክባሪዎቹ እይታ

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ የሚከበረው የደመራ በዓል በርካታ የእምነቱ ተከታዮች አደባባይ ወጥተው እንዳከበሩት DW ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአገር አቀፍ የፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች

በአሜሪካ ኤምባሲ አዘጋጅነት ለወራት የዘለቀው አገር አቀፍ የፈጠራ ውድድር አሸናፊዎቹ ታውቀው ባለፈው ቅዳሜ ተጠናቅቋል። በውድድሩ ወጣቶች በማኅበረሰባቸው ያስተዋሉትን ችግር ለመፍታት ያስችላል ያሏቸውን የፈጠራ ሥራዎች አቅርበዋል። ለመጨረሻው ውድድር ከቀረቡ 31 ፕሮጀክቶች ውስጥ ሦስቱ ተመርጠውም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጎሮ-አዲስ አበባ ነዋሪ ስሞታ

ሰሞኑን ከጥቃት ያመለጡ አንድ የአካባቢዉ ነዋሪ እንዳሉት በቡድን የተሰበሰቡ ወጣቶች በተለይ ማታ በየመንገዱ ዳርቻ እያደፈጡ ወደየቤቱ የሚገባዉን ነዋሪ ያጠቃሉ፤ ይዘርፋሉም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በነበር የቀሩት የአዲስ አበባ የግንባታ እቅዶች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሹማምንት ከዚህ ቀደም «በዋዛ የሚነኩ አልነበሩም» ያሏቸውን ጨምሮ ታጥረው የተቀመጡ 154 ቦታዎች ለመንግሥት ተመላሽ እንዲሆኑ ወስነዋል። ከ400 ሔክታር በላይ ከሚሆኑት ቦታዎች 90 በመቶው ከአጥር የዘለለ ግንባታ አልተሰራባቸውም። በሚድሮክ ኢትዮጵያ፣ በመከላከያ ሚኒስቴርና ኢትዮ-ቴሌኮም እጅ የነበሩ ይገኙበታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ

የዓለም አቀፉ ድርጅት ጉባኤ ከጉባኤዉ በፊት እንደተጠበቀዉ ለዩናይትድ ስቴትስ እና ለኢራን መሪዎች የመወዛገቢያ መድረክ ሆኗል።የተናጥል ወይም የግለኝነት አስተሳሰብ የሚያራምዱት የዩናያትድ ስቴትስ መሪ ዶናልድ ትራምፕ  በጋራ መርሕ ከሚያምኑት ከሌሎች ሐገራት መሪዎች ትችት አላመለጡምም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በፖሊስ ጥቃት የዓይን ብርኃኑን ያጣዉ የሽመና ሥራ ባለሞያ 

ባለፈዉ ሰሞን በአዲስ አበባና አካባቢዉ በነበረዉ ጥቃት የዓይን ብርኃኑን ያጣዉ የአዲስ አበባ ሽሮሜዳ አካባቢ ነዋሪ ፍትህን ጠየቀ። የጋሞ ተወላጅ የሆነዉና በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ በሽመና ስራ ይተዳደር የነበረዉ የ 33 ዓመቱ የልጆች አባት አቶ አስፋዉ ጭቦሮ የዓይን ብርኃኑን ያጣዉ በፖሊስ ድብደባ እንደሆን ለ«DW» ተናግሮአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አምነስቲ ወጣቶች በብዛት የታሰሩበትን ሁኔታ አወገዘ 

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአዲስ አበባ ፖሊስ በሰሞኑ ሁከት እና ግርግር ሰበብ በርካታ ወጣቶችን ማያሰረበትን እና የታሰሩበት አያያዛቸዉ ሰብዓዊ መብታቸዉን ያላከበረ ነዉ ሲል ርምጃውን በማውገዝ መግለጫ አወጣ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በጤናው ረገድ ማኅበራዊ ኃላፊነት

ማንኛውም የጤና ምርመራ እና ህክምና እጅግ ውድ ዋጋ መጠየቅ ከጀመረ ውሎ አድሯል። የሕክምና ምርመራ፤ የመመርመሪያ መሣሪያዎቹ እየረቀቁ እና ቴክኒዎሎጂው እያደገ በሄደ መጠን ዋጋውም እንዲሁ ከፍ እያለ አቅምን እየተፈታተነ መሄዱ የሚታይ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያዉያንን ያሰጋዉ የበር ላይ ምልክት

በኢትዮጵያ ለዉጥ ከተጀመረ ካላፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍል ለውጡን የደገፈና በለውጡ ተስፋ የሰነቀ መሆኑን በተለያዩ የድጋፍ ሰልፎች ሲገልፅ ቆይቷል። ያም ሆኖ ግን ለውጡን ተከትለዉ የተከሰቱ ግጭቶች ባደረሱት የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀል የተነሳ ፤
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች

ባለፉት 70 ዓመታት የጀርመንን እጣ ዕድልን የወሰኑት ትልልቅ የሚባሉት የሃገሪቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ከፖለቲካዉመድረክ እያሟሸሹ መሄዳቸዉን ጥናቶች እያመላከቱ ነዉ, ለዚህም ጠንካራዎች እየደከሙ ደካሞች እየጠነከሩ መምጣታቸዉ በጉልህ እየታየ መምጣቱ ነዉ የሚነገረዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአምስት ኦሮሞ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ 

የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት አንገብጋቢ የወቅቱን የፖለቲካ አስመልክቶ አምስት የኦሮሞ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ አወጡ። በመግለጫቸዉ የኦሮሞ ማንነትን ለማጥፋት እየተደረገ ያለዉን ሙከራ፤ ፊንፊኔን በተመለከተ የሚሉ ጉዳዮች ይገኙበታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በቁማር፤ በሃሺሻ፤ በጫት፤ ቤቶች ላይ ርምጃ ተወስዶአል

የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን: 1,200 ወጣቶች ጦላይ መላካቸዉን ፤ 174 በሕግ የሚጠየቁ ተጠርጣሪዎችን ማሰሩን እንዲሁም ፤ ሕገወጥ ቁማር ቤቶች ፣ ጫት ቤቶች ሺሻ ቤቶች ርምጃ መወሰዱን አስታወቀ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲሲቷን ኢትዮጵያ የመገንባት ውይይት

በኢትዮጵያ አሁን የተጀመረው ለውጥ በሁሉም ክልሎች እንዲቀጥል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መድረክ የአገሪቱ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን አሰባስቦ በሳምንቱ መጨረሻ በግዮን ሆቴል አወያይቷል። አገራዊ እርቅ፣ አገራዊ መግባባት፣ የተቋማት ተሀድሶ እንዲመጣ ይኸው ውይይት መቀጠል እንደሚኖርበትም በውይይቱ የተሳተፉት ተናግረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ወቅታዊዉ ግጭትና የደም ልገሳ

በተለያዩ አካባቢዎች  በተፈጠረዉ ግጭት ሳቢያ የደም እጥረት እያጋጠመ መሆኑን ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ። በግጭቱ  ደም የሚያስፈልጋቸዉ ተጎጅዎች  መበራከት እንዲሁም   መደበኛዉ  የደም ልገሳ ተግባር መስተጓጎል  ለእጥረቱ  ምክንያቶች መሆናቸዉ ተጠቅሷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጎዛ ዛር ጭዳዎች

የፌደራል ይሁን የክልል፤ የወረዳ ይባል የቀበሌ ባለሥልጣን ወይም  የፀጥታ አስከባሪ የሕዝብን ሠላም እና ደሕንነት ማስጠበቅ እንጂ ሕዝብ ከተገደለ፤ከተሰደደ በኋላ «ለቅሶ ደራሽ»፤ አስከሬን ቆጣሪ ፖለቲከኛ አያስፈልገዉም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰኞ መስከረም 14 ስፖርት

በዛሬው የዕለተ ሰኞ ምሽት የስፖርት ዝግጅት የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና እየደራ የመጣውን የተጫዋቾች የዝውውር ክፍያ የሚመለከት ጥንቅር፤ በአንፃሩ ደግሞ የሴቶች የእግር ኳስ ክለቦች ህልውና አደጋ ላይ መሆኑንም የሚዳስስ ዝግጅት ይኖረናል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የወደፊት እቅድ

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ፣ ኢህአፓ ከ46 ዓመት በኋላ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ገብቷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በውጪ ያሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር ግንባታ ወደ አገር እንዲገቡ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ ነው ከፍተኛው የፓርቲው አመራር ቡድን ሰሞኑን ወደ ሀገር የተመለሰው።  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የፎቶግራፍ ጋዜጠኝነት በፎቶግራፍ አንሺዎች ዓይን

የፎቶግራፍ ፍችው «በብርሃን መፃፍ» ማለት ነዉ። ይህም የተባለበት ምክንያት ፎቶ ካሜራን በመጠቀም ብርሃን-አነቃቂ ቁሳቁሶች ላይ በማተኮር የሚወሰድ ምስል ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዉይይት፤ ፍካት እና ፅልመት

የአዲስ አበባ እና ያካባቢዋ ግድያ የደረሰዉ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቀድሞዎቹ አማፂ ቡድናት፤ የአርበኞች ግንቦት ሰባት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ደጋፊዎች አዲስ አበባ ዉስጥ በባንዲራ እና አርማ ሰበብ ሲነታረኩ ከሰነበቱ በኋላ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ የዜጎች መብት እና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ

በፍራንክፈርት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቡራዩ እና አካባቢዋ ጥቃት ሰለባዎችን ለመዘከር ዛሬ ከተማ አስተዳደር ሕንጻ አካባቢ ተሰባስበው የጸሎት እና የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት አካሄዱ። ንጹሃን ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡበትን እና በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉበት ጥቃት ከባህላችን ያፈነገጠ እና ሰብአዊነት የጎደለው ነው ሲሉ አውግዘዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የካሜሩን ቀውስ እና ቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ

በካሜሩን የፊታችን መስከረም 27፣ 2011 ዓም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ይካሄዳል። የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሰረትም የምርጫው ዘመቻ በዛሬው ዕለት በይፋ ዘመቻ ተጀምሯል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በአዲስ አበባ 154 ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ለመንግስት እንዲመለሱ ተወሰነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላለፉት አስራ አምስት ገደማ አመታት ታጥረው የተቀመጡ 154 ቦታዎች ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆኑ ትዕዛዝ አስተላለፈ። "ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ተመላሽ" እንዲሆኑ ውሳኔ የተላለፋባቸው ቦታዎች ከአራት ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ስፋት እንዳላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ እየተመለሱ ነዉ 

በኮልፊ አካባቢ ፊሊፖስ ትምህርት ቤት ዉስጥ ተጠልለዉ ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል ጥቂቶቹ ወደ ቀድሞ መኖርያ ቀያቸዉ እየተመለሱ መሆኑን ተፈናቃዮችን በመርዳት ላይ የሚገኘዉ የርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ዛሬ ለ«DW » ተናገረ። እንደያም ሆኖ አሁንም ግን በፊሊፖስ ትምህርት ቤት ወደ አንድ ሺህ የሚሆኑ ተጠላዩች ይገኛሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዓለም አቀፍ የዘርፈ ብዙ ድህነት መለኪያ ጥናት

