Blog Archives

የድኅረ ወሊድ ጭንቀት

የድኅረ ወሊድ ጭንቀት(postnatal depression) እናቶች ከወለዱ በኋላ የሚያጋጥማቸው፣ ከአንድ ወር እስከ አንድ ዓመት ሊዘልቅ የሚችል የጭንቀት ዓይነት ነው፡፡ ልጅ መውለድ የሚያስከትለውን አዲስ ሁኔታ፣ ጠባይ፣ የሰውነትና የስሜት ለውጥ ለማስተናገድ በሚደረገው እናታዊ ትግል ምክንያት በመጀመሪያዎቹ ቀናት የጠባይ ልውጠት(baby blues) ይከሠታል፡፡ ይህ ግን ለሁለትና ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነው፡፡ ነገሩ ከእነዚህ ቀናት በላይ ከዘለቀ ወደ ጭንቀት ያድጋል፡፡ እርሱም የድኅረ ወሊድ ጭንቀት(postnatal depression) ይባላል፡፡ በዚህ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ የሚገኙ እናቶች ‹ሙዳቸው› ይጠፋል፤ የተሸናፊነት ስሜት ይሰማቸዋል፤ ተስፋ ቢስነት ይነግሥባቸዋል፤ ስለ ተወለደው ሕጻን አብዝተው ይጨነቃሉ፤ አንዳች የሆነ ነገር ልጃቸውን የሚነጥቃቸውና የሚገድልባቸው ወይም የሚያሳምምባቸው ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ፈልገው የሚያመጡት ጠባይ ሳይሆን ወሊድ የሚያመጣባቸው ክስተት ነው፡፡የድኅረ ወሊድ ጭንቀት ቁጣን ያስከትላል፣ ያነጫንጫቸዋል፣ ተናጋሪ አንዳንዴም ጯሂ ያደርጋቸዋል፡፡ እጅግ የሚገርመው ደግሞ የሚቆጡትም፣ የሚነጫነጩትም፣ የሚናገሩትም፣ የሚጮኹትም በሚወዱትና በሚቀርባቸው ሰው ላይ ነው፡፡ ይህም  መውለድ ያመጣው የጠባይ ለውጥ እንጂ ውሳጣዊ የልቡና ለውጥ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የሚነጫነጩበትን፣ የሚቆጡበትንና የሚጮኹበትን ብቻ ለተመለከተ ሰው ትዳሩ የፈረሰ፣ ቤተሰቡ የታመሰ ሊመስለው
Posted in Ethiopian News, Religion

‹ግቡ የአጥቂው፣ ድሉ የቡድኑ ነው›

ሰውዬው አንበሳ ሊያድን ጫካ ይገባል፡፡ እየተሽሎከለከ ዛፍ ለዛፍ ሲያነጣጥር፣ የአንበሳውንም ዱካ እያዳመጠ ሲከተል፣ ቆየና አንድ የአንበሳ ደቦል በቀስቱ አነጣጥሮ ጣለ፡፡ ገና ደስታውን ሳያጣጥም የሰውነት ክፍሎቹ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፡፡ እጁ አንበሳውን አነጣጥሮ የጣለው እርሱ መሆኑን በማስረዳት የተለየ ክብር ሊሰጠው እንደሚገባ ተናገረ፡፡ ይህንን የሰማው እግሩም ‹መጀመሪያውኑ ማን ተሸክሞህ መጥተህ ነው ወጋሁት፣ መታሁት የምትለው› ብሎ ክብሩ የእርሱ መሆኑን ገለጠ፡፡ ነገሩን የታዘበው ዓይንም ‹በምን ዓይተህ ነው ያነጣጠርከው› አለና ክብሩ የእርሱ መሆኑን በኩራት ደሰኮረ፡፡ ጆሮም የአንበሳውን ዱካ እኔ በጽሞና ባልከተል የት ታገኙት ነበር? ሲል ቀዳሚው ባለ ድል እርሱ መሆኑን ደነፋ፡፡ አፍና ሆድም ‹ባልተበላ ምግብ በባዶ ሆድ እንኳን ማደን መታደን አይቻልም› ሲሉ ተከራከሩ፡፡ እንዲህ የሰውነት ክፍሎች ሁሉ እየተነሡ ‹ተኳሹ፣ መራዡ፣ አነጣጣሪው፣ እኔ ነኝ› እያሉ ሲከራከሩ ሰውዬው ወደ ግዳዩ ሳይሄድ ዘገየ፡፡ በዚህ መካከል ዓይን ቀና ቢል አንበሳው ሲሞት ያሰማውን ድምጽ የሰሙ ሌሎች አንበሶች ዙሪያቸውን ከበዋቸዋል፡፡ ዓይን በድንጋጤ ሲፈጥ ያስተዋለው እጅም ለሌሎች አካላት መከባባቸውን ጠቆመ፡፡ ይህን የተመለከተው እግር እሮጣለሁ
Posted in Ethiopian News, Religion

የማይሰለቹት አባት፤ ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ

ንግግራቸው ምንጊዜም ፈዋሽ ነው፡፡ የትኛውም ቦታ ላይ ሆነው ቢሰሙት ለራስ የተላከ ደብዳቤ ይመስላል፡፡ ሃይማኖታቸውን ከንግግራቸው ማወቅ ከባድ ነው፡፡በቅርብ ለሚያውቋቸው ወይም ልብሳቸውን ለተመለከተ ካልሆነ በቀር፡፡ የሚናገሩት ሁሉንም እምነት የሚመለከት ነውና፡፡ የሁለቱን ሲኖዶሶች ዕርቅ ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የሚሊኒየም አዳራሽ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉትን መልእክት ሊቃነ ጳጳሳቱ ከልባቸው ካዳመጡት ‹ሲታረቁ ከሆድ፣ ሲታጠቡ ከክንድ› የሚያደርግ ነው፡፡  እሑድ ዕለት የበጎ ሰው ሽልማት ፕሮግራም ላይ ለክቡር አቶ ለማ መገርሳ ሽልማቱን ያበረከቱት እርሳቸው ነበሩ፡፡ ቢሮክራሲ የሚባል ነገር የማያውቃቸው፤ ነገርን በጉዳዩ ልክ ብቻ የሚመዝኑ¶ የተጠሩበትን ጉዳይ እንጂ የጠራቸውን ሰው ማንነት ከቁም ነገር የማይቆጥሩ፣ የአለቃ ሳይሆን የአባት ጠባይ ያላቸው ናቸው፡- ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ፡፡ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ወደ ሚሊኒየሙ መርሐ ግብር ሲሄዱ ቀዳሚ ሙፍቲ ብቻቸውን ተቀመጡ፡፡ ነጻነት ተስፋዬ ‹ብቻቸውን ከሚሆኑ አብረኻቸው ሁን› ሲለኝ የዘመናት ምኞቴ ነበርና አጠገባቸው ቁጭ አልኩ፡፡ ከአንድ ሽማግሌ አጠገብ መቀመጥ አንድ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ገብቶ የማንበብ ያህል ነው፡፡ የሃይማኖት አባት ሲሆኑ ደግሞ የመጽሐፉ ቁጥርና ጥራት ይጨምራል፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (1832 – 1911 ዓ.ም.)

አበባው አያሌው እንደ ጻፈውእቴጌ ጣይቱ በኢትዮጵያ ታሪክ የጎላ ሥፍራ ካላቸው እጅግ ጥቂት አንስት በግምባር ቀደምትነት የሚጠሩ ናቸው፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያት ንጉሥ ምኒልክን (በኋላ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያን) በሕግ ጋብቻ ካገቡ በኋላ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ አስተዳደርና ሥልጣኔ ያበረከቱት አስተዋጽዖ ነው፡፡ ከበርካታ አስተዋጽዖዎቻቸው ጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡  የዐፄ ምኒልክ አስተዳደር እንዲመቻችና ሥልጣናቸው እንዲጠናከር አስተዋጽዖ ማድረግየዐፄ ምኒልክ የትውልድ ሐረግ ከሰሎሞናውያን ነገሥታት የሚመዘዝ ቢሆንም ከሸዋ አልፎ ከሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች መሳፍንት ጋር እምብዛም አይተሳሰርም፡፡ የእቴጌ ጣይቱ የትውልድ ዘር ሐረግ ግን አብዛኛውን የሰሜን ኢትዮጵያን ከሚገዙት ወይም ከሚያስተዳድሩ መሳፍንት በእጅጉ የተሣሠረ ነው፡፡ የትውልድ ሐረጋቸው ከደምቢያ በደጃች ማሩ (ማሩ ቀመስ ደምቢያ)፣ ከስሜን በደጃዝማች ኃይለ ማርያም፣ ከላስታና ዋግ በዋግ ሹም ክንፉ፣ ከትግራይ በደጃዝማች ገብረ ሚካኤል፣ ከጎጃም በደጃዝማች ዮሴደቅ፣ ከወሎ የጁ ደግሞ በቅደመ አያቷ ዕውቁ የዘመነ መሳፍንት  የወረሴህ መስፍን በራስ ጉግሳ ሙርሳ የተዛመዱ ናቸው፡፡የትውልድ ሐረጓ ከብዙ የሰሜን ኢትዮጵያ መሳፍንት መተሣሠሩ ለዐፄ ምኒልክ ሥልጣን መደላደልና ለአስተዳደሩ መመቻቸት ትልቅ አስተዋጽዖ ነበረው፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የ 2010 ዓ.ም. የበጎ ሰው ሽልማት ዕጩዎች

6ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ይካኼዳል፡፡ በዚህ ዓመት ለሚካኼደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ዕጩዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡1.በመምህርነት ዘርፍ1.  መምህር ሥዩም ቦጋለ( በአዊ ዞን ታላላቅ ሥራዎችን የሠሩ መምህር)2.  መምህር ስመኘው መብራቱ( በደቡብ ጎንደር ታች ጋይንት ልዩ ልዩ ሥራዎችን የሠሩ መምህር)3.  መምህር ስለሺ ካሣዬ(በድሬዳዋና በሐረር ከተማ ታላላቅ ሥራዎችን የሠሩ መምህር)2) ለኢትዮጵያ በጎ የሠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች1.  ኢያን ካምፕቤል (Ian Campbell)(በጣልያን ወረራ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸሙ ግፎችን በማጥናትና በማሳተም ይታወቃሉ)2.  ሬልዶፍ ኬ. ሞልቬር (Reidulf K. Molvaer)(የ Black Lions - መጽሐፍ ደራሲ)3.  ሐጋይ ኡልሪክ (Hagai Ulrich)(ስለኢትዮጵያና መካከለኛው ምሥራቅ ግንኙነት ብዙ መጻሕፍት የጻፉ)3) መንግሥታዊ የሥራ ሐላፊነትን በብቃት መወጣት1.  ዶ/ር አበራ ዴሬሳ (የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩ)2.  ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም3.  ወ/ሮ ሙሉ ወርቅ ገብረ ሕይወት(የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሥራ አስኪያጅ የነበሩ)4) በበጎ አድራጎት ዘርፍ1. አቶ መኮንን ሙላት        (መስማት የተሣናቸውን ከሠላሳ ዓመታት በላይ በመርዳት የሚታወቁ) 2. ሄርሜላ
Posted in Ethiopian News, Religion

ወደ ምዕራብ ሰዎች

የሦስት ወሩን አድካሚና አስደሳች ሩጫ አገባደድነው፡፡ አሁን የቀረን ዝርዝር ሪፖርቱን ተረጋግቶ መጻፍ ነው፡፡ ብዙ አስገራሚ፣ አሳዛኝ፣ አስደሳች፣ አስቂኝ ገጠመኞችን በቀጣዮቹ ቀናት አወጋችኋለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በአሜሪካ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለማነጋገር ወደ አሜሪካ እንደሚሄዱ የታቀደው ግንቦት ወር ላይ ነው፡፡ የዳላሱ የኢትዮጵያውያን ስፖርት በዓል ግብዣ ሲመጣ ነገሩ ሌላ መልክ ይዞ ነበር፡፡ ጋባዡ ማን ነበር? ክልከላውስ ከየት መጣ? በብዕር ወደፊት እንራመድበታለን፡፡ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የርእሳነ መንግሥታት ታሪክ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ ጉዞዎች በዋናነት ከአሜሪካ መንግሥት፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ከሌሎች ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ ነበሩ፡፡ የዲያስፖራው ጉዳይ በጎንዮሽ የሚያዝ ነው፡፡ የዚህኛው ጉዞ ዋናው ልዩነቱ በዋናነት ኢትዮጵያውያንን ለማግኘት የተዘጋጀ መሆኑ ነው፡፡ ለአዲስ ሐሳብ አዲስ አካሄድ በሚል ጉዞውን የሚያስተባብረው ኮሚቴ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከባለ በጎ ፈቃድ ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡ የዳሰሳ ጥናት ተዘጋጀ፡፡ ዝርዝር ዕቅድ ወጣ፡፡ መጀመሪያ በዋሽንግተን ዲሲ በመቀጠል በሎስ አንጀለስ በመጨረሻም በሚነሶታ ኮሚቴዎች ተቋቋሙ፡፡ እንግዳው ነገር ተጀመረ፡፡ የኢሕአፓ፣ የመኢሶን፣ የቅንጅት፣ የኢሕአዴግ፣ የሰማያዊ፣
Posted in Ethiopian News, Religion

ሠለስቱ – 1 የለውጥ ሂደት ሦስት ጉልቻዎች

ከዚህ በፊትም አንሥተነዋል፡፡ አለቃ ገብረ ሐና እንዳስተማሩት ምርጥ ግንባታ ሦስት ነገሮችን ይፈልጋል፡፡ ሠሪ፣ ደንጓሪና አነዋሪ፡፡ የሀገር ግንባታም እንዲሁ፡፡ በሂደቱ ውስጥ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን ሠውተው ሌት ተቀን የሚሠሩለትን ይሻል፡፡ የእግር ኳስ ጨዋታ ሁለመናቸውን በሜዳ ላይ የሚያፈሱ ምርጥ ምርጥ ተጨዋቾችን እንደሚፈልገው ሁሉ፡፡ ሀገራዊ ለውጥ ስለፈለጉት፣ ስለናፈቁትና ስላጨበጨቡለት አይመጣም፣ ቢመጣም አይሳካም፡፡ የለውጡን ተውኔት በሚገባ የሚጫወቱ ምርጥ ተዋንያንንም ይፈልጋል፡፡ በየመዋቅሩ ገብተው፣ በየሥራ መስኩ ተሰልፈው፣ በየኃላፊነቱ ተሰይመው የሚዘውሩ ሠሪዎችን ይፈልጋል፡፡ እነዚህ ገንቢዎች እንዲሁ ሥራ ፍለጋ የሚከማቹ እንጀራ ፈላጊዎች አይደሉም፡፡ዕውቀትና እውነት የሚመራቸው ጠቢባን ናቸው እንጂ፡፡ ዕውቀትና እውነት የማይመራው የሀገር ግንባታና ሀገራዊ ለውጥ ብርሃንና መንገድ በሌለበት ገደላ ገደል እንደመጓዝ ያለ ነው፡፡ ዕውቀት ብርሃን፣ እውነትም መንገድ ነውና፡፡ ያለ ዕውቀትና እውነት የሚሠማሩ ሀገር ገንቢዎች ‹የሚከፈላቸው አጥፊዎች› ማለት ናቸው፡፡  ለውጥ ምርጥ ሠሪዎች ስላሉት ብቻም አይሳካም፡፡ ደንጓሪዎችንም ይፈልጋል፡፡ የደንጓሪ ሥራው ለግንባታ የሚሆነውን በቂና ተስማሚ ዕቃና መሣሪያ ማቅረብ ነው፡፡ ሀገራዊ ለውጥም ለለውጡ ዕውቀትና ክሂሎት የሚያቀርቡ ደንጓሪዎች ያስፈልጉታል፡፡ ዕውቀት የማይመራው ሀገራዊ ለውጥ፣ መሪጌታ እንደማይመራው
Posted in Ethiopian News, Religion

ጊዜ ጠባቂ ቦንብ

አንድን ሕዝብ ወይም ማኅበረሰብ በተመለከተ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደረጉ አሉታዊ የገጽታ ግንባታዎች ውጤታቸው ከሚታሰበውም የከፋ ነው፡፡ በዓለም ላይ አደጋ ላይ የወደቁ ማኅበረሰቦችን ታሪክ ስንመለከት ከሁለት ወገን የመጡ አካላት የቆሰቆሱት እሳት ያስከተለውን ረመጥ እናይባቸዋለን፡፡ አንደኛው እነርሱን ከሚወደው ወገን ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከሚጠላቸው ወገን ነው፡፡የተጠቂው ወገን ነኝ የሚለው አካል ያልተሰጠውን ውክልና እየወሰደ የሚፈጽማቸው ተግባራትና የሚያቀርባቸው ሐሳቦች በተቃራኒ ሆነው ነገሩን ለሚቆሰቁሱት ቢላዋ ያቀብላል፡፡ በጣት የሚቆጠሩ ልዩ ተጠቃሚዎች ሚሊዮኖችን ወክለው ለመታየት ይጥራሉ፡፡ እፍኝ የማይሞሉ አቀንቃኞች የማኅበረሰቡ አፈ ጉባኤ አድርገው ራሳቸውን እየሾሙ የሚናገሯቸው ንግግሮች የዚያ ማኅበረሰብ አቋም መስለው እንዲታዩ ይተጋሉ፡፡ በአንድ ማኅበረሰብ ስም ጥቅም የሚያገኙ አካላት በየዘመናቱ ይፈጠራሉ፡፡ በክርስትናና በእስልምና ስም በተፈጸሙ ወረራዎች፣ ዝርፊያዎች፣ ቅኝ ግዛቶች፣ ጦርነቶችና ጭቆናዎች ተጠቃሚዎቹ አማንያኑ አይደሉም፡፡ ተጠቃሚዎቹ በእምነቱና በአማንያኑ ስም የሚነግዱት አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት እምነቱንም ሆነ አማንያኑን የሚፈልጓቸው ለሁለት ነገር ነው፡፡ ለምክንያትነትና ለከለላነት፡፡ መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደሚባለው ግለሰባዊ ስግብግብነትና የሥልጣን ጥመኝነት ላስከተለው ክፉ ተግባር የተቀደሰው ሃይማኖት ምክንያት እንዲሆን
Posted in Ethiopian News, Religion

አንድ መዝገብ ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ

የደጃዝማች ገርማሜ የሕይወት ታሪክተጻፈ  ከቀኛዝማች ኃይሌ ዘለቃ1937 ዓ.ም1.     ባለ ታሪኩይህ ቀጥሎ የቀረበው በእጅ የተጻፈ ታሪካዊ መዝገብ የዐፄ ምኒልክን መንግሥት በሸዋዎች ብርታት(በአማራና በኦሮሞ መኳንንት) ስላቆሙት ስለ ደጃዝማች ገርማሜ ወልደ ሐዋርያት የተጻፈ ነው፡፡ በ1799 ዓ.ም. የተወለዱት ደጃዝማች ገርማሜ ከአቤቶ ኃይለ መለኮት እስከ ዳግማዊ ምኒልክ ድረስ የኢትዮጵያን መንግሥት ያገለገሉ ባለሟል ናቸው፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ሸዋ ዘምተው ምኒልክን ሲይዙ ግርማሜ በቤተ መንግሥት ነበሩ፡፡ በኋላም ዐፄ ምኒልክ ከቴዎድሮስ ጋር ወደ ጎንደር ሲሄዱ እርሳቸው ተጉለት ቀሩ፡፡ አስቀድመው ግን ምኒሊክን የሚያስመልጡበትን መንገድ ተናግረው ነበር፡፡ የሸዋ መኳንንት አልሰሟቸውም እንጂ፡፡ የተናገሩት ደርሶ ምኒልክ በቴዎድሮስ እጅ ገቡ፡፡ ገርማሜ የመከረው ምክር ጠብ አይልም የተባለው ከዚህ በኋላ ነው፡፡  ገርማሜ ሱባኤ ገብተው ሕልም ሲያዩ ተነሥተው ጎንደር ገቡና ከዐፄ ቴዎድሮስ ተገናኙ፡፡ እዚያም ከምኒልክ ጋር ተቀመጡ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በተወሰኑ ጊዜ ምኒልክ ያመለጡበትን ዘዴ የቀየሱት ገርማሜ ናቸው፡፡ በኋላም በወርቂት እጅ ሲገቡ አታለው ያወጡበትን ብልሃት ያመጡት እርሳቸው ናቸው፡፡ የዐፄ ምኒልክን አልጋ ሸዋ ላይ የተከሉት፤ መንግሥቱን ያደላደሉት፤
Posted in Ethiopian News, Religion

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወንበሮች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጠዋት ወደ ቢሯቸው ማልደው ሲገቡ የእንግዳ መቀበያ ክፍሉ ወንበሮች ተሰልፈው ጠበቋቸው፡፡ ነገሩ እንግዳ ሆነባቸው፡፡ የዚህን ቤተ መንግሥት ባሕል ገና አልለመዱትም፡፡ የተለመዱ ችግሮችን ባልተለመደ መንገድ እፈታለሁ ብለው ለተነሡት ጠቅላይ ሚኒስትር ነገሩ ከተለመደውም የወጣ መሰላቸው፡፡‹ምንድን ነው?› አሉ ሳቅ ይዟቸው፡፡‹አሰናብቱን› አለ ደንዳሳ ትከሻ ያለው የቆዳ ወንበር፡፡በታሪኩ ለመንግሥት ቅርብ የሆኑ እንግዶችን በማስተናገድ ይታወቃል፡፡ ‹ለምን? የት?› አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ‹በቃ እኛንም ጡረታ ያውጡና› አለ ሌላ እምቡር እምቡር የሚል ወንበር፤ የባለሥልጣን መቀመጫ መሆኑን የሥላሴን ዙፋን ከተሸከሙት ኪሩቤል በላይ ይኮራበታል፡፡ ‹እንትናኮ እኔ ላይ ነው የሚቀመጠው› እያለ መጎረር ይወዳል፡፡ ‹ምን ሆናችሁ› አሏቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ እጃቸውን አገጫቸው ላይ አድርገው፡፡‹እኛ ከመጀመሪያው ስንገዛ ለዚህ ዓይነት ነገር መሆኑን የነገረን የለም፡፡ አሁን እየተሠራ ያለው ከለመድነው ውጭ ነው፡፡ ከተገዛንበት ዓላማ ውጭ ነው፡፡ የመርሕ መደባለቅ እያየን ነው› አለ ባለ ደንዳሳ ትከሻው ወንበር፡፡‹ለምን ዓላማ ነበር የተገዛችሁት?› አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልሰሙት የቤተ መንግሥት ምሥጢር መኖሩን እየጠረጠሩ፡፡‹እኛኮ እዚህ ቦታ ብዙ ጊዜ ኖረናል› አለቺ አንዲት ቆንጠር ቆንጠር
Posted in Ethiopian News, Religion

<አገር አጥፋ> አረም

ብሽሽቅ ሃይማኖትም፣ ፖለቲካም፣ ወግም ሥርዓትም አይደለም፡፡ ብሽሽቅ ከከሠረ ኅሊና የሚበቅል ‹አገር አጥፋ› አረም ነው፡፡ ‹አገር አጥፋ› አረም የከብቶች ፀር የዕጽዋት ቀበኛ የሆነ ገበሬ አስቸግር አረም ነው፡፡ ‹አገር አጥፋ› አረም መስከረም መጥባቱን የሚያበሥረንን አደይ አበባ ሳይቀር ከሀገር የሚያጠፋ አረም ነው፡፡ አረሙን ከብቶቹ ስለሚያውቁት በአካባቢው ድርሽ አይሉም፡፡ ለስሙ የሚያፈካውን አበባ ንቦች ከቀሰሙት ማር ሳይሆን የሚገድል መርዝ ነው፡፡ ግዛቱን ሲያስፋፋ ከአውሮፓ ቅኝ ገዥዎችም ይብሳል፡፡ አገር ምድሩን ነው የሚወርረው፡፡ ዋናው ተግባሩ ሌላውን ሁሉ እያወደመ ራሱን ብቻ ማስፋፋት ነው፡፡ የግጦሽ መሬቱን ለመቆጣጠር ግልቢያው ከፍተኛ ነው። በተለይም በአውስትራሊያና በአፍሪካ ከፊል አካባቢዎች ተዛምቷል። በሕንድ «የኮንግረሱ ሳር» በሚል መጠሪያው ይታወቃል። በ28 ቀን እራሱን የሚተካ ሲሆን፤ ዓመቱን ሙሉ አብቦ ይቆያል። እስከ አንድ ሜትር የሚረዝም ሥር ስላለው ሀገሩን ሁሉ ይቆጣጠረዋል። ዘሩ እስከ ሃያ ዓመት መሬት ላይ መቆየት ይችላል። የዋግ ሕምራ ገበሬዎች ‹አገር አጥፋ› ብለው የሰየሙትን ይሄንን አረም ሳይንቲስቶቹ ‹Parthenium hysterophorus› ብለው ይጠሩታል፡፡ብሽሽቅም እንደዚሁ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በፖለቲካውና በሃይማኖቱ መስክ ሠፍኖ
Posted in Ethiopian News, Religion

ጥቁር ድንጋይ

የገንዘብን ጠባይ የእነርሱን ያህል የሚያውቀው የለም የሚባሉት ስዊዘርላንዳውያን እንዲህ ይተርካሉ፡፡አንዲት ውብ ልጅ የነበረቺው አንድ ነጋዴ ነበር፡፡ ከአንድ አራጣ አበዳሪ ከረጢት ሙሉ ብር ተበድሮ ማትረፍ አቅቶት ከሠረ፡፡ የመክፈያውም ጊዜ ደረሰ፡፡ የብድር ውሉ ነጋዴው በጊዜው ብድሩን ካልከፈለ ወደ እድሜ ልክ ወኅኒ እንደሚወረወር ይገልጣል፡፡ ይህ ቀን መድረሱ ለነጋዴውና ለልጁ አስደንጋጭ ሆነባቸው፡፡ የአራጣ አበዳሪው የ80 ዓመት ሽማግሌ፣ ጠባየ ክፉና መልከ ድፉ ነው፡፡ በዚያ አካባቢም እርሱን የሚወደው አንድም ሰው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ነጋዴዎች ገንዘብ ሲፈልጉ ከእርሱ ውጭ የሚያበድራቸው አልነበረም፡፡ ይህ አራጣ አበዳሪ ነጋዴው ከወኅኒ የሚተርፍበትን አንድ ሸውክ አቀረበ፡፡ ‹የነጋዴው ልጅ እኔን ለማግባት ፈቃደኛ ከሆነች ነጋዴው ከወኅኒ ይተርፋል፤ ያለበለዚያ ግን እድሜ ልኩን ይማቅቃል› አለ፡፡ነጋዴውም ልጁም ደነገጡ፡፡ ሁለቱም ለምርጫ አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ በአንዱ አንደኛው በሌላውም ሌላኛው ይሠዋሉ፡፡ የአንዱ መሠዋት ደግሞ ሁሉንም ይሠዋል፡፡ ምን ይደረግ? በሁለት ሞት መካከል የሚደረግ ምርጫ፡፡ መጨነቃቸውን ያየው አራጣ አበዳሪ ሁለተኛ አማራጭ አቀረበ፡፡ ‹እዚህ ማሠሮ ውስጥ ሁለት የባሕር ድንጋዮች እከታለሁ፡፡ ነጭና ጥቁር፡፡ ልጅህም እዚያ ባሕሩ
Posted in Ethiopian News, Religion

ሰው ተዋርዶ ሰይጣን ክብር ያገኘበት ዘመን

የቤተ ክርስቲያናችን የገድላትና የተአምራት መጻሕፍት ሲጻፉ፣ የሰዎቹን ክብር በሚጠብቅ መንገድ ካልሆነ በቀር ችግር ደርሶባቸው ተአምር የተደረገላቸውን ሰዎች የተጸውዖ ስም አይገለጡም፣ ወይም የክርስትና ስማቸው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሰዎቹን በስማቸው መጥራት ቢያስፈልግ እንኳን ለዝርዝር ማንነታቸው በማይመች ስም ይገለጣሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረግበት ዋናው ምክንያት የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር(Human dignity) ለመጠበቅ ነው፡፡ እነርሱ ቢያልፉም እንኳን ልጅና ልጅ ልጅ ይኖራልና፡፡እኅታችን ጌጤ ዋሚ ‹ሩጫን በሚከለክሉ በአጋንንት› ተያዘች ተብሎ የተለቀቀባትን ቪዲዮ ስመለከት በእምነት ስም የሚነግዱ ሰዎች የደረሱበትን ሞራላዊ ኪሣራ አየሁት፡፡ ከመጀመሪያው ሰይጣንን እየቀዱ ለገበያ ማዋል በየትኛውም የቅዱሳን ሕይወት ውስጥ የማናየው ነው፡፡ መቼም ሰይጣን እንደዚህ ዘመን በክብር መድረክ ያገኘበት ጊዜ የለም፡፡ ከዚህም አልፎ ልጅ፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ዓለም አቀፋዊ ተክለ ሰብእና ያላትን አትሌት በዚያ ዓይነት ክብርን በሚነካ ሁኔታ እያሰቃዩ በቪዲዮ ማሳየት ፈጽሞ የእግዚአብሔርን ክብር መግለጥ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰውነትን ማዋረድ እግዚአብሔርን ማዋረድ ነውና፡፡ አስፈላጊ ነው ካለች እርሷ ራሷ ትንገረን እንጂ ይህንን የመሰለ ቪዲዮ እንኳን ሌላው እርሷም ልታሳየን የተገባ አይደለም፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የትውልድ አደራ

ልዑል ራስ መንገሻየኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ2010 ዓምእኔ ከአዲስ አበባ ወደ ስዊዘርላንድ፣ ልዑል ራስ መንገሻ ከቀበና ወደ ዘጠነኛ ዓመት የእድሜ ባለጸጋነት አብረን እየተጓዝን ነው፡፡ ‹የትውልድ አደራ› የሚለውን መጽሐፋቸውን ማንበብ ከአንድ የታሪክ መዝገብ ከያዘ አረጋዊ ጋር ተቀምጦ እንደ ማውጋት ያለ ነው፡፡ ትገረማላችሁ፣ ትመሰጣላችሁ፣ ታለቅሳላችሁ፣ ትስቃላችሁ፣ ከዚያም አልፋችሁ ግን ለምን? ትላላችሁ፡፡ልጅ ሆነው ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ በሰው ትከሻ እንዴት እንደተጓዙ ሲተርኩላችሁ የዛሬ መቶ ዓመት አካባቢ በእግር ይደረግ የነበረውን ጉዞ እየቃኛችሁ አብራችሁ ታለከልካላችሁ፡፡ በትግራይ የነበረውን የመሳፍንት ልጆች አስተዳደግ ሲተርኩት በልጅ ልባቸው ውስጥ ትገረማላችሁ፡፡ አውሮፕላንና መኪና ሲታይ የነበረውን ግርምታ ሲነግሯችሁ በሳቅ ትፈርሳላችሁ፡፡ በሰባት ዓመታችው ራስ  ሥዩም መንገሻ ለራስ መንገሻ ሥዩም ደጃዝማችነት ለማሰጠት ዐፄ ኃይለ ሥላሴን ጠየቁ፡፡ መልሱ የመጣው በስልክ ነበር፡፡ ራስ መንገሻ ሥዩም በስልክ ተጠርተው ሲቀርቡ ለዐፄ ኃይለ ሥላሴ እጅ እየነሡ ነበር ወደ ስልኩ የሚሄዱት፡፡ ንጉሡ በሌሉበት በስልክ እጅ ሲነሣ ማየት ለሕጻኑ መንገሻ አስገራሚ ነገር ነበር፡፡ ‹ልዑል ጌታዬ› ይሏቸዋል አባታቸውን፡፡ የ1928ቱን የጣልያን ወረራን ለመመከት በሰሜን በኩል
Posted in Ethiopian News, Religion

የቤተ ክርስቲያን ዕርቀ ሰላም ጉዳይ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውንና ከ25 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን መለያየት ለመፍታት በድጋሚ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በሀገር ቤትና በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሽማግሌዎች የተጀመረው ጥረት የሁለቱን ወገን አባቶች ይሁንታ አግኝቷል፡፡ ይህ ጥረት ከግብ ደርሶ የመለያየቱ ግንብ እንዲፈርስና አንድነቱ እንዲመጣ የሚመኘውና የሚጸልየው ብዙ ነው፡፡ ችግሩን ለመፍታት የተነሡት ሽማግሌዎች ያጓኟቸውን አራት ዕድሎች በመጠቀም ካለፈው በበለጠ ሊሠሩ ይገባል፡፡ እነዚህ ዕድሎችም፡-       1.      ሁለቱም ወገኖች ሽምግልናውን ለመቀበልና በውይይቱ ለመቀጠል መስማማታቸው      2.     በሀገርና በውጭ ሀገር የሚገኙ የምእመናንና የካህናት ማኅበራት ለዕርቅና አንድነቱ ጠንካራ ድጋፍ መስጠታቸው      3.     ሀገሪቱ ያጋጠሟትን የልዩነት ፈተናዎች በመግባባትና በአንድነት ለመፍታት መነሣሣት የጀመረችበት ወቅት መሆኑ      4.     የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና መንግሥታቸው ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ መደገፋቸው፣ ናቸው፡፡እነዚህን ዕድሎች በመጠቀም ሁለቱም ወገኖች የዕርቅና የአንድነት ሂደቱን ለመጀመር ብቻ ሳይሆን ለመቀጠልና ከፍጻሜውም ለማድረስ መትጋት አለባቸው፡፡ ጊዜው እየሄደ ነው፡፡ ችግሩ ሲከሠት የነበሩት አበው በሁለቱም ወገኖች ዐረፍተ ሞት እየገታቸው ነው፡፡ ሽማግሌዎቹ ጳጳሳትን ካጣን በታሪኩ ላይ የምናደርገው ንትርክ ራሱ ከዕርቁ ሂደት በላይ ይፈጃል፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ዳግማዊውን አለቃ ተክሌ መልሱልን