ሕንድ ባለፈዉ 10 ዓመት ፈጣን መሻሻል አሳይታለች ሲል ዓለም አቀፍ የዘርፈ ብዙ ድህነት መለኪያ ጥናት (MPI) ገለፀ። ድርጅቱ ይፋ ባደረገዉ መረጃ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍራቃ ሃገራት የሚታየዉ ድህነት ግን ከፍተኛ ስጋት ፈጥል ብሏል። በዓለም ዙርያ ከሚገኙ በድህነት ከሚማቅቁ ሰዎች መካከል ግማሹ ሕጻናት መሆናቸዉን አስታዉቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ማህበራዊ መገናኛዎች ስለቡራዩ እና አካባቢው ጥቃት

ኢትዮጵያውን የአዲሱን ዓመት ሁለተኛ ሳምንት የጀመሩት በመርዶ ነው። ሳምንቱ በርካታ ወገኖቻቸው ዳግም በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሰሙበት ነበር። ለወትሮው እንዲህ አሳዛኝ ክስተት ሲሰማ በእውኑ ጥቁር ተለብሶ፣ ፍራሽ ተነጥፎ፣ ሀዘን እንደሚቀመጡት በማህበራዊ ድረ ገጾችም ተመሳሳይ አካሄዶች ይስተዋሉ ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጥላቻ አዘል ንግግር በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች

የኢትዮጵያ መንግስት «የሰዎችን የግል መብትና የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮችን» እንደ ምክንያት በማስቀመጥ በተለያዩ ጊዜያት ማህበራዊ  መገናኛ ዘዴዎችን በመዝጋቱ የተለያዩ የመብት ተሟጋች ግለሰቦችና ተቋማት ትችታቸዉን ሲሰነዝሩ እንደነበር ይታወሳል። መንግስት ያስቀመጠዉን ቀይ መስመር አልፈዉ የተገኙም ሲታሰሩና ሲሰደዱ ነበር።  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ከአፈና ወደ ዴሞክራሲ ወይስ መልሶ ወደ አፈና?

በአመፅ እና ለውጥ ከዚያም መልሶ በአመፅ አዙሪት ውስጥ ለኖሩት ኢትዮጵያውያን የለውጥ ተስፋ እያዩ ማጣት አዲስ አይደለም፡፡ መስከረም በጠባ የመጀመሪያው ሳምንት ላይ የተከሰተው አመፅ እና የመንግሥት የተዝረከረከ ምላሽ እና ግልጽነት የጎደለው የእስር እርምጃ፣ ባለፉት ስድስት ወራት የታየው የለውጥ ተስፋ ሊያመልጥ እንደሚችል ጠቋሚ ምልክት ሆኗል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የመኖርያ ፈቃድ ለፈላሻሙራ ቤተ-ዘመዶች

«አይሁድ የሚለዉ በአጠቃላይ በዓለም ላይ የሚገኙ የአይሁድ ሃይማኖትን የሚከተሉ ማለት ነዉ። ግን ቤተ- እስራኤላዉያን፤ ኢትዮጵያዊ አይሁዳዊ ማለት ነዉ። ቤተ- እስራኤል ከግዕዝ የመጣ ቃል ነዉ ቤቱ እስራኤል የሆነ ሰዉ ማለት ነዉ። ፈላሻሙራ ደግሞ የአይሁድ ሃይማኖቱን ቀይሮ የነበረ አልያም የቀየረ ማለት ነዉ»
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰመጉ ጥሪ እና ማሳሰቢያ

መንግሥት የዜጎችን የሰብዓዊ መብት እንዲጠብቅ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ጥሪ አቀረበ። ይህን ለውጥ በማምጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ያላቸው ቄሮ፤ ፋኖ እና ዘርማ ከአሁን በኋላ ለተሞጋችነትም ለተጠያቂነትም በሚያመች ሕጋዊ አደረጃጀትም እንዲኖራቸው ጠይቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት እና በአፍሪቃ ኅብረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያካበተችው የሰላም ማስከበር ልምድ እውቅና ማግኘቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመለከተ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዩጋንዳ የፖለቲካ ውጥረት

የዩጋንዳ ፖሊስ ለህክምና ከሀገር ውጭ ሰንብተው ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱትን ተቃዋሚ የምክር ቤት አባል በቁጥጥር ስር ማዋሉ በሀገሪቱ ውጥረት ቀስቅሷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአውሮጳ ኅብረት እና ስደት

ሃያ ስምንቱ የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ትናንት እና ዛሬ በኦስትሪያዋ ሳልስቡርግ ከተማ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ አካሂደዋል። መደበኛ ያልሆኑ የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ስብሰባዎች ውሳኔዎች የማይተላለፉባቸው ይሁኑ እንጂ አስቸጋሪ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ መሪዎቹ በጥልቀት በመወያየት ልዩነቶቻቸውን የሚያጠቡባቸው እና ስምምነት የሚፈጥሩባቸው ናቸው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጥላቻ አዘል መልክቶች ቁጥጥር ሊደረግባቸዉ ይገባል

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰዉ የመጣዉን የቡድን ጥቃትና አመፅን መንግሥት ሊያስቆም ይገባል ሲል ዓለምአቀፉ የየሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት «አምነስቲ ኢንተርናሽናል» ገለፀ። በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከአገር ዉጭ የሚሰራጭ ማንኛዉም የጥላቻ መልክት በዓለምአቀፍ ደረጃ ወደ ሕግ ማምጣት እንደሚቻልም አያይዞ ጠቅሶአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ቴክኖሎጂን ለግብርና መጠቀም በኡጋንዳ እና ቡርኪናፋሶ

በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አርሶ አደሮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለማቃለል ቴክኖሎጂን ከግብርና ጋር ለማጣመር ይጥራሉ። በኡጋንዳ ያለች የኮምፒውተር ባለሙያ የተክል ተባዮች እና በሽታዎችን ለመከላከል የሚያግዝ መተግበሪያ (አፕልኬሽን) ለአገልግሎት አውላለች። በቡርኪናፋሶ ደግሞ የጠብታ መስኖ ገበሬዎች ምርታቸውን እንዲያሳድጉ ረድቷቸዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሕጋዊ ማዕቀፍ የሚሻው የኢትዮጵያና ኤርትራ የንግድ ግንኙነት 

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቅ ካወረዱ በኋላ በድንበር አካባቢ ያለው የንግድ ልውውጥ መነቃቃት ጀምሯል። አገራቱ አጠቃላይ ሥምምነት ቢፈራረሙም የንግድ ልውውጥ፣ የመገበያያ ገንዘብ አጠቃቀም እና የታሪፍ ጉዳይ ሕጋዊ ማዕቀፍ አልተበጀለትም። ባለሙያዎች ጉዳዩ በፍጥነት ተቋማዊ ሊሆን እንደሚገባ ይወተውታሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦብነግ ድርድር

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ ኦብነግ የልዑካን ቡድን በኤርትራ መዲና አስመራ ድርድር ጀመሩ። ሁለቱ ቡድኖች ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ በድርድሩ ማዕቀፍ እና በድርድሩ በተነሱ ነጥቦች ላይ መግባባታቸውን ኦብነግ በትዊተር ገጹ ይፋ አድርጓል። ድርድሩንም በቅርቡ እንደሚያጠናቅቁ የኦብነግ የትዊተር ገጽ አስነብቧል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሁለት የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮ/ አባላት መታሰር

ከጥቂት ጊዜ በፊት ወደ ሀገር ቤት የገባው የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአቀባበል ስነ ስርዓት ኮሚቴ አባላት ከነበሩት ወጣቶች መካከል ሁለቱ ዛሬ መታሰራቸው ተሰማ። ብርሀኑ ተክሌ ያሬድ እና መኮንን ለገሠ ለጥያቄ ትፈፈለጋላችሁ ተብለው በፖሊስ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለ DW ተናግረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጠ/ሚ ዐቢይ የጀመሩት ተሀድሶ በተንታኖች እይታ

ጠ/ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የጀመሩት አስተዳዳራዊ ስልት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪቃም ትኩረት እንደሰጠ በአህጉሩ ሰላም እና ደህንነት ላይ የሚሰሩ ተንታኞች አስታወቁ። ተንታኞቹ እንደሚሉት፣ ጠ/ሚ የሚከተሉት አስተዳዳራዊ ስልት ከአካባቢው ሀገራት በቅርብ ተባብረው በመስራት የአፍሪቃ ሀገራትን ሰላምና ደህንነት የማራመድ ዓላማም ያለው ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ውጥረት የሚታይበት የኮንጎ ምርጫ ዘመቻ

በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ በጎርጎሪዮሳዊው ታህሳስ 23፣ 2018 ዓም ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ ይደረጋል። ይሁንና፣ በምርጫው ለሚወዳደሩት ግለሰቦች ውጊያ በቀጠለበት በሀገሪቱ ምሥራቃዊ አካባቢ የምርጫ ዘመቻ ማካሄድ ግን እጅግ አዳጋች ሆኗል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በጀርመን የኢትዮጵያውያን ሕይወትና አገራዊ ራዕይ

ኢትዮጵያ ዉስጥ የተጀመረዉ ለዉጥ በተለያዩ ሐገራት ተሰደዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ቀልብ በመሳቡ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ በዝግጅት ላይ መሆናቸዉን በየአጋጣሚዉ እየገለፁ ነዉ።ቁጥራቸዉ ጥቂት ቢሆንም ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱም አሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የቡራዩ እና አካባቢው ተፈናቃዮች ቅሬታ

በቡራዩና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ በሳምንቱ መጨረሻ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎች 12 ሺህ ገደማ መድረሳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ተፈናቃዮች ከመንግስት ተገቢውን እርዳታ እያገኘን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸው አሰምተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የመኢአድ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰሞነኛ የፖለቲካ ሁኔታዎች

የኢትዮጵያ መላው አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በአዲስ አበባ እና አካባቢው ከሰሞኑ እየታየ ባለው አለመረጋጋት ላይ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። በሀገሪቱ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ከድርጅቱ እና ከሌሎች አካላት ስለሚጠበቀው እርምጃም ምላሽ ሰጥቷል።  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጥቃትና ግጭት የቀሰቀሱ ቡድን አባላት ተይዘዋል ተባለ

በቡራዩና በአከባቢዋ ነዋሪዎች መካከል ግጭት የቀሰቀሱት «99 አባላትን የያዙ እና የፖለቲካ አላማ ያላቸዉ» ቡድኖች ናቸዉ ሲሉ የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለ«DW» ተናገሩ። ከእነዚህም ዉስጥ ስድስት ሰዎች ሲያዙ ቀሪዎቹን ለማያዝ ፖሊስ እያሰሰ መሆኑን  ዶክተር ነገሪ አስታዉቀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ከሰሞኑ ጥቃት አስቀድሞ ምልክቶች እንደነበሩ ጥናት አመለከተ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ እየተከሰቱ ያሉት ሁከቶችና ብሔር ተኮር ጥቃቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ቀደም ብሎ ምልክቶች መታየታቸውን አንድ የዳሰሳ ጥናት አመለከተ። ጥናቱን ያደረጉት የስነ ማህበረሰብና የህግ ባለሙያ በፀጥታ ኃይሉ ቸልተኝነትና ቀድሞ ዝግጅት አለማድረግ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ እና ጉዳት እየደረሰባቸው እንዳለ አብራርተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኤርትራ የዴሞክራሲ ለዉጥ ይደረግ ይሆን ?

የተለያዮ ዴፕሎማቶችና የብዙኃን መገናኛዎች የሰመረ ያሉት የኤርትራና የኢትዮጵያ የወዳጅነት ግንኙነት በኤርትራ ለዴሞክራሲንና ለገደብ የለሹ ብሔራዊ ዉትድርና ተሃድሶ ያመጣል ሲሉ መናገራቸዉ ህልም ነዉ ሲል መቀመጫዉን ለንደን ብሪታንያ ያደረገዉ የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ገልፆአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰኞ መስከረም፤ 7 ፤ 2011 ዓ.ም የስፖርት ዝግጅት

በ 45ኛው የ  «BMW» የበርሊን ማራቶን  ኢትዮጵያውያን አትሊቶች ሩት አጋ እና ጥሩነሽ ዲባባ 2፥18፥34 እና 2፥18፥55 በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰባት ፖለቲካ ፓርቲዎች ሥምምነት

ብሔር እና የፖለቲካ አመለካከትን ተኮር ያደረገ ነዉ የተባለዉን በኢትዮጵያ የሚታየዉን ግጭት ለመታገል በሃገር ዉስጥ ያሉና ከዉጭ የገቡ በአጠቃላይ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች በኅብረት ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ ተሰማ። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዛሬ መግለጫም ሰጥተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የ2011 አንገብጋቢ የወጣቶች ጥያቄዎች ምንድናቸው?

የ2011 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ DW ለወጣት አድማጮቹ የተለያዩ ጥያቄዎች አቅርቦ ነበር። ባለፈው ዓመት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ባሉ ወጣቶች ዘንድ የተስተዋለው የስርዓት አልበኝነት እና የመንጋ ፍርድን አስመልክቶ የቀረበው ጥያቄ አንዱ ሲሆን “በአሁኑ ወቅት የወጣቶች ዋነኛ ጥያቄዎች ምንድናቸው?”  የሚለው ደግሞ ሌላኛው ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አቦል ጥበብ

«በ 2010 በጣም ብዙ ለዉጥ የሚመስሉ ንፋሶች ያየንበት ነዉ። በርግጥ ለዉጥ መምጣት አለመምጣቱን የምንወስነዉ ወደፊት ነዉ። የአንድነት ነፋሱ እንዳለ ሆኖ በጣም አስጊና አስፈሪ የሆኑ ነገሮች እየታዩ ነዉ። ለኢትዮጵያ አንድነት፤ ለፍቅር ለመቻቻል እና ለተሻለ ነገር፤ የጥበብ ሰዎች የመፍትሄ ሃሳብ ማምጣት መጀመር አለብን ብዬ አምናለሁ።» ገጣሚዋ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአዲስ ዓመት አከባበር በአሜሪካ

በተለይ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጋዜጠኞች ከፍተኛ ምሑራን ኢትዮጵያ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢንጂነሩ ሞት ሰበብ፤ የታማኝ ንግግር እና የራያ ጥያቄ

የህዳሴው ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን አጥፍተዋል መባሉ፤ አርቲስትና የመብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ በባህር ዳር ያሰማው ንግግር በሰፊው አነጋግረዋል። የራያ ተወላጆችን በተመለከተ የተሰማው ቅሬታና የትግራይ ክልል መልስ፤ እንዲሁም ለውሳኔ ቀረበ የተባለው የአዲስ አበባ ዲጂታል መታወቂያም አወያይቷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የከሰል ጡብ ስራ በኬምስትሪ ተመራቂዎች

በሳይንሱ ዘርፍ የከፍተኛ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለመመረቂያ የሚያዘጋጇቸው ጥናታዊ ጽሁፎቻቸው መደርደሪያ ከማሞቅ የዘለለ ጥቅም አይሰጡም የሚል ትችት በተደጋጋሚ ሲቀርብ ይደመጣል። የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አምስት ተማሪዎች የጥናታቸውን ውጤት ወደ ተግባር ለውጠው ጭስ አልባ ከሰል እያመረቱ ይገኛሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ከወደ ቻይና የሚጠበቀው የብድር ማስተካከያ 

የቻይና 12 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ያለባት ኢትዮጵያ በአበዳሪዋ ማስተካከያ ይደረግላት ዘንድ ትጠብቃለች። ባለሙያዎች የመክፈያ ጊዜን በማራዘም አሊያም የአከፋፈል ለውጥ ሊኖር እንደሚችል ተስፋ አላቸው። ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ በቻይና ቆይታቸው ከኤክዚም ባንክ ሊቀ-መንበሪት ሑ ዢያዖሊያን ጋር ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ መክረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የማህፀን ጫፍ ካንሰርና ክትባቱ

በአለም ላይ በገዳይነታቸዉ ከሚታወቁት የካንሰር አይነቶች የሴቶችን የመራቢያ ክፍል የሚያጠቃዉ የማህፀን ጫፍ ካንሰር አንዱ ነዉ። በሽታዉ በኢትዮጵያም በገዳይነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ወሳኔ ለመተግበር ወሰነች

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዉ የአልጀርሱን ስምምነት እና በአልጀርሱ ሥምምነት መሠረት የተሰየመዉ የድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔን ገቢራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት «ያለማመንታት በቁርጠኝነት» የሚሰራ መሆኑን ገልጧል። መንግሥት የሚቆጣጠራቸውን ትላልልቅ ኩባንያዎች እና ድርጅቶች በተወሰነ ደረጃ በአክስዮን ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ መታቀዱንም አስታውቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዶቼቬለ ምሥረታ 65ተኛ ዓመት 

ተዓማኒነት የዶቼቬለ መለያ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ፒተር ሊምቡርግ ይናገራሉ። ሊምቡርግ እንዳሉት ከ96 በመቶ በላይ የዶቼቬለ አድማጮች እና ተከታዮች ጣቢያው የሚያስተላልፋቸው መረጃዎች ተዓማኒ ናቸው ብለው ያስባሉ። በርሳቸው አስተያየት ይህ የጣቢያው መለያ አድማጮችን ይዞ ለመዝለቅ እድል ሰጥቶታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ የተደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለማንሳት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ አዋጁ መነሳቱና የተሰጠ አስተያየት

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት ባለፈዉ ቅዳሜ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበዉን ረቂቅ የዉሳኔ ሃሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ ሥብሰባ ማፅደቁን በርካታ ኢትዮጵያዉያን አወደሱ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጀርመን እና የእስራኤል ግንኙነት

በአይሁዳውያን ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ጀርመን እና እስራኤልን በልዩ መንገድ አስተሳስሯቸዋል። ሁለቱ ሀገራት የናዚ አገዛዝ ካበቃ ከ70 ዓመት በኋላ ዛሬ ከሞላ ጎደል መደበኛ የሚባል ግንኙነት ጀምረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በሐኪም ስህተት የአልጋ ቁራኛ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ

ከቀዶ ህክምና በኋላ ፣በሐኪሞች ስህተት ሳይነቃ ፣ላለፉት 13 ዓመታት ጂዳ ሆስፒታል የሚገኘውን ታዳጊ ወጣት መሐመድ አብዱልአዚዝን ወደ ሀገር ቤት ለመውሰድ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች መዘጋጀታቸዉ ተነገረ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የመሬት መንሸራተት ስጋትና መፍትሔው

ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንሸራረት ተከስቶ ጥቂት ለማይባሉ ሰዎች ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። የመሬት መንሸራረት ክስተት ኢትዮጵያ ውስጥ እንግዳ እንዳልሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአየር ንብንብረት እና የአፍሪቃ አደጋ መከላከል ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዘውዱ እሸቱ ይናገራሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

​​​​​​​ ስፖርት፤ ግንቦት 27 ቀን፣ 2010 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአስመራጭ ጠቅላላ ጉባኤ እያወዛገበም፣ እያነታረከም ትናንት እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ዘልቋል። ፌዴሬሽኑ ራሱ ያወጣውን መመሪያ ራሱ ሲጥሰውም ተስተውሏል። በስተመጨረሻ ግን ፕሬዚዳንቱንም፣ ምክትሉንም ሌሎች አስተዳዳሪዎችንም መምረጡን ይፋ አድርጓል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኦኤምኤን ኢትዮጵያ ቢሮዎች ሊከፍት ማቀዱ

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የኦሮሚያ ሚድያ ኔትዎርክ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች ቢሮ ለመክፈት ማቀዱን አስታወቀ። ድርጅቱ በስድስት ቋንቋዎች ሙያዊ አገልግሎቱን ለኅብረተሰቡ ለማበርከት እንቅስቃሴ መጀመሩንም አመልክቷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አንጎላ የጀመረችው የተሀድሶ ለውጥ

በአንጎላ መዲና ሉዋንዳ በሀብታሞች እና በድሆች መካከል ያለው ግዙፍ ልዩነት እጅግ ጎልቶ ይታያል። የትልቆቹ ዓለም አቀፍ ተቋማት የናጠጡ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በሚገኙበት አካባቢ ድሆች የአንጎላ ዜጎች በልመና ተሰማርተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢጣሊያ አዲስ መንግስት ተመሠረተ

አምስት ኮኮብ እና ሊጋ የተባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚሕ ቀደም ያቀረቡትን ካቢኔ የኢጣሊያ ፕሬዝደንት ሰርጂዎ ማታሬላ ዉድቅ አድርገዉት ነበር።ከብዙ ዉዝግብ፤ድርድር እና ሽምግልና በኋላ ዛሬ የተመሠረተዉ መንግሥት የካቢኔ አባላት ከቦታ ለዉጥ በስተቀር ካለፈዉ ብዙም የተለዩ አይደሉም
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአቶ አንዳርጋቸው መፈታትና የመረጃ መጣረሶች

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት የዛሬው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ጥንቅራችን ማጠንጠኛ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ይለቀቃሉ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ብተለያዩ ሰዎች የተለያዩ መረጃዎች ሲተላለፉ ነበር። መረጃዎቹ መጣረስ ተስተውሎባቸዋል። ​​​​​​​አሸባሪ ተብለው የነበሩ አንዳንድ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ክስ በኢትዮጵያ ተቋርጧል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጥቃትን በቴክዋንዶ መከላከል ይቻል ይሆን? 