‹አራቱ ኃያላን› የተባለውን መጽሐፍ በ2006 ዓ.ም. ጎንደር ላይ ስንመርቅ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ መሪጌታ እንደ ሥራቸው ስለሚባሉ የተክሌ አቋቋም ሊቅ አንሥተው ‹የተክሌ አቋቋም ከጊዜ በኋላ ቢጠፋ ወይም እኔ አንድ ነገር ብሆን ብለው 9 ካሴት የሚሆን ዜማ በካሴት ቀርጸው አስቀምጠዋል› ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም ‹እንደሥራቸው መቋሚያ ይዞ ሲዘም እንኳን ሰዎች ንቦች ይመሰጣሉ› ሲሉ ስለ እርሳቸው መሰከሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ‹እንደሥራቸው› ማን ናቸው? የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ ይመላለስ ጀመር፡፡ በተለያየ አጋጣሚ የደብረ ታቦርና የተክሌ አቋቋም ሊቃውንትን ባገኘሁ ቁጥር እኒህን ሊቅ በተመለከተ እጠይቃቸው ነበር፡፡ ሁሉም የሚመሰክሩልኝ ‹ከአለቃ ተክሌ በኋላ የመምህር እንደሥራቸውን ያህል አቋቋምን የሚያውቀው የለም› በማለት ነው፡፡ ዛሬ በቦታው የሚገኙት የደብረ ታቦር ኢየሱስ አለቃ መልአከ ታቦር ኃይለ ኢየሱስ ፋንታሁንና የተክሌ ምስክሩ የኔታ መርሻ መምህር እንደሥራቸውን ሲያነሡ ዕንባ ይቀድማቸዋል፡፡ በምስክር ትምህርት ቤቱ ዛሬም ‹የእንደ ሥራቸው ዜማ› እየተባለ የእርሳቸው ስልት ይሰጣል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የድጓና የአቋቋም ሊቃውንት አስተያየት ሊቁ እንደሥራቸው በዜማ ዕውቀታቸውና ስልታቸው ከተድባበ ማርያሞቹ አዛዥ
Posted in Ethiopian News, Religion

ኃይሌ ፊዳ እና የግሌ ትዝታ

በአማረ ተግባሩ (ዶ/ር)2010 ዓ.ም.ዋጋ 111.50በኢትዮጵያ የአብዮት ታሪክ ውስጥ ስንት ሊቃውንት፣ ስንት ቅኖች፣ ስንት የዋሐንና ስንት ባለ ራእዮች ልዩነትን በመገዳደል ለመፍታት በተወሰደው ርምጃ ወድቀው እንደቀሩ ከሚያስረዱን መጻሕፍት አንዱ ይህ መጽሐፍ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ስሙን በክፉም በደግም ስለምንሰማው ሰው ስለ ኃይሌ ፊዳ የአብሮ ኗሪ ምስክርነት ነው፡፡ ጸሐፊው አብሮት ሠርቷል፣ አብሮት ኖሯል፣ አብሮትም ታሥሯል፡፡ እስከዛሬ ይህ ሁሉ መዓት ሲወርድበት ለምን ዝም እንዳለም አስገራሚ ነው፡፡ ምናልባት የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላን መጽሐፍ እየጠበቀ ይሆናል፡፡ የዚያ ዘመን ኃያላን እንዴት ዓይነት ሐሳብ፣ መንገደና ተዋሥኦ እንደነበራቸው በኃይሌ ፊዳ ሕይወት ውስጥ እናየዋለን፡፡ እንኳንም አንዳንዶች ተረፉ፡፡ በርግጥ በሕይወት መትረፋቸውን ያልተረፉትን ለማጠልሸት የተጠቀሙበት አሉ፡፡ ተነሥተው እንደማይሞግቷቸው ስለሚያውቁ ከደርግ በላይ በሟቾች ላይ በታሪክ አጻጻፋቸው የጨከኑባቸውም አሉ፡፡ የደርግ ዓላማ ቀርቶ የመኢሶን፣ የኢሕአፓ፣ የኢዲዩ፣ የኢጭአት ዓላማዎች ቢሳኩ ኖሮ ኢትዮጵያ ዛሬ ምን ትመስል ይሆን? እንድንል ያደርጉናል እንዲህ ዓይነት መጻሕፍት ስናይ፡፡ ደራሲው ጨዋነትን፣ ወንድምነትን፣ ጓድነትንና ሚዛናዊነትን ለማደላደል የሄደበትን ጥረት አደንቃለሁ፡፡ ሰሚ ሲኖር፤የ66ቱ ትውልድ የጻፏቸውን፣ የተጻጻፏቸውንና ያሳተሟቸውን ድርሳናት በአንድ
Posted in Ethiopian News, Religion

ስድስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር የእጩዎች ጥቆማ ተጀመረ

ለሀገርና ለሕዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት ስድስተኛው መርሐ ግብሩን ከግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም አንሥቶ የእጩዎች ጥቆማ በመቀበል በይፋ ይጀምራል፡፡ ስድስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት የሚካሄድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡  ለዚህ የሽልማት መርሐ ግብር በአሥር ዘርፎች ማለትም     1.  በመምህርነት ዘርፍ     2.  ንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ     3.  ማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ     4.  ሳይንስ ዘርፍ     5.   ቅርስና ባሕል ዘርፍ  6.   መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ      7.   ኪነ ጥበብ (በሙዚቃ ዜማ ድርሰት ዘርፍ)       8.   ሚዲያና ጋዜጠኛነት ዘርፍ     9.   ለኢትዮጵያ በጎ ሥራ የሠሩ የውጭ አገር ዜጎች ዘርፍ    10.  በጎ አድራጎት ዘርፍከሕዝብ የእጩዎችን ጥቆማ ለመቀበል ተዘጋጅተናል፡፡በበጎ ሰው ሽልማት ከ2005 ዓ.ም አንሥቶ በተካሄዱት አምስት የሽልማት ወቅቶች፤ አገራችን የምትኮራባቸውና የላቀ አርአያነት ያለው ተግባር ያከናወኑ ሰዎች ዕውቅና የተሰጣቸው ከሕዝብ በቀረቡ ጥቆማዎችና በዳኞች ውሳኔ መሠረት ነው፡፡ የበጎ ሰው ሽልማትን ለዚህ ያበቃውም በሽልማቱ ሂደት የሕዝብ ተሳትፎ
Posted in Ethiopian News, Religion

ዳጋ እስጢፋኖስ – የመነነው ገዳም (ክፍል ሁለትና የመጨረሻው)

ዳጋ፣- የጣና ሞገስዳጋ እስጢፋኖስ የኢትዮጵያ ታሪክ ማዕከል ነው፡፡ ከመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ አንሥቶ ነገሥታቱ፣ መኳንንቱ፣ ጳጳሳቱና ምእመናኑ የሀገሪቱ ታሪክ ባለ አደራ አድርገውታል፡፡ የመስቀሉን ክፋይ ጨምሮ አያሌ ንዋየተ ቅድሳትን፣ የነገሥታት የወግ ዕቃዎችን፣ ካባዎችንና አክሊሎችን ዳጋ በክብር ጠብቆልናል፡፡ በሀገሪቱ የደረሱ የእርስ በርስ ጦርነቶችና ወረራዎች ወደ ገዳሙ ባለመዝለቃቸው ከ800 ዓመታት በላይ የተጠበቁ ቅርሶችን ዳጋ አቅፎ ይዟል፡፡ ከተገነባ ከ300 ዓመት በላይ የሆነው ሙዝየሙ በእነዚህ ቅርሶች ተጣብቧል፡፡ መጽሐፍ በመጽሐፍ ላይ፣ ዕቃ በዕቃ ላይ ተነባብሯል፡፡ ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ቅርስና ባህል ወዳጆችና አክባሪዎች እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ አንድ ሆነን ልንነሣ የሚገባበት ደረጃ ላይ ነው፡፡ ዕቃ ቤቱ ዘመኑን ጨርሶ በአንድ በኩል ተሰንጥቋል በሌላ በኩል እየተናደ ነው፡፡ በዚህ የተቀደሰ ተራራ ላይ ገዳሙን፣ መንፈሳዊነቱን፣ ታሪኩንና ቅርሱን የሚመጥን ሙዝየም መሥራት አለብን፡፡ ያ ካልሆነ ታሪካችንን ተረት ከመሆን አንታደገውም፡፡የዳጋ ጥንታውያን ቅርሶችዳጋ፣ ዝምተኛ ገዳም ነው፡፡ እንደ ሌሎቹ ገዳማት ምእመናን ሆ እያሉ ለንግሥ እንዲመጡለት የሚቀሰቅስ ገዳም አይደለም፡፡ ጸጥታውንና ርጋታውን ይፈልገዋል፡፡ ከካህናቱ ጸሎት፣ ከአዕዋፉ ዝማሬ፣ ከጣና
Posted in Ethiopian News, Religion

ዳጋ እስጢፋኖስ – የመነነው ገዳም

በ13ኛው መክዘ መግቢያ(እንደ ገዳሙ ታሪክ በ1268 ዓ.ም) የሐይቅ እስጢፋኖስ የአቡነ ኢየሱስ ሞአ ደቀ መዝሙርና የዐፄ ይኩኖ አምላክ(1263-1277 ዓ.ም.) ወንድም በነበሩት በአቡነ ኂሩተ አምላክ የተመሠረተው ዳጋ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም እስካሁን ድረስ በታሪክ ጥንታዊ፣ በእምነት ኦርቶዶክሳዊ፣ በአነዋወር ገዳማዊ፣ በሕይወት ተባሕቷዊ ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ ገዳሙን በሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስም የቆረቆሩት የሐይቅ እስጢፋኖስን ለማሰብ ይመስላል፡፡ ጥንታውያን የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ከሚታወቁበት መለያ አንዱ ብዙ ጊዜ የሚጠሩት በሰማዕታት (ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ ቅዱስ ቂርቆስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ በአርባዕቱ እንስሳ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ዳጋ ሲመጡ በእመቤታችን ስም የተሠራች ቤተ ክርስቲያን ማግኘታቸውን የገዳሙ ታሪክ ይናገራል፡፡ አካባቢው ከአኩስም ዘመን ጀምሮ ክርስትና የተስፋፋበት በመሆኑ ይህ የሚደንቅ አይደለም፡፡ የእመቤታችንን ታቦት ወደ ደቅ ደሴት በመውሰድ የቅዱስ እስጢፋኖስ ታቦት የገባው በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን መሆኑ ይነገራል፡፡ ገዳሙ ከጣና ሐይቅ በስተ ምሥራቅ በጣና ማዕከላዊ ሥፍራ ላይ ከደቅ ደሴት አጠገብ ይገኛል፡፡ የደሴቱ ስፋት ሦስት ኪሎ ሜትር ያህላል፡፡ ቤተ
Posted in Ethiopian News, Religion

ውስጠ ወይራ

ነፍስ ሔር አቡነ ጴጥሮስ እንዲህ ነግረውኝ ነበርሰውዬው ቅኔ ሊቀኝ ቅኔ ቤት ይሄዳል፡፡ የገጠሙት መምህር ቀናነት አልነበራቸውምና ተቀኝቶ እንዲወጣ አልፈለጉም፡፡ ‹ሶበ› ብሎ ተቀኝቶ ሲመጣ፣ ‹እስመ› ብለው ያርሙታል፡፡ ‹እስመ› ብሎ ሲቀኝ ‹አምጣነ› ብለው ያስተካክሉታል፤‹አምጣነ› ብሎ ሲመጣ ‹አኮኑ› ይሉታል፡፡ ተሰቃየ፡፡ በዚህ ቢላቸው በዚያ የሚፈልገውን ዕውቀት አግኝቶ የሚፈልግበት ደረጃ እንደማይደርስ ገባው፡፡ በብዙ መንገዶች ለማባበልም፣ ለመለማመጥም፣ ጽሙድ እንደ በሬ ቅኑት እንደ ገበሬ ሆኖ ሊያገለግላቸውም ሞከረ፡፡ አልሆነም፡፡ በመጨረሻ መረረው፡፡አንድ ቀን አራቱንም አስገብቶ አንድ ቅኔ አዘጋጀና ወደ መምህሩ ዘንድ ሄደ፡፡ ሲሄድም ባዶ አጁን አልነበረም፡፡ በጋቢው ውስጥ የወይራ ፍልጥ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ከተቀበሉት ይቀበላሉ፤ ካልተቀበሉትም ወይራው ሥራውን ይሠራል፡፡መምህሩ ዘንድ ሲቀርብ በጋቢው ውስጥ የተሸፈነውን የወይራ ፍልጥ አዩት፡፡ እርሱም ድምጹ ከፍ አድርጎ ‹ሶበ፣ አኮኑ፣ እስመ፣አምጣነ፣› ብሎ ቅኔውን ተቀኘ፡፡ከዚያም መምህሩን ‹እንዴት ነው?› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ መምህሩም ‹ምንም አይል ውስጠ ወይራ ነው› አሉት አሉ፡፡ሕዝብም እንደዚህ ነው፡፡ በዚህም በዚያም ሲል መንገዱን ሁሉ ከዘጋህበት የመረረው ቀን ‹ሶበ፣ አኮኑ፣ እስመ፣አምጣነ፣› ብሎ ሁሉንም አከታትሎ ያመጣዋል፡፡ በዚያ ጊዜ መርጠህ
Posted in Ethiopian News, Religion

የሙሴ + አሮንና ሖር = ድል

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ የመሪና የተባባሪ ድርሻን ከሚገልጡ ታሪኮች አንዱ የሙሴና፣ የአሮንና የሖር ታሪክ ነው(ዘጸ. 17÷8-16)፡፡  አማሌቃውያን ከእስራኤል ጋር ሲዋጉ ኢያሱ ጎልማሶቹን ይዞ ከአማሌቃውያን ጋር ይዋጋ ነበር፡፡ ሙሴ ደግሞ ወደ ኮረብታው ወጣ፡፡ ሙዜ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርጋሉ፡፡ ሙሴ ደክሞት እጁን ባወረደ ጊዜ ደግሞ አማሌቅ ድል ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሙሴ ቀኑን ሙሉ ዋለ፡፡ በመጨረሻ ግን የሙሴ እጆች ከበዱ(ደከሙ)፡፡ ይህን የተመለከቱት አሮንና ሖር ለሙሴ የድንጋይ ወንበር አዘጋጁለት፤ ሙሴም እዚያ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ እጁን ዘረጋ፡፡ ድሉም ለእስራኤል ሆነ፡፡ ነገር ግን አሁንም ሙሴ እጆቹ እየደከሙ መጡ፡፡ አሮንና ሖርም በግራና በቀኝ ሆነው የሙሴን እጆች ከፍ አድርገው ደገፏቸው፡፡ ያን ጊዜ ሙሴ እጆቹን አነሣ፡፡ እስራኤልም አማሌቅን ፈጽመው ድል አደረጉ፡፡ አንድ መሪ ውጤታማ የሚሆው ብቻውን አይደለም፡፡ እንኳንና በሰዎች የተመረጠ መሪ እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ እንኳን ብቻውን ውጤታማ መሆን አልቻለም፡፡ መሪ ምን ጠቢብ፣ ጎበዝ፣ ውጤታማ፣ ተወዳጅና ዐቅም ያለው ቢሆንም እንኳን እንደ ሙሴ እጆች መዛሉ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህም እንደ አሮንና እንደ
Posted in Ethiopian News, Religion

ተምሬ ተምሬ¡

አብሮ አደግ ጓደኛዬን ባለፈው አሜሪካ አገኘሁት፡፡ ጽኑ ሰው ብርቱ ኃይል፡፡ በትምህርት ድህነት ይፈረከሳል ከተባለ ቁጥር አንድ መዶሻው እርሱ ነው፡፡ የእናት የአባቱ ቤት ከትምህርት ቤታችን ስድስት ሰዓት ይርቃል፡፡ ይህን ሁሉ እየተጓዘ መማር ስለማይችል ከትምህርት ቤቱ የአንድ ሰዓት ርቀት ላይ ቤት ተከራይቶ ነበር የሚማረው፡፡ ቤተሰቦቹ ወዳሉበት ገጠር ቅዳሜ ጠዋት ይሄድና እሑድ ከሰዓት ስንቁን ቋጥሮ ይመለሳል፡፡ ያችን ስንቅ ቆጥቦ ከሰኞ እስከ ዓርብ ይመገባል፡፡ ነገን ዛሬ ላይ ለመትከል እንደሚቻል አምኖ የሚያገኘውን ዕድል ሁሉ ይጠቀማል፡፡ እርሱን ፈተና አያሸንፈውም፤ እርሱ ራሱ የኑሮ ፈተናዋ ነው፡፡ እርሱ ፈተና የሚገጥመው ወላጅ አምጡ የተባለ ዕለት ነው፡፡ ስድስት ሰዓት ተጉዞ የሚመጣ ወላጅ አያገኝም፡፡ ጉዳዩን ራሱ ለወላጆቹ ማስረዳት ከባድ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የርሱ ወላጆች ይቀያየራሉ፡፡ አንድ ቀን ያንዱን፣ ሌላ ቀን ደግሞ የሌላውን ወላጅ ይወስዳል፡፡ጽሑፉ እንደ ጤፍ የደቀቀ፣ ነገር ግን እንደ ቆሎ የደመቀ ነው፡፡ ለምንድን ነው? ስንለው ‹ደብተር ቶሎ እንዳያልቅብኝ ነው› ይላል፡፡ የተሰጠውን የቤት ሥራ እዚያው ትምህርት ቤት ውስጥ በጊዜ ይሠራል፤ የታዘዘውን ያለ
Posted in Ethiopian News, Religion

ከመጽሐፈ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ ጋር የተገኘው ለዐፄ ዘርአ ያዕቆብ የቀረበው ሙገሳ:- ስለ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ መጽሐፍ የግእዝ ትርጉም ምን ይነግረናል?

ይህ ከዚህ ቀጥሎ የተጻፈው ሙገሳ በፈረንይ ቤተ መጻሕፍት በቁጥር BNF ethiopien 68 ተመዝግቦ በተቀመጠው መጽሐፈ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ መጽሐፉ ክፍለ ክርስቶስ በተባለ ሰው አስጻፊነት፣ ዘወልደ ማርያም በተባለ ጸሐፊ፣ በብርሃን ሰገድ ዐፄ ኢያሱ ጊዜ(1723-1747 ዓ.ም.) የተገለበጠ ነው(fol. 107b)፡፡ በመጽሐፉ መጨረሻ የሚገኙት የኅዳግ ማስተዋሻዎች በንጉሥ ኢያሱና በንጉሥ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ዘመን የተመዘገቡ የመጻሕፍት ዝርዝሮችን ይዘዋል፡፡ ‹ኆልቆ መጻሕፍት ዘፃና› ይላል(107b,108a)፡፡ ፃና የተባለችው ገዳም ማን እንደሆነች የጠየቅን እንደሆነ በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ ‹ተወጥነት መሠረተ ሕንጻሃ ለመቅደሰ ቂርቆስ ዘፃና[1]› የሚል ንባብ አለ(108b)፡፡ ይህም መጽሐፉ የጣና ቂርቆስ ንብረት እንደነበረ ያስረዳናል፡፡ በነዚያ የመጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ በሁለቱም የቆጠራ ዘመናት 2 መጽሐፈ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ እንደነበረ ይገልጣል፡፡ እንግዲህ በኋላ ዘመን አንዱ ወቶ ፈረንሳይ ተሻግሯል ማለት ነው፡፡ በመቅድሙ ላይ ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብን(fol.1a) በጸሎቱ ላይ ደግሞ አድያም ሰገድ ኢያሱን ያነሣል፡፡ ጊዮርጊስ ወልደ ዓሚድ(1199-1267ዓ.ም.) ክርስቲያን ዓረብ የታሪክ ጸሐፊ ነው፡፡ በግብጽና በሶርያ በቤተ መንግሥት ታላቅ ቦታ ነበረው፡፡ ከ1255-1261 ዓ.ም. ባለው ዘመን ውስጥ ከአዳም
Posted in Ethiopian News, Religion

የዐቢይ ንግግር ሰባት አዕማድ

የሀገሬ ሰው ‹ካልተናገረ አይታይ ብልሃቱ፣ ካልታረደ ዓይታይ ስባቱ› ይላል፡፡ ንግግር የሰው ልጅ ከተሰጡት የላቁ ጸጋዎች አንዱ ነው፡፡ ንግግር ሰዎችን ሊያግባባቸው፣ ወደ አንድነትና ኅብረት ሊያመጣቸው፣ ሊያከራክራቸውና ሊያወያያቸው ኃይል አለው፡፡ ከመሪዎች ከሚጠበቁ ነገሮች አንዱ ኃይል ያለው ንግግር ነው፡፡ ኃይል ያለው ንግግር በሚመርጣቸው ቃላት፣ በሚጠቀምበት ድምፀት፣ በሚያቀርባቸው አገላለጦች፣ በሚሰጣቸው ምሳሌዎች፣ በሚቀርብበት ተፋሰስ፣ በሚዋቀርበት አሰካክና በምጣኔው ይታወቃል፡፡ ሊደመጥ፣ ሊነበብ የሚችል፣ በሐሳቡ ባንስማማም በአቀራረቡ የሚማርከን፣ በዝርዝሩ ባንግባባም ሐሳቡ ግን የሚገባን፤ ባንወደውም የምናደንቀው ንግግር ከመሪዎች ይጠበቃል፡፡ ዐፄ ምኒልክ ለዐድዋ ጦርነት ሕዝቡን ለመጥራት ያወጁት ዐዋጅ ከዐዋጅነቱ ይልቅ የመሪ ጥሪ የሆነ ቃል አለው፡፡ በውስጡ ንጉሡንና ሕዝቡን የሚያቀራርብ፣ የሀገሪቱን ችግር የሚገልጥ፣ ከሕዝቡ የሚፈልጉትን የሚያሳይ፣ ሀገር ስትጠራው እምቢ ብሎ የቀረ የሚገጥመውን ዕጣ ፈንታ የሚያመላክት ቃል ነው፡፡ መላዋን ኢትዮጵያ ለአንድ ዓላማ ያሰለፈና ውጤቱን በዐድዋ ተራሮች ላይ ያሳየ ቃል ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ሀገር ምጥ ላይ በምትሆንበት ጊዜ የመሪዎች ንግግር ወይ ፈዋሽ ወይ አባባሽ ይሆናል፡፡ ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል እንዲሉ፡፡ አነጋገሩ የሚያግባባ፣ የሚጠራና
Posted in Ethiopian News, Religion

ኀሠሣ መጻሕፍት

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ አባቶቻችን ለመጻሕፍት የነበራቸው ፍቅር ነው፡፡ የሌሉትን ካሉበት አስመጥተው አስተርጉመው፤ ለደራስያኑ ቀለብና ቤት ሰጥተው፣ ሲጨርሱም ሹመውና ሸልመው እንዴት ያስጽፉ እንደነበር የተረፉት መዛግብት የሚነግሩን አስደናቂ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ ዛሬም በየአድባራቱና ገዳማቱ ከ240ሺ በላይ መጻሕፍት መኖራቸው ይገልጣል፡፡ በመላው ዓለም ተበትነው ከ30 ሺ በላይ መጻሕፍት እንዳሉ ይነገራል፡፡ አንዳንዶቹ መጻሕፍት ስማቸውን እንጂ ራሳቸውን መጻሕፍቱን አላገኘናቸውም፡፡ መጽሐፈ ከሊላ ወዲምናህ፣ መጽሐፈ ዮሴፍ ወእስኔት እስካሁን አልተገኙም፡፡ ከሊላ ወዲምናህ ከ16ኛው መክዘ በፊት እንደነበረ አባ ባሕርይ በመዝሙረ ክርስቶስ ያነሣዋል፡፡ የሐይቅ እስጢፋኖሱ የመጻሕፍት ዝርዝር ከሊላ ወድምናሕን ይጠቅሳል፡፡ መጽሐፉ ግን ዛሬ በሐይቅ የለም፡፡ አባ ጊዮርጊስም በልዩ ልዩ ድርሰቶቹ መጽሐፈ ዮሴፍ ወእስኔትን ያነሳዋል፡፡ ጥንት ምን ዓይነት መጻሕፍት እንደነበሩን መዝግበው ካስቀመጡልን መዛግብት መካከል ዛሬ በብሪትሽ ሙዝየም የሚገኘው የሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የብራና መጽሐፍ አንዱ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንዋ በመካከለኛው ዘመን ታዋቂ ነበረች፡፡ ነገሥታቱም እየተገኙ ያከብሯታል፤ ርስትና ስጦታም
Posted in Ethiopian News, Religion

የጣና ቂርቆስ መጻሕፍት በሦስት ዘመናት

በፒዲኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑጥንታውያን ጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ ካህናትና ምእመናን፤ ነገሥታት መኳንንት፣ ወይዛዝርት ባላባቶች መጻሕፍትን እያስጻፉ ለየገዳማቱና አድባራቱ ይሰጡ ነበር፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በእሳት፣ በጦርነት፣ በዝርፊያና በስጦታ ያለቁት አልቀው የቀሩት ቀርተዋል፡፡ አንዳንድ ገዳማት የነበሯቸው መጻሕፍት ዝርዝር በብራና መጻሕፍት ላይ ይመዘግባሉ፡፡ እነዚህን መዛግብት ዛሬ ስናነባቸው ስንት መጻሕፍት እንደጠፉ ይነግሩናል፡፡ በሌላው ሀገር የተወሰዱትስ ምንም በስደት ቢኖሩ ሕልውናቸው አልጠፋም፡፡ ሕልውናቸው የጠፉት መጻሕፍት ናቸው የሚያስቆጩት፡፡ ከትናንት ብንዘገይ ከነገ እንድንቀድም የቀደሙትን የሥነ ጽሑፍ ሀብቶቻችንን መቃኘት፣ ማጥናትና መጠበቅ አለብን፡፡ ሀገር የምትቆመው በዕውቀትና በእውነት ነውና፡፡ ዕውቀትን ያለ እውነት፣ እውነትንም ያለ ዕውቀት ማሰብ አይቻልም፡፡  ቀጥሎ የቀረበው ዝርዝር ዛሬ በፈረንሳይ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ በቁጥር 68 ተመዝግቦ ከተቀመጠውና ይሄ ዝርዝር ከተጻፈበት ከመጽሐፈ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ የተገኘ ነው(fol.107b)፡፡ በመጀመሪያው ሰንጠረዥ(1) የተቀመጠው በብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጊዜ ከ1723-1747 ዓ.ም. ባለው ዘመን መካከል መምህር ወልደ ኢየሱስ የገዳሙ መምህር እያሉ በተደረገው ቆጠራ የተመዘገበው ነው፡፡ በሁለተኛው ሠንጠረዥ (2) ያለው ደግሞ በዐፄ ኢዮአስ ዘመነ መንግሥት 1747-1761 ዓ.ም. ባለው ዘመን መምህር
Posted in Ethiopian News, Religion

‹የግእዝ ሥነ ጽሑፍ በየዓይነቱ›

ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስተዋሻዎች  ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እነዚህን ማስተዋሻዎች የሰበሰብኩት በዋሽንግተን ዲሲ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ ለማቅረብ ነበር ይላሉ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ዘመናት በየአድባራቱና በየአዳራሹ ብንጋብዛቸው ኖሮ ስንት መጽሐፍ እናተርፍ ነበር? በሀገራችን አንድ ሊቅ ሲሞት ብቻውን አይሄድምአራት ሰው ሞተ ተቀበረ ዛሬድጓ ጾመ ድጓ መዋሥዕት ዝማሬ ተብሎ ለአንድ ሊቅ የተገጠመው ይሄንን ይነግረናል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ያሉ በሁለት እጅ የማይነሡ ሊቃውንት እንደ ጥገት ላም ሊታለቡ፣ እንደ ወይን ዛላ ሊለቀሙ ይገባል፡፡ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከጎተራቸው መዝገን ይገባል፡፡  ‹ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስተዋሻዎች› የሚለው መጽሐፋቸው ከዘመነ አኩስም እስከ 20ኛው መክዘ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መልክና ዓይነት ምን እንደሚመስል፤ ሥነ ጽሑፉን ማጥናት የሚሰጣቸውን ጥቅሞች፣ በውስጡ የያዛቸውን ነገሮች፤ እነማን እንደ ደከሙበት፣ ሳናውቃቸው ስለቀረነው ቀደምት ሊቆቻችን የሚነግሩን ነገር እንደ ወንዝ ይዞ የሚፈስ ነው፡፡ከዓይነት ከዓይነቱ እየተረጎሙ ያቀረቡልን የግእዝ ሥነ ጽሑፍ ዓይነቶች ሦስት ጥቅሞች አሏቸው፡፡ የግእዝን የረዥም ዘመን የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ያሳያሉ፤
Posted in Ethiopian News, Religion

ከማስታገሻው ወደ መፈወሻው

የሚፈቱትን ለመቀበል የወጣው ሕዝብመንግሥት መረራ ጉዲናን፣ እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን፣ በቀለ ገርባንና ሌሎችንም የፖለቲካ እስረኞችን መፍታቱ አንድ ርምጃ ወደፊት ነው፡፡ ቢያንስ ያንዣበበውን የሥጋት ደመና ይገፈዋል፡፡ የሀገሪቱንም ዜና ከ‹ታሠሩ› ወደ ‹ተፈቱ› ይቀይረዋል፡፡ የተስፋ ብልጭታም በሕዝቡ ላይ ይጭራል፡፡ ከታሠሩት ጋር አብሮ ለታሠረውም ወገን ትልቅ እፎይታ ነው፡፡ አብሮ ግን ሁለት ነገሮች ተያይዘውና ቀጥለው መምጣት አለባቸው፡፡ 1.      መፈታት ያለባቸውን ወገኖች ጨርሶ መፍታት፡- የክስ ዐንቀጻቸው ምንም ይበል ምን በሕዝቡ ዘንድ በፖለቲካዊ ሐሳባቸውና ሥራቸው የታሠሩ መሆናቸው የሚታመንባቸው ብዙ ዜጎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ የሚታወቁ በመሆናቸው በየማኅበራዊ ሚዲያው ስማቸው ይነሣል፤ ሌሎቹ ደግሞ የሚጮኽላቸውም ሆነ የሚሰለፍላቸው የሌላቸው ናቸው፡፡ መንግሥት ሁለቱንም በመፍታቱ ያተርፋል እንጂ አይከስርም፡፡ አሁን እንደምናየው በሕዝቡ ላይ ሥጋት አንዣቧል፡፡ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንኳን ሳይቀር ፍርሐት እየነገሠ መሆኑን በቀላሉ ለማየት ይቻላል፡፡ መንገድ ሊዘጋ ነው፣ ነዳጅ ሊጠፋ ነው፣ እህል ሊወደድ ነው፣ ችግር ሊፈጠር ነው፣ የሚለው ወሬ ጉዳቱ ከኢኮኖሚው በላይ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ለመላክ ሦስት ጊዜ ማሰብ እየጀመሩ
Posted in Ethiopian News, Religion

የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ (ክፍል ስድስት እና የመጨረሻው)

በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ ይህንን ይጫኑየጌታቸው ኃይሌ መከራከሪያፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ዘርአ ያእቆብን በተመለከተ በቅርቡ ሁለት ጽሑፎችን አውጥተዋል፡፡ የመጀመሪያው በ2006 ዓ.ም. ባሳተሙት ‹ሐተታ ዘዘርአ ያእቆብ› በሚለው መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ የሰጡት ትንታኔ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በ2017 ባወጡት Ethiopian Studies in Honor of Amha Asfaw በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ያቀረቡት ጥናት ነው፡፡ ጌታቸው ኃይሌ ዘርአ ያእቆብ በካቶሊክ ሚስዮናውያን ተጽዕኖ ውስጥ የወደቀ፣ ፍልስፍናውንም በአብዛኛው ከእነርሱ የወሰደ ኢትዮጵያዊ ዳዊት ደጋሚ ደብተራ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ለዚህ ድምዳሜ መድረሻ ያነሷቸው ነጥቦች አሉ፡፡ አንድ በአንድ እንያቸው፡፡ 1.      ኡርቢኖ የሐተታ ደራሲ ከሆነ ለምን በግእዝ ይጽፈዋል? ምክንያቱም የጻፈው ለኢትዮጵያውያን ነው እንዳንል ሁለቱንም ቅጅዎች ወደ ፈረንሳይ ልኳቸዋል፡፡ በሐተታዎቹ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች ደግሞ ለአውሮፓውያን አዲስ አይደሉም፡፡2.     የቅጅ ቁጥር 234 በኡርቢኖ የእርማት ሥራ ተሠርቶበታል፡፡ ኡርቢኖ የራሱን ሥራ ለምን ያርመዋል?3.     ሐተታ ኢትዮጵያዊውን መዝሙረ ዳዊት በሚገባ በሚያውቅ ሰው የተዘጋጀ ነው፡፡ ‹በዳዊት ደጋሚ ደብተራ›፤ መዝሙረ ዳዊት የዕለት የጸሎት መጽሐፉ ካልሆነ በዚህ መጠን አይጠቅሰውም፡፡ ይህ ደግሞ ዳዊትን በቃላቸው
Posted in Ethiopian News, Religion

የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ (ክፍል አምስት)

ለመሆኑ ሐተታዎቹ ምን ይነግሩናል? 1.  ዘርአ ያእቆብ የተወለደው ከአክሱም ካህናት ወገን መሆኑን ይነግረናል፡፡ በአኩስም የትኛው ክፍል ወይም ቦታ እንደሆነ ግን አይገልጥም፡፡ ይህ ግን ዘርአ ያእቆብ በሌሎች ነገሮች ከሚሰጠን ዝርዝር የተለየ ነው፡፡ የወደቀበትን ገደል ሥፍር ሳይቀር 25 ክንድ ከስንዝር መሆኑን ይነግረናል፡፡ እንዲያውም በእኛ ድርሳናት ያልተለመደ የተወለደበትን ቀንና ዘመንም ይገልጥልናል፡፡ ልጁ የተወለደበትን ቀንና ዘመንም ይገልጥልናል፡፡ አኩስም ውስጥ የተወለደበትን ቦታ ግን አይነግረንም፡፡ ኡርቢኖ አኩስም አካባቢ ስለነበረ ነው ይህን የትውልድ ቦታ የመረጠው ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ 2. የዘርአ ያእቆብ የዓለም ስሙ ‹ወርቄ› ነው፡፡ ‹ወርቄ፣ ብርቄ፣ ድንቄ› የሚሉ የስም አወጣጦች በአማራው አካባቢ እንጂ በአኩስም አካባቢ የተለመዱ ስሞች አይደሉም፡፡ ኡርቢኖ በደብረ ታቦር አካባቢ ሲኖር የሰማውን ስም መሆን አለበት የተጠቀመው፡፡3.   ዘርአ ያእቆብ ትርጓሜ መጻሕፍት እንደተማረ ይነግረናል፡፡ በቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርት ብሉይ፣ ሐዲስ፣ ሊቃውንትና መጻሕፍተ መነኮሳት ናቸው፡፡ ዝርዝር ማቅረብ የሚወደው ዘርአ ያእቆብ ጠቅልሎ ‹መጻሕፍትን ተማርኩ› የሚለውን ለመቀበል አስቸጋሪ ነው፡፡ ያውም ‹የሀገራችን መምህራን እንዴት እንደሚተረጉሟቸው፣ ፈረንጆችም እንዴት እንደሚተረጉሟቸው ተማርኩ›
Posted in Ethiopian News, Religion

የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ (ክፍል አራት)

የፍልስፍናው ይዘታዊማስረጃዎች ኮንቲ ሮሲኒ እንደሚለው የሐተታ ዘርአ ያእቆብን ፍልስፍና ከዳ. ኡርቢኖ ደብዳቤዎች ጋር ለማስተያየት ሞክሮ ነበር፡፡ ዳ. ኡርቢኖ በግንቦት 1854 ለአንቶንዮ ዲ. አባዲ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ሰውን የዚህ ዓለም ማዕከል አድርጎ የሚያይበትን አመለካከቱን አንጸባርቆ ነበር፡፡ ይህም አስተሳሰብ በሐተታ ዘርአ ያእቆብ ላይ በዚያው መልኩ ይገኛል፡፡ ኡርቢኖ ‹አንዳች ነገር ባውቅ ያ ከእግዚአብሔር ያገኘሁት ነው፡፡ ማንም አላስተማረኝም.. ስለ ፈጣሪና ሀልዎቱ እውነት የሆነ ሐሳብ እንዳለኝ አምናለሁ፡፡ ይህንንም ከማንም ባለመቀበሌ እኮራለሁ› ሲል በደብዳቤው ላይ ገልጦታል፡፡ በመስከረም 1854 በጻፈው ሌላ ደብዳቤ ደግሞ ብቸኝነቱ ከፈጣሪና ከዓለማት ጋር ለመገናኘትና በደስታ ለመኖር የሚቻልበትን መንገድ ለመመርመር እንደገፋፋው ይገልጣል፡፡ ‹እግዚአብሔር መኖሩን አምናለሁ፤ ሌላው ነገር ግን ሊያረካኝ ስላልቻለ እቃወመዋለሁ› ሲል ገልጦ ነበር፡፡ ይህን መሰሉ ሐሳብ በሐተታ ዘርአ ያእቆብም ውስጥ ይገኛል፡፡ በርግጥ ይህንን ደብዳቤ የጻፈው ሐተታ ዘርአ ያእቆብን ካገኘ ከሁለት ዓመታት በኋላ በመሆኑ ማን ከማን እንደወሰደው ግልጽ አይደለም የሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብሎ ከጻፋቸው ብቸኝነቱን ከሚጠቅሱት ደብዳቤዎቹ ጋር ስናነጻጽረው ይህ ሐሳብ
Posted in Ethiopian News, Religion

የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ (ክፍል ሦስት)

አባ አየለ ተክለ ሃይማኖትና ዳ. ኡርቢኖአባ አየለ ተክለ ሃይማኖት በዳ. ኡርቢኖ ዘመን የነበረ ካቶሊካዊ ሚሲዮናዊ ነው፡፡ በአቡነ ያዕቆብ ይመራ የነበረው የትግራይ ካቶሊክ ሚሲዮናዊ ልዑክ አባል ነበር፡፡ ከትግራይ ወደ ጎንደር መጣ፡፡ ምንም እንኳን ዳ. ኡርቢኖ የተመላለሰበትን መሥመር በሚገባ ቢያውቀውም የእርሱ ዋናው ትኩረት ግን የሚሲዮን አገልግሎት ላይ ነበር፡፡ ዳ. ኡርቢኖ ግን ሚሲዮናዊ ተልዕኮውን ትቶ በቤተ ልሔም አጠገብ ይኖር ነበር፡፡ ይሠራ የነበረው ሥራ ግን ለሌሎቹ የሥራ ባልደረቦቹ ግልጽ አልነበረም፡፡ ኮንቲ ሮሲኒ እኤአ በ1916 የአባ ተክለ ሃይማኖትን ማስታወሻ አሳትሞ ነበር[1]፡፡ በዚህ ማስታወሻቸው ላይ ዳ. ኡርቢኖ ከቤተልሔም ደባትር ከደብተራ አማርከኝ(ምናልባት ደብተራ አሰጋኸኝ ይሆናል) እና ከሊቀ ካህናት ጎሹ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንደነበረው ይገልጣሉ፡፡ ከእነርሱም የፍሪ ማሶናውያንንና የመናፍቃንን መጽሐፍ መግዛቱን ይናገራሉ፡፡ በዚህ ማስታወሻ ላይ ዳ. ኡርቢኖ ብዙ መጻሕፍትን እንደሚያስጽፍ፤ የእነዚህ መጻሕፍት ደራሲ ራሱ ቢሆንም ነገር ግን የብእር ስም እንደሚጠቀም፣ ይህም መጽሐፍ ወርቄ እንደሚባል፣ ስምሙ የተሰጠው ደራሲው ነው ተብሎ በታሰበው ሰው ስም መሆኑን ያትታሉ፡፡ አባ ተክለ ሃይማኖት ‹ሐተታ ዘርአ
Posted in Ethiopian News, Religion

ቀውስጦስ – የበረሓ ምንጭ

ሲያምኑ እንደ አብርሃም ነው፣ ሲሠሩ እንደ ላሊበላ፡፡ ሲያስተምሩ እንደ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው፣ ሲተጉ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ፤ ከቆረጡ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው፣ ከሞገቱ እንደ ሳዊሮስ፡፡ ከመረቁ የሚጠቅሙትን ያህል ከረገሙም ይጎዳሉ፤ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከሆነባቸው ክብር፣ ፕሮቶኮል፣ ስምና ዝና አይገድባቸውም፡፡ ከቀበሌ እስከ ቤተ መንግሥት ይሞግታሉ፤ በፍትሕ አደባባይ መፍትሔ ካጡ ‹ይግባኝ ለክርስቶስ‹ ብለው ለሰማያዊው ፍርድ ቤት ያቀርባሉ፡፡አረጋዊ ናቸው፣ ግን እንደ ወጣት ይሠራሉ፤ ሊቀ ጳጳስ ናቸው ነገር ግን እንደ ሰንበት ተማሪ ይሮጣሉ፣ የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፣ ግን በሁሉም ይወደዳሉ፤ ትምህርታቸው ከሰው ልብ ዕንባቸው መንበረ ጸባዖት ይደርሳል፡፡ በርሳቸው ዘንድ ትንሽ የለም፣ ትልቅም የለም፡፡የርሳቸውን ስም የያዘው ቅዱስ የዛሬ 700 ዓመት እንዲሁ እንደርሳቸው ነበር፡፡ ቅዱሱ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሲሆን ያስተምራል፣ ገዳማትን ይተክላል፣ ደቀ መዛሙርትን ያፈራል፣ ነገሥታትን ይገሥጻል፣ ለእምነቱ ጥብቅና ይቆማል፣ ግፍንና በደልን ይጸየፋል፡፡ ቅዱስ ቀውስጦስ ዘመሐግል፡፡ በሰማዕትነትም ያረፈው ንጉሥ ዓምደ ጽዮን ከክርስትናው ወጥቶ ሁለት ሚስት አግብቶ፣ የተቃወሙትን ቅዱሳን በግፍ ባሳደደ ጊዜ ነው፡፡ በንጉሡ
Posted in Ethiopian News, Religion

ኩሬአውያን

click here for pdfትውፊታውያን የሀገራችን ሰዓሊዎች የማያመዛዝንን ሰው ሲስሉ አንድ ዓይና አድርገው ይስሉት ነበር፡፡ ሰፋ አድርጎ የማያይ፤ እውነትን በከፊል ብቻ የሚቀበላት፤ ከሚያውቀው ውጭ ሌላ ነገር ያለ የማይመስለው ነው ማለታቸው ነው፡፡ ‹እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል› የሚል አባባልም አለ፡፡ ዕውቀትህን፣ አመለካከትህንና አካሄድህን ባሻሻልክ ቁጥር ያላየኸውን ታያለህ፣ ያልሰማኸውን ትሰማለህ፤ ያልተገለጠልህ ይገለጥልሃል፤ የረቀቀው ይጨበጥልሃል፤ እውነት ነው ያልከው ውሸት፣ ውሸት ነው ያልከውም እውነት ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ሲሉ ነው፡፡ ቀደምት ሊቃውንት ሁለት ዓይን የተሰጠን በአንዱ የራሳችን በሌላው የሌላውን ለማየት ነው፡፡ ሁለት ጆሮ የተሰጠን በአንዱ የራሳችንን በሌላው የሌላውን ለመስማት ነው፡፡ ሁለት እጅ የተሰጠን በአንዱ ለመስጠት በሌላው ለመቀበል ነው፡፡ ሁለት እግር የተሰጠን በአንዱ ወደራሳችን በሌላው ወደ ሌላው ለመሄድ ነው ይሉ ነበር፡፡  ሞንጎልያውያንም ከዚህ ጋር የሚሄድ ብሂል አላቸው፡፡ በአንዲት የሞንጎልያ ትንሽ መንደር ውስጥ በምትገኝ ኩሬ አንዲት ዓይን ብቻ ያለቺው ዕንቁራሪት ይኖር ነበር፡፡ ለእርሱ ዓለም ማለት ያቺ ኩሬ፣ ንጉሥም ማለት እርሱ ነው፡፡ ከእርሱ ኩሬ የተሻለ ቦታ፣ ከእርሱም የበለጠ ዕድለኛ የለም፡፡ የሚመኘው ነገር
Posted in Ethiopian News, Religion

ከአሸናፊዎች መዳፍ -ወደ- የተሸናፊዎች ወገብ

 click here for pdf‹ሰላም ከተሸናፊዎች ወገብ እንጂ ከአሸናፊዎች መዳፍ አትገኝም› የሚል ወርቃማ አባባል አላቸው የካናዳ ጥንታውያን ሕዝቦች (First Nations)፡፡ አደን ልዩ ችሎታቸው የነበረውና በዚህች ሀገር ከሺ ዓመታት በፊት ሠፍረው መኖር የጀመሩት እነዚህ ሕዝቦች አያሌ የእርስ በርስ ጦርነቶችንና ችግሮችን ለመፍታት የቻሉት በዚህ ምክንያት እንደነበረ ይነገራል፡፡ ሁለት ጎሳዎች በአደንና በእርሻ ቦታ ወይም በድንበር ምክንያት በተፈጠረ ችግር ወደ ጦርነት ይገባሉ፡፡ የእነዚህ ጥንታውያን ሕዝቦች ሽማግሌዎች ግን ጦርነቱ በአንደኛው አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ አይፈቅዱም፡፡ ጦርነቱ ሲደረግ የተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው የሚታገሡት፡፡ የዚህን ምክንያቱን ሲያስረዱ ደግሞ ‹ሁለቱም ወገኖች የጦርነቱን አስከፊ ገጽታ መቅመስ አለባቸው› ይላሉ፡፡ የችግር መፍቻው መንገዳቸው ወደ ባሰ ችግር እየወሰዳቸው መሆኑን ከምክርና ከትምህርት ይልቅ በተግባር እንዲያዩት ጊዜ ይሰጧቸዋል፡፡በኋላ ግን በመካከል ይገባሉ፡፡ ‹ጦርነቱ በአንደኛው ወገን አሸናፊነት መጠናቀቅ የለበትም› የሚል እምነት አላቸው፡፡ ሁለቱም ወገኖች ቀን ጣላቸው፤ ችግር ለያያቸው፤ መንገድ አጣላቸው እንጂ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ የእነዚህ ወንድማማቾች ትግል በአንደኛው አሸናፊነት ከተጠናቀቀ ሰላም አይገኝም፡፡ አሸናፊው ጨቋኝ፣ በቀለኛ፣ ጉልበተኛና ዘራፊ ሆኖ ይቀራል፡፡ ተሸናፊው
Posted in Ethiopian News, Religion

ኑ! ሀገሬን እናዋልዳት

አዋላጇ ጠፍታ ልጁም በእግሩ መጥቶእናቲቱ ሞተች ልጅዬውም ሞቶየሚል የልቅሶ ግጥም አለ። ነፍሰ ጡር እናት ስትወልድ ልጁ በእግሩ ከመጣ አደጋ ነው ይባላል። ጎበዝ አዋላጅ አግኝታ ልጁ በአናቱ እንዲመጣ ልታግዛት ይገባል። ያ ካልሆነ ግን ባልተስተካከለ መንገድ የመጣውን ልጅ ለመውለድ የምታምጠው እናት፣ ለረዥም ጊዜ በማማጧ የተነሣ ደክማ ለሞት ትዳረጋለች። ልጇም የመሞት ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። መውለድ ደስታ የሚሆነው ልጁ በሰላም ተወልዶ፣ ለእናቱ ጤናና ደስታ ካመጣ ነው። መውለድ ካልተስተካከለ ማርገዝ ብቻውን ድካም ነው። ለዚህ ነው ነፍሰ ጡሮች በሕክምና እርዳታ ሲታገዙ ቆይተው፣ በሕክምና እርዳታ እንዲወልዱ የሚመከረው።ሀገር ለውጥን ልትወልድ የምትችለው የለውጥን ጽንስ በጤናማ መልኩ አርግዛ በጤናማ መልኩ እንድትወልድ የሚረዷትን ሐኪሞች ካገኘች ነው። ጽንሱ ጤናማ መሆኑን በየጊዜው የሚከታተሉ፤ ችግር ሲፈጠር ወዲያው መፍትሔ የሚሰጡ። ስትወልድም ልጁም እናቲቱም ጤንነታቸው በተጠበቀበት መንገድ እንድትወልድ የሚረዱ አዋላጅ ሐኪሞች ያስፈልጓታል። ይህ ሲጠፋ ልጁም እናቲቱም ለሞት ይዳረጋሉ።ኢትዮጵያ ብዙ ጊዜ ለውጥን ፀንሳ ታውቃለች። ብዙ ጊዜ የማታገኘው ጎበዝ አዋላጅ ሐኪም ነው። በዚህ ምክንያትም ብዙ ጊዜ ልጇ ሞቶባታል።
Posted in Ethiopian News, Religion

ተቀምጠው የሰቀሉት

click here for pdf የኢራቅ ኩርዶች እንዲህ ይተርካሉ፤አንዲት የልዑል ልጅ ነበረች፡፡ አንድ የምታፈቅረው ልጅም ነበረ፡፡ ታድያ ከአንድ የቤተ መንግሥቱ ጠባቂ ጋር ትመካከርና ይህንን ፍቅረኛዋን ክፍሏ ድረስ ታስገባው ነበር፡፡ የቤተ መንግሥቱ ጥበቃ የተወሰነ ገንዘብና ልብስ ትሰጠው ስለነበር በደስታ ምሥጢሩን ይደብቅ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡ ልዕልቲቱና ፍቅረኛዋ አፕል ቆርጠው እየተጫወቱ ይበሉ ነበር፡፡ ሁለቱም አፋቸውን ከፍተው የአፕሉን ቁራጭ አንዳቸው ወደሌላቸው አፍ ወርውሮ የማስገባት ጨዋታ ነበር የሚጫወቱት፡፡ እየተሳሳቁ የአፕል ቁራጭ ወደየአፎቻቸው ሲወረውሩ ልዕልቲቱ የወረወረችው የአፕል ቁራጭ ድንገት የፍቅረኛዋ ጉሮሮ ውስጥ ተቀረቀረ፡፡ ውኃ ብትሰጠው፣ ማጅራቱን ብትመታው ሊወርድለት አልቻለም፡፡ ኡኡ ብላ እንዳትጮህ ልጁ ማነው? እንዴትስ መጣ ? ለሚለው ጥያቄ የምትመልሰው የላትም፡፡ በዚህ መካከል ልጁ ትንፋሽ አጥሮት ሞተ፡፡የልጁ የመውጫ ሰዓት ሲደርስ የጥበቃ ሠራተኛው መጣ፡፡ እንደቀድሞው ግን ልጁን ደብቆ ሊያስወጣው አይችልም፡፡ አሁን ያለው ሬሳው ነው፡፡ ‹እባክህን የምትችለውን ሁሉ አድርገህ ይህንን ሬሳ አውጣልኝ፤ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ አደርግልሃለው› አለቺው፡፡ የጥበቃ ሠራተኛውም ‹ምንም ችግር የለውም፤ የምፈልገው ግን ገንዘብ ወይም
Posted in Ethiopian News, Religion

ሦስቱ የሕዝብ ማስጠንቀቂያዎች

click here for pdfሕዝብ ለመሪው በሦስት ደረጃ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ‹አርም› የሚል ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ሕዝቡ ሦስት ነገሮችን አምኗል ማለት ነው፡፡ አንድም መሪው በጎ ኅሊና አለው፤ ለማረም የሚችል ዐቅም አለው፤ ችግሩ የተፈጠረው ከአሠራሩ ላይ ነው ብሏል፡፡ አንድም ደግሞ ሕዝቡ መሪው እንደማንኛውም ፍጡር ተሳሳተ እንጂ ራሱ ስሕተት አይደለም፡፡ ስለዚህ ሊያርም ይችላል ብሎ አምኗል፡፡ በመጨረሻም ሕዝብ መሪውን ይወዳል፣ ስሕተቱን ግን ይጠላል ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ የደረሰ መሪ የታደለ የሚሆነው ስሕተቶቹን ነቅሶ ‹ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅ በርጥቡ› ለማረም ከቻለ ነው፡፡ የሚሳሳት ፈጣሪ እንደሌለ ሁሉ የማይሳሳት መሪ የለም፡፡  መሪዎችን ታላቅና ታናሽ የሚያደርጋቸው ስሕተታቸውን ለማመንና አምነውም ለማረም ያላቸው ዐቅምና ቁርጠኛነት ነው፡፡ መሪ የሕዝቡን ጥቆማ ሰምቶ፣ የሕዝቡንም ልብ አድምጦ ችግሩን በጊዜ ካረመ ስሕተቱ ከሥራ የመጣ እንጂ ከመሪው ጠባይ የመነጨ አይደለም ብሎ ሕዝብ በመሪው እንዲተማመን ያደርገዋል፡፡ ‹ከሰው ስሕተት፣ ከብረት ዝገት አይጠፋም› ብሎ ያልፈዋል፡፡ ሕዝብ የነገረውን ስሕተት ከማረም ይልቅ ‹እኔ ደኅና ነኝ ችግሩ ከአፈጻጸሜ የመጣ ነው› እያለ ችላ ካለው ሕዝብ
Posted in Ethiopian News, Religion

በ4ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መሳተፍ ለምትፈልጉ

4ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓም ከቀኑ በ7፡30 በአዲስ አበባ 22 አካባቢ በሚገኘው አቤል ሲኒማ ይከናወናል፡፡ በዚህ መርሐ ግብር መሳተፍ ለምትፈልጉ 150 ሰዎች መግቢያ ተዘጋጅቷል፡፡  ዛሬ፣ ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓም ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ በኢሜይል begosew2008 @gmail .com ስምዎትንና የስልክ ቁጥርዎትን ይላኩ፡፡ ቀጥሎ ማረጋገጫ(Confirmation) ይላክልዎታል፡፡ ማረጋገጫው ከደረሰዎ በኋላ ከዓርብ ነሐሴ 20 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ምርፋቅ ካፌና ሬስቶራንት በመሄድ ስልክ ቁጥርዎን በመንገር ካርዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡  መልካም ዕድል
Posted in Ethiopian News, Religion

የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ታወቁ

click her for pdf ጋዜጣዊ መግለጫለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደውና ለሀገራቸውና ለወገናቸው ላቅ ያለ አገልግሎት የሰጡ ዜጎች የሚከብሩበት የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ በአቤል ሲኒማ አዳራሽ ይከናወናል፡፡ በዕለቱ የክብር እንግዶች፣ ተሸላሚዎች፣ ዕጩዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና መገናኛ ብዙኃን  በሚገኙበት ሥነ ሥርዓቱ ይከናወናል፡፡ የበጎ ሰው ሽልማት ኮሚቴ ያለፉትን ሦስት ዝግጅቶች ሂደት ሲያከናውን እንደኖረው ለዚህ ክብር መብቃት አለባቸው የተባሉ ዜጎች በሕዝቡ የተጠቆሙ ሲሆን፤ በየዘርፉ ከተጠቆሙት ዜጎች መካከልም ሥራዎቻቸው ተመዝነው ሦስት ሦስት ዕጩዎች ተለይተዋል፡፡ በእነዚህ እጩዎች ላይ አምስት አምስት ዳኞች (በየዘርፉ) ደምጽ እየሰጡ ነው፡፡ የየዘርፉ ተሸላሚዎችም ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓም በሚካኼደው ሥነ ሥርዓት ይከበራሉ፡፡መገናኛ ብዙኃንና ሌሎች የመገናኛ አካላት እጩዎችን በማስተዋወቅና በማክበር ለሀገራቸው በጎ የሚሠሩ ዜጎችን ለማብዛት የበኩላቸውን እንዲወጡ እየጠየቅን ዕጩዎቹን በየዘርፋቸው እንደሚከተለው እንገልጣለን፡፡  1.    መምህርነት·         ተ/ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው (በአዲስ አበባ ዩኚቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ መምህር)·         ተ/ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የነበሩ)·         መ/ር
Posted in Ethiopian News, Religion

ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት

click here for pdfጥንታውያን የአብነት ሊቃውንት ‹ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት ነው› ይላሉ፡፡ መታመሙን ላወቀ፣ መድኃኒቱን ለፈለገ፣ መድኃኒቱንም በትክክል ለወሰደ፣ ወስዶም ለዳነ ሰው ሕመም ለትምህርት ይሆነዋል፡፡ ሦስት ነገር ይማርበታልና፡፡ አንድም ዳግመኛ እንዳይዘው ጥንቃቄን፣ አንድም ቢይዘው ሊትርፍ የሚችልበትን መፍትሔን፣ አንድም ደግሞ ለሌላው የሚመክረው ልምድን ያተርፋል፡፡ ያለበለዚያ ግን የሕመም መጨረሻው ሞት ነውና ላንዱ ትምህርት የሆነው በሽታ ሌላውን ይገድለዋል፡፡አሁን ታመናል፡፡ ሕዝቡ የሚያነሣው ጥያቄ፣ መንግሥት የሚሰጠው ምላሽ፣ የሃይማኖት ‹አባቶች› የሚያወጡት መግለጫ፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ከግራ ከቀኝ የሚያናፍሰው ነገር፣ ደጋፊና ተቃዋሚው ከወዲህ ወዲያ የሚሠናዘረው ዱላ ሕመም ላይ መሆናችንን የሚገልጥ ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን መታመሙን የሚያምን፣ መድኃኒቱን የሚፈልግና መድኃኒቱንም በተገቢው ሁኔታ የሚወስድ መንግሥትና ሕዝብ ነው፡፡መጀመሪያ መተማመን የሚያስፈልገው ‹ችግር አለ ወይ?› የሚለው ላይ ነው፡፡ አዎን ችግር አለ፡፡ እየሆኑ ያሉት ነገሮች የሚነግሩን ችግር መኖሩን ነው፡፡ ችግሩ እነ እንትና ያነሣሡት፣ የቀሰቀሱት፣ ያደራጁት ምናምን ማለታችን ችግር መኖሩን አያስቀረውም፡፡ በሀገራችን ‹የጥያቄ ክፉ የለውም፤ የመልስ እንጂ›  ይባላል፡፡ የጥቂቶች ወይም የብዙዎች፣ የእነ አንቶኔ ወይም የነ
Posted in Ethiopian News, Religion

ቆሻሻ መጣል ክልክል ነው

click here for pdfየሰዎችን አስተሳሰብ ሊለውጡ የሚችሉ ንግግሮችን በማድረግ የሚታወቀው ዓምደኛው ዴቪድ ጄ. ፖላይ ‹የቆሻሻ መኪና ሕግ (The Law of the Garbage Truck)  የተሰኘ ተወዳጅና ተደናቂ መጽሐፍ አለው፡፡ ይህንን መጽሐፉን ለመጻፍ መነሻ የሆነው ኒውዮርክ ውስጥ አንድ ቀን በታክሲ ሲጓዝ ያጋጠመው አደጋ ነበር፡፡ እርሱ የሚሄድበትን ታክሲ ከጎኑ የመጣ ሌላ መኪና ሊገጨው ለጥቂት ተረፈ፡፡ ስሕተቱ ከጎን የነበረው መኪና ሾፌር ነበር፡፡ ነገር ግን አደጋ አድራሹ ሾፌር በስሕተቱ ከመፀፀት ይልቅ መስኮቱን ከፍቶ የታክሲውን ሾፌር መሳደብና ማበሻቀጥ ጀመረ፡፡ የታክሲው ሾፌር ግን ፈገግ ብሎ እጁን ለሰላምታ በማውለብለብና ‹መልካም ቀን ይሁንልህ› በሚል የምኞት ቃል አለፈው፡፡ጄ. ፖላይ ነገሩ ስላስገረመው የታክሲው ሾፌር ጠየቀው፡፡ ‹ጥፋተኛው ያኛው ሾፌር ነው፡፡ ይባስ ብሎም መስኮቱን ከፍቶ ሲሰድብህ ነበር፡፡ አንተ ግን መልካም እንደተደረገልህ ሁሉ ፈገግ አልክለት፤ እንዲያውም እጅህን አውጥተህ ሰላምታ ሰጠኸው፡፡ መልካም ምኞትህንም ገለጥክለት፡፡ ግን ለምን?› ሲል ጠየቀው፡፡ የታክሲውም ሾፌር አሁንም ፈገግ ብሎ ‹ብዙ ሰዎች የቆሻሻ መኪኖች ናቸው፡፡ ቆሻሻውን ተሸክመውም የሚያራግፉበት ቦታ ይፈልጋሉ፡፡ የያዙት ቆሻሻ
Posted in Ethiopian News, Religion

ደብተራ

click here for pdf  ከአንዳንድ ሰዎች ጋር የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በተመለከተ ስንነጋገር ‹ደብተራ የጻፈው› ማለት ይቀናቸዋል፡፡ ይሄ ንግግራቸው ከሁለት ስሕተቶች የመነጨ ነው፡፡ አንደኛው ስለ ደብተራ ካለማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ስለ መጻሕፍቱ ካለመረዳት የሚመጣ ነው፡፡ ‹ደብተራ› የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉሙ ‹ድንኳን› ማለት ነው፡፡ ይህም ቢሆን ‹ሐይመት› ከሚለው ቃል ፍች ይለያል፡፡ ‹ሐይመት› ለማንኛውም አገልግሎት የሚውለውን ድንኳን ሲያመለክት ‹ደብተራ› ግን በዋናነት ለቤተ መቅደስነት የሚውለውን ድንኳን ያመለክታል፡፡ ‹ደብተራ ኦሪት› - የብርሃን ድንኳን እንዲል፡፡ በመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ላይ ነገሥታቱ ከሀገር ሀገር ሲጓዙ አብራቸው የምትጓዝ የጸሎት ታቦት ነበረቻቸው፡፡ ለዚህች ታቦት የምትሆን ድንኳን አዘጋጁ፡፡ ታቦቷ በቤተ መንግሥት ግቢ ተተክላ ትቀመጥና ንጉሡ ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀስ ተነቅላ ትንቀሳቀስ ነበር፡፡ በዚህች የቤተ መንግሥት የድንኳን መቅደስ ውስጥ ለአገልግሎት የሚመረጡት በዕውቀታቸውና በንጽሕናቸው የተመሰገኑ ነበሩ፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አባት በዚህች ድንኳን ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ነበረ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በዚህች የድንኳን ቤተ መቅደስ ውስጥ አገልግሏል፡፡ በዚህች ቤተ መቅደስ የሚያገለግሉት ካህናት አንዱ ሥራቸው ንጉሣውያን ቤተሰቦችን ማስተማር
Posted in Ethiopian News, Religion

መሪ(ሪዳ) እና ገዥ(ሐጉካይ-ሻ)

click here for pdfየሩቅ ምሥራቆቹ ጃፓኖች እንዲህ የሚል ለዓለም የተረፈ ታሪክ አላቸው፡፡ በ17ኛው መክዘ ላይ በዓይን ሕመም የሚሰቃይ ጎ- ሳይ የተባለ አንድ የጃፓን ንጉሥ ነበረ፡፡ በሀገረ ጃፓን የሚገኙ ሐኪሞችን ሁሉ ጠርቶ ለስቃዩ መድኃኒት እንዲፈልጉለት ቢያዝም ሊያገኙ ግን አልቻሉም፡፡ በኮርያ፣ በቻይና፣ በሞንጎልያና በሩሲያ ሳይቀር ታዋቂ የሆኑ ባለ መድኃኒተኞችን እየጠራ፣ ገንዘብና ሥልጣን ለመሸለምም ቃል እየገባ ሕመሙን ለማዳን ሞከረ፡፡ ግን አልተቻለውም፡፡ በመጨረሻም ሞንጎልያ ውስጥ በኡውስ ሐይቅ አጠገብ ዑላንጎም በተባለ መንደር እጅግ የታወቀ ባለ መድኃኒት መኖሩ ተሰማ፡፡ንጉሥ ጎ- ሳይም ኦይራት የተባሉትን የሞንጎልያ ሲራራ ነጋዴዎች ይህን ባለመድኃኒት እንዲያመጡለት ወርቅ ሰጥቶ ላካቸው፡፡ ከአራት ወራት በኋላም ኦይራት የሚባሉት ሲራራ ነጋዴዎች ባለመድኃኒቱን በድንክየዎቹና ፀጉራሞቹ ግመሎች ጭነው አመጡለት፡፡ ንጉሥ ጎ-ሳይ ባለ መድኃኒቱ መምጣቱን ሲሰማ የመዳን ተስፋው ለመለመ፡፡ ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒተኛ ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብቶ ንጉሡን አገኘው፡፡ ንጉሡም ከሚያሰቃየው የዓይን ሕመም ከፈውሰው የፈለገው ሁሉ እንደሚሰጠው ቃል ገባለት፡፡ ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒተኛ የንጉሡን ሕመም ለማዳን የሚችል መድኃኒት እንዳለው ነገር ግን ንጉሡ መዳን የሚችለው አንድ
Posted in Ethiopian News, Religion