#77ከመቶው በተሰኘው የወጣቶች ዓለም መሰናዶ በጾታዊ ጥቃት ላይ እናተኩራለን። የጾታ ጥቃት በመኖሪያ ቤት በባልና ሚስት መካከል ብቻ የሚፈጸም አይደለም። ጉልበት የሌላቸው በተለይ ታዳጊ ልጃገረዶች በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ ጥቃቱ ሊደርስባቸው ይችላል። በኬንያ ተፈፅመዋል የተባሉ ጥቃቶች ባለሥልጣናት ለችግሩ መፍትሔ ፍለጋ እንዲጀምሩ አስገድዷቸዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

«ባሕል መንገድን ይመራል» ፕሮጀክት በኢትዮጵያ

መቀመጫዉን በስዊድንና በኢትዮጵያ ያደረገዉ ሰላም ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ድርጅት ባህል ላይ ያተኮረ የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ቀርፆ ሥራዉን ጀምሯል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ተስፋ የተጣለባቸው አዲሶቹ የጤፍ እና ማሽላ ዝርያዎች

የኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  የሀገሪቱን “የሰብል ልማት ታሪክ ሊቀይሩ” የሚችሉ ናቸው ያላቸው የጤፍ እና የማሽላ ዝርያዎች በምርምር መገኘታቸውን ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። ዝርያዎቹ አንዴ ከተዘሩ በኋላ ተገቢው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ከ10 እስከ 20 ዓመታት ምርት የሚሰጡ ናቸው ተብሏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

5,500 ዶላር ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህፃናት ሕክምና ክፍል ምን ይገዛል?

ሁለት ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ጎ ፈንድሚ በተባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ድረ-ገፅ በኩል ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት የሕክምና ክፍል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ጥረት እያደረጉ ነው። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ትንባሆ ያለማጨስ ዓለም አቀፍ ዕለት

ፈረንሳይ ካፈለው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የአጫሽ ዜጎቿ ቁጥር በ1 ሚሊየን መቀነሱን ይፋ አድርጋለች። ትንባሆ በተለይ በልብ እና የመተንፈሻ አካልት ጉዳት ብሎም ለድንገተኛ የደም ዝውውር መታወክ እንደሚዳርግ ሃኪሞች ያሳስባሉ። በየዓመቱም በትንባሆ መዘዝ ከ7 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጣሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በጀርመን ተሸላሚው ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር

በሕይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽዖ ነው ጀርመን ውስጥ እጅግ ታዋቂ በኾነው ተቋም ተሸላሚ የኾኑት። የተለያዩ ሀገር-በቀል ቅጠላ ቅጠሎች እና እጽዋት ላይ ምርምር በማከናወን መድኃኒቶችን ቀምመው በስማቸው አስመዝግበዋል፤ በጀርመን ሀገር ልዩ ክብር በሚሰጠው የአሌክሳንደር ሁምቦልት ተቋም ተሸላሚው ፕሮፌሰር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲሱ ካቢኔ የምሁራንና የባለሞያዎች መንግሥት ነዉን?

የኢትዮጵያ መንግስት አዲስ ካቢኔ ማወቀሩን ተከትሎ አስተያየቶች ከየአቅጣጫው እየጎረፉ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አዲስ የሚያዋቅሩት ካቢኔ የፓርቲ አባላት ያልሆኑ የምሁራን እና የባለሙያዎች (ቴክኖክራቶች) ስብስብ እንደሚይዝ ጥቆማ ሰጥተው ነበር፡፡ የሚኒስትሮቹን ሹመት ከቃላቸው አንጻር የሚመዝኑ ጥያቄዎችን ማንሳት ጀምረዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲሱ የመንግሥት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ

በትናንትናዉ ዕለት የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21 አዲስ ተሿሚዎችን ሚኒስትርነት አጽድቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአፍሪቃ ወጣቶች ቀን

«የአፍሪቃ የሰብዓዊ መብቶች ዓመት በ2063ዓ,ም ወደምንፈልጋት አፍሪቃ» የሚል መርህ ያነገበዉ የያዝነዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2o16 የአፍሪቃ ወጣቶች ቀን በትናንትናዉ ዕለት አዲስ አበባ ላይ በአፍሪቃ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤት ተከብሯል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ዉኃ መሳቢያ

ከሠሃራ በስተደቡብ የሚገኙ እና ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪቃ ሃገራት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ አዲሱ የዉኃ  መሳቢያ ሞተር ሁነኛ መፍትሄያቸዉ ነዉ ተባለ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ጉዳይ በጀርመን ፖለቲከኛ እይታ

ኒማ ሞሳቫት በጀርመን ምክር ቤት የግራዎቹ ፓርቲ ተወካይ ፣ ጀርመን እና የአውሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ ህዝብን ተጠቃሚ የማያደርጉ አሠራሮች እንዲቀየሩ ጥረት እንዲያደርጉ ለዶይቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ጠይቀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የሂዩማን ራይትስ ዎች ማስጠንቀቂያ

ሂዩማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም ያወጣው መመሪያ የሰብዓዊ መብት ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠነቀቀ፡፡ መመሪያው የተለጠጡ እና አሻሚ አንቀጾችን ያካተተ ነው ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ “ትርጉም የሌለው፣ ህግ የመሰለ መፈክር ላይ የተመሰረተ ትንታኔ” ሲል የተቋሙን መግለጫ አጣጥሎታል፡፡ 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የብዝሃ- ሕይወት ስብጥር ጥናት

ኢትዮጵያ በብዝሃ ህይወት ስብጥር በተፈጥሮ የታደለች ሀገር መሆኗን ተመራማሪዎች ይናገራሉ። በሀገሪቱና በዉጭ ሳይንቲስቶች ትብብርም በእጽዋቱ ዘርፍ ሰፋ ያለ ጥናት ተካሂዷል፤ አሁንም እየተካሄደ ነዉ። የተገኙ የጥናት ዉጤቶችን መሠረት ያደረገ የጥበቃ ሥራ መሠራት እንደሚኖርበትም ተመራማሪዎቹ ያሳስባሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት ጥቅምት 21 ቀን፣ 2009 ዓ.ም

በደብሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ለድል በቅተዋል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድን ዘንድሮ ምን ነካው? አስብሏል። በ15 ነጥብ ወደ 8ኛ ደረጃ  አሽቆልቁሏል። ቸልሲ ቀንቶት ደረጃውን አሻሽሏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የደኅንነት ሥጋት የተጫናቸው የውጪ ባለወረቶች

በኢትዮጵያ የፍራፍሬ እና አበባ እርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ የውጪ ኩባንያዎች በተቃውሞ የከፋ ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ መፃኢ ዕጣ ፈንታቸው አስግቷቸዋል። በባሕር ዳር አካባቢ የአበባ እርሻ የወደመበት ኤስሜራልዳ የተሰኘው የኔዘርላንድስ ኩባንያ ሥራውን አቋርጧል። ለሠራተኞቻችን እና ለንብረታችን የደኅንነት ዋስትና እንሻለን የሚሉም አሉ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት ጥቅምት 14 ቀን፣ 2009 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ዘንድሮ እጅግ በተቀዛቀዘ መልኩ ዘግይቶ ጀምሯል። ጨዋታው ለምን ከተያዘለት የጊዜ ገደብ ሊሸጋሸግ እንደቻለ በይፋ ባይገለጥም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ሊያያያዝ እንደሚችል የሚገምቱ አሉ። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በፖርትስማውዝ ብሪታንያ የ10 ማይልስ የጎዳና ሩጫ ትናንት አሸናፊ ኾናለች።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሊቢያ ከቃዛፊ መገደል በኋላ

አካባቢዉን የወረሩት ሚሊሺያዎች ቃዛፊን ከጉድባ ዉስጥ አወጧቸዉ።ቆስለዋል።ያዩ እንደሚሉት ማራኪዎቹ ሰዉዬዉን መኪና ላይ ሲያወጧቸዉ ሌሎች ሚሊሺዎች ደረሱ።ማራኪዎቹ «አትግደሉት እንፈልገዋለን» ይላሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዳናቸዉ ያልተገኘዉ የጋምቤላ ህጻናት

ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ከጋምቤላ ታፍነው ወደ ደቡብ ሱዳን ከተወሰዱ ህጻናት መካከል ስድሳ ስምንቱ አሁንም ድረስ ያሉበት እንደማይታወቅ ጉዳዩን የሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ቡድን አስታወቀ፡፡ ህጻናቱ ለባርነት ይዳረጋሉ የሚል ስጋቱንም ገልጿል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኦሮሞ የሕግ ባለሞያዎች ማኅበር ጉባኤ በለንደን

እንደ ተሳታፊዎቹ የጉባኤው ዓላማ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን የሚያስማማ አንድ አግባቢ ሃሳብ ላይ መድረስ እንጂ ከጉባኤው በፊት እንደተወራው የኦሮምያን የመተዳደሪያ ደንብ ማውጣት ወይም የኦሮምያን ጦር ማቋቋም አልነበረም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የካሌ ስደተኞ መነሳት

ፈረንሳይ ወደ ብሪታንያ ለመሻገር በድንበር ግዛትዋ ካሌ ዉስጥ ድንኳን ተክለዉ የሚኖሩትን በሽዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የማዛወር ሥራን ዛሬ ጀመረች። ስደተኞቹን ከቦታዉ የማስለቀቅ ሥራ በጀመረበት በዛሬዉ ዕለት ብቻ ከ2000 እስከ 2500 ስደተኞች በስድሳ አዉቶቡሶች እንደሚወሰዱ ተመልክቶአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጨፌ ኦሮሚያ አስቸኳይ ስብሰባ

ጨፌ ኦሮሚያ ባካሄደዉ አስቸኳይ ስብሰባ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ ባካሄደዉ ዉይይት «ህዝብን ወክለዉ» በምክር ቤቱ ዉስጥ ያሉት የአዋጁን አስፈላጊነትና አፈፃጸሙን ለኅብረተሰቡ የተጠናከረ ሃሳብ ማስጨበጫ መስጠት እንደሚያስፈልግ፤ ችግር ሲፈጠርም በአስቸኳይ የሚፈታበትን መንገድ መፈለግ አለባቸዉ የሚለዉ ላይም ማተኮሩን ለመረዳት ተችለዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታው አምባው የጦር መሣሪያ አያያዝ በሕግ አግባብ ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስበዋል። ሆኖም የአዋጁ አፈፃጸም መመሪያ ትጥቅ ማስፈታት አንዳልሆነ ተናግረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጅምላ እስር ያሰጋቸዉ ወጣቶች