የሰሎሞን ፍርድ

clik here for pdfሦስት ነጋዴዎች ድንገት አንድ ቀን በንጉሥ ሰሎሞን የዘውድ ችሎት ተገኙ፡፡ ሦስቱም ለብዙ ዘመን አብረው ለመነገድ ተማምለው፣ ግመል ጭነው፣ ገንዘብ ቋጥረው፣ ስንቅ አንጠልጥለው፣ ሀገር ጥለው የሄዱ ናቸው፡፡ ‹ንጉሥ ሆይ› አለ አንዱ በዙፋኑ ፊት እጅ ነሥቶ፡፡ ‹እኛ አብረን ለመነገድ ተስማምተን መንገድ የጀመርን ጓደኛሞች ነን› አለ፡፡ሁለተኛውም ነጋዴ ተቀብሎ ‹ቃላችንንም አክብረን ለንግድ ሩቅ ሀገር ስንጓዝ ድንገት የሰንበት በዓል ደረሰብን› ሲል ቀጠለ፡፡ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ሰንበትን አክብረን ለመዋል ስለፈለግንም ድንኳን ከተከልንበት ቦታ ራቅ አድርገን ጉድጓድ ቆፍረን ገንዘባችንን በከረጢት ቀበርነው፡፡ ከመካከላችን ማናችንም ገንዘቡን ተደብቀን ላንወስድ መሐላ ፈጽመን ነበር፡፡ በማግሥቱ ግን ወደ ጉደጓዱ ሄደን ስንቆፍረው ገንዘባችንን አጣነው› አለና አስረዳ፡፡ የመጀመሪያው ነጋዴም አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ‹ንጉሥ ሆይ ጉድጓዱን ስንቆፍርም ሆነ ገንዘቡን ስንደብቅ ሌላ ሰው ያየን የለም፡፡ ከሰረቅነው እኛው ነን፡፡ ነገር ግን ማናችን እንደሰረቅን ልንተማመን አልቻልንም› አለ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞን በልቡ ‹መስረቅ የቻለ ሰው መዋሸትና መሐላን ማፍረስ አያቅተውም› ብሎ አሰበና  ነገሩን ቀለል አድርጎ ‹ነገ ተመልሳችሁ ስትመጡ ማን እንደሰቀረው እነግራችኋለሁ›
Posted in Ethiopian News, Religion

ኩሬና ወንዝ ምሁራን

cleck here for pdfሰሞኑን ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን የሕይወት ታሪክ አሳትሞ አቅርቦልናል፡፡ መጽሐፉ በላቀ የታሪክ ሞያ የተሠራ፣ የታላላቅ ሰዎችን የሕይወት ታሪክ ለሚሠሩ ሰዎችም እንደ ሞዴል ሊያገለግል የሚችል የታሪክ ጥናት ድርሳን ነው፡፡ መጽሐፉን ሳነብ ከመጽሐፉ ይዘት ይልቅ የመጽሐፉ አዘጋጅና አዘገጃጀት ነበር በአእምሮዬ የሚመላለሰው፡፡ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ታሪክ የተመለከቱ ጥናቶችንና መጻሕፍትን አዘጋጅቶ አሳትሞ ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ የጥናት ጽሑፎቹና መጻሕፍቱ የተዘጋጁት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው፡፡ ብዙዎቹም የታተሙት ከሀገር ውጭ በሚታተሙ ጆርናሎች ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የፕሮፌሰር ባሕሩ ብቻ ሳይሆን የአብዛኞቹ የሀገራችን ምሁራን መንገድ ነው፡፡ በሁለት ምክንያት ያደርጉታል፡፡ በአንድ በኩል በአካዳሚው የሚኖራቸውን የሞያ ሂደት ማስቀጠልና አካዳሚያዊ መዓርጎችን ማግኘት የሚችሉት በታወቁ ዐውደ ጥናቶች በሚያቀርቧቸውና በዕውቅ ጆርናሎች በሚያሳትሟቸው የጥናት ወረቀቶች አማካኝነት ስለሆነ፡፡ እነዚህ ጆርናሎች ደግሞ በብዛት(እንዲያውም ሁሉም ማለት ይቻላል) የሚገኙት በውጭ ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማት ስለሆኑ፡፡ ሌላው ደግሞ የሀገራችን የአካዳሚያዊ ዕውቀት መሸመቻና ማስሸመቻ ቋንቋ እንግሊዝኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እነርሱም የተማሩት፣ የመመረቂያ ጥናቶቻቸውንም የሠሩት በእንግሊዝኛ(አልፎ አልፎ
Posted in Ethiopian News, Religion

ኤጲደቅስዮ

click here for pdfፊሳልጎስ የተሰኘዉና በ2ኛው መክዘ በእስክንድርያ ተጽፎ በ5ኛው መክዘ ወደ ግእዝ የተተረጎመው መጽሐፍ ‹ኤጲዲቅስዮ› ስለሚባል ዛፍ ይተርካል፡፡ ይኼ በሕንደኬ ሀገር የሚገኝ ዛፍ ሁለት ጠባይ አለዉ፡፡ አርጋብ የዛፉን ፍሬ ስለሚወዱት በእርሱ ላይ እየተሰበሰቡ ይመገቡታል ይላል መጽሐፉ፡፡ እንደ እባብ ላሉ እንስሳት ደግሞ ጥላዉ እንኳን ከነካቸዉ ይሞታሉ፡፡ ነገር ግን ለእባቦቹ ሌላ ዘዴ ለግሷቸዋል፡፡ ርግቦችን ለማጥመድ የሚመጡት እባቦች የፀሐይ ጥላ ባላረፈበት አቅጣጫ፣ ወይም ፀሐይ ስትጠፋ ወይም ደግሞ ደመና ሲጋርድ ወደ አካባቢዉ ይመጡና ያደፍጣሉ፡፡ ዛፉን ርግቦችም እባቦችም ይፈልጉታል፡፡    ይህ ዛፍ በላቲኑ አምቢዴክትረስ(ambidextrous) ይባላል፡፡ ‹አምቢ› ማለት ‹ሁለቱም› ማለት ሲሆን ‹ደክስተር› ማለት ደግሞ ‹ትክክል› ማለት ነዉ፡፡ ‹አምቢዴክትረስ› ማለትም ‹በሁለቱም በኩል ትክክል የሆነ› ማለት ነዉ፡፡ የእንግሊዝኛው ቃል መጀመሪያ ተግባር ላይ የዋለዉ በሕግ ሰዎች ዘንድ ነዉ፡፡ አንተም ልክ ነህ፣ አንተም ልክ ነህ ብሎ ከከሳሽም ከተከሳሽም ወገን ጉቦ ለሚቀበል ዳኛ ነበር ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለዉ፡፡   ርግቦቹ ወደ ኤጲደቅስዮ ዛፍ ሲመጡ ሁለት ነገር ተስፋ አድርገዉ ነዉ፡፡ በአንድ በኩል
Posted in Ethiopian News, Religion

መውጣትና መውረድ

click here for pdfከቀናት በፊት ለሥራ ጉዳይ ባሕርዳር ነበርኩ፡፡ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስንጨዋወት ማኅበረሰባችን ከሥልጣናቸው የሚወርዱ ሰዎችን በበጎ የመቀበል ልማድ አለው ወይ? የሚል ነገር አነሣ፡፡ እኔም ‹ከሥልጣን ወርደው በሰላም የኖሩም በመከራ ያሳለፉም ዐውቃለሁ› አልኩት፡፡ ዐፄ ካሌብ ሥልጣናቸውን ትተው አባ ጰንጠሌዎን ገዳም ሲገቡ በልጃቸው በገብረ መስቀል ዘመን የደረሰባቸው መከራ የለም፡፡ ምናልባት ግን ያን ጊዜ የክርስትናው ጣዕሙ ያልጠፋበት ዘመን በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ በጎንደር ዘመን ግን አድያም ሰገድ ኢያሱ ሥልጣናቸውን ትተው ገዳም ቢገቡ ተተኪዎቻቸው የመነኑበት ድረስ መጥተው ገድለዋቸዋል፡፡ ሁለቱም በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል፡፡ወዳጄ ግን ‹ባህሉ ከሥልጣን ለወረደ ሰው ክብር የሚሰጥ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ ሹምን ያበረታታል፡፡ ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል የሚለውም የዚህ ምስክሩ ነው› አለና በሰሞኑ የገጠመውን ነገረኝ፡፡ ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች የአንዱ ዲን የነበረ ሰው  መኪናም፣ አበልም፣ ሥልጣንም፣ ክብርም ነበረው አለ፡፡ ሲወጣ ሲገባም እጅ ነሺው፣ ደጅ ጠኚውም ብዙ ነበረ አለ፡፡ በኋላ ታዲያ በአንዳንድ ጉዳዮች ምክንያት ከኃላፊነቱ እንዲነሣ ይወሰናል፡፡ ስብሰባው የተደረገው በዚያው እርሱ ይመራው በነበረው ኮሌጅ ግቢ ውስጥ
Posted in Ethiopian News, Religion

ሦስቱ ሳጥኖች

click here for pdfኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ሳጥኖች አሉ፡፡ ሁለቱ ሳጥኖች በጣም ይፈለጋሉ፡፡ ስለሚፈለጉ ወይ ይዘረፋሉ፤ ወይ ይሰረቃሉ፡፡ አንደኛውን ሳጥን ግን ዞሮ የሚያየው የለም፡፡ ሁለቱ በውስጣቸው በጣም ተፈላጊ ነገር አለ ተብሎ ስለሚታመን ሳጥኖቹ በፖሊስ በዘበኛ፣ አንዳንዴም በወታደር ይጠበቃሉ፤ አንደኛው ሳጥን ግን ጠባቂ የለውም፡፡ ውስጣቸው ያለው ነገር ሲጨምር የሚያመጡት ለውጥ አለ ተብሎ ስለሚታሰብ ሁለቱ ሳጥኖች ቶሎ ቶሎ ይቆጠራሉ፡፡ አንደኛው ሳጥን ግን የሚያስታውሰው የለም፡፡ ሁለቱ ሳጥኖች የምርጫ ሳጥንና የገንዘብ ሳጥን ናቸው፡፡ አንዱ ውስጥ ሥልጣን፣ ሌላው ውስጥ ገንዘብ አለ፡፡ ሥልጣን ያለበትን ሳጥን ፖለቲከኞች ይፈልጉታል፡፡ ስለዚህም ይሰብሩታል፣ ይገለብጡታል፡፡ ገንዘብ ያለበትን ሳጥን ሙሰኞች ይጓጉለታል፡፡ ይሰብሩታል፤ ይገለብጡታል፡፡ ሕዝቡም ስለእነዚህ ስለሁለቱ ሳጥኖች ጉዳይ ይከታተላል፡፡ ሲዘጉና ሲከፈቱ ኮሚቴ ያቋቁማል፡፡ ሲቆጠሩና ሲመዘኑ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ ሥልጣንና ገንዘብ ስላለባቸው፡፡ሦስተኛው ሳጥን ግን ከእነዚህ ሁሉ ይለያል፡፡ ዘጊ እንጂ ከፋች የለውም፡፡ ሠሪ እንጂ ተከታታይ የለውም፡፡ በውስጡ ያለውን ነገር ለማወቅ ባለቤቱም፤ ሕዝቡም አይጓጉም፡፡ ማንም እንደልቡ ያገኘዋል፡፡ ግን አይጠቀምበትም፡፡ ጥበቃ የለውም፤ ግን ማንም አይሰብረውም፡፡ ተመልካች ያጡ ወረቀቶችን በውስጡ
Posted in Ethiopian News, Religion

የሦስት ደብዳቤዎች አዙሪት

click here for pdfየአንድ ትልቅ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበረ ሰው ከደርጅቱ ሲለቅ ለተተኪው ሰው ሦስት ደብዳቤዎችን በሦስት ፖስታዎች አሽጎ በላያቸውም ላይ 1፣ 2 ና 3 ቁጥር ጽፎ ሰጠው፡፡ ተተኪውም ‹ምን ላድርጋቸው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ‹ድርጅቱን በምታስተዳድርበት ጊዜ ችግር በገጠመህ ቁጥር በየተራ ከፍተህ አንብባቸው› አለና መለሰለት፡፡ ርክክቡም በዚህ ተጠናቀቀ፡፡አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ሥልጣኑን እንደተረከበ ከያቅጣጫው ተቃውሞ በረታበት፤ በጉጉት ጠብቀውት የነበሩት ሁሉ ተስፋ ያደረጉትን ለውጥ በአጭሩ ማየት ስላልቻሉ መበሳጨትና ግፊት ማድረግ ጀመሩ፡፡ ‹ከበሮ በሰው እጅ ሲይዙት› እንደሚባለው ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ የሞሰቡ መስፊያ ጠፋበት፡፡ የዘሐውንም ውል ማግኘት አልቻለም፡፡ ድርጅቱም በችግር ተወጠረ፡፡ ከዚህም ከዚያም ተበደልን፣ መብታችን ተረገጠ፣ ተገፋን፣ ተናቅን፣ የሚሉ ድምጾች በረከቱ፡፡   በዚህ ጊዜ ቁጥር አንድ የተጻፈበትን ፖስታ ከፈተና የተጻፈውን አነበበው፡፡ ‹ካንተ በፊት የነበረውን ኃላፊ ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ውቀስ› ይላል፡፡ የድርጅቱን ሠራተኞች ሰበሰበና ከእርሱ በፊት የነበሩት ኃላፊዎች ያጠፉትን ጥፋት፣ የሠሩትን ስሕተት፣ ያደረሱትን በደልና የፈጠሩትን ችግር መዘርዘር ጀመረ፡፡ አሁን ለተከሰተው ነገር ሁሉ ተጠያቂዎቹ እነርሱ መሆናቸውንና እርሱ
Posted in Ethiopian News, Religion

ኑ፤ ኢየሩሳሌም እንሂድ!

click here for pdf‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘውና በ1590 ዓም የተጻፈው መጽሐፍ በገዳሙ የተፈጸሙ አስደናቂ የቅዱሳን ታሪኮች ተመዝግበውበታል፡፡ ከእነዚህ አንዱ ‹ኢየሩሳሌም እንሂድ› የሚለው ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩ የተፈጸመው በእጨጌ ዮሐንስ ከማ ዘመን [ከዐፄ ይስሐቅ (1407-1423) እስከ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ(1426-1469 )የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበረ የደብረ ሊባኖስ 7ኛ አበ ምኔት] ነው፡፡ በደብር (በደብረ ሊባኖስ) ውስጥ ስሙ ፍሬ ቡሩክ የተባለ ሰው ነበረ፡፡ አንድ ቀንም ወደ አንደ አረጋዊ ዘንድ ደረሰ፡፡ ፊቱንም ሻክሮና ወይቦ አገኘው፡፡ ያም ወንድም አረጋዊውን ሥጋው እንደዚህ የመነመነበትን ምክንያት ጠየቀው፡፡ አረጋዊውም ‹በላየ ላይ ምንም ሕመም የለም፤ ነገር ግን አንድ ነገር ያስጨንቀኛል፡፡ የመጸዳጃ ቤት የለኝም፡፡ በዚህም ምክንያት የት እሄዳለሁ ብዬ ምግብ ከመብላት እከለከላለሁ› አለው፡፡ ያም ወንድም ሰምቶ ወደ ቤቱ ሄደና ሲመሽ የሚወደውን ወንድም ጠርቶ ‹ና ኢየሩሳሌም እንሂድ› አለው፡፡ እርሱም ‹አስቀድመን ጸሎት ሳናደርግ፣ ለመንገድም ስንቅን ሳናዘጋጅ እንዴት ድንገት እንሄዳለን› አለና መለሰለት፡፡ ያም ወንድም ‹እንዲህ አትበል፤ ነገር ግን የምነግርህን ስማ፡፡ እነሆ የመጸዳጃ ቤቱ ሞልቶበት በረሃብ የሚሞት አንድ አረጋዊ አለ፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የበጎ ሰው ሽልማት አራተኛው መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ

ለሀገርና ለሕዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት አራተኛው መርሐ ግብር ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓም በይፋ ተጀምሯል፡፡የ2008 ዓ.ም ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› ዘርፎች  መምህርነት  ቅርስ እና ባሕል ሳይንስ  መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣንግድና ሥራ ፈጠራ ማኅበራዊ ጥናት  ስፖርት የበጎ አድራጎት ሥራ ኪነ ጥበብ - ( በድርሰት ዘርፍ ብቻ ሚድያ እና ጋዜጠኝነትየ2008 ዓ.ም ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› የጥቆማ መስፈርቶችጠቅላላ መስፈርቶችየሚጠቆሙ እጩ በጎ ሰዎች፡-በየተሰማሩበት ዘርፍ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ መልካም የሚሠሩ፣ ሀገራዊ ተልዕኳቸውን በብቃትና በልዩ ልዕልና የሚወጡ፣ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ለውጥ አምጭ ተግባር የፈጸሙና የሚፈጽሙ፤ በብዙ ሰዎች የማይደፈርን ተግባር በተነሣሽነት የከወኑ፣ ለድጋፍ ፈላጊ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነት ወስደው የሠሩ፣ የሀገሪቱ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባሕል፣ እንዲጠበቅ የሀገሪቱ ሥልጣኔ ከፍ ከፍ እንዲል የሠሩና የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን መሆን ይኖርባቸዋል፡፡የሚጠቆሙ እጩ በጎ ሰዎች፡-ሥራቸው ሀገራዊ ፋይዳ እና ለሌሎች አርአያነት ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተጠቋሚ በጎ ሰዎች ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሥነ ምግባር ደረጃ ያሟሉ እና አብዛኛው
Posted in Ethiopian News, Religion

‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› ማለት ሊቀር ነውን?

click here for pdfቅዱስ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን እንደራሴ ሹመት በተመለከተ ለመወያት የያዘው አጀንዳ የመንግሥት ተወካይ ባለበት እንዲታይ መወሰኑን ዛሬ ጠዋት ሰማን፡፡ ከብጹዐን ጳጳሳት በቀር ካህናትና ቆሞሳት እንኳን የማይገቡበት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማኝ ይሁን ኢአማኒ፣ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን የማይታወቅ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝበት መጋበዙ የደረስንበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳየን ነው፡፡ በአንድ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ወሳኝ አካል መሆኑን ስናስበው፤ በሌላ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚደረገው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው፤ ውሳኔውም በሐዋርያት ሥራ እንደተገለጠው ‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› የሚባልበት ነው(የሐዋ. 15፣29) የሚለውን ስናየው ‹የመንግሥት ተወካይ ይኑርልን› የሚለውን ውሳኔ ኢሃይማኖታዊ ነው ያሰኘዋል፡፡ ለአንድ የሲኖዶስ ጉባኤ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት አልበቃው ብሎ ነው የመንግሥትን ተወካይ የሚጋብዘው? ‹ሱባኤ ይዘን፣ ጸሎት አድርገን፤ አንድ ገዳም ወርደን፣ ከእግዚአብሔር ጋር መክረን› አይደለም ይሉን አባቶቻችን፡፡ ‹የመንግሥትን ተወካይ ጋብዘን› ነው ያሉን፡፡ እንዲያውም ቀኖናው የሊቀ ጳጳሳቱ(ፓትርያርኩ) ጉዳይ ሲታይ ‹በመቀመጫቸው መካከል አንድ ወንበር አስቀምጠው፣ ቅዱስ ወንጌሉን በዚያ ላይ አኑረው፣ ሊቀ
Posted in Ethiopian News, Religion

ሺአውያን

click here for pdfበፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2000 ዓም ጥቂት ዘመናት ቀደም ብለው የተወለዱትንና በአሁኑ ዘመን እስከ 30ዎቹ እድሜዎች ያሉትን ትውልዶች ሺአውያን(Millennials) ብለው ይጠሯቸዋል፡፡ በአሜሪካ ሻውያን(ሺአውያን) እጅግ የተጠኑና ብዙ የተወራላቸው ትውልዶች መሆናቸው ይነገራል፡፡ አንዳንዶችም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ውስጥ ተወልደው፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ውስጥ አድገው፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ውስጥ ለወግ ለማዕረግ የሚደርሱ ትውልድ ይሏቸዋል፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያና ትሥሥር መንደሮችን ሁሉ ባዳረሰበት፣ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ግለሰባዊ ተደራሽነትን በያዙበት፣ ወላጆች ለትምህርት ይበልጥ ትኩረት በሰጡበት ዘመን የተፈጠሩ ትውልዶች በመሆናቸው እነዚህ ነገሮች በአስተሳሰባቸው፣ አነዋወር ዘያቸውና ፍልስፍናዎቻቸው ላይ ተጽዕኖ አሳድረውባቸዋል ተብሎ ይገመታል፡፡ የሴቶች፣ የሕጻናት፣ የእንስሳት፣ የተመሳሳይ ጾታ፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የአካል ጉዳተኞች፣ ጉዳዮች በሚቀነቀኑበት ዘመን የሚገኙ ናቸውና የእነዚህ ነጸብራቅ ይታይባቸዋል፡፡ ዓለም ተያያዥና በቀላሉ ተደራሽ በሆነችበት የሉላዊነት ወቅትም ስለሚገኙ ክፉውንም ሆነ ደጉን የመካፈል ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ልጅን ተገንዝቦና አስገንዝቦ እንጂ ጠብቆ ማዳን የማይቻልበት ዘመን ነው፡፡  በሀገራችን ጥናት ባይደረግም በምዕራቡ ዓለም ግን ሻውያን አጥለቅላቂው ትውልድ ተብሎላቸዋል፡፡ በአሜሪካና በእንግሊዝ የተደረጉ ጥናቶች ሻውያን ከቀደምት ትውልዶች ይልቅ ብዛትና ስብጥር
Posted in Ethiopian News, Religion

ሶስና በኢትዮጵያ

click here for pdfበመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ የፍርድ ታሪኮች አንዱ የሶስና ፍርድ ነው፡፡ እሥራኤል ወደ ባቢሎን ተማርከው በነበሩ ጊዜ ኢዮአቄም እና ሶስና የተባሉ ባልና ሚስቶችም ተማርከው ነበር፡፡ የባቢሎን ሥርዓተ መንግሥት ከየሀገሩ የተማረኩ ፈላስያን የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፈቅዶ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የራሳቸውን ፍርድ ቤቶች አቋቁመው የራሳቸውን ጉዳዮች ይዳኙ ነበር፡፡ በዚህ የእሥራኤል ዳኝነት አንድ ጉዳይ ቀረበ፡፡ሶስና የምትባል በመልኳ ይህ ቀረሽ የማትባለው የኢዮአቄም ባለቤት በሞት በሚያስቀጣው የአመንዝራነት ወንጀል ተከሰሰች፡፡ በዚያ ዘመን በሀብት ሻል ያሉ የባቢሎን ሰዎች ቤታቸውን በኤፍራጥስ ወንዝ አቅራቢያ ሠርተው በወንዙ ዳር በሚገኙት የአትክልት ሥፍራዎች ውስጥ የገላ መታጠቢያዎችንና የመዋኛ ገንዳዎችን ያዘጋጁ ነበር፡፡ እነዚህ የመናፈሻ ሥፍራዎች በአጥር የታጠሩ ሆነው የራሳቸው በር ነበራቸው፡፡ ኢዮአቄምና ሶስና  ከፈላስያኑ ወገን በሀብትም በክብርም ላቅ ያሉ ስለነበሩ ይህ ሀብት ነበራቸው፡፡ ሀብት ክብር ብቻ ሳይሆን መዘዝም ያመጣል፡፡ በኢዮአቄም ቤት ለችሮታም፣ ለመጠለልም፣ ከባቢሎን ባለ ሥልጣናት ለመገናኘትም እያሉ የሚሰበሰቡ ብዙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ መካከል ሁለቱ የተከበሩ የሕዝብ መምህራን ናቸው፡፡ ሕዝቡ በዐዋቂነታቸውና
Posted in Ethiopian News, Religion

‹ፌስዳቢ›

እነሆ በሀገራችን አዲስ ጎሳ መፈጠሩ ተሰማ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ሰዎች የጎሳ ማንነታቸውን ለማስከበር፣ ባህላቸውንና ታሪካቸውን ለመግለጥ ሲታገሉ ነበር የምናየው፡፡ ታሪክ የማያልቅባት ኢትዮጵያ የነባር ጎሳዎችን መብት ማስከበር ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ጎሳዎችንም መመሥረት አለብኝ ብላለች፡፡ በርግጥ በሕገ መንግሥቱ ላይ ነባር ጎሳዎችን በተመለከተ እንጂ አዲስ ጎሳ እንዴት እንደሚመሠረት፣ ቢመሠረትም እንዴት ዕውቅና እንደሚያገኝ የተጻፈ ነገር የለም፡፡ ይሄ አዲስ ጎሳ ‹ፌስዳቢ‹ ይባላል፡፡ ትርጉሙም ‹በፌስ ቡክ በኩል ተሳዳቢ› ማለት ነው ሲሉ የጎሳው ዋና መሪ ፌስ ቡከኛ ጨርግደው በቀደም ዕለት መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ የዚህ ጎሳ መገኛ ክልል ‹ፌስቡክ› የተባለው አካባቢ ሲሆን የጎሳው ቋንቋ  ደግሞ ‹ስድብ› ይባላል፡፡ ‹ስድብ› በተባለው ቋንቋ ወግ መሠረት አማርኛን ሆነ ትግርኛን፣ ኦሮምኛንም ሆነ ሶማልኛን፣ እንግሊዝኛንም ሆነ ዐረብኛን መጠቀም ይቻላል፡፡ ዋናው የቋንቋው ሰዋሰው ሕግ የሚያዘው በእነዚህ ሁሉ ፊደላትም ሆነ ቋንቋዎች ‹ስድብ› መተላለፉን ነው፡፡ ‹ስድብ› የተባለው ይህ የ‹ፌስዳቢዎች› ቋንቋ አምስት አካባቢያዊ ዘዬዎች እንዳሉት በጥናት ተረጋግጧል፡፡ ልክ አማርኛ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የሸዋ፣ የወሎ እየተባለ በዘዬ እንደሚከፈለው ማለት ነው፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ሕይወት- ሌስተርና ቼልሲ

click here for pdfይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ የጥላውን ያህል ቅርብ ነው፡፡ ‹እኖራለሁ ብለህ ሥራ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም? መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣ ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣ ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ? ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡ እነ እገሌ ካሉ፣ እነ እገሌ ቦታውን ከያዙ፣ እነ እገሌ እዚያ ላይ ከወጡ፣ በቃ አይሳካልኝም አትበል፡፡ ሌስተርን ያየ እንዲህ አይልም፡፡ ለወትሮው የእንግሊዝ እግር ኳስ ማንቸስተር ዮናይትድና ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሴናልና ቼልሲ በእግራቸው ርግጥ፣ በእጃቸው ጭብጥ አድርገው የሚዘውሩት ይመስል ነበር፡፡ መቼም ዋንጫውን ከእነዚህ ከአራቱ አንዱ እንጂ ሌላው ይቀምሰዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር፡፡ ‹ሙሴ በሩቁ ከነዓንን አያት እንጂ አልወረሳትም›
Posted in Ethiopian News, Religion

ሥርዓተ ዕለተ ስቅለት ዘደብረ ሊባኖስ

click here for pdfከ500 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕለተ ስቅለትን እንዴት ታከብር እንደነበር በመጠኑ ሊያሳዩን ከሚችሉ መዛግብት አንዱ ‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘው መዝገብ ነው፡፡ ዜና ደብረ ሊባኖስ በ1586 ዓም የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ አምስት ነገሮችን ይዟል፡፡ የደብረ ሊባኖስን ታሪክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት እስከ ዐፄ ሰርጸ ድንግል ዘመን፤ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጥንታዊ ሥርዓተ ማኅበር፤ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጥንታዊ ሥርዓተ ጸሎት፤ በመጽሐፈ መነኮሳት መልክ የተጻፈ የልዩ ልዩ መነኮሳት አስደናቂ መንፈሳዊ ሕይወት እና በዐፄ ሰርጸ ድንግል ዘመን የተፈጸሙ አንዳንድ ሀገራዊ ኩነቶች፡፡ እስካሁን በተደረገው ጥናት ዜና ደብረ ሊባኖስ ሦስት ቅጅዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው በፓሪስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት፣ በአንቶንዮ ዲአባዲ ስብስብ ውስጥ በቁጥር 108 ተመዝግቦ የሚገኘው፤ ሁለተኛው ከደብረ ጽጌ ማርያም የተገኘውና በማይክሮ ፊልም ተነሥቶ በEMML 7346 ተመዝግቦ የሚገኘው፤ ሦስተኛው ደግሞ በደቡብ ጎንደር ማኅደረ ማርያም ደብር የሚገኘው ቅጅ ነው፡፡ ከሦስቱም ቁልጭ ብሎ የሚነበበው የማኅደረ ማርያሙ ቅጅ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከምናገኛቸው ጉዳዮች አንዱ በቤተ ክርስቲያን በዓላት
Posted in Ethiopian News, Religion

የሰርቆ አደሮች ስብሰባ

clicke here for pdfሰሞኑን በአዲስ አበባ አንድ ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ሌቦች ስብሰባ አድርገው ነበር፡፡ የስብሰባው መሪ ቃል ‹የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሌቦች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?› የሚል ነው፡፡ ስብሰባው እንደተጀመረ አንደኛው የታወቀ ሌባ እጁን አወጣና ‹መፈክሩ ላይ የተጠቀስንበት ስም ትክክል አይደለም፡፡ ገጽታችንን የሚያበላሽ ነው› ሲል አስተያየት ሰጠ፡፡ ጭብጨባ አዳራሹን ሞላው፡፡‹ታድያ ምን ይሁን፤ መቼም ሌባ መሆናችን ርግጥ ነው› አሉ ሰብሳቢው፡፡‹ጠየም አድርጉት፤ እንደ ባለጌ ጥፊ ድርግም አይደረግም› አሉ ሌላ አስተያየት ሰጭ፡፡‹እኮ ምን እንባል› አሉ ሰብሳቢው፡፡‹ሌሎቹ ሠርቶ አደር፣ አርብቶ አደር፣ ወቶ አደር፣አርሶ አደር ከተባሉ እኛም ‹ነጥቆ አደር› ነው መባል ያለብን› ይኼው ጸደቀ፡፡ ‹የሕዝቡ ምሬት ጨምሯል፡፡ ሕዝቡ በሌቦች መማረሩን በተደጋጋሚ እየገለጠ ነው፡፡ አንድ ቀን መሣሪያ ቢያጣ እንኳን አካፋና ዶማ ይዞ መነሣቱ አይቀርም፡፡ ከተንተከተከ እሳቱ ጨምሮክዳኑን ይገፋል የፈላበት ሽሮሲባል አልሰማችሁም፡፡ ያን ጊዜ ደግሞ ለሁላችን መግቢያ ቀዳዳው ጠባብ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛው ራሳችን መፍትሔ ማምጣት አለብን› አሉ ሰብሳቢው፡፡ ‹ስንናገር ለይተን መናገር አለብን፡፡ ሌባ
Posted in Ethiopian News, Religion

ማኅደረ ማርያም – ማኅደረ ታሪክ

click here for pdf ማኅደረ ማርያምሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በፋርጣ ወረዳ፣ ከደብረ ታቦር 28 ኪሎ ሜት ርቀት ላይ፣ በ2450 ሜትር ከፍታ ከባሕር ወለል በላይ፣ በቧኢት ተራራ ላይ ወደተተከለቺው ማኅደረ ማርያም ደብር ተጉዤ ነበር፡፡ የጉዞዬ ዋና ዓላማ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ለምሠራው ጥናት ተጨማሪ መረጃዎችን ፍለጋ ነው፡፡ ማኅደረ ማርያም ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ጋር ቅርበት ከነበራቸው የጎንደር አድባራት አንዷ ናት፡፡ ሁለት እጨጌዎችንም አበርክታለች፡፡ ከግራኝ ወረራ በኋላ ወዲያው ከተተከሉ አድባራት አንዷ በመሆኗ ከግራኝ በፊትና በኋላ ላለው የሀገራችን ታሪክ የመገናኛ ድልድይ ናት፡፡በ1572 ዓም ዐፄ ሰርጸ ድንግል የመንግሥቱን መቀመጫ ከሸዋ ወደ ጎንደር ወስዶ የእንፍራንዝን ከተማ ቆረቆረ፡፡ በ1580 ዓም ደግሞ ወደ እስቴ ጉዞ አደረገ፡፡ በመንገዱ ላይ ጉማራ የተባለው ወንዝ ሞልቶ አዞ ሲዋኝበት ተመለከተ፡፡ በዚህም የተነሣ ከማኅደረ ማርያም በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት አርቦ ከተማን ከተመ፡፡ ባለቤቱ እቴጌ ማርይም ሥና ግን እነ አዝማች ዘሥላሴንና አዛዥ ዓምዴን ይዛ ወደ በጌምድር ተሻገረች፡፡ ጉዞ ማኅደረ ማርያምእቴጌ ማርያም ሥና ወደ በጌምድር
Posted in Ethiopian News, Religion

አራቱ የጠባይ እርከኖች

click here for pdfየሰው ልጅ አራት የጠባይ እርከኖች አሉት ይላሉ ትውፊታውያን ሊቃውንት፡፡ በነባሩ የኢትዮጵያ ትምህርት መሠረት ጠባይና ባሕርይ ይለያያሉ፡፡ ‹ባሕርይ› ማንነት ነው፡፡ በፍጥረትህ ታገኘዋለህ፡፡ ይዘህው ትኖራለህ፡፡ አትለውጠውም፤ አታሻሽለውም፡፡ ለምሳሌ ሰውነት ባሕርይ ነው፡፡ ሰው መሆንን፣ እንስሳ ወይም ዛፍ ወይም ውኃ በመሆን አትለውጠውም፡፡ ‹ጠባይ› ደግሞ በተፈጥሮ፣ በልምድ፣ በዕውቀት፣ በውርስ፣ የሚገኝ አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ ልማድ፣ አኳኋን፣ አነዋወር፣ አመል ነው፡፡ በትምህርት የጠባይ ለውጥ እንጂ የባሕርይ ለውጥ አይመጣም የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ የባሕርይ ለውጥ ማለት ጨርሶ ማንነትን መለወጥ ማለት ነውና፡፡ ሰው ምንም እንኳ አንድ ዓይነት ሆኖ ቢፈጠር በትምህርቱ፣ በባህሉ፣ በልምዱ፣ በልምምዱ፣ በእምነቱ፣ በፍላጎቱና በምርጫው የተነሣ በተለያዩ የጠባይ ደረጃዎች ውስጥ ሊኖር ይችላል፡፡ እነዚህ የጠባይ ደረጃዎች አውሬነት፣ እንስሳነት፣ ሰውነትና መልአክነት ናቸው፡፡ ከአንደኛው ወደ ሌላኛው ማደግና መሻሻል የሚቻለውም አንደኛውን ተረድቶ፣ አርሞና ገርቶ ለሌላኛው ተገዥ በማድረግ ነው፡፡ ዝቅተኛው የጠባይ ደረጃ አውሬነት ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ መልአክነት ነው፡፡ የታችኛውን ሳይገሩና ሳይገዙ ቀጥሎ ያለውን ጠባይ ገንዘብ ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች ለጊዜው እንደ ተዋናይ ይጫወቱ ይሆናል፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ!

click here for pdf ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው፡፡ እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ፡፡ አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበታትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማኅበረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ አይሁድ ሀገር ፍለጋ ከሺ ዓመታት በላይ መኳተን አልነበረባቸውም፡፡ በአውሮፓ የሚኖሩት ጂፕሲዎች የታወቀ ማኅበረሰብ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሀገር የላቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ጂፕሲ የሚባል ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ጂፕሲ የሚባል ሀገርም ይኖር ነበር፡፡ ግን የለም፡፡በአሜሪካ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ‹በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን› የምትባል ሀገር ግን የለቺም፡፡ 1.3 ሚሊዮን የሚደረሱ ግሪኮች በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡ ‹የአሜሪካ ግሪኮች› የምትባል ሀገር ግን የለችም፡፡ ‹ግሪክ ሲሠራ አሜሪካ ይኖራል፣ ሲያረጅ ግሪክ ይጦራል› የተባለው ሀገር ሰው ብቻ ስላልሆነ ነው፡፡  ሰዎች ተሰብስበው ሀገር ሊመሠርቱ አይችሉም፡፡ በየሀገሩ የተሰበሰቡ ማኅበረሰቦች ‹ኮሙኒቲ› ይባላሉ እንጂ ሀገር አይባሉም፡፡ ሀገር ሀገር ለመሆንና ለመባል ከሰው በተጨማሪ የምትፈልገው ብዙ ነገር
Posted in Ethiopian News, Religion

ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት

click here for pdf‹የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ› ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር፡፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅስያ የአንዲት ክርስቲያን ምእመንን መሬት ወስዳ ባሰቃየቻት ጊዜ ለተግሣጽ የተናገረው ነው፡፡ እንዳለው አልቀረም አውዶቅስያ ባደረሰችበት መከራ ተግዞ በዚያው ሞትን ተቀብሏል፡፡ እውነተኛ አባት ስለ በጎቹ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል እንጂ በጎቹን ለራሱ ክብርና ጥቅም ሲል አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ፓትርያርክ ማለት በግሪክ ‹ታላቅ አባት› ማለት ነው፡፡ የታላቅ አባት ተግባር የልጆቹን ሥራ ማፍረስ አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን መክሰስ አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን እንጂ አባት አያስፈልግም፡፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ጠርቶ መውቀስ እንጂ በር መዝጋት አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፡፡ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ማቀፍ እንጂ ማባረር አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን አለ፡፡ ፓትርያርኩ እንጨት የሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደዋዛ በአንድ ሙሰኛ ሲነጠቅ ተኝተዋል፤ በመሐል ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሠሩ ሕንጻዎች በጎጆ ቤት ዋጋ በሙስና
Posted in Ethiopian News, Religion

ሦስቱ ወዳጆች

click here for pdfአንድ ሊቅ እንዲህ ይመክሩ ነበር፡፡ ሰው ለዕውቀት የተሰጠ፣ ለትግል የሠለጠ፣ ለመሪነትም የተመረጠ ይሆን ዘንድ ከሦስት ዓይነት ወዳጆች ጋር መዋል አለበት ይላሉ፡፡ አንድም ከእርሱ ከሚበልጡ፣ አንድም ከእርሱ ከሚስተካከሉ፣ አንድም ደግሞ ከእርሱ ከሚያነሱ፡፡ለአንድ ሰው እነዚህ ሦስት ዓይነት ወዳጆች ወሳኞች ናቸው፡፡ ከሦስቱ አንዱ ሲቀር፣ ወይም ደግሞ ከሦስቱ የተወሰኑት ሲበዙ ችግር አለው፡፡ የሰውዬው የአእምሮ ጤንነት ይጓደላል ወይም ይዛባል፡፡ የሚኖረው ኑሮ፣ የሚጨብጠው ዕውቀት፣ የሚሰጠው ብያኔና የሚመራበት መርሕ ርቱዕ አይሆንም፡፡ ድቀተ ልቡና ያገኘዋል፡፡ ድቀተ ልቡና ማለት ልቡና የትክክለኛነትን መርሕ ስቶ ሲወድቅ ነው፡፡ ልቡና ለስሜትና ለግልብነት ተሸንፎ፣ ከ‹ፍትርት› ጎዳና ሲወጣ ድቀት አገኘው ይባላል፡፡ ‹ፍትርት› ማለትም ማመዛዘንን ገንዘቡ ያደረገ ቀና የሥልጡንነት አካሄድ ነው፡፡ ሰው ከእርሱ ከሚበልጡት ጋር የዋለ እንደሆነ ከልምዳቸው ይማራል፣ ከብስለታቸው ይቀስማል፣ ከእድሜ ጥጋባቸው ይቋደሳል፡፡ የሚደርስበትን ነገ ዛሬ አሻግሮ ለማየት ይጠቅመዋል፡፡  ዛሬ ላይ ሆኖም የነገውን ለማቀድ ያስችለዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በእድሜም በዕውቀትም፣ በልምድም ከእርሱ የሚበልጡ ናቸውና ቢያጠፋ ለመገሠጽ፣ ቢሳሳት መንገድ ለማሳየት፣ ቢጎድልበት ለመሙላት፣ አያፍሩትም አይፈሩትም፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

በዓሉ ግርማ- ሕይወቱና ሥራዎቹ

በእንዳለ ጌታ ከበደየካቲት 2008 ዓምዋጋ፡- 120 ብር clicke here for pdfእንዳለ ጌታ ከበደ በዓሉ ግርማን እንደ ጌታ ነፍስ ዘርቶ እንደደአልዓዛር ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ከትውልድ ቀየው ጀምሮ ‹እስከ መቃብሩ› ደረስ እየተከተለ፡፡ መዛግብቱን ያገላብጣል፣ እናውቃለን የሚሉትን ይጠይቃል፣ ያውቃሉ ብሎ የገመታቸውን ያናግራል፤ ሄዶበታል፣ ውሎበታል፣ ገብቶበታል፣ ወጥቶበታል የተባለው ቦታ ድረስ እየገባ ‹ማጀት በጎረሰው፣ ደጃፍ በመለሰው› ያገኘውን ያህል ይነግረናል፡፡ ሰው የሚያውቀውን ሲጽፍ፣ የሚጽፈውንም ሲያውቅ እንዴት የሚያጠግብ እንጀራ እንደሚጋግር በእንዳለ ጌታ መጽሐፍ ልኬቱን እናገኘዋለን፡፡ ከሱጴ እስከ ደርግ እሥር ቤት፣ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ፣ ከአሠሪ እስከ አሣሪ፣ ከወዳጅ እስከ አሳዳጅ ድረስ መረጃ ፍለጋ የኳተነው ‹ለሞተው› በዓሉ ነፍስ ሊዘራ እንጂ ለሌላ ነገር ነው ብሎ ለማመን እጅግ ጅል መሆንን ይጠይቃል፡፡  መጽሐፉ በቀብር ላይ እንደሚነበብ የሕይወት ታሪክ ሙቀት አልባ አይደለም፡፡ ድርቀት የተለየው፣ወዝ የተዋሐደው እንጂ፡፡ እንደ አንድ የሀገራችን ታሪክ ጠገብ ሽማግሌ ሆኖ ያወጋናል፡፡ ቃለ መጠይቅ ያደረገላቸውን ሰዎች እንደ አጃቢ ገጸ ባሕርይ ያስመስላቸዋል፡፡ በዓሉን ደግሞ እንደ ዋናው ገጸ ባሕርይ፡፡ ‹ተናደደ፣ ጠረጲዛ መታ፣ ፊቱን ጥቁር
Posted in Ethiopian News, Religion

ጆሮና ቀንድ

click here for pdf አንድ ጥጃ የሚያሳድግሰው ነበር፡፡ ጥጃውን ሲፈልግ ጆሮውን ይጎትተዋል፣ ሲፈልግ በዱላ ይዠልጠዋል፣ ሲፈልግ ጨው እያላሰ ይስበዋል፣ ሲፈልግ ደግሞ በገመድ አሥሮ ያስከትለዋል፡፡ በዚህ መንገድ ሄዶ ጥጃው አደገና  ወይፈን ሆኖ ቀንድ አበቀለ፡፡ የጥጃውም ባለቤት እንደለመደው በዱላ ሊመታው፣ ጆሮውን ሊጎትተው፣ በዱላም ሊዠልጠው ተነሣ፡፡ ያን ጊዜ ጥጃው አፍንጫውን ወደ መሬት አስነክቶ አኩረፈረፈና እንደ ስፔን በሬ ተወርውሮ በቀንዱ ወጋው፡፡ ሰውየውም ወገቡን ይዞ እየተጎተተ ቤቱ ደረሰ፡፡ ታሞ ሊጠይቁት የሄዱ ጎረቤቱ የሆነው ነገር ሰሙና ‹ወዳጄ የጆሮና የቀንድን ዘመን እንዴት መለየት አቃተህ?› አሉት፡፡ ‹የጆሮና የቀንድ ዘመን ምንድን ነው?› አላቸው ወገቡን አሥሮ እየተገላበጠ፡፡ ‹በመጀመሪያ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ በለጠው› ሲባል አልሰማህም፡፡ ጥጃው መጀመሪያ ጆሮ ብቻ ስለነበረው ያልከውን ሁሉ ይሰማህ፣ ይታዘዝህ ነበር፤ ብትመታው ይችላል፣ ብትጎትተው ይከተላል፣ ብታሥረው ይታሠራል፡፡ ጆሮ ብቻ ስለነበረው መስማት ብቻ ነበር የሚችለው፡፡ በኋላ ግን ቀንድ አበቀለ፡፡ ቀንድ ካበቀለ በኋላ እንደ ድሮው እጎትተዋለሁ ብትል አይሆንም፡፡ አሁን ከተስማማው ይቀበልሃል፤ ካልተስማማው ግን መዋጋት ይጀምራል፡፡ አሁን አንተ
Posted in Ethiopian News, Religion

ሰርግና ሰዓት

click here for pdfለጊዜ ያለንን አነስተኛ ግምት አጉልተው ከሚያሳብቁብን ክዋኔዎች አንዱ ሰርግ ነው፡፡ ሰርገኛ በጊዜው ከመጣ ትዳሩ ይፈርሳል የተባለ ይመስል አንድና ሁለት ሰዓት ዘግይቶ መምጣት ይቅርታም የማያስጠይቅ ልማድ ሆኗል፡፡ በሰዓት ተለክቶ በሚከፈልበት በምዕራቡ ዓለም የሚኖሩ የሀገሬ ልጆች እንኳን ‹የዘሬን ያንዘርዝረኝ› ብለው ሁለት ሰዓት ካላረፈዱ ያገቡ አይመሰስላቸውም፡፡ አብረዋቸው የሚሠሩ የሌላ ሀገር ዜጎችንና ኢትዮጵያውያንን የሚጋብዙበት ሁለት ዓይነት የጥሪ ካርድ እንዲያሳትሙ ይገደዳሉ፡፡ የሐበሻና የፈረንጅ፡፡ የፈረንጁ ካርድ ከሐበሻው ካርድ ሁለት ሰዓት ዘግይቶ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ሰርጉ ላይ ሁለት ዓይነት ማርፈዶች ናቸው የሚፎካከሩት፡፡ በአንድ በኩል ስድስት ሰዓት የተጠራው ሰርገኛ ሁለት ሰዓት ዘግይቶ ስምንት ሰዓት ላይ ሲመጣ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ስድስት ሰዓት የጠሩት ሙሽሮች ቢያንስ ሦስት ሰዓት ዘግይተው ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይመጣሉ፡፡ አርፍዶ የመጣው ሰርገኛም፣ አስረፍደው የመጡት ሙሽሮችም በረፈደ ሰዓት በመጀመራቸው ምንም ሳይሰማቸው አዳራሹን በእልልታ ያቀልጡታል፡፡ በርግጥ ለአንዳንድ ሰው ጊዜ ማለት ወር፣ ከዚያም ካለፈ ቀን ማለት ነው፡፡ ጊዜ ማለት ሰዓትና ደቂቃ ያልሆነለት ሰው ብዙ ነው፡፡ የኛ ሀገር ሰዓትና
Posted in Ethiopian News, Religion

አደጋውና ማስጠንቀቂያው

click here for pdfከሁለት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሆድ ዕቃ የመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፡፡ አየር መንገዱ ያስመረቀውን ዘመናዊ ኮሌጅ በማስመልከት የአየር መንገዱን ነገረ ሥራ እንድንጎበኝ ተጋብዘን ነበር፡፡ የጥገና ቦታውን፣ የካርጎ ማዕከሉን፣ አዳዲስ እያስፋፋቸው የሚገኙ የካርጎና የጥገና ቦታዎችን አይተናል፡፡ የአየር መንገዱን የሆድ ዕቃ ለሚመለከት ሰው ከጥንት ጀምሮ እየካበት፣ እየተሳለጠና እየሠለጠነ የመጣውን ይህን ታላቅ ሀገራዊ ድርጅት እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ ለመረዳት ያስችለዋል፡፡ እንዲያውም እኛ ሀገር እንደ አበሻ መደኃኒት ሁሉም ነገር ምሥጢር ስለሚሆን ነው እንጂ ልጆቻችን በጉብኝት ፕሮግራሞች የአየር መንገዱን የሆድ ዕቃ የማየት ዕድሉ ቢኖራቸው ኖሮ አየር መንገዱንም እንዲወዱ የፈጠራ ፍልጎታቸውም እንዲጨምር ያደርገው ነበር፡፡  በጥገና ክፍሉ የጀመረው ጉብኝት በካርጎ ክፍሉ በኩል አድርጎ በአዳዲስ የማስፋፋያ ፕሮጀክቶቹ በኩል ሲጠናቀቅ ዓይኔ አንድ ነገር ላይ ዐረፈ፡፡ ነገሩ የተጻፈው በአየር መንገዱ የጥገና ክፍል ግድግዳ ላይ ነው፡፡ ለእኔ ከጥገና መሣሪያዎች፣ ከጠጋኞቹ ብቃትና ለጥገና ብቃቱ የተለያዩ ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ከሰጡት ዕውቅና ባልተናነሰ የሳበኝ በየግድግዳው የተለጠፉት የደኅንነት ማሳሰቢያዎቹ ናቸው፡፡  ‹አደጋውን ሪፖርት
Posted in Ethiopian News, Religion

…መቼ ተነሱና የወዳደቁት…" ጂጂ

ግልጽ ደብዳቤ ለመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት(ያሬድ ሹመቴ)  ይድረስ ለ ዶ/ርክንደያ ገ/ህይወትለጤናዎ እንደምን አሉ?ክቡርነትዎ በአካል ተያይተን አናውቅም። ከስምዎ እና ከስራ ድርሻዋ ውጪ ስለርስዎ ምንም የማውቀው ነገር የለኝም። ነገር ግን ወቀሳ ለማቅረብ ይህንን ደብዳቤ ስጽፍልዎ እርስዎን ባለማወቄ ምክንያት ስህተት ሰርቼ ከአቅምዎ እና ጥሩነትዎ ውጪ የሆነ አስቀያሚ ነገር ከጽሁፌ ቢወጣ በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ።እርስዎ በሚያስተዳድሩት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ስለሚገኘው አንድ ታሪካዊ ቦታ ላስተዋውቅዎ ነው። እርስዎ አጥሩን ለማሳጠር የወጣውን ወጪ እና የጊቢውን ስፋት በካሬ ሜትር ማወቅዎን እንጂ ውስጡ ስላለው እንቁ ታሪክ እንደማያውቁ እጠራጠራለሁ። ስለዚህም በእርግጠኝነትና በድፍረት ታሪኩን ላስተዋውቅዎ ወድጃለሁ። ምክንያቱ ደግሞ ታላቁን ታሪክ የሚያውቁ ቢሆን ኖሮ የቦታውን አያያዝ ያሳምሩት ነበርና ነው።እንዳየሱስ በተለያዩ የታሪክ ፀሀፊያን ዘንድ ከዓድዋ ድል ጋር ስሙ በደማቅ ሁኔታ የሚነሳው መቀሌ የእንዳየሱስ ምሽግ ነው።ወራሪው የጣልያን መንግስት በ1888ዓ.ም ለአመታትሲቋምጥባት የኖረችውን ኢትዮጵያ በወረረበት ወቅት ሰሜናዊውን ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛቱ ውስጥ እያደረገ ወደታች በመግፋት እስከ አሸንጌ ሀይቅ ድረስ ግዛቱን አሰፋ። ይህንንም ወረራ በመመከት ህዝባቸው አንድ ሆኖ
Posted in Ethiopian News, Religion

የጋማ ከብቶች

click here for pdfበቀደም ድሬዳዋ ላይ ዓሣ ዘነበ ብለን ከአንድ ወዳጄ ጋር ስናወራ ‹ባክህ ይሄ እንኳን የጋማ ከብቶች ወሬ ነው› አለኝ፡፡ እኔም አነጋገሩ ገርሞኝ ‹የጋማ ከብቶች ደግሞ እነማን ናቸው› ስል ጠየቅኩት፡፡‹የማያመነዥኩ ናቸዋ› አለና አሳጠረው፡፡‹እኮ ከድሬዳዋ ዓሣ ጋር ምን ያገናኘዋል›  ‹እኔ ድሬዳዋ እንኳን ዓሣ የዓሣ ፋብሪካ ቢወርድላት ችግር የለብኝም፡፡ ለምን፣ እንዴት፣ መቼ፣ ማን፣ ፊትና ኋላ፣ ቀኝና ግራ የሚባሉ ነገሮች ፋሽናቸው አለፈ እንዴ? አንድ ሚዲያ ‹ዓሣ ዘነበ› ከማለቱ በፊት በጋዜጠኛውና በሚዲያ ኃላፊዎች ላይ ‹ማመዛዘን› የሚባለው ነገር መዝነብ ነበረበት፡፡ ያንን የዘገበ ዘጋቢ ዓሣ ሊያዘንብ የሚችል ታሪካዊ፣ ሳይንሳዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ አየር ንብረታዊ፣ ሌላም ምክንያት መኖር አለመኖሩን ሳያጣራ፣ በየቦታው ተዘዋውሮ ሳያረጋግጥ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በኅሊናው መዝኖ ከግምት በላይ ሳያልፍ፣ እንዴት ለዘገባ ያበቃዋል፡፡ ይኼ የጋማ ከብትነት ይባላል፡፡ የጋማ ከብት ይበላል ግን አያመነዥክም፡፡ ያገኘውን መዋጥ ብቻ ነው፡፡ እስኪ የቀንድ ከብቶችን ተመልከት ቀን የበሉትን ማታ ጋደም ብለው በጽሞና ሲያመነዥኩት ታዳምጣለህ፡፡ ይፈጩታል፣ ይሰልቁታል፣ ያጣጥሙታል፣ ያወጡታል፣ ያወርዱታል፡፡ አንዴ ገባ ብለው እንዲሁ አይተውትም፡፡ ፊውዝ
Posted in Ethiopian News, Religion

መኪና አሳዳጅ ውሾች

አንድ የአፍሪካ የሽምቅ ውጊያ መሪ ለብዙ ዓመታት በሽምቅ ውጊያ ታግሎ ነባሩን መንግሥት ካስወገደ በኋላ ለ12 ዓመታት ሀገሪቱን መራ፡፡ ሕዝቡ በሽምቅ ተዋጊነቱ ጊዜ የወደደውን ያህል በመንግሥትነቱ ጊዜ ሊወደው አልቻለም፡፡ ሲመጣ በጭብጨባና በሆታ ተቀበለው፣ ሲውል ሲያድር እያዘነበት ሄደ፣ ሲቆይ ተቀየመው፣ ሲሰነብት ተቃወመው፣ ሲከርምም ዐመፀበትና ከሥልጣኑ አባረረው፡፡ ‹ከሽምቅ ውጊያ በኋላ› After ‹Guerrilla fighting› የተሰኘውን መጽሐፉን ሲጽፍ ከሀገሩ ተባርሮ በሰው ሀገር ያገኘው ናይጄርያዊው ደራሲ ቶማስ ኙዌንጌ ስሙን እንደማይጠቅስ ቃል ገብቶለት አነጋግሮት ነበር፡፡ የሽምቅ ውጊያ መሪው ‹ሆ› ብሎ በእልልታ የተቀበለው ሕዝብ ‹ሂድ› ብሎ በቁጣ ለምን እንዳባረረው ሲገልጥለት እንዲህ ነበር ያለው፡፡‹የነበረውን መንግሥት ጥለን ሥልጣን ለማግኘት ታግለናል፡፡ ሕዝብን ከጭቆና ነጻ ለማውጣት፣ ፍትሕና እኩልነትንም ለማስከበር ታግለናል፡፡ አሁን ሳስበው የተዘጋጀነው እስከ ቤተ መንግሥቱ ላለው ጉዞ ነበር፡፡ ቤተ መንግሥት ስንገባ ምን ማድረግ እንዳለብን በቅጡ አላሰብንበትም፡፡ የነበረውን ስለ ማስወገድ እንጂ የተሻለ እንዴት እንደምናመጣ በደንብ አልሠራንም፡፡ ቤተ መንግሥቱን ከውጭ ስታየውና ውስጡ ሆነህ ስትኖርበት ይለያያል፡፡ ሥልጠኑን ለማግኘት ስትታገልና ስታገኘው ልዩነት አለው፡፡ መሬት ላይ
Posted in Ethiopian News, Religion

የደጃች ውቤ ልቅሶ

click here for pdfዐፄ ቴዎድሮስ በበጌምድር ማንም ለሞተ ዘመዱ እንዳያለቅስ የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ‹ሰው ሁሉ ዕንባውን ያጠጣ ነበር፡፡› በዚህ መካከል ደጃች ውቤ ሞቱና ለእቴጌ ጥሩ ወርቅ ወደ መቅደላ መርዶ ተላከ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም ሕዝቡን ‹ለደጃች ውቤ አልቅሱልኝ› ብለው አዘዙ፡፡ ሰውም ሁሉ ዘመዱ ሲሞት የቀረበት ልቅሶ ያን ጊዜ ወጣለት፡፡ ይህንን ያየች የበጌምድር አልቃሽየኔታ ደጅ አዝማች ሁልጊዜ ደግነትዛሬ እንኳን ለድኻው ዕንባ አስተረፉለትብላ ገጠመች ይባላል፡፡ ያን ቀን በበጌምድር ወጥቶ የማያውቅ ሰው አደባባይ ወጥቶ፣ ተለቅሶ የማያልቅ ልቅሶ ተለቀሰ ይባላል፡፡ ከወጣው በጌምድሬ መካከል ደጃች ውቤን የሚያውቃቸው፣ ለደጃች ውቤም ያለቀሰላቸው ጥቂት ነው አሉ፡፡ አብዛኛው ሰው ያለቀሰው ከዚህ በፊት ለሞተውና ተከልክሎ ሳያለቅስለት ለቀረው ዘመዱ ነበር፡፡ በየማርገጃው የወረደው ሙሾ ደጃች ውቤን ከሚያስታውስ ይልቅ ቴዎድሮስን የሚወቅሰው ይበዛ ነበር አሉ፡፡ በዚህ የተነሣ የደጃች ውቤ ልቅሶ በድምቀቱ ተወዳዳሪ አጥቶ ይኖራል፡፡ ምክንያትና ሰበብ ይለያያሉ፡፡ ምክንያት የአንድ ነገር መነሻ ሥር መሠረቱ፣ ቫይረሱና ጀርሙ፣ መንሥኤውና መብቀያው ነው፡፡ ሰበብ ግን ያ በአንዳች ምክንያት ሲበቅል፣ሲያድግ፣ ሲጎነቁል፣ ሲከካ፣
Posted in Ethiopian News, Religion

ከንብ ጋራ ኑሮ

click here for pdfበገድለ ወለተ ጴጥሮስ ላይ እንዲህ የሚል ታሪክ አለ፡፡ እምነ ወለተ ጴጥሮስ ወደ ዋልድባ ገዳም በገባች ጊዜ ለአንዲት እናት ረድእ ሆነች፡፡ እኒህ እናት ፈጽሞ ጠባይ የሚባል ያልፈጠረባቸው ነበሩ፡፡ አሁን የተናገሩትን አሁን ይሽሩታል፣ በሆነው ባልሆነው ይቆጣሉ፤ ከእርጅናቸው ብዛት የተነሣ ይነጫነጫሉ፤ ትእዛዛቸው ሁሉ ውኃ ቀጠነ ነው፡፡ በዚህ ዐመላቸው የተነሣ ማንም ከእርሳቸው ጋር ለመኖር ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ከእርሳቸው ጋር ለመኖር ፈቃደኛ ሆና ለረዥም ጊዜ ያገለገለቻቸው ወለተ ጴጥሮስ ነበረች፡፡አንድ ቀን መነከሳዪያቱ ተሰባስበው ‹እንዴት ከእኒህ እማሆይ ጋር ለዚህን ያህል ዘመን አብረሽ ለመኖር ቻልሽ? እንዴትስ ታገሥሻቸው? እንዴትስ መሮሽ ጥለሽ አልወጣሽም? ሲሉ ጠየቋት፡፡ ወለተ ጴጥሮስም ‹ንብ ታውቃላችሁ? እኒህ እናት ንብ ናቸው፡፡ ከእርሳቸው የሚገኝ ብዙ ዕውቀት፣ ብዙ ጥበብ፣ ብዙ ልምድ፣ ብዙ ታሪክ፣ ብዙም ጸጋ አለ፡፡ ነገር ግን እናንተ መናደፋቸውን ብቻ ነው የምታዩት፤ ስለዚህም ማሩን ከእርሳቸው ልትቆርጡ አልቻላችሁም፡፡ ንብ ትናደፋለች፣ ነገር ግን ማር የሚገኘው ከምትናደፈው ንብ ነው፡፡ የማትናደፈው ዝንብ ቆሻሻ እንጂ ማር የላትም፡፡ እኔ ግን ከንብ ጋር እንዴት
Posted in Ethiopian News, Religion

እውነት ስትሰቀል

click here for pdf (የዴንቨር መድኃኔዓለም ካህናትና ምእመናንን ባሰብኩ ጊዜ ይህንን ጻፍኩ) ሰሞኑን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዴንቨር ከተማ ተገኝተው የዴንቨር መድኃኔዓለምን በተመለከተ ‹ከእናት ቤተ ክርስቲያን ወጥቷል› ብለው መናገራቸውን ስሰማ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለምን በቅዱስ ያዕቆብ መንበር ሥር መሆን የለባትም /አለባተ በሚል ከ50 ዓመታት በፊት በፍርድ ቤት ክርክር ሲደረግ አንድ ሕንዳዊ አባት የሰጡት ምስክርነት ትዝ ያለኝ፡፡   በሕንድ ፍርድ ቤት የሕንድን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለማየት ከ50 ዓመታት በፊት ክርክር በተደረገ ጊዜ የሶርያውን መንበር የተቀበሉ ምእመናን ከባድ ፈተና ላይ ወድቀው ነበር፡፡ በአንድ በኩል በሶርያ መንበር የነበሩ አበው ለሕንድ ቤተ ክርስቲያን ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው ምእመናኑ ይማረራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከመንበሩ መነጠሉ ጥንታዊውን መንገድና ሥርዓት አዛብቶ ለተኩላ ስለሚዳርግ ያስጨንቃቸዋል፡፡ በፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በተመለከተ የተጠየቁት አባ ያዕቆብ የተባሉ ሕንዳዊ መነኮስ ‹እኔ መንበረ ያዕቆብ ስል ስለ እምነቴና ስለ ሥርዓቴ እየተናገርኩ እንጂ በቦታው ዛሬ ስለተቀመጡት አባቶች አይደለም፡፡ እነርሱ እንደሰውነታቸው ይበረታሉ ወይም ይደክማሉ፤ ይሠራሉ ወይም ይሰንፋሉ፡፡ ያቺ
Posted in Ethiopian News, Religion

ኢዛናና የነገረ ክርስቶስ እምነቱ

click here for pdfበኢትዮጵያ ታሪክ ክርስትናውን በይፋ ያወጀው ንጉሥ ኢዛና ነው፡፡ ኢዛና ክርስትናውን በይፋ በማወጅ ብቻ ሳይሆን በድንጋይ ላይ የጦርነት ታሪኩን መዝግቦ በማቆየትም ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን የታሪክ ሊቃውንት በኢትዮጵያ ክርስትና የተሰበከበትን ጊዜ ከ4ኛው መክዘ ቢጀምሩትም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ግን ከጃንደረባው መጠመቅ አንሥተው ይቆጥሩታል፡፡ በኢትዮጵያ የክርስትና ትምህርት ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም ኦፊሴላዊ እምነት የሆነውና መሠረት ባለው ጽኑ ዐለት ላይ የተተከለው ግን በ4ኛው መክዘ የፍሬምናጦስን ስብከትና ሹመት፣ የኢዛናንም ወደ ክርስትና መመለስ ተከትሎ ነው፡፡ ንጉሥ ኢዛና ከክርስትና ጋር የነበረውን ታሪክ በተመለከተ የሚነግሩን አራት ዓይነት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች አሉ፡፡ ሁለቱ በግሪክና በግእዝ፣ ሦስተኛው በግእዝ ብቻ፣ አራተኛው ደግሞ በግሪክ ብቻ የተጻፉ ናቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ኢዛና በመንግሥቱ ላይ ያመጹ ሕዝቦችን(ቤጃዎችን) ለመውጋት ያደረገውን ዘመቻ የያዙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ሲሆኑ ሁለቱ ጽሑፎች[1](ግሪኩና ግእዙ) ተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸው ናቸው፡፡ ይሄ የኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በአንዱ ገጽ በግሪክ የተጻፈ ሲሆን በሌላው ገጽ ደግሞ በግእዝና በሳባውያን(ግእዝን በሳባውያን ፊደል) የተጻፈ ነው፡፡ በዚህ
Posted in Ethiopian News, Religion

ፈረንጅ ሆይ ናና

click here for pdfፈረንጅ ሆይ ናና ፈረንጅ ሆይ ናናአንተ ስትናገር ይታመናልናፈረንጅ ሆይ ናና ፈረንጅ ሆይ ናናአንተ ስትናገር ትሰማለህናፈረንጅ ሆይ፤አንተ ገድላቱንና ድርሳናቱን፣ ዜና መዋዕሎችንና ታሪከ ነገሥቱን፣ የፍልስፍናውንና የጥበቡን፣ የመድኃኒቱንና የጠልሰሙን ነገር ከግእዝ ወደ እንግሊዝኛ ስትተረጉመው ሁሉም ያደንቅሃል፣ ያነብሃል፡፡ ይጠቅስሃል፡፡ ‹ከውጭ ድረስ መጥተው የኛን ታሪክ አጥንተው› እየተባለ ይነገርልሃል፡፡ እኛ ያደረግነው ቀን ግን ‹የደብተራ ጽሑፍ፣ የነፍጠኛ ድርሰት፣ ያበሻ ተረት ተረት ይባላል፡፡ እናም ፈረንጅ ሆይ ና፡፡ አባቶቻችን ለሺ ዘመናት ያቆዩትን የጽሑፍ ቅርስ ወሰድ፣ ስረቅ፣ አውጣ፣ ግእዝ ተማርና ተርጉም፤ ተርጉምና በዶላር ሺጥልን፡፡ ያን ጊዜ በእንግሊዝኛ ስታመጣው - ፓ- እያልን እናነብሃለን፡፡ምን ማንበብ ብቻ ግእዙን ብንጠቅሰው የደብተራ ድርሰት፣ የቄሶች ግሳንግስ፣ የድሮ ናፋቂ፣ ምናምን ስለምንባል ምናለ በእንግሊዝኛ ብታመጣልንና ‹የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዜና መዋዕል› ብለን ጠቅሰን መከራ ከምናይ ‹The chronicle of king zare’a yae’qob> ብንል ማናለበት፡፡ እኛ ስለ ንግሥተ ሳባ ስንናገር ተረት ይሆናል፤ አንተ ሮምን የመሠረቷት ሮሙለስና ሙለስ የተባሉ ተኩላ ያሳደገቻቸው ልጆች ናቸው ስትል ግን ሁሉ ያምንሃል፡፡ ደግሞ ያንተ
Posted in Ethiopian News, Religion