ለከተሜ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች የሰሞኑ ሁኔታ መረጋጋትን አልፈጠረላቸዉም። በየቦታዉ የሚሰማዉ የእስር ዜና ጭንቀትን እና ጥርጣሬን ፈጥሮባቸዋል። የተወሰኑት በየአካባቢያቸዉ መደበቅን የመረጡ ሲሆን ጥቂቶቹ ደግሞ ቀያቸዉን ለቀዉ ከዘመድ አዝማድ ተጠግተዉ እስርን ለማምለጥ ሞክረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ ተጠናቀቀ

ለሁለት ቀናት የዘለቀዉ የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ ዛሬ ተጠናቀቀ። ጉባኤዉ ከታለመዉ ዉጤት ላይ ባይደርስም በዋናነት በኅብረቱ እና ካናዳ መካከል ነፃ ንግድ ስምምነት ላይ ያተኮረ ድርድር አካሂዷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የፓሪሱ የአየር ንብረት ጉባኤ እና አፍሪቃ

ፓሪስ ላይ ባለፈዉ ዓመት የተመድ የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ ፤ አፍሪቃስ በቀጣይ የድርሻዋን ምን መሥራት ይጠበቅባታል በሚል የተካሄደዉ ጉባኤ ተጠናቀቀ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ስጋት

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት ለስድስት ወራት የደነገገዉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወትሮም በቋፍ የነበረዉን የሰብዓዊ መብት ይዞታ ወደ ከፋ ደረጃ ሊያሸጋግረዉ እንደሚችል እያሳሰቡ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በምክር ቤት ጸደቀ

በኢትዮጵያ በቅርቡ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ዛሬ ጸደቀ። 7 አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ተቋቁሞ መጽደቁም ተገልጧል። ፕሪቶሪያ የሚገኘው የጸጥታ ጥናት ተቋም ኃላፊ ያኪ ሲልየር፦ መርማሪ ቡድኑ «ነፃ እና ገለልተኛ ሊሆን ይገባል» ብለዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

   የዓለም ቀይ መስቀልና አፍሪቃ

ፕሬዝደንቱ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያወጀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አንስተዉ መነጋገራቸዉን አስታዉቀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአሜሪካ ዕጩ ፕሬዝደንቶች ክርክር

የዲሞክራቲክዋ ፓርቲ ዕጩ ሒላሪ ክሊንተንና የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸዉ ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ላስቬጋስ ከተማ ያደረጉት ክርክር በዉጪ ጉዳይ መርሕ፤ በስደተኞች ይዞታ እና በምጣኔሐብት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢንተርኔት በመዘጋቱ ኢትዮጵያ ላይ የደረሰው ኪሳራ

ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ለ30 ቀናት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ማጣቷን መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው ጥናት ጠቋሟል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአተም ቅጥልጣይ ማሽኖች

ዘንድሮ በኬሚስትሪ ዘርፍ ለኖቤል ሽልማት የበቁት 3 ተመራማሪዎች የአተም ቅጥልጣይ ማሽኖች (molecular machines) ንድፍ እና ውኅደት ላይ ባከናወኑት ጥልቅ ምርምር እንዲሁም ግኝት ነው። ለመኾኑ የአተም ቅጥልጣዮች እንደምን ማሽን ሊኾኑ ይችላሉ? የሽልማቱ መሠረታዊ ጥያቄ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና ኢትዮጵያውያን በጀርመን

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደነንገጉ እና ለአዋጁም ማስፈፀሚያ ብዙዎች አፋኝ የሚሏቸውን መመሪያዎች ማውጣቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ውስጥ ከቷል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሃይድሮ ፍሎሮ ካርቦን ቅነሳ

ዓለም የሙቀት መጠን እንዲቀንስ ለማድረግ ሃገራት ሊወስዷቸዉ የሚገቡ ርምጃዎች ላይ ስምምነቶች እየተደረሱ መሆኑ እየተነገረ ነዉ። ኪጋሊ ሩዋንዳ ላይ የተሰባሰቡት 200 የሚሆኑት ሃገራት ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ሃይድሮ ፍሎሮ ካርበንን አጠቃቀም ላይ ገደብ ለማድረግ መስማማታቸዉ ተሰምቷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የተቃዋሚዎች ሥጋት

የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የአዋጁ አተገባበር መመሪያ በቋፍ ላይ የነበረውን የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝ የደፈጠጠ ነው ሲሉ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ወቀሱ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲሱ የተ.መ.ድ. ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ 

የቀድሞው የፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒሥትር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዓለም ከፍተኛው ዲፕሎማት ሆነው በመጪው ጥር ባንኪ ሙንን ይተካሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሀና ወንድምስሻ እና ግጥሞቿ

የስነፅሁፍ ዝንባሌዋን ለማዳበር ከረዷት ውስጥ አስተማሪየ ትልቁን ስፍራ ይይዛሉ ትላላለች ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት ስፖርት ጥቅምት 7፣ 2009 ዓም

ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ትናንት የአምስተርዳም እና የቶሮንቶ የማራቶን ውድድሮችን በአንደኝነት ጨርሰዋል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የጋዜጦች ፈተና

“የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ይጥሳል” የሚል ትችትን እያስተናገደ የሚገኘው ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ ተጽእኖው ከወዲሁ በግልጽ ከታየባቸው መስኮች መካከል የጋዜጠኝነት እና የመገናኛ ብዙሃን ስራ ይገኝበታል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስና መፍትሔዉ

ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ከደቡብ ዲላ እስከ ሰሜን አርማ ጮኾ የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያዉያን በየዕለቱ በየሥፍራዉ እየተገደሉ፤ አካላቸዉ እየጎደለ፤ እየተደበደቡ እየታሰሩ ነዉ።የመንግሥት እና የባለሐብት መኪኖች፤ ፋብሪካዎች፤ የእርሻ ማሳዎች፤ ሌላዉ ቀርቶ ቤተ-እምነቶች እየጋዩ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሜርክል ጉብኝት በኢትዮጵያ

የጀርመን መራኂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ኢትዮጵያን ጨምሮ በሦስት የአፍሪቃ ሃገራት ያደረጉት የሦስት ቀናት ጉብኝት በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ኾኗል። በተለይ መራኂተ-መንግሥቷ ኢትዮጵያን በይፋ የጎበኙት ሀገሪቱ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተደነገገ በሁለተኛው ቀን መኹኑ ጠንካራ ትችት አስከትሎባቸዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ለአሜሪካን የስለላ ተቋም የሚሰልልዉ ያሁ

ግዙፉ የኢንተርኔት ግንኙነት መረብ ያሁ ባለፈዉ ዓመት በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ የኢሜይል ተጠቃሚ ደንበኞቹን በምሥጢር ሲሰልል እንደነበር መረጃዎች እየወጡ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ወደ ቀዉስ አዘቅት የምትንደረደረዉ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ወደ አዘቅት እየተንደረደረች በመሆንዋ የጉዳዩን አሳሳቢነት መንግሥት ሊያጤነዉ እንደሚገባ  የዶይቼ ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ዛሬ በጀርመንኛ ይፋ ባደረገዉ ኃተታዉ አሳስቦአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የንብረት ዉድመት የተቃዉሞ እንቅስቃሴ እና እንድምታዉ  

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ የንብረት ዉድመትና ጥፋት ማስከተሉ፤ መሠረታዊዉን የመብት ጥያቄ እያደበዘዘዉ ነዉ ሲሉ ነዋሬዎች ገለፁ። የፖለቲካ ተንታኞች በበኩላቸዉ የንብረት ዉድመቱ የሕዝቡን የመብት ጥያቄ ቢያደበዝዘዉም ትግሉን ግን ሊገታ አይችልም ሲሉ አስተያየት ይሰጣሉ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሰሞኑ ክራሞት

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ያለፈውን አመት ተረጋግተው አላሰለፉም፡፡ በየግቢዎቻቸው በሚቀሰቀሱ ተቃውሞዎች ምክንያት ጉዳት ሲደርስ፣ ተማሪዎች ሲታሰሩ እና ትምህርት ሲቋረጥ እየተመለከቱ ነው ዓመቱ በአዲስ ዓመት የተተካው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ የግብፅ አቋም 

በኢትዮጵያ የተከሰተዉ የፖለቲካ ቀዉስ የግብጽ እጅ አለበት በሚል በቀረበዉ ቅስ ላይ ተቀማጭነታቸዉ አዲስ አበባ የሆነዉ የግብጽ አንባሳደር አቡባካር የሁለቱን ሃገሮች ጥሩ ግንኙነት በመግለጽ ክሱን አስተባበሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በጀርመን የሽብር ተጠርጣሪዉ ራሱን ማጥፋቱ

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ በጀርመን ኬምኔትዝ ከተማ በጥገኝነት ይኖር የነበረ ሶርያዊ ከፍተኛ ጥቃት ሊያደርስ ነዉ በሚል የሽብር ጥርጣሪ ቤቱ ተፈትሾ ተቀጣጣይ ፈንጂ መስርያ ቁስ ከተገኘበትና ከተሰወረበት በሃገሩ ልጆች ተይዞ በፖሊስ ቁጥጥር ከዋለ ከቀናት በኋላ በታሰረበት ክፍል ዉስጥ ራሱን መግደሉ ተገለፀ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ጉዳይ በአውሮጳ ፓርላማ

በውይይቱ ላይ የፓርላማ አባላት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር አለበት ባሉት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ኮሚሽኑ ለዘብተኛ አቋም ይከተላል ሲሉ ወቅሰዋል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አወዛጋቢዉ የአይ ኤም ኤፍ የኢኮኖሚ ትንበያ

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪቃ  የኢኮኖሚ መሪነትን  በመጪዉ ዓመት ከኬንያ እንደምትረከብ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቁዋም በምህፃሩ አይ ኤም ኤፍ ከሰሞኑ ባወጣዉ የትንበያ ዘገባዉ አመልክቷል። ተቋሙ በዘገባዉ የኢትዮጵያን የዉጭ  የቀጥታ መዋእለ-ንዋይ ፍሰትን ለትንበያዉ መነሻ ካደረጋቸዉ  መስፈርቶች ዉስጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት ታሰሩ

የየፓርቲዉ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ በስልክ እንደገለፁት አንድ የአመራር አባል እና አምስት አባላቱ የታሰሩበት ምክንያት በዉል አይታወቅም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የኅብረተሰቡ አስተያየት

አዋጁን በተመለከተ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን አስተያየት አሰባስበናል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዲላው ጥቃት ያስከተለው ጉዳት

ጥቃት አድራሾቹ በብዛት በመውጣት አዛውንት ህጻን ሴት ሳይለዩ ሕይወት ማጥፋታቸውን ፣ ሰዎችን ማቁሰላቸውን እና ቤቶችን እና የተለያዩ ንብረቶችን ማቃጠላቸው ተገልጿል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ሂዩመን ራይትስ ዋች

ሚስ ሌስሊ ሌፍኮ ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር መፍትሄ ካሏቸው መካከል በህገ ወጥ መንገድ በፀረ ሽብር ህግ የታሰሩትን ተቃዋሚዎች መፍታት እና ለሞቱት እና ለቆሰሉት ካሳ መስጠት ይገኝበታል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢንጂኔር ኃይሉ ሻዉል ሥርዓተ ቀብር

ባለፈዉ ሳምንት ያረፉት ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ የኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ግብዓተ መሬት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ። ረዘም ላለ ጊዜ የጤና ችግር ያጋጠማቸዉ ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በህክምና ሲረዱ በቆዩበት በታይላንድ ነበር ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በዓለም የረሀብ ደረጃ መዘርዝር

በመላዉ ዓለም ረሀብን ለመቀነስ የሚደረገዉ ጥረት አዎንታዊ ርምጃን እያሳየ መሆኑን ዛሬ ይፋ የሆነዉ የዓለም የረሀብ ደረጃ መዘርዝር አመልክቷል። መዘርዝሩ በተለይ በአዳጊ ሃገራት የነበረዉ የረሀብ ሁኔታ 29 በመቶ መቀነሱን ቢጠቅስም፤ አሁንም ግን የረሀብ ደረጃዉ አሳሳቢ የሆነባቸዉ ሃገራት መኖራቸዉን ግልፅ አድርጓል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኦሮሚያ እና በደቡብ የሚታየዉ አመጽ እና ግጭት፤

በኢትዮጵያ ለወራት የዘለቀዉ ፀረ መንግሥት ተቃዉሞ አሁን አሁን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫም እያመራ መሆኑን በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገለጹ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታው

በአዋጁ ግጭቶችን ሊያስነሱ ይችላሉ የተባሉ ፅሁፎች ማዘጋጀት እና ማሰራጨትን ተከልክሏል ። የአገር ሠላምን አደጋ ላይ ይጥላሉ የሚባሉ የመገናኛ ዘዴዎችን መንግሥት መዝጋት ይችላል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የየመን ጦርነት እና እልቂት

ሰዎቹ ፖለቲከኛ፤ ወታደር፤ነጋዴ፤አስተማሪ፤ የመንግስት ሙያተኛ ወይም የቤት ሰራተኛ ይሆኑ ይሆናል።ቅዳሜ ከዚያ አዳራሽ የሰባሰባቸዉ ግን ለቅሶ ነበር።ሁለት አዉሮፕላኖች መጡ።ካዳራሹ ዉጪ የነበረዉ ሰዉ ሽቅብ ከማንጋጠጡ፤ አካባቢዉ ተደበላለቀ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደነገገ

የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ዛሬ አስታወቀ። አዋጁ ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚቆይ ሲሆን ተግባራዊ የሆነውም ከትናንት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም አንስቶ መሆኑ ተገልጿል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ሚና እና ኢትዮጵያ

ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች (Social Media) ከመደበኛዉ መገናኛ ዘዴ ይበልጥ በፍጥነት መረጃዎችን ለሕዝብ በማድረስ፤ የግለሰብ፤ የማኅበራት የድርጅቶች አስተያየቶችን በማሰራጨትና ከሁሉም በላይ ሠዎችን እርስ በርስ በማገናኘት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረጉ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጀርመን መራሒተ መንግሥት የአፍሪቃ ጉብኝት

የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለሶስት ቀናት ጉብኝት የፊታችን እሁድ ወደ ሳህል አካባቢ ሀገራት ይጓዛሉ። ጉብኝታቸው በዋነኝነት ስደተኞች በብዛት ወደ አውሮጳ እየመጡ ባለበት ሁኔታ በተፈጠረው ቀውስ ላይ ያተኩራል።  ሜርክል ከአፍሪቃ ጋር ባለው ግንኙነት ላይ አዲስ አሰራር ለመፍጠር ይፈልጋሉ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ወጀብ እና ማዕበል 877 ሔይቲዎችን ገደለ

ማቲው የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኃያል ወጀብ እና ማዕበል የ900 ግድም ሔይቲ ተወላጆችን ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ሲደርስ መዳከሙ ተገለጠ። ማቲው ያገኘውን እየገነዳደሰ እና እየገደለ በካሪቢያን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የፍሎሪዳ የባሕር ጠረፍ ለ4 ተከታታይ ቀናት ብርቱ ጥፋት አድርሷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ሁኔታ እና ፍሪደም ሃዉስ

የኢትዮጵያ ሁኔታ እና ፍሪደም ሃዉስ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ የቀጠለዉ ተቃዉሞ

በመንግስት በኩል በክልሉ እየተካሄደ ስላለዉ ጉዳይ መረጃ ለመዉሰድ ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ የመንግስት መገናኛ ብዙኃኖች በሰበታ ብቻ «ከ40 ሺህ በላይ ሰራተኞችን የሚያሳትፉ 11 ፋብሪካዎችና 60 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች» መዉደማቸዉን ዘግበዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ዉሎ

በአዲስ አበባ አካባቢ በሚገኙ ከተሞችና ቀበሌዎችም ተቃዉሞዉ ቀጥሎ፤ የመንግስት እና የድርጅቶች መኪኖች መሰባበር ወይም መቃጠላቸዉ ተሰምቷል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የተዉኔቱ ፈርጥ ተስፋዩ ገሰሰ

ሰማንያኛ ዓመታቸዉን መስከረም 17 ከአከበሩ ከቀናት በኋላ በስልክ ያገኘናቸዉ የመድረኩ ፈርጥ ፤ የተዉኔቱ ምሁር ተባባሪ ፕሮፊሰር ተስፋዩ ገሰሰ ነበር ያደመጥነዉ። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ሰነበታችሁ፤ በአገር ፍቅር በብሔራዊ ትያትር ብሎም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የባህል ተቋም ኮሌጅ አገልግለዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ከሰሀራ በስተደቡብ ሀገራት እና የዓለም ባንክ ዘገባ 

ከሰሀራ በስተደቡብ የሚገኙ ሀገራት ዘንድሮ 1,6% የምጣኔ ሀብት እድገት ብቻ እንደሚያስገኙ የዓለም ባንክ ሰሞኑን ያወጣው ዘገባ አስታወቀ። እንደ ዘገባው፣ ይኸው እድገት ባለፉት ሁለት አሰርተ ዓመታት ከተመዘገበው ጋር ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

    የመምሕራን ቀን፤ የካሜሩን ምሳሌ

ቦኮ ሐራም ሰሜናዊ ካሜሩን ዉስጥ ጥቃት ማድረስ ከጀመረ ስድስተኛ ዓመቱ ነዉ።በዚሕ ጊዜ ዉስጥ ቡድኑ የተለያዩ ትምሕርት ቤቶችን አጥቅቷል። የኮሴሬይ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤትም አልቀረለትም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ፖሊስ በናትናኤል ጉዳይ ላይ ይግባኝ አቀረበ

እነ ናትናኤል የተያዙት ከትናንት በስተያ አዲስ አበባ ስታድዮም አካባቢ በሚገኘው ላሊበላ ሬስቶራንት ውስጥ ባለፈው እሁድ ቢሾፍቱ ስለደረሰው የሰዎች ሞት ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ ተወያይታችኋል በሚል መሆኑን አቶ አምሀ ከናትናኤልን እና ከጓደኞቹ እንደሰሙ ተናግረዋል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ተቃዉሞ በአዲስ አበባና አከባቢዋ

በኦሮሚያ ልዩ ዞን አንዱ ከተማ የሆነችዉ በቡራዩ ከተማ የተካሄደዉ ተቃዉሞ እንደነበር በተለምዶዉ ዋላጋ ሰፈር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲሱ የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ተመረቀ

ግንባታው 3.4 ቢሊዮን ዶላር የፈጀው ይኽው የባቡር መስመር ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ሲጀምር በቀን 5,600 ሰዎች እና 3500 ቶን ቁሳቁሶችን ማመላለስ ይችላል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በቢሾፍቱ የሞቱት ጉዳይ እንዲጣራ መጠየቁ

ጎሜሽ የአውሮጳ ህብረት በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝምታ ከማለፍ እንዲቆጠብም አሳስበዋል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የተቃውሞ ሰልፍ በበርሊን

በቅርቡ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፣መንግሥት የሰብዓዊ መብት ረገጣን እንዲያቆም ተጽእኖ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በህክምናው ዘርፍ የዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚ

ስዊድን መዲና ስቶኮልም የሚገኘው የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ በሕክምናው ዘርፍ የዘንድሮው የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ጃፓናዊው ዮሺኖሪ ዑሱሚ መሆናቸውን ሰኞ ዕለት ይፋ አድርጓል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

    የመምሕሩ መታሰርና ሲፒጄ

«ሲ ፒ ጄይ» በሚል የእንግሊዘኛ ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ መምሕርና የአምደ መረብ ጸሐፊ ሥዩም ተሾመ የታሰረዉ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ሳይሆን አይቀርም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአውሮጳ ኅብረት እቅድ እና የሀንጋሪ ተቃውሞ

ሀንጋሪያውያን የአውሮጳ ኅብረት ፣ አባል ሀገራት ስደተኞችን እንዲከፋፈሉ ባወጣው እቅድ ላይ ከትናንት በስተያ የሰጡት ድምፅ ውድቅ ሆኗል። ከድምፅ ሰጭዎቹ አብዛኛዎቹ እቅዱን ቢቃወሙም ድምጹን ለመስጠት የወጣው ህዝብ ቁጥር ከ50 በመቶ በማነሱ ህዝበ ውሳኔው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። መንግሥታት ግን አሁንም የህብረቱን እቅድ መቃወሙን ቀጥሏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የከተሞች የአየር ብክለት

ከዓለማችን ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆነዉ ሕዝብ የዓለም የጤና ድርጅት ተገቢ ከሚለዉ የንፁሕ አየር ጥራት እጅግ ዝቅ ባለ እና የተበከለ አየር ባላቸዉ ከተሞች እንደሚኖር ይገልጻል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የቢሾፍቱ ግድያና የጀርመኑ ድርጅት

በጀርመንኛ «ገዜልሻፍት ፊውር በድሮተ ፈልከር» የተሰኘዉ ድርጅት ሐላፊ ዑልሪሽ ዲሊዩስ እንደሚሉት ባለፈዉ ዕሁድ ቢሾፍቱ ዉስጥ የተፈፀመዉ ግድያ በገለልተኛ ወገኖች መጣራት አለበት።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

 የቢሾፍቱ ግድያና ፀሎት

ፓትሪያርክ ብፁዑ አቡነ ማቲያስ ለሟቾች ፀሎት እንዲደረግ መወሰኑን ያስታወቁት ትናንት ነበር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ከኢሬቻ እልቂት በኋላ የተባባሰዉ ተቃዉሞ 

በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ በነበረዉ የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በታዳሚዎቹና በፀጥታ ኃይላት መካከል በተፈጠረዉ ግጭት የብዙ ሰዉ ሕይወት ማለፉ እየተዘገበ ነዉ። ይህንን ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃዉሞ መባባሱንና አሁንም የሰዉ ሕይወት እየጠፋ ነው ተብሏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሀዘን ያጠላበት የኢሬቻ በዓል

በኢትዮጵያ ቢሾፍቱ ከተማ ሊከበር በተዘጋጀዉ የኢሬቻ በዓል ለሞቱ ወገኖች መንግሥት የተሰማዉን ሀዘን በመግለጽ ብሔራዊ ሀዘን ቀን አዉጇል። ይህን ክስተት ተከትሎ በሰሜን አሜሪካ፤ ካናዳ እና ዩናይትድ ስቴትስ የተከበረዉ የኢሬቻ በዓል ሀዘን አጥሎበት ነዉ የተጠናቀቀዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጀርመን ዉህደት የጨለመ ገጽታ

26 ዓመት ያስቆጠረዉ የምሥራቅ ምዕራብ ጀርመን ዉህደትና በመጤዎች ጥላቻ የጨለመዉ ገፅታ፤
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ተጨዋቾች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማሊ አቻው ተሸንፎ ከማጣሪያው ውጪ ሆኗል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ጨዋታዎች መሪው ማንቸስተር ሲቲ ነጥብ ጥሏል።  ማንቸስተር ዩናይትድ ነጥብ ሲጋራ፤ አርሰናል አሸንፏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢሬቻ፤ተቃዉሞና ግድያ

የመንግሥት ባለሰልጣናት በሚቆጣጠሯቸዉ መገናኛ ዘዴዎች እንዳሉት የፀጥታ ሐይላት በተኮሱት ጥይት የተገደለ ሰዉ የለም ።የአይን ምስክሮች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ግን የመንግስትን መግለጫ ሐሰት ይሉታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢሬቻ በዓል በርካቶች ሞቱ

ደብረዘይት ውስጥ ዓመታዊው የኢሬቻ በዓል ዛሬ ወደ ጸረ-መንግሥት ተቃውሞ ተቀይሮ ፖሊስ በተኮሰው አስለቃሽ ጢስ እና ጥይት እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ግርግር በርካቶች ተረጋግጠው መሞታቸውን የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘገቡ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የምሁራን ዉይይት እና ሚና

በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተካሄደዉ የምሁራን ዉይይት እና ምሁራን በሀገሪቱ በፖለቲካ ያላቸዉ ሚና
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የቅርስ ውድመት እና «አይሲሲ» ያሳለፈው ብይን

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፡ «አይ ሲ ሲ» በጦር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸውን አህመድ አል ፋቂ አል ማህዲን በዘጠኝ ዓመት እስራት እንዲቀጡ መበየኑ የሚታወስ ነው። ለወትሮው ዓመታት የሚወስድበት ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት፡ በማህዲ ላይ ብይኑን ያስተላለፈው ካሁን ቀደም በታሪኩ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሺሞን ፔሪዝ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ከተለያዩ የዓለም ሃገራት የመጡ መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች እንዲሁም ታዋቂ ፖለቲከኞች በተገኙበት የቀድሞዉ የእስራኤል ፕሬዚደንትና የታዋቂዉ ፖለቲከኛ የሺሞን ፔሪዝ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፀመ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዘረኝነት ጥላቻ በፖላንድ 

ፖላንድ በሚገኙ ስደተኞች ላይ የዘረኝነትና የጥላቻ ጥቃት መድረሱን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸዉን የተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ጨምሮ መገናኛዎች መዘገባቸዉ ተገለጸ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሺሞን ፔሪስ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ከተለያዩ የዓለም ሃገራት የመጡ መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች እንዲሁም ታዋቂ ፖለቲከኞች በተገኙበት የቀድሞዉ የእስራኤል ፕሬዚደንትና የታዋቂዉ ፖለቲከኛ የሺሞን ፔሬስ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፀመ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢሬቻ እና አዲሱ ትውልድ

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እና የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ የኦሮሞ ሰዎችን የሚያገናኘው የኢሬቻ በዓል በመጪው እሁድ ይከበራል። በዓሉ በወጣቶች ዘንድ ምን ያክል ይታወቃል? እንዴትስ ይከበራል?
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአሜሪካ ጥቁሮች ቤተ-መዘክር

ቤተ መዘክሩን ለማሠራት ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ  ወጪ ሆኖበታል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አፍሪቃዉያን ተገን ጠያቂዎችና የመሰደዳቸዉ መንስዔ

የስደተኞች ቀዉስን በተመለከተ የጀርመን ፖለቲካ አትኩሮቱ በአብዛኛዉ በሶርያ፤ በኢራቅና በአፍጋኒስታን ላይ ነዉ። ባለፈዉ ዓመት ጀርመን የገቡት አብዛኞቹ ስደተኞች ከነዚህ ሦስት ሃገራት ቢሆንም የሜዲተራንያ ባሕርን አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ የገቡ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ጥቂት አይደሉም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ማኅበረሰቡና  የሴቶች ትግል

«ኢትዮጵያ ገና በሴቶችዋ ወይም ገና በእናቶችዋ መጠቀም ያልቻለች ሃገር ናት።ለዝያ ነዉ አሁንም ወደ ኋላ የምንወድቀዉ ፤ የምናዝነዉ ፤ የምናለቅሰዉ። እናቶቻችንን ፤ እህቶቻችንን፤ ሴት ልጆቻችንን በፖለቲካ ዓለምም ሆነ በሌሎች ዘርፍ የሚችሉትን ቦታ መስጠት ስላልቻልን ነዉ።ኢትዮጵያ ገና በሴቶችዋ በእናቶችዋ መጠቀም ያልቻለች ሃገር ናት።»
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃዉሞና የገዢዉ ፓርቲ ጉባኤዎች

የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ (ሕወሐት) ስብሰባ እንደ ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) አቻዉ በባለሥልጣናቱ ላይ የወሰደዉ ተጨባጭ እርምጃ የለም። የአመራር ለዉጥ ለማድረግ መወሰኑ ግን ተዘግቧል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዱር እንስሳ ንግድን የተመለከተዉ ከፍተኛ ጉባዔ 

የአፍሪቃ ዝሆኖች ጥርስ እና የአዉራሪስ ቀንድ ሽያጭ ዝዉዉር ኢትዮጵያን ጨምሮ የምሥራቅ፤ መካከለኛና የደቡባዊ አፍሪቃ ሃገራትን እያወዛገበ ነዉ። በደቡብ እና ምሥራቅ እስያ ገበያዉ የደራዉ የዝሆን ጥርስ ለሃብት መገለጫ እና ለጥበብ ሥራዎች ይዉላል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በአካባቢ ፖለቲካዊ ጉዳይ የኢጋድ ስብሰባ 

ለምሥራቅ አፍሪቃ በየነ መንግሥታት ለ«ኢጋድ» አባል አገሮች ለእድገታቸዉ እንደ አማራጭ የፊደራሊዝም አወቃቀር ይበጃል በሚል ከሰሞኑ ጥናቶች ቀርበዋል። ጥናቱ የቀረበዉ በአፍሪቃ ቀንድ የማኅበራዊ ፖሊሲ ጥናት ተቋም መሆኑ ተመልክቶአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዶይቼ ቬለ የአማርኛው ስርጭት መታፈን

የዶይቼ ቬለ የአማርኛ ስርጭት ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ  ሆን ተብሎ እየታፈነ ወይም እየታወከ መሆኑ  ተገለጸ። የመሥሪያ ቤቱ የቴክኒክ ባለሙያዎች እንደረሱበት፣ ስርጭቱ የሚታወክበት ቦታ እና የጊዜ ርዝመት የተለያየ መልክ አለው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

  ከአዲስ- ጅቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ

የኢትዮጵያን የኤኮኖሚ እድገት ያፋጥናል ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያላትንም ትስስር ያጠናክራል የተባለለትን 656 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉን የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ግንባታም ላለፉት አራት ዓመታት በመገንባት ላይ ይገኛል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ተስፋ የተጣለበት የባሕር ውስጥ ማሳ

የቀድሞው አሳ አስጋሪ የባሕር ውስጥ ገበሬ ሆኗል። ብሬን ስሚዝ ከኒው ዮርክ አቅራቢያ በሚገኝ የባሕር ዳርቻ የማሳያ እርሻውን መከወን ከጀመረ ሰነባበተ። ስሚዝ የሰው ልጅ የአመጋገብ ሥርዓትን ለመቀየር ሁነኛው መንገድ የባሕር ውስጥ እርሻ ነው የሚል እምነት አለው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የቀድሞዉ የእስራኤል ፕሬዝደንት ሞት

የእስራኤል ሕዝብ በቀድሞ ፕሬዝደንቱ በሺሞን ፔሬስ ሞት የተሰማዉ ሐዘን ሲገልፅ ነዉ የዋለዉ። ከአንድ ሳምንት በፊት ጭንቅላታቸዉ ዉስጥ ደም በመፍሰሱ በሕክምና ሲረዱ የቆዩት ፔሬስ ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ነዉ ያረፉት።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጥቂት ዲያስፖራ ትግራይ ተወላጆች መግለጫ

በውጭ ሀገር ከሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች መካከል ወደ 34 የሚጠጉት ሕወሀት ኢህአዴግ ከስልጣን ወርዶ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ሰሞኑን ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠይቀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ደቡብ ሱዳን፤ ዳግም ለጦርነት?