ላስቬጋስ – ጎንደር

click here for pdfአሜሪካ ስመጣ ሦስት ቦታ ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይማርከኛል፡፡ ላስቬጋስ  ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ሚካኤል፣ ዴንቨር መድኃኔዓለምና ሚነሶታ ቅድስት ሥላሴ፡፡ ሃይማኖታቸውን የተረዱ፣ ለአገልግሎት የተጉና ምራቃቸውን የዋጡ ክርስቲያኖች ያሉበት ቦታ፡፡ ወደነዚህ ቦታዎች ስመጣ ከማስተምረው የምማረው ይበልጣል፡፡ በአስቸጋሪው የአሜሪካ ኑሮና ፈተና ውስጥ የቤተ ክርስቲያን እምነትን፣ ሥርዓትና ትውፊትን ጠብቆ፣ ጊዜንና ገንዘብን ሠውቶ፣ የቤተ ክርስቲያንንም አንድነት ጠብቆ ለማገልገል የሚደረገው ተጋድሎ እንኳን የኔ ቢጤውን ሊቃውንቱንም የሚያስደምም ነው፡፡ በተለይ የወጣቶቹ አገልግሎት ጎላ ሚካኤል፣ ተምሮ ማስተማር፣ መርካቶ ተክለ ሃይማኖት ወይም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ያላችሁ ነው የሚመስላችሁ፡፡ላለፉት አምስት ሳምንታት ላስቬጋስ ነበርኩ፡፡ ‹‹የኃጢአት ከተማ›› እያሉ አሜሪካኖች የሚጠሯት የቁማር ከተማ ውስጥ፡፡ ከቅዳሜና እሑድ ይልቅ ረቡዕና ኀሙስ የዕረፍት ቀን በሆነባት ከተማ፡፡ ከሚፈቀደው ይልቅ የማይፈቀደውን ኃጢአት መዘርዘር በሚቀልባት ከተማ፡፡ ክረምቱ ሲመጣ ሙቀቷ እንደ ገሃነም በሚያቃጥልባት ከተማ፤ ዙሪያዋን በተራራ ታጥራ መሐሏ እንደ ድስት ጎድጉዶ፣ ቁማር ላይ የተጣደች ድስት በምትመስለው ከተማ፡፡ በታዋቂው የኔቫዳ በረሃ ውስጥ በምትገኘው ከተማ፡፡ ከተመሠረተች 110 ዓመት
Posted in Ethiopian News, Religion

የወታደሮቻችን ነገር

አፕሪል 12፣ 1868 የተጻፈclick here for pdfየመቅደላው ጀግና ዐፄ ቴዎድሮስ በመጨረሻዋ ሰዓት ለጄኔራል ናፒየሪ በጻፉት ደብዳቤ አበክረው የጠየቁት ነገር ከሁለት ቀናት በፊት በተደረገው ውጊያ የወደቀውን የወዳጃቸውንና የጦር መሪያቸውን የፊታውራሪ ገብርዬን አስከሬን ለመቅበር እንዲፈቀድላቸው ነበር፡፡ ‹‹ፊታውራ ገብርዬን የኔን ወዳጅ ሳላነሣው ያደርኩ ከሞትኩኝ ሁሉንም አብረው ይቅበሩኝ ብየ ነበር፡፡ ቁሜ ከዋልኩ ግን ልቅበረው ይፍቀዱልኝ›› ይላል ደብዳቤው፡፡ ለሀገሩና ለወገኑ በክብር የተሠዋ አስከሬኑም የክብር ዕረፍት ይሻዋልና፡፡ አሜሪካኖችና አውሮፓውያን የተሰጣቸውን ግዳጅ ለመወጣት የዘመቱ ወታደሮቻቸው ሲሠው በክብር አስከሬናቸውን ወደ ሀገር በማምጣት በብሔራዊ ሥነ ሥርዓት የመቅበር ያልጠፋ ልማድ እንዳላቸው በየጊዜው ሚዲያው ያሳየናል፡፡ እነዚህ ወታደሮች ሀገራዊ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የዘመቱ በመሆኑ መሥዋዕትነታቸውም ሀገራዊ ሆኖ መታሰብ አለበት፡፡ በኢትዮጵያ የቅርብ ዘመን ታሪክ የተሠዉ ወታደሮችን በክብር የመዘከር፣ በክብር የመቀበልና በክብር የመቅበር ሥነ ሥርዓት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት የተሠዉ ስንት ወታደሮች ናቸው? የተሠዉትስ ወታደሮች መርዶ እንዴት ተነገረ? የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውስ እንዴት ተከናወነ? ሚዲያውስ ለዚያ ምን ዓይነት ሽፋን ሰጠው? የሁል ጊዜ ጥያቄዬ ነው፡፡ እኔ
Posted in Ethiopian News, Religion

አቡነ ቴዎፍሎስ ‹ያላረፉት› ፓትርያርክ

   click here for pdfሰሞኑን የቀድሞው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ የጻፉትንና ‹አብዮቱና ትዝታዬ› የተሰኘውን መጽሐፍ ሳነብብ ስለ አቡነ ቴዎፍሎስ አሟሟት የጻፉትን አገኘሁ፡፡ ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ እስካሁን ከጻፉት የቀድሞ ባለሥልጣናት በሁለት ነገር ተለይተውብኛል፡፡ የመጀመሪያው በቡድንና በጋራ ለሠሯቸው ስሕተቶች ይቅርታ መጠየቃቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሁሉም ወገኖች የተፈጠሩትን ያለፉትን ስሕተቶች ለማረም ያስችላል ያሉትን የጋራ መድረክ ሐሳብ ማቅረባቸው ነው፡፡ምንም እንኳን በዘመነ ደርግ የተፈጠሩት ስሕተቶችና ጥፋቶች ደርግ ብቻውን ያደረጋቸው ባይሆኑም አንዱና ዋነኛው ተዋናይ ደርግ ነበርና ለተሠሩት ጥፋቶች ይቅርታ መጠየቃቸው ለሌሎች አካላትም አርአያነት ያለው ነው፡፡ ዋናው የደርጉ መሪ ያ ሁሉ ጥፋት ሲሠራ ‹እኔ አላውቅም ነበር›› ብለው በካዱበት ሁኔታ ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ የራሳቸውን ይቅርታ መጠየቃቸው ለሰማዩም ለምድሩም ጉዟቸው ምትክ አልባ ተግባር የሚሆን ነው፡፡ ክብር ይስጥልን፡፡ ያ ዘመን በተሻለ እንመራለን ብለው የተነሡ ፖለቲካዊ ኃይሎች እንደየዐቅማቸው ስሕተቶችን የሠሩበትና ጥፋቶችን ያጠፉበት ዘመን ነው፡፡ ሁሉንም ጥፋት ለደርግ በመስጠት እጅን መታጠብ አይቻልም፡፡ እርሳቸው እንዳሉትም የደርግን ባለ ሥልጣናት ብቻ ወደ ፍርድ
Posted in Ethiopian News, Religion

የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች

  click here for pdfክፍል አንድ በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከሚነሡ መንፈሳውያን ጥቄዎች መካከል አንዱ የጥምቀትና አጥማቂዎች ጉዳይ ነው፡፡ ጥምቀት(የክርስትና ጥምቀትን አይመለከትም) በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ምእመናን ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙባቸው ከእግዚአብሔር ከተሰጡ ጸጋዎች አንዱ ነው፡፡(2ኛ ነገሥት 5፤ ዮሐ. 5፣ዮሐ. 9)፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ውስጥ በልዩ ልዩ ገድላተ ቅዱሳን ላይ እንደምናነበው በጠበል ሕዝቡን ሲፈውስ ኖሯል፡፡ ሕዝብ ፈውስ የሚያገኝባቸው እንደ ሰሊሆምና እንደ ቤተ ሳይዳ የታወቁ የቃል ኪዳን ቦታዎችም ነበሩ፡፡ አሁን በያዝነው ዘመን አያሌ ‹አጥማቂ> የሚባሉ ሰዎች ተነሥተዋል፡፡ ክብራቸውን የሚገልጥ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፣ መቁጠሪያ ይሸጣሉ፣ ቅባት ይቀባሉ፣ አዳራሽ ከፍተው ወይም ሕዝብ በሜዳ ሰብስበው እንፈውሳለን ይላሉ፤ ሰይጣን ተናገረ የሚባለውን በካሴት ቀድተው ይሸጣሉ፡፡ ከዚህ ቀጥዬ በማቀርባቸው አሥር ምክንያቶች እነዚህን ሐሳውያን መቀበል የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡ 1.      በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ገዳማዊ ሕይወት፣ ክህነታዊ ሕይወት፣ የጸሎት ሕይወት ወይም ሌላ አንዳች ተጋድሎ ሳይኖረው ማጥመቅ ብቻ ሥራው የነበረ ክርስቲያን የለም፡፡ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች የሌላው መንፈሳዊ ሕይወታቸው ውጤት ወይም
Posted in Ethiopian News, Religion

እህል ወይስ አረም ?

click here for pdf አሁን ባለንበት ዘመን ያለን የኢትዮጵያ ትውልድ የሀገራችንን ታሪክ፣ የሕዝቦች የእርስ በርስ ግንኙነትና የመሪዎቻችንን ሁኔታ ስንነጋገርና ስንጽፍ በአብዛኛው አሉታዊውን ነገር ይበልጥ ጎልቶ እንዲወጣ፣ ጥላቻ እንዲበቅል፣ ቂም እድሜ እንዲያገኝ፣ ልዩነት እንዲሰፋ፣ ጠብም ሥር እንዲሰድ በማድረግ ላይ የተመሠረተ ሆኖ ይታያል፡፡ ርግጥ ነው በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ የመስተጋብር ችግሮች ሁሉ በኛም ሀገር ተፈጥረዋል፡፡ በኛ ሀገር የተፈጠሩትም በሌሎች ይገኛሉ፡፡ በዓለም ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ የኩራትም የውርደትም፣ የፍቅርም የጠብም፣ የሰላምም የጦርነትም፣ የእኩልነትም የጭቆናም፣ የመረዳዳትም የመጠፋፋትም፣ የሥልጣኔም የስይጣኔም ታሪኮች አሉ፡፡ እንኳን በአንድ ሀገር የሚኖሩ የተለያየ ዘውግ፣ ቋንቋ፣ እምነትና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ቀርተው በተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባሕልና የኑሮ ደረጃ የሚገኝ የአንዲት ሀገር አንድ ወጥ ሕዝብ እንኳን በውስጡ ጽጌረዳም እሾህም አለው፡፡  የሚገርመው ነገር ኢትዮጵያን ከዓለም የተለየች የሚያደርጋት ምን እንደሆነ አለመታወቁ ነው፡፡ ኢትዮጵያኮ ሲኦልም አልነበረችም መንግሥተ ሰማያትም አልነበረችም፡፡ ሀገር ነበረች፣ አሁንም ሀገር ነች፡፡ ሀገር የሚገጥማት ፈተና ሁሉ ገጥሟታል፤ ሀገር የሚኖራት ጸጋ ሁሉ ታድሏታል፡፡ በአንዳንድ የታሪክ ምእራፏ ለመንግሥተ
Posted in Ethiopian News, Religion

‹አርቲስቶቹ›ን ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን

አንድ ጆሮና ጊዜ የገጠሙለት ሰው ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው የተማረው ትምህርት የለውም፡፡ ሁለት ችሎታ ግን ነበረው፡፡ ሲባል የሰማው እውነትም ይሁን ስሕተት ልቅም አድርጎ ይይዝና ሌላ ቦታ ሄዶ የተማረው ያህል ያንደቀድቀዋል፡፡ ሁለተኛው ችሎታው ደግሞ አፈ ጮሌ ስለሆነ ነገር በምላሱ ይቆላል፡፡ ያንንም ይኼንንም እያቆላመጠ ከተማሩትና ከተመራመሩት በላይ ከብሮና ታፍሮ ይኖራል፡፡ አንድ ቀን የማያውቀውን ቀለም ሲያዜም የሰሙት ሊቅ አፍረው አቀረቀሩ፡፡ እርሱ ግን ከዕውቀት የደነገለ ነበርና አልገባውም፡፡ በኋላ ቀረብ ብሎ ‹ደኅና ነዎት የኔታ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ደኅና ነህ›› ብለው ዝም አሉት፡፡ እርሱም ያላወቁት ስለመሰለው ‹አላወቁኝም መሰል መሪጌታ እኮ ነኝ› አላቸው፡፡ሊቁም ‹ዐዉቄሃለሁ› አሉት፡፡ እንዳቀረቀሩ፡፡ ‹ታድያ ምነው ካወቁኝ ከነ ማዕረጌ ሳይጠሩኝ ቀሩሳ› አላቸው፡፡ ‹አንተን አከብራለሁ ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው›› አሉት ይባላል፡፡እኔም ‹እርቲስቶቻችን› የሚለው ቃል በትእምርተ ጥቅስ ያደረግኩት ሊቁ የፈሩትን ፈርቼ ነው፡፡ እንዳልተውባቸው ደግሞ ምን ብዬ እንደምጠራቸው ግራ ገብቶኝ፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማውን መርሐ ግብር በዕለቱ ለማየት ስላልቻልኩ ቪዲዮውን ነው የተመለከትኩት፡፡ ሊነግሩን የፈለጉት ስለ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ፣ ስለ ሀገራችን
Posted in Ethiopian News, Religion

የዕብድ ኀሙስ

click here for pdf የታደለ አገልጋይ የበላዩን ከስሕተት ይጠብቃል፡፡ ‹አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ› እንዲሉ፡፡ አክዓብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት(871-852 ቅልክ) የነበረ ንጉሥ ነው፡፡ የሚስቱን የኤልዛቤልን ቃል ሰምቶ ነቢያተ እሥራኤልን ሊያጠፋ ተነሣ፡፡ ብዙዎች በሰይፉ ጠፉ፣ ብዙዎችም አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ በአክአብ ቤተ መንግሥት ውስጥ ግን አብድዩ የተባለ ልብ ያለው ባለሟል ነበር፡፡ ንጉሡን ከጥፋቱ ማዳን ቢያቅተው በንጉሡ ስሕተት ባለመስማማቱ 100 ነቢያትን በሁለት ዋሻ ውስጥ ደብቆ የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየመገበ ከአክዓብ ጥፋት አድኗቸው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ነቢያት የእሥራኤል የዕውቀትና የእምነት መሪዎች ናቸው፡፡ የእሥራኤል ባህል፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ዕውቀት የሚተላለፈው በነቢያት ትውፊት ነበርና፡፡ ነቢያቱን ማጥፋትም ሀገሪቱን ያለ ታሪክ፣ ዕውቀት፣ ባህል፣ ሥርዓትና ቅርስ ማስቀረት ነበር፡፡ ለዚህ ነው አብድዩ የንጉሡን ዐዋጅ ማስቀየር ቢያቅተው ነቢያቱን ደብቆ እየመገበ ሀገሪቱን ከከባድ ጥፋት የታደጋት፡፡  ይህንን ሥራውን ማንም እንዲያውቅለትም፣ እንዲያውቅበት አላደረገም፡፡ ዓላማው ዕውቅና ጥቅም ማግኘት ሳይሆን ሀገር ማትረፍ ነውና፡፡ የንጉሡን የጥፋት ዐዋጅ ማስቀረት አልችልም ብሎ ዝም አላለም፤ ነገር ግን
Posted in Ethiopian News, Religion

3ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተካሄደ

click here for pdfየምርጫ ሂደቱ ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የበጎ ሰው ሽልማት ለሦስተኛ ጊዜ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በአኩስም ሆቴል ተከናወነ፡፡ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ተሸላሚዎች፣ የተሸላሚ ቤተሰቦች፣ ዕጩዎች፣ የክብር እንግዶችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ በዕለቱ ለዕጩዎች የዕጩነት የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ለአሸናፊዎች ደግሞ የክብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል በዳኞች የተመረጡት የዚህ ዓመት የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች የተመረጡባቸው ዋነኛ መሥፈርቶች ሦስት ሲሆኑ እነርሱም በዘመናቸው ካገኙት ዕድል በመነሣት በሞያቸው የተጓዙበት ርቀት፤ አርአያ በመሆን ወይም ፈር በመቅደድ፣ ወይም ችግርን በመፍታት ወይም ደግሞ አዲስ መንገድ በመቀየስ፣ ወይም በጎ ተጽዕኖ በማሳረፍ ወይም ሌሎችን በማፍራት ያበረከቱት አስተዋጽዖ፤ እና ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ ያላቸው አበርክቶ የሚሉት ናቸው፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ ሌሎች ዝርዝር መመዘኛዎች ታይተዋል፡፡ በዚህ መሠረት  1.      በሳይንስ ዘርፍ - ፕሮፌሰር አበበ በጅጋ2.     በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ- አቶ ደሳለኝ ራሕመቶ3.     በበጎ አድራጎት ዘርፍ - ወ/ት ትርሐስ መዝገበ4.     በቢዝነስና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ - ሰላም ባልትና5.     በስፖርት ዘርፍ -
Posted in Ethiopian News, Religion

የበጎ ሰው ሽልማት ፕሮግራም አዳራሽ ተቀየረ

ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በካፒታል ሆቴል ሊደረግ የነበረው የበጎ ሰው ሽልማት ፕሮግራም በቦታ መደራረብ ምክንያት ወደ አኩስም ሆቴል ተዛውሯል፡፡ ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ እየጠየቅን መልእክቱን ለማስተላለፍ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡ ሰዓቱ አልተለወጠም፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የበጎ ሰው ሽልማት ፳፻፯ መርሐ ግብር ላይ ተሳተፉ

ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም፣ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሚደረገው የበጎ ሰው ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡  ከረቡዕ ነሐሴ 20 ቀን ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምረው  ወደ በጎ ሰው ገጸ ድር www.begosew.com ይሂዱ፡፡ እዚያ በሚያገኙት የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ ይመዝገቡ፡፡ ምዝገባዎን ሲፈጽሙ የተሳታፊነት ቁጥር በስልክ ወይም በኢሜይል ይላክልዎታል፡፡ ቁጥርዎን ይዘው ከሚቀጥለው ሰኞ (ነሐሴ 25 ቀን 2007) ዓም ጀምረው አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት፣ ከፎርሺፕ የጉዞ ወኪል ጀርባ ወደሚገኘው ምርፋቅ ካፌና ሬስቶራንት በመሄድ የመግቢያ ካርድዎን ይውሰዱ፡፡ ምዝገባዉን ለማጠናቀቅ የሞባይል ቁጥር ወይም የኢሜይል አድራሻ ያስፈልጋል፡፡  መልካም ዕድል
Posted in Ethiopian News, Religion

የ2007 ዓም የበጎ ሰው ሽልማት ዕጩዎች ታወቁ

click here for pdfለ3ኛ ጊዜ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሚከናወነው ‹የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት› በየዘርፉ የተመረጡ የመጨረሻዎቹ  አምስት ዕጩዎች ታወቁ፡፡ ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ በተሰጠው የሕዝብ ጥቆማ መሠረት ታሪካቸውና ሥራቸው ተሰብስቦ፣ በበጎ ሰው ሽልማት የምርጫ ሂደት ኮሚቴ የተመረጡት 45 ዕጩዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ለመጨረሻው ውድድር ለመራጭ ዳኞች ታሪካቸውና ሥራቸው የቀረበ ሲሆን እስከ ነሐሴ 15 ቀን ድረስ የመጨረሻዎቹ 9 ተሸላሚዎች ይታወቃሉ፡፡ ምንም እንኳን በመጨረሻ የሚሸለሙት 9 ተሸላሚዎች ቢሆኑም በሕዝብ ተጠቁመው፣ በምርጫ ኮሚቴው የመጨረሻው ደረጃ መድረሳቸው በራሱ ክብር ስለሆነ፡፡ 45ቱም ዕጩዎች ለሀገር የሠሩ በጎ ሰዎች ተደርገው ይታሰባሉ፡፡ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ነሐሴ 30 ቀን ቅዳሜ፣ ከሰዓት በኋላ፣ በካፒታል ሆቴል ይከናወናል፡፡ዝርዝራቸው የሚከተለው ነው፡፡በ፳፻፯ ዓም በልዩ ልዩ ዘርፎች ዕጩ የሆኑ በጎ ሰዎችበሳይንስ ምርምር  ዘርፍ ዕጩዎች1.     ፕ/ር ኢ/ር አበበ  ድንቁ (አአዩ)2.     ኬሚካል መሐንዲስ ጌታሁን ሄራሞ 3.     ዶክተር አበበ በጅጋ  4.     ፕሮፌሰር አሥራት ኃይሉ5.     ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)በሥነ ጥበብ ዘርፍ ዕጩዎች1.    
Posted in Ethiopian News, Religion

ራስ ዓምዱ፡- ከየመን እስከ አትሮንሰ ማርያም

click here for pdf በኢትዮጵያ ታሪክ ከሌላ ሀገር መጥተው እዚህ ሀገራችን ውስጥ ኖረው፤ ወልደውና ከብደው፣ ሁሉንም ነገሯን ወርሰው፣ ሀገሬው የሚደርስበት ደረጃ ደርሰው፣ ሀገር እንደሆነው ሆነው፣ ታሪክ የሠሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ዛሬ ዛሬ ጠባብነት በአያሌው አጥቅቶናል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎቻችንም አብረውን የኖሩትን፤ ነገር ግን በባሕል፣ በእምነትና ቋንቋ ከእኛ የሚለዩትን እንደ እንግዳ ፍጡር ማየት ቃጥቶናል፡፡ ከአንድ አካባቢ የመጣ ኢትዮጵያዊ በሌላ አካባቢ ባዕድነት ሲሰማው፣ ይህቺ ሀገር እንዲህ ሆና ተፈጥራ እንዲህ ሆና የኖረቺ ትመስለዋለች፡፡ ግን እንዲህ አልነበረቺም፣ እንዲህም አይደለቺም፣ እንዲህም አትኖርም፡፡እንዲህ እንዳልነበረቺ ከሚያሳዩን ታሪኮቻችን አንዱ የራስ ዓምዱ ታሪክ ነው፡፡በዛግዌ ሥርወ መንግሥት ጊዜ ከየመን፣ ከዮሴፍ ነገድ የሆነ ስሙም በነገዱ ስም ዮሴፍ የተባለ አንድ ኦይሁዳዊ ሰው ወደ አምሐራ ሀገር እላወዝ ወደሚባል ቦታ መጣ፡፡ ይህ ሰው እጅግ የተከበረና በጣምም ባዕለ ጸጋ ነበረ ይለናል በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም የሚገኝ አንድ መጽሐፍ(EMML no. 1768, fol. 88r,)፡፡ እርሱም በዚያ ሀገር መኖር ጀመረ፡፡ አምባ ናድንም ወለደ፣ አምባ ናድም ጎጃም ሰገድን፣ ጎጃም ሰገድም አምኃ ጽዮንን፣ አምኃ ጽዮንም
Posted in Ethiopian News, Religion

ዕውቀት ቦታ ሲያጣ

click here for pdf ታላላቅ የሚባሉ ተቋማት አንድን ነገር ሲሠሩ ያንን የተመለከተ ሞያ ያላቸውን ሰዎች የማማከር ነገር እየቀረ፣ እንዴው በቦታው ላይ በተመደቡ፣ ካገኙበት ቦታ ብቻ ገልብጠው በሚያመጡ አካላት እየተዳደርን መሆኑን ከሚያሳዩን ነገሮች አንዱ የምናትማቸው ካላንደሮቻችን ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር የሺ ዓመታት ጉዞን የተጓዘ፣ ከሀገሪቱ ባሕል፣ እምነት፣ ፖለቲካ፣ ግብርና፣ የአየር ሁኔታና ታሪክ ጋር በብርቱ የተሣሠረ መሆኑን እንኳን እኛ ባለቤቶቹ ሀገሪቱን በተመለከተ የሚያጠኑና የሚጠይቁ ሁሉ ያውቁታል፤ ያደንቁታልም፡፡ይህ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት ራሱን የቻለ ሞያ ሆኖ በሀገር ቤት ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የኖረ፣ ለብዙ መቶ ዓመታት የሚያገለግሉ ቀመሮች ተዘጋጅተውለት ማንም ሰው በቀላሉ የዘመኑን ቁጥርና ሁኔታ እንዲያውቀው ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ አሁን አሁን ግን ‹ዋርካዎች ተቆርጠው እምቧጮ ሲበቅል፣ ጋኖቹ ጠፍተው ምንቸቶች ጋን ሲሆኑ› ታላላቆቹ ተቋማት ሳይቀሩ ይህንን ለዘመናት የዘለቀ የዘመን መቁጠሪያ እንደፈለጉ ያደርጉት ጀመር፡፡  ይህ ዓመት 2007 ዓም ጳጉሜን 6 ቀን ናት፡፡ ስለዚህም አዲሱ ዓመት መስከረም አንድ ቅዳሜ እንጂ ዓርብ አይውልም፡፡ የዘመን መቁጠሪያ መጻሕፍቱ ሁሉ ይህንን ከመቶ ዓመታት
Posted in Ethiopian News, Religion

ዝርዝርና ጥቅልል

click here for pdf ወንዶችንና ሴቶችን በተመለከተ ከተጻፉ መጻሕፍት መካከል ከርእሱ ጀምሮ የሚገርመኝ አንድ መጽሐፈ አለ፡፡ ‹‹why Men Don’t have a clue & Women always need more shoes›› ይላል፡፡ ባልና ሚስቱ የመጽሐፉ ደራስያን አላንና ባርባራ ፔዝ የወንዶችንና የሴቶችን ግንኙነት ጤናማና ሰላማዊ ለማድረግ አንዱ ዋናው መንገድ ሁለቱ በነገሮች ላይ ያላቸውን ልዩነት ጠንቅቆ ማወቅና በዚያ ላይ ግንኙነትን መመሥረት ነው ይላሉ፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ካነሷቸው አስገራሚ የወንዶችና ሴቶች የአነዋወርና አስተሳሰብ ልዩነቶች መካከል አንዱ ነገሮችን የሚያዩበት መንገድ ነው፡፡ ሴቶች ነገሮችን በዝርዝርና አበጥረው የማየት አዝማሚያና ተሰጥዖ አላቸው ይላሉ፡፡ ለምን? እንዴት? የት? ከዚያስ? እያሉ ነገሮችን ይፈተፍቷቸዋል፡፡ ወንዶቹ ‹ዝርዝር ኪስ ይቀዳል› በሚለው የአራዶች መመሪያ ተመርተው ነው መሰል ነገርን በጥልቁና በዝርዝሩ ከማየት ይልቅ ጠቅላላውን ነገር ስለሚመርጡ ስለ አንድ ጉዳይ በዝርዝር ሲጠየቁ ቁጥጥር የተደረገባቸው፣ ምርመራ የተካሄደባቸውና አለመታመን የተፈጠረባቸው መስሏቸው ቁጣ ይቀድማቸዋል፡፡ ነገሩ የመጣው ጉዳዮችን በዝርዝር በሚያየው የሴቶች ልቡናና ነገሮችን መጠቅለል በሚወደው የወንዶች ልቡና መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው፡፡ እዚህ ላይ እንዲያውም አንድ ምሳሌ ያነሳሉ፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

እህልና አረም

click here for pdf የሀገሬ ገበሬ ዘር ያስቀምጣል፡፡ መርጦና መጥኖ፡፡ ሁሉም እህል ዘር አይሆንምና፡፡ በተቻለ መጠን ወፍ ያልቆረጠመው፣ ነቀዝ ያልቀመሰው፣ ሌላ ነገር ያልተቀላቀለበት፣ ያልተሸረፈና ያልተቦረቦረ፣ ሲያዩት የሚያምር፣ ሲበሉት የማያቅር ተመርጦ በልዩ ሁኔታ በልዩ ቦታ ይቀመጣል፡፡ አቀማመጡም የራሱ ሞያ አለው፡፡ ሞያውን ችሎ የሚያስቀምጠው ገበሬ ዘንድ ‹እገሌ ዘንድ ዘር አይጠፋም› እየተባለ አገር ይጠይቀዋል፤ ለሀገርም ዘር ያተርፋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ጠብቆ ያኖረውን ዘር ሲዘራው ግን እንደ ገበሬው ቋንቋ የሚበቅለው ‹እህልና አረም ነው፡፡›› ፈልጎ ከዘራው እህል ጋር የማይፈልገው አረም አብሮ ይበቅልበታል፡፡ መጽሐፉስ ‹ዘሩ በበቀለ ጊዜ አረሙ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ› አይደል የሚለው፡፡ ገበሬው አረሙን ሁለት ጊዜ ነው የሚታገለው፡፡ መጀመሪያ እንዳይበቅል በመከላከል፡፡ ዘሩን የሚመርጠው፣ አበጥሮና አንጠርጥሮ፣ ለቅሞና ሸክፎ የሚይዘው ለዚህ ነው፡፡ ዘሩ የሚወድቅበትን መሬትም አስቀድሞ መንጥሮና አስተካክሎ፣ ጎልጉሎና ለቅሞ ያጸዳዋል፡፡ አረም እንዳይኖረው ሲል፡፡ ይህንን አልፎ ከዘሩ ጋር አብሮ አረሙ ሲበቅል ግን ቢችል ‹ሆ› ብሎ በደቦ ባይችል እርሱና ቤተሰቡ ወጥተው አረሙን ያርሙታል፡፡ ‹ለአረም ቦታ መስጠት ደግም አይደል›› ይላል ገበሬው፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የኛ ሠፈር ፍርድ

click here for pdf እኛ ሠፈር ነው፡፡ አንዲት ሴትዮ በእኩለ ሌሊት እሪታዋን አቀለጠቺው፡፡ እኛም እየተንጋጋን ከቤታችን ወጣን፡፡ ሠፈርተኛው፣ የአካባቢ ጸጥታ አስከባሪዎች፣ መንገደኛው፣ የቀበሌ ሹሙ፣ ውሾቹ እንኳን ሳይቀሩ የተጮኸበት ቤት ጋ ተሰበሰቡ፡፡ ጎረምሶቹ የቤቱን በር ሰብረው ሲገቡ ባሏ ሚስቱን ውኃ ውኃ በሚያሰኝ ዱላ ይደበድባል፡፡ ጎረምሶቹ ዱላውን ነጥቀው እርሷን ከቤት አወጧት፡፡ ልብሷ ተቀዳዷል፤ የተረፈውም በደም አበላ ተጠምቋል፡፡  ከጸጥታ አስከባሪዎች አንዱ ‹‹ለምን ይህንን ያህል በመጮኽ ሠፈሩን ጸጥታ ትነሻለሺ›› አላት ደም በደም የሆቺውን ሴትዮ፡፡ አልመለሰቺም፡፡ እርሷ ደሟን በልብሷ እየጠረገቺ ታለቅሳለቺ፡፡ እንኳን መልስ የምትሰጥበት በሕይወት የምትቆዪበት ዐቅም ያላት አትመስልም፡፡ ‹‹ሁልጊዜ ኮ ነው የምትጮኸው፤ እኛ ሠፈሩን ሰላማዊና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ ቀን ከሌት እንለፋለን፡፡ የኮብል ስቶን መንገድ አሠራን፣ የጥበቃ ቤት አሠራን፣ ዛፍ ተከልን፤ ትልልቅ ቢል ቦርዶችን ሰቀልን፣ ምን ዋጋ አለው፡፡ ይቺ ሴትዮ ሌሊት ሌሊት የሠፈሩን ሰላም ትበጠብጠዋለቺ›› አለ የአካባቢው ሹም በምሬት፡፡‹‹ለምንድን ነው ሠፈሩን እንዲህ የምታሸብሪው?›› አላት ጸጥታ አስከባሪው፡፡‹‹ ይልቅ እርሱን ‹ለምን ትደበድባታለህ›? ብላቺሁ አትጠይቁትም›› አለቺ ደሟን እየጠረገቺ፡፡‹‹የችግሩን ምንጭ
Posted in Ethiopian News, Religion

የሚባላውን ጅብ ጥሪ

 click here for pdfፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ በ1985 ዓም ታትማ በነበረቺው ውይይት መጽሔት(ቅጽ 2፣ ቁጥር 1) ላይ የዐፄ ኃይለ ሥላሴን ዘመንና የንጉሡን ሁለት መልክ የነበረው አመራር ገምግመው ነበር፡፡ መጀመሪያ ተራማጅ በኋላ ደግሞ ወግ አጥባቂ እየሆኑ የመጡት ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ከሃምሳ ዓመታት በዘለለው የንግሥና ዘመናቸው ለሀገሪቱ አስፈላጊ ከመሆን ተነሥተው አላስፈላጊ ወደመሆን የደረሱት ለምን ነበር? የሚለውን የምሁሩ ድርሳን በሚገባ ያሳየናል፡፡ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ተፈሪ መኮንን ተብለው ሥልጣን በያዙባቸው የመጀመሪያ ዓመታት ሀገሪቱን በለውጥ ጎዳና የሚወስዱ ርምጃዎችን በመውሰድ፣ የሀገሪቱን ማዕከላዊ አስተዳደር በማጠናከር፣ ትምህርትን በማስፋፋት፣ በዐፄ ምኒሊክ ዘመን የተጀመሩ ዘመናዊ አሠራሮችን ሥር ይዘው እንዲጎለብቱ በማድረግ፣ የሀገሪቱን አዲስ ሕገ መንግሥት እንዲረቀቅና እንዲጸድቅ በማድረግ ተራማጅ መሪ ሆነው ብቅ ብለው ነበር፡፡ ለውጥ ይሻ የነበረው የዘመኑ አዲስ ትውልድም የተፈሪ መኮንን ደጋፊና ተባባሪ ሆኖ ተሰልፎ ነበር፡፡ ተፈሪ መኮንንን እንደ አዲሲቱ ኢትዮጵያ መሪ፣ የሥልጣኔ አራማጅ፣ ወደ አዲስ ዘመን አሸጋጋሪ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፡፡  በርግጥም እስከ ጣልያን ወረራ በነበሩት ዘመናት ተፈሪ መኮንን የታሰበላቸውን ያህል ባይሆንም
Posted in Ethiopian News, Religion

ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና

click here for pdf ልጁ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡ ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ  ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣ ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ ሊያጽናናትና ሊያበረታት ሞከረ፡፡ እርሷ ግን ማማረሯን፣ መማረሯንም አላቆመቺም፡፡ እንዲያውም ምሬቷ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ፤ ኑሮዋንም እየጠላቺው፣ ፈተናዋንም እየፈራቺው መጣቺ፡፡ አንድ ቀን መኖር አስጠልቷት፣ ችግሩና መከራም በርትቶባት፣ ምሬቷም ጫፍ ደርሶ መጣቺ፡፡ ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ መኖር አልፈልግም፤ ይህንን ያህልስ እኔ ለምን እፈተናለሁ፤ ለምንስ ችግር ይበረታብኛል፤ ለምንስ ሁሉም ነገሮች ይጠሙብኛል፤ በቃ እኔ መኖር የለብኝም›› እያለች ታለቅስ ነበር፡፡አባቷ ምክሩ ሁሉ እንዳልሠራ፣ የነገራትንም ሁሉ እንደዘነጋቺው ተረዳ፡፡ ‹‹ተከተይኝ›› አላትና ወደ ማዕድ ቤት ገቡ፡፡ ወንበር ሰጣትና እርሱ ወደ ምግብ ማብሰያው ሄደ፡፡ ኮመዲኖውን ከፈተና ዕንቁላል፣ ድንችና የተፈጨ ቡና ይዞ መጣ፡፡ እርሷ ግን ትዕግሥቷ አልቆ ነበር፡፡ በልቧም ‹‹እኔ ኑሮ መርሮኝ እርሱ ምግብ ሊጋብዘኝ ይፈልጋል›› ትል ነበር፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ይህም ያልፋል

click here for pdf አንድ ንጉሥ አማካሪዎቹን ሰበሰበና እንዲህ ሲል አዘዛቸው፡፡ ‹‹ስከብርም ሆነ ስዋረድ፣ ሳገኝም ሆነ ሳጣ፣ የሁሉም የበላይ ስሆንም ሆነ የበታች፣ እጅግ ስደሰትም ሆነ ስከፋ፣ ድል ሳደርግም ሆነ ድል ስሆን፣ ዝናዬ ሲናኝም ሆነ ሲከስም፣ ያንን ነገር በሰላምና በጥበብ እንዳልፈው የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር ስጡኝ፡፡ ላስታውሰው የምችል፣ መንገዱንም የሚመራኝ፣ ከልክ አልፌ እንዳልሄድ፣ ከልክ ወርጄም እንዳልወድቅ፣ የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር አምጡልኝ፡፡ የተወሳሰብ ፍልስፍና አልፈልግም፣ ቀላልና ግልጽ የሆነውን እሻለሁ፡፡ ይህንን ሳትይዙ እንዳትመለሱ››አማካሪዎቹ ከቤተ መንግሥቱ ወጥተው ለአራት ወራት ያህል መከሩ፡፡ አነሡ ጣሉ፤ በመጨረሻም የደረሱበትን ሐሳብ በብራና ጽፈው ወደ ንጉሡ ዘንድ መጡ፡፡ የተጠቀለለውንም ብራና ሰጡት፡፡ ንጉሡም ገለጠና አነበበው፡፡ እንዲህ ይል ነበር ‹‹ይህም ያልፋል››፡፡ ለምን? አላቸው ንጉሡ፡፡በየትኛውም የሥልጣንና የሀብት ከፍታ ላይ ብትሆን፣ በየትኛውም የዝናና የክብር ሠገነት ላይ ብትደላደል፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ግፍ አትሠራም፣ ፍትሕ አታዛባም፣ ድኻ አትበድልም፣ ከልክህም አታልፍም፡፡ ራስህን ዘላለማዊ አድርገህ ካሰብክ፣ ጊዜ የማይቀየር ዓለምም የማትዞር ከመሰለህ ግን ራስህን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ ሳታገኝ ነገሮች
Posted in Ethiopian News, Religion

ጾምና የዩኒቨርሲቲዎቻችን አስተዳደር

click here for pdfየሰኔ ጾም መግባትን ተከትሎ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የምግብ ክርክሮች መፈጠራቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ‹የጾም ምግብ ምግብ ይሠራልን› ብለው በሚጠይቁ ተማሪዎችና ‹ያቀረብንላችሁን ብቻ ብሉ› በሚሉ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች መካከል ነው ክርክሩ፡፡ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች ይህንን የተማሪዎችን ጥያቄ ላለመቀበል የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች ከሦስት የዘለሉ አይደሉም፡፡ የመጀመሪያው ሃይማኖታዊ አክራሪነትን ከመዋጋት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የአንድ ሰው መጾምና መጸለይ የአክራሪነት መመዘኛዎች መሆናቸውን የሚያሳይ ምንም ዓይነት መዝገበ ቃላት ሊቀርብ ባይችልም፡፡ መንግሥት መመሪያ ሰጠን እንዳይሉም መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች አክራሪነትን ለመተርጎም የሚያዘጋጃቸው መዛግብት ጾምን የአክራሪነት መግለጫ አድርገው ያቀረቡበት ጊዜ የለም፡፡ አክራሪነት፣ ሽብርተኛነት፣ ጽንፈኛነት የሚሉት ጽንሰ ሐሳቦች በጥንቃቄና ገደብ ባለው ሁኔታ የማይተረጎሙ ከሆነ ለመለጠጥና የተፈለገውን ሁሉ ለማካተት ምቹዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሐሳቦች ለተቋማትና ባለ ሥልጣናት ግላዊ ትርጎማ የተመቹ በመሆናቸው በማሳያዎች፣ በመግለጫዎችና ገደብ ባለው ሁኔታ መተርጎምን የሚጠይቁ ናቸው፡፡ በወጣቶች በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የእምነት አክራሪነት እንዳይፈጠር ከተፈለገ የእምነት አክራሪነትን ከዩኒቨርሲቲዎች ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ሁሉንም ሊያግባባ በሚችል ሁኔታ መተርጎምንና ግልጽ የሆኑ ማሳያዎችን
Posted in Ethiopian News, Religion

ከመጸዳጃ ቤቱ ፊት ለፊት

 click here for pdfአሜሪካ ዳላስ የሚኖር አንድ ወዳጄ ለትምህርት ከሠላሳ ዓመታት በፊት ፈረንሳይ እያለ የገጠመውን እንዲህ ነግሮኝ ነበር፡፡ ከዩኒቨርሲቲ ጓደኞቹ ጋር ምግብ ለመብላት ይወጣሉ፡፡ የገቡበት ምግብ ቤት ደረጃው ከፍ ያለ ነበር፡፡ የምግቡን ዝርዝር ያዩና ስሙ ደስ ያላቸውን ያዛሉ፡፡ ምን ዓይነት ነው? እንዴት ነው የሚሠራው? ምን ምን ያካትታል? የሚለውን የምግብ ማውጫ ዝርዝር ለማየት ዕድል የሰጠ ወይም አስተናጋጇን የጠየቀ ከመካከላቸው የለም፡፡ ሁሉም ያንኑ አዘዙ፡፡ አስተናጋጇም ጠረጲዛውን ካስተካከለቺ በኋላ በሰሐን ሙዳ ሙዳ ሥጋ በአራት መዓዝን ቆርጣ አመጣችና በየፊታቸው ከቢላዋና ከሹካ ጋር አስቀመጠች፡፡  ፊታቸው ፈካ፣ ሀገራቸው የተውት ጥሬ ሥጋ ፈረንሳይ ድረስ ተከትሎ በመምጣቱ ተገረሙ፡፡ ምናልባት አበሻነታችንን ዐውቃ ይሆን ጥሬ ሥጋ ያመጣችልን? ብለውም አሰቡ፡፡ አዋዜ ባለመኖሩ ቢያዝኑም  በቢላዋ እየቆረጡ ጠረጲዛው ላይ በነበረው ቁንዶ በርበሬ እየጠቀሱ ያጣጥሙት ጀመር፡፡ ናፍቆት አሳስቷቸው ባንዴ ሰሐኑን ባዶ አደረጉት፡፡ የጥሬ ሥጋውን ነገር እያነሡ ሲደሳሰቱ አስተናጋጇ እሳቱ የፋመበት አራት መጥበሻ ይዛ መጣች፡፡ ፈገግ ብላ መጥበሻዎቹ ያሉበትን ትሪ መሰል ነገር ጠረጲዛው ላይ ስታስቀምጠው ግን
Posted in Ethiopian News, Religion

‹አያሌው ሞኙ›

click here for pdf ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው መክዘ ከተነሡት ኃያላን መኳንንት አንዱ ናቸው፡፡ የራስ ብሩ ወልደ ገብርኤል ልጅና የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ ሲሆኑ የወገራ አውራጃ ሹም፣ የስሜን አውራጃ ገዥ፣ ልጅ ኢያሱ ከተያዙ በኋላ ደግሞ የንጉሠ ነገሥቱ ጦር አዛዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡   ደጃዝማች አያሌው ብሩ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ወደ ሥልጣን እንዲመጡ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት ሰዎች መካከል ናቸው፡፡ መኢሶ ላይ ከልጅ ኢያሱ ጦር ጋር በተደረገው ጦርነት ተፈሪ መኮንን እንዲያሸንፉ ደጃዝማች አያሌው ከፍ ያለ ሚና ነበራቸው፡፡ ራስ ጉግሣን ለመያዝ አንቺም ላይ በተደረገው ውጊያም የደጃዝማች አያሌው ጀግንነት ወሳኝ ነበር፡፡ እንዲያውም በዚህ ጦርነት ለሚያበረክቱት ውለታ የራስነትን ማዕረግ እንደሚያገኙ ከንጉሥ ተፈሪ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፡፡ በኋላ ግን በአንድ በኩል የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ በመሆናቸው፣ በሌላ በኩልም ከቀድሞዎቹ የዐፄ ምንሊክ ባለ ሥልጣናት ወገን ስለሆኑ ተፈሪ ቃላቸው አጠፉባቸው፡፡ከሁሉም በላይ ደጃዝማች አያሌውን ያሳዘናቸው በንጉሡ ግብዣ ላይ የነበራቸው ፕሮቶኮል መወሰዱ ነበር፡፡ እንደ ከፍተኛ መኳንንት በንጉሡ ቀኝ በኩል የነበራቸውን የክብር ወንበር ለራስ ደስታ እንዲለቁ መደረጉ
Posted in Ethiopian News, Religion

ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል

ደራሲ፡- ሮማን ፕሮቻዝካትርጉም፡- ደበበ እሸቱአሳታሚ፡-  ፀሐይ አሳታሚ ድርጅትቦታና ዘመን፡- ሎስ አንጀለስ፣ መጋቢት 2007ዋጋ፡- 10 ዶላርባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ ለሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ የኦስትሪያ ቆንስላ ውስጥ ተመድቦ ሠርቷል፡፡ ከአዲስ አበባ የወጣው ከዲፕሎማት ሥራውና መብቱ ጋር የሚፃረር ተግባር ሲያከናውን በመገኘቱ በ1926 ዓም ተባርሮ ነው፡፡ ፕሮቻዝካ Abyssinia the Powder Barrel" በሚል ርእስ በ1927 ቪየና ላይ አውሮፓውያን ትዮጵያን ሊወርሩና ሊይዙ የሚገባበትን ምክንያት የሚያቀርብ መጽሐፍ አሳተመ፡፡ መጽሐፉ ABISSINIA PERICOLO NERO (አቢሲንያ፡- ጥቁሯ አደጋ/ሥጋት) በሚል ርእስ የጣልያን ወረራ ከመጀመሩ አንድ ዓመት በፊት በ1927 ዓም በጣልያንኛ ተተርጉሞ ወጣ፡፡  ጣልያን ሀገሪቱን በወረረበት በ1928 ዓም ከወረራው ትንሽ ወራት ቀደም ብሎ በዋና ዋና የአውሮፓ ቋንቋዎች ተተርጉሞ እየታተመ ተሠራጭቶ ነበር፡፡ ፕሮቻዝካ ኢትዮጵያን አምርሮ የሚጠላ መሆኑን በጽሑፉ ሁሉ ይገልጠዋል፡፡ ነጮችን የሚጠሉ ሕዝቦች ያሉባት፣ የነጮች ክብርና መብት የማይጠበቅባት፣ ሥልጣኔ ያልጎበኛት፣ ብሔረሰቦች የሚጨቆኑባት፣ ጽዳት የሌለባት፣ አረመኔነት የነገሠባት፣ እምነቷ ከጥንቆላ ጋር የተቀላቀለ፣ ዜጎቿ ዓይናቸውን ጨፍነው ፎቶ የሚነሡ፣ መኳንንቱ ባዶ እግራቸውን የሚሄዱ፣ አንድነት የሌላት ሀገር መሆኗን ማስረጃ የሚለውን
Posted in Ethiopian News, Religion

ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በኢትዮጵያ ባሕል ውስጥ፡- <አቦ> እንደ ማሳያ

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ማን ናቸው? አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ ተክለ ሃይማኖት(EMML 3051) 18ኛው መክዘአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በ13ኛው መክዘ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ግብጻዊ ቅዱስ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መረጃዎች መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ የሚባለው በዐፄ ላሊበላ ዘመን ነው፡፡ የትውልድ ቦታቸው በላዕላይ ግብጽ ንሒሳ   (የአሁኑ ባሕቢት አል ሐጋራ) ነው፡፡ [በርግጥ አንዳንድ ሊቃውንት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው፤ ነገር ግን የወላጆቻቸው ስም በሚገባ ለመታወቅ ባለመቻሉ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እናታቸው አቅሌስያ (ቤተ ክርስቲያን)፣ አባታቸውም ስምዖን (ካህን) እንደተባሉና የዚህም ምክንያቱ ከቤተ ክርስቲያን የተገኙ ለማለት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አንድ መጽሐፈ ታሪክም ‹አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብጹዐን ወቅዱሳን ተወልዱ በኢትዮጵያ› ይላል፡፡EMML 5538,f 55]አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከ500 ዓመታት በላይ በዚህ ምድር ላይ መኖራቸውንና ከትግራይ እስከ ሸዋ ባለው ክፍል ተዘዋውረው ማስተማራቸውን፡፡ በዚህም ምክንያት ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስንና ምድረ ከብድ ገዳማትን መትከላቸውን ታካቸው ያሳያል፡፡ ያረፉት በዐፄ ሕዝብ ናኝ ዘመን
Posted in Ethiopian News, Religion

"እናቴን አደራ"

(ያሬድ ሹመቴ) አያልቅበት ስንታየሁ ሱዳን ውስጥ ለ3 ዓመት ያህል የኖረ የብርሀኑ ጌታነህ ወዳጅ ነው። የሚናፍቃቸውን እና ያላባት ብቻቸውን ያሳደጉትን፤ ለስደቱ ምክንያት የሆኑትን እናቱን ለማየት የዛሬ ዓመት ገደማ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ሱዳን በነበረበት ወቅት ከራሱ ተርፎ እናቱን ለመርዳት የሚልካት ጥቂት ገንዘብ በስተርጅናቸው ሰው ቤት ተቀጥረው የጉልበት ስራ ከመስራት አላዳናቸውም። ወይዘሮ አለሚቱ በላይነህ ልጃቸው ሱዳን ሳለ የሚልክላቸው ገንዘብ ከቤት ክራይ ክፍያ ውጪ የማይሸፍንላቸው ቢሆንም፤ ችግራቸውን ለልጃቸው ነግረው ከማሳቀቅ፤ በስተርጅናቸው የጉልበት ስራ ውስጥ ገብተው ኑሮዋቸውን በመከራ ተያይዘው ቆዪ። የእናቱ ነገር የማይሆንለት አያልቅበት፤ በናፍቆቱ ምክንያት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ግን ሱዳን እያለ ይልክ የነበረው ገንዘብ ምን ያህል የእናቱን ህይወት ፈቅ ማድረግ እንደተሳነው ተረዳ። የዚያን ጊዜ ታድያ ከሱዳን አድማስ ማዶ፤ እናቱን ለመጦር ይችልበት ዘንድ ተስፋ የጣለበትን የባህር ላይ ጉዞ ህልም ሰነቀ። ለልጆቹ ህይወት በእጅጉ ከሚጨነቀው የረዥም ጊዜ ወዳጁ ብርሀኑ ጌታሁን ጋርም ሀሳባቸው ገጠመ። ወደ ሊቢያም በጋራ ሊሻገሩ ተቃጠሩ። ልጆችን ለማሳደግና እናትን ለመጦር። አያልቅበት በሀምሌ 5፣ 2007
Posted in Ethiopian News, Religion

ትኩረት የሚሹት ሁለቱ የሰማዕቱ የብርሃኑ ልጆች

በግፈኛው አይሲስ ከተሠዉት ወንድሞች መካከል ብርሃኑ ጌታነህ የተባለው በአዲስ አበባ አቧሬ አካባቢ ይኖር የነበረው ወንድም ይገኝበታል፡፡ ብርሃኑ ከሀገሩ የወጣው ከአራት ወራት በፊት ሲሆን ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበረ፡፡ ቤተሰቦቹ እንደሚናገሩት ወደ ሱዳን ሲሄድ ለባለቤቱ የ3 ወር የቤት ኪራይ ከፍሎ ነበር የሄደው፡፡ ሁለቱ ልጆቹ የስምንትና የአራት ዓመት እድሜ ያላቸው ሲሆኑ ቤተሰቡ በችግር ላይ እንደሚገኝ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው መሐመድ ካሣ ማክሰኞ ምሸት ወደ አሜሪካ ልበር ስል ነግሮኝ ነበር፡፡ እስካሁን መርዶ የተረዱት የሰማዕታቱ ቤተሰቦች ወላጆች፣ እኅቶች ወይም ወንድሞች ሲሆኑ ብርሃኑ ግን ባለቤቱና ገና ክፉና ደግ ያልለዩት ሁለቱ ልጆቹ ናቸው የተረዱት፡፡ ፎቶ፡- ያሬድ ሹመቴከሰማዕታቱ ቤተሰቦች መካከል ይበልጥ ትኩረት የሚፈልጉት እነዚህ ምንም የማያውቁ ሕጻናትና እናታቸው ናቸው፡፡ መማር፣ ተምሮም ማደግ አለባቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ መኖሪያ ቤትና የትምህርት ቤት ክፍያ ይፈልጋሉ፡፡ እናታቸውንም በሥራ ማሠማራት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም የክፉዎቹ ሥራ ውጤት እንዳይኖረው እነዚህን ሁለት ሕጻናትና እናታቸው እንርዳ፡፡ ቤታቸው አቧሬ አድዋ ድልድይ አካባቢ ነው፡፡  ጉዳዩን በሚገባ ለመረዳትና ርዳታውን ለማስተባበር መሐመድ ካሣን ብታነጋግሩት
Posted in Ethiopian News, Religion

ጀማል ማነው?

‹ጀማል› የተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየት ‹ጀማል› የተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡ ፍቅሩ  ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡ ‹ጀማል› ነው ተብሎ ሲነገርለት የነበረው ወንድማችን ግን ኤፍሬም የተባለ ኤርትራዊ፣ ቃኘው ሠፈር ይኖር የነበረ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለት መርዶ እንደመጣባቸው እየገለጡ ነው፡፡ በአንድ በኩል በአሰቃቂ ሁኔታ በአይሲስ መሠዋቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ‹ሙስሊም› ነው መባሉ ነው፡፡ ኖርዌይ የነበሩ ኤርትራውያን ክርስቲያኖች ወዲያው ነበር ነገሩን የተቃወሙት፡፡ ነገር ግን አሥመራ ያሉት ቤተሰቦቹ እስኪረዱ ድረስ ትክክለኛ ስሙን ለመግለጥ አልተፈለገም፡፡ በዚህ መዘግየት የተነሣም ብዙ የፈጠራ ታሪኮች ተፈጠሩ፡፡ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች በላኩልኝ የውስጥ መልእክት የጀማልን ሙስሊምነት መካድ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ያላቸውን ድጋፍና ፍቅር መካድ ነው ሲሉ ገልጠዋል፡፡ ለእኔ ግን ከተፈጠረው ‹ጀማል› ይልቅ
Posted in Ethiopian News, Religion

እየተስተዋለ

click here for pdf እነዚህ ወገኖቻችን ሰማዕታት ናቸው፡፡ ሃይማኖታቸውን አንለውጥም ብለው የተሠዉ፡፡ ‹ስደተኛ ኢትዮጵያውያን› የሚለውን አገላለጽ ነፍሴ ትጸየፈዋለች፡፡ ከአኩሪው የሰማዕትነት ተግባራቸው በላይ ስደተኛነታቸው ለማጉላት ስለሚያኮበኩብ፡፡ ሰው በሀገሩ ቢኖር፣ ቢሠራና ቢከብር የመጀመሪያ ምርጫው ነው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያውያን፡፡ ነገር ግን ‹እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል› ይባላልና የቸገረው ቢሰደድ ምን ይፈረድበታል? በርግጥ ስደቱ በሰላም፣ በሕግና በጤና ቢሆን የማይወድ የለም፡፡ ግን ሁል ጊዜ ይቻላል ወይ? ምቹ ሁኔታስ አለ ወይ? ዛሬ ከአውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራልያ፣ ከአፍሪካና እስያ ገንዘባቸውን እየላኩ አንዳንዴ ከቡና በላይ አንዳንዴም ከቡና ቀጥሎ የውጭ ምንዛሬውን የሚያስገኙልን ወገኖች አብዛኞቹ ዛሬ ‹ሕገ ወጥ› በምንለው መልኩ የሄዱ አይደለም ወይ? እንዲያ እንዲሆኑ ያደረጋቸውን መሠረታዊ ምክንያት መፍታት እንጂ የሆኑበትን መንገድ ማውገዝ ምን ይጠቅማል?   በሀገራችን ኢትዮጵያ እየኖሩ በአክራሪዎችና አሸባሪዎች ሕይወታቸው የተሠዉ ክርስቲያኖች አልነበሩም ወይ? በ1980ዎቹ መግቢያ በአሰቦት ገዳም የታረዱት መነኮሳት፣ በአርሲ ኮፈሌ የተገደሉትን ምእመናንና በ1998 ዓ.ም. በጅማ በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተሠዉት ምእመናንና ካህናት ስደተኞች ሆነው አልነበረምኮ? ክርስቲያን ስለሆኑ እንጂ፡፡ በአይሲስ እጅ
Posted in Ethiopian News, Religion

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን!ዘሰ አምነኒ በቅድመ ሰብእ አነኒ አአምኖ በቅድመ አቡነ ዘበሰማያት በሰው ፊት ያመነኝን ሰው እኔም በሰማያዊ አባቴ ፊት አምነዋለሁ የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል 10÷32ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተከበራችሁ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት ወጣቶችምእመናንና ምእመናትቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ መሥዋትነት አብሯት የኖረታሪክ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም በልዩልዩ ዘመናት ልጆቿ በግፍ ተገድለው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡በስድስተኛው ክፍለ ዘመን በናግራን፣ በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በዮዲት ጉዲት፣ በዐሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ አሕመድ፣ በዐሥራ ዘጠነኛውና ሃያኛው ክፍለ ዘመን በውጭ ወራሪ ኃይሎች በርካታ የሰማዕትነት ታሪኮች አልፈዋል፡፡ይሁን እንጂ በሁሉም ዘመን የተነሡባት አሳዳዶችና ገዳዮች ከነታሪካቸው ሲጠሩ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአምላኳ ጥበቃና በልጆቿ ጽናት ሰማዕታቷን አክብራ ለሰውልጅ መንፈሳዊ ሀብትን እያደለች አሁንም አለች ወደፊትም ትኖራለች፡፡ዛሬ እነዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወጣቶች በጠባቡ በር ተጉዘው በደማቸው ማሕተም ወደ መንግሥተ ሰማያት የገቡ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የክርስትና እምነት ጽኑ ምስክሮች ናቸው፡፡  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Posted in Ethiopian News, Religion

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

click here for pdf ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም.እስመ በእንቲኣሁ ይቀትሉነ ኲሎ አሚረ፡፡ ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን:: መዝ.43፡22 ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ ነው፡፡ ይህንንም ስንል ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ምንም በደል ሳይገኝበት በአይሁድ ተከስሶ በግፍ የሞት ፍርድም ተፈርዶበት በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ የሰው ልጆችን ዕዳ በደል ደምስሶ ነጻ እንዳወጣንና ዘለዓለማዊ ሕይወትን እንዳደለን በማመን እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ በማለት በሰጠው አምላካዊ ትእዛዝ መሠረት ትመራለች ማለታችን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንም ይህንኑ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት አምነው በሥራ ሲገልጡ ኑረዋል፤ ዛሬም በዚሁ እውነታ ይገኛሉ፡፡ስለእውነት መሥዋዕትነት መክፈል ለቤተ ክርስቲያን እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ በየዘመናቱ እግዚአብሔር ለዚህ ክብር ያደላቸው ቅዱሳን ሰዎች የጌታን ፈለግ ተከትለው ስለክርስትናቸው ወይም በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ በማመናቸውና ይህንንም በይፋ በመመስከራቸው ብቻ በክፉዎች ሰዎች እጅ በሥጋቸው መከራ እየደረሰባቸው ለሞት
Posted in Ethiopian News, Religion

እግዜር ያተረፋት ነፍስ ምስክርነት

አሁን ከማልታ ባገኘሁት መረጃ በቀደም ከተሠዉት ወንድሞቻችን ጋር የነበረ ፣በእግዚአብሔር ቸርነት አምልጦ ትሪፖሊ የገባ ወንድም አግኝቼ ነበር፡፡እርሱ እንደነገረኝ በአጅዛቢያና ቤንጋዚ መንገድ ላይ የአይሲስ አራጆች የሊቢያ መንግሥት ወታደሮችን ዩኒፎርም  ለብሰው በዚያ የሚያልፉትን ለመያዝ ይጠብቃሉ፡፡ በአካባቢው ወደ ትሪፖሊ የሚጓዙ መንገደኞችን ሲያገኙ ይይዛሉ፡፡ ሱዳኖችንና ሶማልያውያንን ሙስሊሞች ናቸው ብለው ስለሚያስቡ ወዲያው እንዲሄዱ ይለቋቸዋል፡፡ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያንን ግን ለብቻ ይይዛሉ፡፡ ከዚያም ሙስሊሞችን ለብቻ ክርስቲኖችን ለብቻ ያሰልፏቸዋል፡፡ በመቀጠልም ክርስቲያኖችን በኮንቴይነር ውስጥ ከትተው ወዳልታወቀ ሥፍራ ይወስዷቸዋል፡፡ ምግብ የሚሰጧቸው በየሦስት ቀን ነው፡፡ሙስሊሞችን ደግሞ ይለቋቸዋል፡፡በቀደም ዕለት አይሲስ በባሕር ዳርቻ የሠዋቸው ክርስቲያኖች በሰውነታቸው ላይ የመስቀል ምልክት የነበረባቸውን መርጦ ነው፡፡ እነርሱን በተለየ ኮንቴይነር አስቀምጧቸው ነበር፡፡ ይኼንን መረጃ የነገረኝ ሰው ሊገደሉ ተመርጠው ከተለዩት ወገን ነበረ፡፡ ሌሎች በኮንቴይነር ያስቀመጣቸው ክርስቲያኖችም አሉ፡፡ ምናልባት ከዚህ የከፋ ዜና እንሰማ ይሆናል፡፡ አምላክ ይጠብቀን፡፡ አሁንም የአይሲስ አራጆች የመንግሥት ወታደሮችን ልብስ ለብሰው ሌሎች ስደተኞችን እየያዙ ነው፡፡ይኼ መረጃንውን ያደረሰኝ ሰው ሊያመልጥ የቻለው ሌሎች ክርስቲያኖችን በጨለማ ወደ ኮንቴይነሩ ለማስገባት ኮንቴይነሩን በከፈቱበት ጊዜ
Posted in Ethiopian News, Religion

ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን ሰማዕታት

click here for pdf በተለያዩ የባለ ሥልጣናትና የእምነት መሪዎች መግለጫዎች ላይ በሊቢያ ምድር የተሠዉትን ሰማዕታት በኢትዮጵያዊነታቸው ወይም በስደተኛነታቸው ብቻ አደጋ እንደደረሰባቸው ተድርጎ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተሠዉትም እምነታቸውን አንለውጥም ስላሉ ነው፡፡ አይሲስ የሠዋቸው በኢትዮጵያዊነታቸው አይደለም፡፡ አይሲስኮ ዜግነት የለውም፡፡ ዐረቦች፣ አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እስያውያን የተቀላቀሉት አሸባሪና አሰቃቂ ድርጅትና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ባለፈው ሰሞን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዝ ወደ አይሲስ ለመግባት ያደረጉትን ጥረት በመገናኛ ብዙኃን ሰምተን ነበር፡፡ አይሲስ አገር የለውም፡፡  እነዚህ ወንድሞቻችንማ ማተብ የሚያደርጉበትን አንገት ለእምነታቸው ሲሉ የሰጡ ቅዱሳን ሰማዕታት ናቸው፡፡ እኛ በቃል ብቻ የምንናገረውን ሰማዕትነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን በተግባር ያሳዩ የተግባር ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ምናልባት ባለ ሥልጣናቱና ሚዲያዎቹ ይህንን ለመናገር የከበዳቸው ሌሎች አማኞችን እናስከፋለን ብለው አስበው ይሆናል፡፡ እውነት ለመናገር ግን በግድ ሃይማኖታቸውን ወደ እስልምና (ያውም አይሲስ ወዳጣመመው የእስልምና አመለካከት) መቀየር ነበረባቸው ብሎ የሚከራከር ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡ ቢኖርም አመለካከቱን እንዲፈትሽ ማድረግ እንጂ እርሱን ላለማስቀየም እውነቱን መካድ አያስፈልግም፡፡የአይሲስን ሐሳብ ተቀብለው፣ እምነቱን
Posted in Ethiopian News, Religion

የጎንደር ከተማ መንፈሳውያን ወጣቶች የአሸባሪው የአይሲስን ኢሰብአዊ ድርጊት አወገዙ፡፡

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የመንፈሳውያን ወጣቶች ማኅበራትና የማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማዕከል አባላት በላኩት መግለጫ በአሸባሪውና አረመኔው አይሲስ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን ጭካኔ አውግዘዋል፡፡ በመግለጫው ላይ እንደተገለጠው ‹‹‹‹ISIS›› የሽብር ቡድን 30 ኢትዮጵያውያንን ክርስቲያን በመሆናቸውና ሃይማኖታችንን አንቀይርም በማለታቸው ርህራሄ በጎደለው ሁኔታ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላትና በጥይት በመደብደብ የፈጸመው ዘግናኝ ተግባር  ኢትዮጵያዊነትን የሚፈታተን፣ ታላቅ ኀዘንን በክርስቲያኖች ላይ ፈጥሯል፡፡›› ብሏል፡፡ በማያያዝም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው ሊደረጉ ይገባል ያሏቸውን አራት ሐሳቦች ለሀገረ ስብከቱ አቅርበዋል፡፡የመግለጫውን ሙሉ ቃል ቀጥሎ መመልከት ይቻላል፡፡   ይህንን በመጫን መግለጫውን ያንብቡይህንን በመጫን መግለጫውን ያንብቡ 
Posted in Ethiopian News, Religion

የሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ታወጀ

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ከነገ ሚያዝያ 14 ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፡፡ቅዱስ ሲኖዶስ በአሸባሪዎች የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ባወጣው ባለ ዘጠኝ ዐንቀጽ መግለጫ ለሰማዕታቱ ተገቢውን ቀኖናዊ ክብር እንደሚሰጥ ገልጧል፡፡ ለዚህም የሰማዕታቱን ቤተሰቦች የመረጃ ትብብር ጠይቋል፡፡ ‹‹የጀግና እናት አታለቅስም›› ያለው መግለጫው የሰማዕታቱ ቤተሰቦች የልጆቻቸው ሰማዕትነት በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ስላለው በዚህ እንዲጽናኑ አደራ ብሏል፡፡ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ከመንግሥት ጋር አብሮ የሚሠራ ዐቢይ ኮሚቴ እንደሚያቋቁምም ገልጧል፡፡መግለጫውን ቀጥሎ ያንብቡትበተያያዘ ዜና ዛሬ ከሰዓት ዐሥር ሰዓት ላይ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ ሰማዕታቱ ቤተሰቦች በመሄድ ጸሎት እንደሚያደርጉና እንደሚያጽናኑ ተነግሯል፡፡  ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲህ ሲሠራ ‹ሲኖዶስ ሲኖዶስ› ይላል፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ቂርቆስ በኀዘን ማቅ

click here for pdfዛሬ እኩለ ቀን ላይ ከፖኤቲክ ጃዝ አባላትና ከሌሎች የኪነ ጥበብ ሰዎች ጋር ወደ ቂርቆስ ሄጄ ነበር፡፡ ያቺ ሳቂታዋና ተጫዋቿ ቂርቆስ ኀዘን ወርሯታል፡፡ የቂርቆስን ልጆች አውቃቸዋለሁ፡፡ ማልታ፣ ግሪክ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ስዊዘርላንድ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ መሳቅ ነው፣ መጨዋት ነው፡፡ መቀለድ ነው፡፡ ችግር እነርሱ ጋር የለም፡፡ ካገኙ ተካፍለው ካጡ ተሳስቀው ያልፉታል፡፡ መተዛዘን፣ መረዳዳት፣ ነገር ማቅለል ማን ይችላቸዋል፡፡ እንግሊዝ ሀገር የደረሱት በመንገድ ያለቁትን የሚያስቡበት ዓመታዊ የመታሰቢያ ቀን አላቸው፡፡ ከቂርቆስ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱይላሉ የማልታ ልጆች፡፡ ዛሬ ያ ሁሉ ሳቅና ጨዋታ በኀዘን ተቀይሯል፡፡ የልጆቻቸውን መሞት በቪዲዮ በተመለከቱ ወላጆች፣ ማንነታቸውን ከቪዲዮው ለመለየት አቅቷቸው በሰቀቀን ውስጥ በሚገኙ ወላጆች፣ የልጆቻቸውን መረጃ ፈልገው መልስ ባጡ ወላጆች ቂርቆስ ተሞልታለች፡፡ ትጠይቃለች፤ መልስ ግን አላገኘችም፡፡ እንዴት ያለው ትምህርት፣ እንዴት ያለው ጥበብ፣ እንዴት ያለው ብልሃት እንደሚያጽናናት እንጃ፡፡  እኔ በልቅሶ ቤት ሄጄ ብዙም አላለቅስም፡፡ ዛሬ ግን አለቀስኩ፡፡ በተለይ የባልቻ እናት ‹ፍቅር እስከ መቃብር› እያሉ ሲያለቅሱ ስሰማ ዕንባዬን መቆጣጠር
Posted in Ethiopian News, Religion