ሱዳን የሚገኙት የቀድሞዉ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻር በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሚመራዉና ጁባ በሚገኘዉ መንግሥት ላይ ይፋዊ ጦርነት አዉጁ። ከካርቱም ሱዳን በወጣዉ መግለጫ መሠረት፤ ሬክ ማቻር ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሚመራዉ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ሕገ ወጥ መሆኑን  ማወጅ ይፈልጋሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰማያዊ ፓርቲ አቤቱታ 

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉን ጠቅላላ ስብሰባ ከሰሞኑ ማካሄድ እንዳልቻለ ተነግሯል። የምርጫ ቦርድ እንደሚለዉ ስብሰባዉ ያልተካሄደዉ የፓርቲዉ ጽሕፈት ቤት የሚገኝበት ስፍራ በርካታ ተሰብሳቢ አባላቱን ለማስተናገድ ስለማይበቃ በመኢአድ ቅጥር ግቢ ያቀደዉ ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሺሞን ፔሬስ ህልፈተ ሕይወት

የቀድሞው የእስራኤል ፕሬዚደንት ሺሞን ፔሬስ አረፉ። የ93 ዓመቱ ታዋቂ ፖለቲከኛ ከሁለት ሳምንታት በፊት ደም ጭንቅላታቸው ውስጥ ከፈሰሰ በኋላ ሀኪም ቤት መግባታቸው የሚታወስ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አውሮጳ እና የስደተኞች ቀውስ

ባለፈው ዓመት የበርካታ ስደተኞች መተላለፊያ እና መድረሻ የነበሩ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የህብረቱ ድንበር ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግበት ተስማምተዋል ። የሀገራቱ መሪዎች ባለፈው ቅዳሜ ቭየና ኦስትርያ ውስጥ ባካሄዱት ጉባኤ ወደፊት ሊከሰት የሚችል ሌላ የስደተኛ ቀውስን ለመከላከል ያስችላሉ ባሏቸው ሌሎች እርምጃዎችም ላይ ተስማምተዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን

ኢትዮጵያዉያን ጨምሮ 220 አፍሪቃዉያን ስደተኞችን ትናንት ወደ የሃገራቸዉ መመለስዋን የየመን ባለስልጣናት ገለፁ። የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት ዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዛሬ ባወጣዉ ዘገባ መሰረት የመን ወደየሃገራቸዉ ከመለሰቻቸዉ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ በደቡባዊ የኤደን ወደብ ከተማ የነበሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ናቸዉ።  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ውይይት

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ውይይት የትምህርት ጥራት እና ሌሎች ርዕሶች ለውይይት ቢቀርቡም ፣ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ቅድሚያ እንዲሰጠው ተሳታፊዎቹ ባነሱት ጥያቄ መሠረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የፓሪሱ ስምምነት ተግባራዊነት

የፓሪሱ ስምምነት አንድምታ እና ተግባራዊነት፤
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንታዊ እጩዎች የቲቪ ክርክር

በዩኤስ አሜሪካ የፊታችን እጎአ ኅዳር ስምንት ለሚደረገው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩት የዴሞክራት እና የሬፓብሊካን ፓርቲዎች እጩዎች ሂለሪ ክሊንተን እና ዶናልድ ትራምፕ ትናንት የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን ክርክራቸውን አካሄዱ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

    የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ

የማኅበሩን ፤ የሌሎች ወገኖችን፤ የመገናኛ ብዙሃንን ማስጠንቀቂያ መንግሥት «ጆሮ ዳባ ልበስ» በማለቱ፤ ከሁሉም በላይ የሕዝቡን ብሶት ከቁብ ባለመቁጠሩ የተጠራቀመዉ ቅሬታ ወደ ሥርዓት ለዉጥ ጥያቄ ንሯል።-እንደ አቶ ፋንታሁን።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሶሪያ ጦርነትና የሐያላኑ ዉዝግብ

ከሶቬት ሕብረት መፈረካከስ በኋላ ወደ ወዳጅነት ተቀይሮ የነበረዉ የረጅም ጊዜ ጠባቸዉ በዩክሬን ፖለቲካዊ ቀዉስ ሰበብ ዳግም በተጋጋመበት ወቅት መሆኑ ነዉ።በዩክሬን ሰበብ   በማዕቀብ እየተቀጣጡ፤ በጦር ሐይል እየተዛዛቱ ሶሪያ ዉስጥ መሸጉ የሚባሉ አሸባሪዎችን በጋራ እንዉጋ የሚለዉን የሞስኮዎች ጥያቄ መቀበል ለዋሽግተኖች ፖለቲካዊ ኪሳራ  ነዉ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት 16.01.2009

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር ጎልደን ሌብል ሲል  ከፈረጃቸው 13 የጎዳና ውድድሮች  መካክል አንዱ የሆንው 43ኛው የበርሊን ማራቶን ውድድር ትላንት  ተካሂዶ ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆነዋል። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

  የአዉሮጳ ኢንቨስትመንት ባንክ ብድር ለኢትዮጵያ 

የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች እንደሚሉት ካለፈዉ ሕዳር ጀምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተቀጣጠለዉ ተቃዉሞና ግጭት ሐገሪቱን ለመዋዕለ ነዋይ ፍሰት የማትመች አድርጓታል።የመብት ተሟጋቾች ደግሞ የኢትዮጵያን መንግሥት በመብት ረጋጭነት እየወቀሱት ነዉ።የአዉሮጳ ባንክ በዚሕ ወቅት በጨቋኝነት ከሚወቀሰዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መዋዋሉን ተገቢ አይደለም የሚሉ አሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ

በመላዉ ኢትዮጵያ የመስቀል በዓል በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በነገው ዕለት  ይከበራል። ዛሬ በዋዜማው ደግሞ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የደመራ በዓል ስነ ስርዓት ተካሂዶዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያውያን በበርሊን ማራቶን ድል ተቀዳጁ

ጀርመን መዲና በርሊን ውስጥ ዛሬ በተከናወነው የማራቶን ሩጫ ፉክክር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት አበሩ ከበደ ድል ተቀዳጁ። አትሌት ቀነኒሳ 42 ኪሎ ሜትሩን የሩጫ ውድድር ያሸነፈው የኬንያው ብርቱ ተፎካካሪ ዊልሰን ኪፕሳንግን ጥሎ በማለፍ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኮንሶ ጥያቄ ግጭት እና መፍትሄው

መንግሥት ኮንሶ በሰገን ዞን የተጠቃለለው ህዝቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ይላል ። ጥያቄውን የሚያቀርቡትንም የግል ጥቅማቸውን ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ሲል ይከሳል ። ኮሚቴው በበኩሉ በዚህ ውሳኔ ህዝቡ ማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞቹን ተነፍጓል ሲል ይከራከራል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ቡሩንዲ እና የተመድ ምርመራ ውጤት

ስለቡሩንዲ የወጣ አንድ የተመድ ዘገባ፣ የፖለቲካ ታዛቢዎች ከብዙ ጊዜ ወዲህ የጠረጠሩትን ፣ ማለትም፣ በዚችው ሀገር ውስጥ ሆን ተብሎ የሚፈፀም የቁም ስቅል ማሳየት ተግባር እና ካለ ፍርድ ቤት እውቅና የሚፈፀም ግድያ መፈፀሙን አረጋገጠ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግር እና የወጣቶች አስተያየት

ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ንግግራቸው በማህበራዊ ድረ-ገፆች አጠቃቀም ላይ የሰጡት አስተያየት አከራካሪ ሆኗል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሶማሊያ ምርጫ ምን ይዞ ይመጣል?

ለሁለት አስርት ዓመታት መንግስት አልባ ሆና የቆየችው እና በእርስ በእርስ ጦርነት አሳር አበሳዋን ስታይ የባጀችው ሶማሊያ አንጻራዊ የሚባል መረጋጋት ከሰፈነባት ጥቂት ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ የሽግግር መንግሥት አዋቅራ፣ ፓርላማ መስርታ፣ ጎረቤቶቿ በየጊዜው ከሚሰበሰቡበት ማህበር ዕድምተኛ መሆን ከጀመረች ከረመች፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሩሲያ ግብ በሶርያ

በሶርያዉ የእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ ሩሲያ መሳተፍ ከጀመረች አንድ ዓመት ሊሆናት በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተዋል። የፖለቲካ ተንታኞች ሞስኮ በዚህ ግጭት ዉስጥ ለመግባት የተነሳችበትን አላማ አጋሯ የሆኖት ፕሬዝደንት ባሽር አላሳድ መንበር እንዳይገለበጥ በማድረግ፤ ዩናይትድ ስቴትስንም ለድርድር በጠረጴዛ ዙሪያ በማስቀመጥ አሳክታለች ባይ ናቸዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የከተሞች የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር በኢትዮጵያ

የኢትዮጽያ መንግስት በ36 ቢሊዮን ብር በጀት በከተሞች የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ሊዘረጋ ማቀዱን አስታወቀ።በመርሃ ግብሩ ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። መንግሥት እንደሚለው መዲናዋን አዲስ አበባን ጨምሮ በ 11 ከተሞች ተፈጻሚ የሚሆነዉ ይኸዉ እቅድ ከ600 ሺህ በላይ ሰወችን ተጠቃሚ ያደርጋል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አደገኛው የአፍሪቃዉያን ስደት

አፍሪቃዉያን ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ሲሞክሩ ከሚደርስባቸው እንግልት እና የሞት አደጋ በተጨማሪ በተለያዩ የአፍሪቃ አገራት እስር ቤቶች ስቃያቸው መባባሱ ተገለፀ። ሱዳን በጃንጁዊድ ሚሊሺያዎች ወደ ሃገርዋ የሚገቡ ስደተኞችን ታድናለች።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጦርነት ልጆች

ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 88 ሺህ ሕፃናት በአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት ለጥገኝነት ተመዝግበዋል። ከእነዚህ መካከል ገሚሱ ከአፍጋኒስታን የተሰደዱ ናቸዉ። ሀገራቸዉ ዉስጥም በርካታ የጦርነት ልጆች ለመሰደድ ዕድላቸዉን እየተጠባበቁ ነዉ። አፍጋኒስታን ዉስጥም በአሁኑ ወቅት 1,2 ሚሊየን ሰዎች ስደት ላይ ናቸዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የህዳሴው ግድብ የጥናት ስምምነት ጋ/መግለጫ

በዓባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የህዳሴ ግድብ በአካባቢው ላይ ሊያደርሰው የሚችል ተፅዕኖ ስለመኖር አለመኖሩ፣ እንዲሁም፣ ወደ ሱዳን እና ወደ ግብጽ በሚፈሰው የውኃ መጠን ላይ ላይ የሚያሳርፈውን ተፅዕኖ እንዲያጠኑ በተመረጡ ሁለት የፈረንሳይ ኩባንያዎች ተፈጥሮ የነበረው ልዩነት ከጥቂት ቀናት በፊት መወገዱ የሚታወስ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኮለኙ የፊልም ፊስቲቫልና ኢትዮጵያዉያኑ

ዘንድሮ ለ 14ኛ ጊዜ በምዕራብ ጀርመንዋ በኮለኝ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃ ፊልም ፊስቲቫል የሁለት ኢትዮጵያዉያን የፊልም ስራዎችን ጨምሮ በአፍሪቃና ከአፍሪቃ ዉጭ የሚኖሩ አፍሪቃዉያን ፊልሞች የቀረቡበት እና የፊልም ባለሞያዎቹ ክህሎት የታየበት መድረክ ነው ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የራይት ላይቭሊሁድ ሽልማት

ቦምብ፤ሚሳዬል፤ አረር፤ ጥይቱን ያፈናዳ-የተኩሰዉ ወገን ማንነት ለነሱ ከቁብ የሚገባ አይደለም።ሰዉ ነዉ ቁም ነገራቸዉ።ሕይወት ማዳን ነዉ-ዓላማቸዉ። በየእሳት፤ጢስ፤ጠለስ፤ ዉድመቱ መሐል ዘለዉ ይገባሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሳይበር ጥቃትና ስጋቱ

ኮምፕዩተርና በይነመረብ በዓለማችን የሰዎችን የዕለት ተዕለት ሥራዎች ከማቃለል ጀምሮ ዓለም አቀፋዊ ትስስርና ቅርርብ እስከመፍጠር የዘለቀ ተፅዕኖ እንዳለዉ እየታየ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News