ወደ ባሕላችንና እምነታችን ስንመለስ

 click here for pdfበሊቢያ ምድር እምነታቸው ወንጀል ሆኖባቸው በአይሲስ የተሠዉትን ሰማዕታተ ሊቢያ በተመለከተ መንግሥታዊና የሃይማኖት ተቋማት ሊያደርጉ ስለሚገባው ነገር ስንለው ስንለው ቆየን፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ባሕላችንና እምነታችን እንመለስ፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን ስማቸውንና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን የምታውቁ ንገሩን፡፡ በባሕላችን መሠረት ልቅሶ እንድረሳቸው፡፡ ኀዘናቸው እነርሱ ብቻ አለመሆኑን እንንገራቸው፤ መከራቸውን እንካፈላቸው፡፡ እንደ ባሕሉ ማድረግ ያለብንን እናድርግ፡፡ ይኼ ከዘወትሩ ኀዘን ይለያል፡፡ የተሠዉበት ምክንያት፣ የተሠዉበት ሁኔታ፣ ለመሥዋዕትነት ያቀረቧቸው አሸባሪዎች ማንነት ከዘወትሩ ይለያቸዋል፡፡ ኀዘኑ የወላጅ፣ የዘመድ የመንደር፣ የዕድር ብቻ አይደለም፡፡ ከፕሬዚዳንቱ እስከ እኔ ላለነው ሁሉ ኀዘን ነው፡፡ ስለዚህም እንደየአመቺነቱ ከፕሬዚዳንቱ ጀምሮ በየደረጃው ያለን እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ልቅሶ እንድረስ፤ ሰውነታችንን፣ ለዜጎቻችን ያለብንን ኃላፊነት፣ ለቤተሰቦቹ ያለንን የመጽናናት ምኞት በመግለጫ ብቻ ሳይሆን በባሕሉ መሠረት እንግለጠው፡፡ ፖለቲካዊ ዲስኩሩን፣ ነጥብ ለማስቆጠር መጨቃጨቁን፣ የተለመደ ቢሮክራሲያዊ አሠራሩን ትተን ወደ ባሕላችንና እምነታችን እንመለስ፡፡ ባሕል የሌለን እምነት የሌለን አንምሰል፡፡ ለእንደዚህ ያለ ወቅት የሚሆን ወግና ሥርዓት አለን፡፡  ያለ ወግ የመየጣውን ዕዳ በወግ እንክፈለው፡፡ ታዋቂ ሰዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት
Posted in Ethiopian News, Religion

ከኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

በትናትናው ዕለት ISIC የተባለው አሸባሪ ቡድን ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን መረጃዎች በተለያዩ የብዙሀን መገናኛዎች መውጣት መጀመራቸውንና መረጃውን ለማጣራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ከመንግስት ተገልጻል። የተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ አስነዋሪና አረመኔያዊ ድርጊት በመሆኑ መንግስት በምሬት እንደሚያወግዘው መግለፁ ይታወሳል።በአሁኑ ጊዜ የሟቾቹ ምስል እየተጣራ ከተለያዩ አካላትም ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋግጧል።የኢትዮጵያ መንግስት በንፁሀን ዜጎቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት በእጅጉ ማዘኑን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።ቀጣይ መንግስት የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚገለፁ ሲሆን በነገው ዕለትም የሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትየሚሰበሰብ ሲሆን በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በገፍ ለተገደሉ ዜጎቻችን የ3ቀናት የሀዘን ቀን እንደሚታወጅና በመላው ሀገራችንና በኢትዮጵ ኢንባሲዎች ባንዲራችን ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ውሳኔ ያሳልፋል።በትናትናው ዕለት እንደተገለፀው መንገስት አስቀድሞ የጀመረውን የፀረ ሽበር ትግል አጠናክሮ የሚቀጥልበት ሲሆን በንጹሀን ላይ የደረሰው የሽብር አደጋ ለአፍታም ቢሆን ከጀመረው ትግል እንደማያዘናጋው ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማረጋገጥ ይወዳል። በዚህ አጋጣሚ መላው የሀገራችን ዜጎች በፀረ ሽብር ላይ የከፈትነውን ዘመቻ አጠናክረን እንድንቀጥልበት መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።  የእኔ ሐሳብየተወካዮች ምክር
Posted in Ethiopian News, Religion

ሰማዕታተ ሊቢያና የሲኖዶሱ መግለጫ

click here for pdfየቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ በቃ፡፡  ደግሞስ ‹የዜግነትና የማንነት መረጃውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው› የሚሉን ማነው ጥረት እያደረገ ያለው? መንግሥት ነው ካላችሁ ‹መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው› በሉ እናንተም ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ ንገሩን፡፡ ቤተሰቦቻቸውኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ ለምን ለየሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመስጠት
Posted in Ethiopian News, Religion

ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ በአሸባሪው አይሲስ እጅ በሰማዕትነት የተሠውትን ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ዛሬ ጠዋት 5፡30 ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከውጭ ሀገር ጉዞ ቀርተው በመንበረ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ የሰጡ ሲሆን ሌሎች የእምነት ተቋማትም ተመሳሳይ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡  መግለጫውን ተመልከቱት፡፡ 
Posted in Ethiopian News, Religion

የምናዝነው ስንት ሰው ሲሞት ነው?

በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡  ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው? ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም
Posted in Ethiopian News, Religion

ኢትዮጵያውያኑ ሰማዕታት

ዛሬ የዓለም መገናኛ ብዙኃን የ30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በኢስላሚክ ስቴት በሰማዕትነት መገደል ሲዘግቡ ነበር፡፡ ሰው በእምነቱ ብቻ ሰማዕትነት የሚከፍልበት ዘመነ  ሰማዕታት አንደገና ታድሶ እየተነሣ ነው፡፡ ትናንት ግብጻውያን ምእመናን የከፈሉትን ሰማዕትነት ዛሬ ኢትዮጵያውያኑ ከፍለውታል፡፡ ክርስቲያን መሆን ወንጀል ሆኖ፡፡  ሰማዕታቱስ ወደሚወዱት ጌታ ሄደዋል፡፡ ይህ ጊዜ ግን የኢትዮጵያ መንግሥትና የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት የሚፈተኑበት ጊዜ ነው፡፡ የግብጽ መንግሥትና የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለግብጽ ሰማዕታት ያደረጉትን በቅርብ ዓይተናል፡፡ የኛዎቹ በሚዛን የሚመዘኑበት ወይ ቀልለው ወይም ከብደው የሚገኙበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ እግዚአብሔር ከሰማዕታቱ በረከት ይክፈለን፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የሳይንቲስቱ ልጅ ጥያቄ

click here for pdfባለፈው እሑድ፣ የትንሣኤ ዕለት ማልዳ ነው ከዕንቅልፏ የተነሣቺው፡፡ እናቷ ቤተ ክርስቲያን አድራ፣ አባቷ ደግሞ ሌሊት ከውጭ ሀገር ገብቶ ደክሟቸው እንደተኙ አልተነሡም፡፡ እርሷም በጠዋት የተነሣቺው ጓደኛዋ አደራ ስላለቻት ነው፡፡ ‹‹የቴሌቭዥን የትንሣኤ ፕሮግራም የተቀረጸው እኛ ቤት ነው›› ብላ አጓጉታታለቺ፡፡ የተነሣቺው ጓደኛዋን በቴሌቭዥን ለማየት ስትል ነው፡፡ ደግሞ ‹ዘፈን ምናምን አቅርቤያለሁ› ብላታለቺ፡፡ የጓደኛዋ አባት ‹ፍቅር እዚህም እዚያም›፣ ‹ትሄጅብኛለሽ› እና ‹ፍቅር በኪችን ውስጥ› የተሰኙ ሦስት አስቂኝ የፍቅር ፊልሞች ላይ የሠራ ‹ታዋቂ አርቲስት› ነው፡፡ ጓደኛዋ እንደነገረቻት ከሆነ የበዓሉ ፕሮግራም እነርሱ ቤት ሲቀረጽ የቀረ አርቲስት የለም፡፡ በዓሉ ራሱ ሕዝቡን ሊያዝናና ስለማይችል ‹ዘና እንዲያደርጉት› ተብሎ ቀልደኞቹ ሁሉ እነርሱ ቤት መጥተው ነበር፡፡  ከቀረፃው ማግሥት ጓደኛዋ ትምህርት ቤት ስትመጣ የታዋቂ አርቲስቶችን ፊርማ በየደብተሯ ሰብስባ መጥታ ጓደኞቿን ሁሉ ስታስቀናቸው ነበር፡፡ በርግጥ ክፍል ውስጥ እርሷና ጓደኞቿ ትምህርታቸውን ረስተው የአርቲስቶችን ፊርማ ሲያደንቁ ያዩዋቸው መምህራቸው እንደ መገሰጽ ቢያደርጉም፣ እንደመስማት ያላቸው ተማሪ ግን አልነበረም፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው ታዋቂ አይደሉማ፡፡ ደግሞ መምህር ከመቼ ወዲህ
Posted in Ethiopian News, Religion

ግብረ ሕማማት

click here for pdf በቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሕይወት ውስጥ ታላቅ ቦታ ካላቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ‹መጽሐፈ ግብረ ሕማማት› ነው፡፡ ሊቃውንቱ ‹ግብር› የሚለውን ‹አገልግሎት› ብለው ይተረጉሙትና ‹ግብረ ሕማማት› ማለት ‹በሕማማት ወቅት የሚፈጸም አገልግሎት› ማለት ነው ይላሉ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹እርሱ ሕመማችንን ተሸከመ›(ኢሳ 53÷4) በማለት የገለጠው ኃይለ ቃል ለሰሙኑም ሆነ ለመጽሐፉ ስያሜ መነሻ መሆኑንን ሊቃውንቱ ይገልጣሉ፡፡ ሐዋርያትም በሥርዓት መጽሐፋቸው ‹ወአንትሙሰ ተዐቀቡ ወግበሩ ተዝካረ ሕማማቲሁ - እናንተ ግን ተጠበቁ፣ የሕማማቱንም መታሰቢያ አድርጉ› ብለው ደንግገዋል (ግብረ ሕማማት፣ 1996፣9)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ‹ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማተ ወልዱ ክብረ ወስብሐተ - የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና ብሎ የጠራ እግዚአብሔር ይመስገን› ብሎ ገልጦ ነበር፡፡ (ዝኒ ከማሁ፣10)  ግብረ ሕማማት ከበዓለ ሆሳዕና እስከ በዓለ ፋሲካ የሚከናወነውን ሥርዓት የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነው፡፡ የመጽሐፉ የተወሰነ ክፍልና ሥርዓቱ ከ8ኛው መክዘ ቀደም ብሎ ጀምሮ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነበረ፡፡ አሁን ያለውን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የሰሙነ ሕማማት መጽሐፍ (ፓሻ) ያዘጋጁት አቡነ ገብርኤል 2ኛ(1131-1145) የተባሉት የግብጽ ቤተ ክርስቲያን
Posted in Ethiopian News, Religion

ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት

በግእዝ የተጻፉ ጥንታውያን መዛግብት ከተጻፉበት ዓላማ በተጨማሪ ሌሎችንም አገልግሎቶች ሲሰጡ ኖረዋል፡፡ አብዛኞቹ የተጻፉት ለሃይማኖት ማስተማሪያነትና ለታሪክ መመዝገቢያነት ቢሆንም በየዘመናቱ የተፈጠሩትን ማኅበራዊ ክስተቶች ተከትለው ሌሎችንም አገልግሎቶች ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ አንደኛውን እንመለከታለን፡፡ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እንደ ሰነዶች  ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ሆነው ሲያገለግሉ የኖሩበትን አሠራር፡፡ በጥንታውያን የግእዝ የብራና  ጽሑፎች  ላይ ከሃይማኖታዊና ታሪካዊ ይዘቶች በተጨማሪ በመጻሕፍቱ መጀመሪያና መጨረሻ በሚኖሩ ባዶ የብራና ቅጠሎች፣ በኅዳጎች፣ በራስጌና  በግርጌ ክፍት ቦታዎች ላይ ውሎችን፣ ቃል ኪዳኖችንና ስጦታዎችን ሲመዘግቡ ኖረዋል፡፡ እነዚህ ምዝገባዎች በተዋዋዮቹ፣ በገዥዎቹና  ሻጮቹ፣  በስጦታ ሰጭዎቹ ወዘተ መካከል የሚኖሩትን ስምምነቶች በማስፈር እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት እየሆኑ ማገልገላቸውን ያሳዩናል፡፡( ጥናታዊ ጽሑፉን ቀጥሎ ካለው የፒዲኤፍ ፋይል ይመልከቱ)click here for pdf
Posted in Ethiopian News, Religion

የአድዋ ዘማቾች

click here for pdf የጉዞው መሥራቾችትናንት(እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓም) በጨጨሆ የባሕል ምግብ አዳራሽ በተደረገ አንድ መርሐ ግብር ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር፡፡ ‹ጉዞ አድዋ› ይባላል መርሐ ግብሩ፡፡ ከዛሬ 119 ዓመት በፊት ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓለም ታሪክ ያልተለመደ አዲስ ታሪክ ለመሥራትና ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የማይደረስበት ከፍታ ላይ ለማስቀመጥ ሲሉ ከመላዋ ሀገሪቱ አንድ ሆነው ወጥተው፣ አንድ ሆነው ወደ አድዋ ዘምተው ነበር፡፡ ያኔ ብዙዎቹ የተጓዙት በእግራቸው ጋራ ሸንተረሩን፣ አረሁን ገደሉን እየተሻገሩ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሀገራዊ ፍቅር ነበር፡፡ ያ አንድነትና የሀገር ፍቅር ስሜት ነበር ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችንን ሊደግሙት እንጂ ሊረሱት የማይገባ ታሪክ እንዲሠሩ ያደረጋቸው፡፡ይህንን የአድዋ መንፈስና ዝና፣ ክብርና ላቅ ያለ ኢትዮጵያዊነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ፤ አድዋ እንደ አንድ ተራ ሥነ ሥርዓት በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ከማስቀመጥና ‹አስቦ ከመዋል› የዘለለ ትውልዳዊ ፋይዳ እንዲኖረው ለማድረግ፤ አድዋ እንደ ባለሞያ ጠጅ በየጊዜው ከጥንስሱ እየተቆነጠረ በየትውልዱ እንዲጠጣ ለማስቻል፤ እንደ ሰራፕታ ዱቄት በየዘመናቱ ቡኾ ውስጥ እንደ እርሾ እየተጨመረ እንዲበላ ለማብቃት፣ አድዋ
Posted in Ethiopian News, Religion

እነሆ አምስት ዓመት

click here for pdf የዳንኤል ዕይታዎች የጡመራ መድረክ ከተጀመረ እነሆ ዛሬ መጋቢት 14 ቀን 2007 ዓም አምስተኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡ በዚህ ጉዞ ውስጥ፣ ተማምረናል፣ ሐሳብ ተለዋውጠናል፣ ተገዳድረናል፣ ተሟግተናል፣ ተወቃቅሰናል፣ ተሰናዝረናል፡፡ ሁሉም ግን ለበጎ ሆኗል፡፡ የጉግል መረጃ እንደሚያሳየው እስከ ዛሬ ድረስ 11.1 ሚልዮን ሰዎች የጡመራውን መስኮት ጎብኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ በ114 ሀገሮች የሚገኙ አማርኛ አንባቢዎች ዓይናቸው የጣሉ ሲሆን እንደ ቅደም ተከተላቸው አሥር ከፍተኛዎቹ ጎብኝ ሀገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ዩናይትድ ስቴት አሜሪካ፣ ሕንድ፣ ጀርመን፣ ካናዳ፣ የተባበሩት የዓረብ ኤምሬቶች፣ ራሽያና አውስትራልያ፡፡ አንባቢዎቻችን ያሉባቸው ሀገሮች ደግሞ እነዚህን ይመስላሉ፡- 1. Ethiopia, 2. United States 3. Indonesia 4. Germany 5. Canada 6. Norway 7. Ireland 8. United Kingdom 9. (not set) 10. India 11. Sweden 12. Italy 13. Australia 14. Netherlands 15. Switzerland 16. United Arab Emirates 17. Nigeria 18. South Africa 19. France 20. Saudi Arabia 21. Eritrea 22. Kenya 23. Belgium 24. Denmark 25. South Korea
Posted in Ethiopian News, Religion

የአማርኛ ቋንቋ ከየት ወዴት፤ ተግዳሮቶቹና መፍትሔዎቹ

 click here for pdfየባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋምን አሠራር በተመለከተ ለተዘጋጀው ጉባኤ የቀረበ  ባሕር ዳር የካቲት 3-5 ቀን 2007 ዓም የአማርኛ ቋንቋ ታሪካዊ ጉዞየአማርኛ ቋንቋን ጉዞ በአጭሩ ለመመልከት እንድንችል፣ የዚህን ታላቅ ጉባኤ ጊዜንም ላለመውሰድ በአምስት ምዕራፍ ማየቱ ይጠቅማል ባይ ነኝ፡፡ እነርሱም1.    ከጥንት እስከ 13ኛው መክዘ2.   ከ13ኛው መክዘ እስከ 16ኛው መክዘ3.   ከ16ኛው መክዘ እስከ ዘመነ ቴዎድሮስ4.   ከዘመነ ቴዎድሮስ ዘመነ ምኒሊክ5.   ከዘመነ ምኒሊክ እስከ አሁን  1.   ከጥንት እስከ 13ኛው መክዘ አማርኛ በዚህ ዘመን እንዲህ በሚባል ሕዝብ መነገር ጀመረ ብሎ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ያጠኑት ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ አገኛኘቱን በተመለከተ እስካሁን ቦታ ይዘው የሚከራከሩ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው፣ በሰፊው የሚነገረውና ለብዙ ዓመታት የቆየው አመለካከት አማርኛ ከሌሎች ቋንቋዎች ተቀይጦ ምናልባት በ4ኛው መክዘ አካባቢ ከአኩስም ወደ ደቡብ በመጡ ዘማቾችና አዝማቾች አማካኝነት የተፈጠረ(pidgin theory) ነው የሚል ሲሆን በዚህ መላ ምት መሠረት ከሰሜን ወደ ደቡብ እየተስፋፋ የመጣ፤ ከግእዝ ትንሽ ለየት ያለ ሴማዊ ቋንቋ በሚናገሩ አዝማቾችና የኩሽ፣ የኦሞና የዓባያዊ ቋንቋዎች
Posted in Ethiopian News, Religion

ሸዋ ረገድ ገድሌ

click here for pdf የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌበጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌበጥይት ገዳይ ነጭ ብርገድሌየሴት ወንድ ናት ሸዋረገድ ገድሌተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ የጠላት ወረራ ጊዜም አኩሪ ጀብዱ የፈጸሙትን የአርበኛዋን የሸዋረገድ ገድሌን ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ ሰሞኑን ቀርቧል፡፡ ‹ሸዋ ረገድ ገድሌ፣ የአኩሪ ገድላት ባለቤት›  ይሰኛል፡፡ ሺበሺ ለማ ጽፎት ዶክተር ክፍሌ ማርቆስ ገድሌ አሳትመውታል፡፡በአምስት ዓመቱ የፋሽስት ወረራ ጊዜ ለሀገራቸው አኩሪ ገድል በመፈጸምና ለነጻነታችን ዋጋ በመክፈል ስማቸው ከሚነሡ ሴቶች ሸዋረገድ ገድሌ ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ በ1878 ዓም የተወለዱት ወ/ሮ ሸዋ ረገድ ገድሌ ሁለገብ እንደነበሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡ የቤተ ክህነቱን ትምህርት ተምረዋል፡፡ ትዳርን አልፈልግም ብለው ምናኔን መርጠው ኢየሩሳሌም ድረስ ተጉዘዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የባንክ ተጠቃሚዎች፣ የአክሲዮን ገዥዎች፣ የፋብሪካ ተካዮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ የጉለሌ ቅዱስ ገብርኤልንም ያስተከሉት እርሳቸው ነበሩ፡፡ የሸዋረገድን ስም ይበልጥ ከፍ አድርጎ ያስጠራው አርበኛነታቸው ነው፡፡ የኢጣልያ ጦር ሊጎርሰን ማሰፍሰፉ ሲሰማ በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ተቆርቋሪ ዜጎች በተቋቋመው የሀገር ፍቅር ማኅበር አባልነት መጀመሪያ ከተመዘገቡት ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ እርሳቸው ነበሩ፡፡ ወራሪው ፋሽስት አዲስ
Posted in Ethiopian News, Religion

የደብረ ሊባኖሱ እልቂት

   click here for pdfኢያን ካምፕቤል ፋሽስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ላይ ስለ ፈጸመቺው አሰቃቂ እልቂት የሚተርክ ‹The Massacre of Debre Libanos, Ethiopia 1937› የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይኼ ብዙ ጊዜ የማይነገርለት ነገር ግን እርሳቸው ‹ፋሽዝም ከፈጸማቸው ጆሮ ጭው የሚያደርጉ የጭካኔ ሥራዎች አንዱ ነው› ብለው የገለጡት ዘግናኝ የሃያኛው ክፍለ ዘመን ሰብአዊ አረመኔነት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በጥናት ተመሥርቶ በዝርዝር ቀርቧል፡፡ ጣልያኖች የኢትዮጵያውያንን የጀግንነት መንፈስ ለመስበር ከመጀመሪያው ተዘጋጅተው ነበር የመጡት፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ አንድ ርምጃ የወሰዱት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ማንበርከክ ነው፡፡ ምንም እንኳን የተወሰኑ ጳጳሳት ከእነርሱ ጋር ለመሥራት ባያንገራግሩም እንደ አቡነ ጴጥሮስ ያለ ቆራጥ አባት መፈጠሩ፤ ብዙዎች ገዳማትና አድባራት አርበኞችን መርዳታቸው፤ ካህናቱም ወግጅልኝ ድጓ ወግጅልኝ ቅኔወንዶች ከዋሉበት እውላለሁ እኔእያሉ ሀገራቸውን ለመከላከል በረሐ መውረዳቸው ጣልያኖችን ዕረፍት ነሥቷቸው ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓም በግራዝያኒ ላይ በተቃጣው የመግደል ሙከራ ዋነኞቹ ተሳታፊዎች አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ጋር ግንኙነት አላቸው
Posted in Ethiopian News, Religion

አዳቦል

click here for pdf በምሥራቅ ጎጃም ገበሬዎች ባሕል የኑግ ክምር አዳቦል ይባላል፡፡ የኑግ ክምር ቀላል በመሆኑ ነገረ ቀላል የሆነውን ሰው አዳቦል ይሉታል፡፡ እነርሱ አዳቦል የሚሉት ነገረ ቀላል ሰው ሦስት ነገሮች የሌሉትን ነው፡፡ ወይ ሲናገር አዲስ መረጃ የማይሰጠውን፣ ወይም ዕውቀት የማያዳብረውን ወይም ደግሞ ለሁኔታው የማይመጥን ነገር የሚናገርውን፡፡ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሐዲስ ዓለማየሁ የባሕል ማዕከል ዓመታዊ በዓል ምሽት ላይ በኛ ጠረጲዛ ዙሪያ የነበሩ ምሁራን ይህንን የገበሬውን ነገር ሲሰሙ አዳቦልነት በሦስት ነገሮች የተነሣ ሊመጣ ይችላል ሲሉ ሐሳብ ሠነዘሩ፡፡ የመጀመሪያው ለንግግርና ለጽሑፍ ካለመጠንቀቅ ነው፡፡ ለማን፣ ምን፣ እንዴት ልናገር ብሎ የማያስብና እንዳመጣለት ብቻ የሚናገር ወይም የሚጽፍ ሰው ንግግሩ ወይም ጽሑፉ አዳቦል ይሆናል፡፡ ቃላት ይደረደራሉ፤ ዐረፍተ ነገሮች ይሰካካሉ፤ ዐናቅጽ ይሰደራሉ እንጂ አእምሮን ያዝ ወይም ልብን ስልብ የሚያደርግ ፍሬ ነገር አይገኝበትም፡፡ በውስጡ ንጥረ ነገር የሌለው ሆድ የሚሞላ ምግብ እንደመብላት ነው፡፡ ሆድን ይሞላል እንጂ ለሰውነት ድጋፍ አይሆንም፡፡ ሰምተው ወይም አንብበው ሲጨርሱ የሚይዙት ነገር አይኖርም፡፡ ወፍጮ ቤት ደርሶ የመጣ ሰው ቢያንስ
Posted in Ethiopian News, Religion

እየደመሰሱ መቅዳት

 click here for pdfለረዥም ዓመታት በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ የሠራ ጋዜጠኛ ለአንድ ጥናት ወደ ጣቢያው ይሄዳል፡፡ ከ30 ዓመታት በፊት እርሱ ራሱ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ነበር፡፡ ቃለ መጠይቁ የተደረገላት ሴት አሁን በሕይወት የለቺም፡፡ ለዚህ ነበር እርሷ የሰጠቺውን ቃል ፍለጋ ወደ ሬዲዮ ጣቢያው የሄደው፡፡ ያገኘው ግን የጠበቀውን አልነበረም፡፡ የተቀዳው ቃለ መጠይቅ የለም፡፡ ምነው? አለ ጋዜጠኛው፡፡ ‹‹ብዙ ካሴቶችን እየደመሰስን ቀድተንባቸዋል፡፡ በዚያ ምክንያት ያንን ቃለ መጠይቅ አሁን አታገኘውም›› አሉት፡፡ እርሱም በዚህ አዝኖ ወጣ፡፡ለነገሩ እርሱ በካሴቱ አዘነ እንጂ ከኢትዮጵያ ታሪክ መገለጫዎች አንዱ እየደመሰሱ መቅዳት ነው፡፡ የሚመጣ መንግሥት ወይም ባለሥልጣን፣ ዐዋቂ ወይም ታዋቂ፣ ታሪክ ጸሐፊ ወይም ዐቅድ ነዳፊ ከእርሱ በፊት ለነበረው ነገር ዋጋ ሰጥቶ፣ የየራሱን ሥራ ከመሥራትና የዘመኑን አሻራ ከማኖር ይልቅ ያለፈውን መደምሰስ ይቀናዋል፡፡  ሀገር የማታልቅ ሕንጻ ናት፡፡ መሠረቷ ዛሬ አልተጣለም፡፡ መሠረቷ ከተጣለ ቆየ፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ የየራሱን ድርሻ እየገነባ ይቀጥላል፡፡ የመጣው ሁሉ ባለው ላይ አዳብሮ፣ አሻሽሎ ወይም አሣምሮ የሚጨምር ከሆነ ሀገር እያደገች፣ እየበለጸገችም ትሄዳለች፡፡ የመጣው ትውልድ ሁሌም
Posted in Ethiopian News, Religion

ፍቅር እስከ መቃብርን የጻፉት ‹‹ሐዲስ›› ናቸው ወይስ ‹‹ዓለማየሁ››?

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲየሐዲስ ዓለማየሁ የባሕል ማዕከል 3ኛ ጉባኤ ላይ የቀረበ‹‹አበሻ ባል ሚስቱ ስታረግዝ እርሱ ዕንቅልፍ አይወስደውም›› ይባላል፡፡ ስለምን ቢሉ የልጅ ስም ፍለጋ፡፡ ስም ደግሞ በአበሻ ምድር እንዲሁ አይወጣም፡፡ ቢቻል ከአያት፣ ካልተቻለም ከአባት ጋር የሚገጥም፣ ዘመኑንና ሁኔታውን የሚያሳይ፣ ተስፋንና  ምኞትን የሚያመለክት፣ አንዳንዴም ድጋፍንና ተቃውሞን የሚገልጥ መሆን አለበት፡፡ ‹ጅል እንደ ሠራው በርና መቃን የማይገጥም ስም ይዘህ. ይባላልኮ፡፡ በተለይ በሰሜኑ ማኅረሰብ ስም መጠሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እንደ መዝገብ ታሪክን፣ እንደ ሚዲያ ሐሳብን፣ እንደ መጽሐፍ ፍልስፍናን፣ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት እምነትን፣ እንደ ሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞን የሚያሳይ  የመገናኛ መሣሪያ ጭምር ነው፡፡በደርግ ዘመን ተቆራጭና መዋጮ በዝቶ ሠራተኛውን መከራ ሲያሳየው፣ በባሕርዳር ጥጥ ፋብሪካ የነበረ በዛብህ የተባለ ወዛደር ለሁለት ልጆቹ ‹ተቆራጩ› እና ‹መዋጮው› የሚል ስም አወጣላቸው፡፡ የልጅ እናቱ በየአሥራ አምስት ቀኑ የልጆቿን ተቆራጭ ልትወስድ ስትመጣ ደመወዝ ከፋዩ ድምፁን ከፍ አድርጎ ‹ተቆራጩ በዛብህ› ‹መዋጮው በዛብህ› እያለ የሕዝቡን ተቃውሞ ሲገልጥ ኖሯል፡፡ በአብዮቱ ዘመን የተወለዱ ብዙ ልጆች ‹አብዮት› የሚለውን ስም በመያዝ ታሪክ መዝግበው
Posted in Ethiopian News, Religion

ጠላ፣ ጥብስና ግድብ

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲመኙት የኖረ፣ የትውልድን ሕልም እውን ያደረገ፣ በዘመናዊ ታሪካችን ውስጥ ሊጠቀስ የሚችል የዚህ ትውልድ ሥራ ነው፡፡ ‹ዓባይን መገደብ› ታላቅ ሐሳብ፣ ታላቅም ውሳኔ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከአካባቢው ሀገራት ጋር የምታደርገውን ውይይት ቋንቋውን የቀየረ፣ የግዮን ምንጩ ከኢትዮጵያ ተራሮች መሆኑን ከብራና አውርዶ መሬት ላይ የጻፈ ነው፡፡  ስለ ሕዳሴው ግድብ የሚሠሩት ማስታወቂያዎች ግን ፈጽሞ ግድቡን የማይመጥኑ፣ እንኳን ለዓባይ ግድብ ለኛ ቤት አጥርም የማይሆኑ፣ በውስጣቸው ምንም ዓይነት ሀገራዊ ርእይና ፍልስፍና የሌለባቸው፤ ከጠላና እንጀራ የማያልፉ ናቸው፡፡ እንዴው ግድቡ አፍ ስለሌለው እንጂ በስም ማጥፋትና በክብረ ነክ ወንጀል ይከስ ነበር፡፡  የታሪክ ባለሞያዎች፣ የፖለቲካ ጠበብት፣ የኪነ ጥበብ ልሂቃን፣ የእምነትና የባሕል ምሁራን፣ የሥነ ቃል አጥኒዎች፣ የሐሳብ መሪዎችና የሕዳሴ ኮከቦች መነጋገሪያ፣ መከራከሪያ፣ ሐሳብ ማራቀቂያ፣ ትውልድ መቅረጫ፣ ትውልድ ማነሣሻ፣ መሆን የነበረበት የሕዳሴው ግድብ የቀልደኞች ማቧለቻ ሲሆን እንደማየት ያለ የክፍለ ዘመኑ ርግማን የለም፡፡ እኔ እንዲያውም እነዚህ ግድቡን የማይመጥኑ ማስታወቂያዎች በግብጽ ነው እንዴ ስፖንሰር የሚደረጉት? እላለሁ፡፡ ግድቡኮ የግንባታ ሂደት ጉዳይ ነው፡፡ መንግሥት
Posted in Ethiopian News, Religion

ዝቋላ ሀገሩ የት ነው?

click here for pdfየዚህች ሀገር ባለቤቶች ሁላችንም ካልሆንን በቀር በተናጠል ማንም ባለ ግዛት ሊሆን አይችልም፡፡ ሉሲ አማራ ትሁን ኦሮሞ፣ አፋር ትሁን ሶማሌ፣ ጉሙዝ ትሆን ትግሬ፣ ወላይታ ትሁን ጋሞ የሚያውቅ የለም፡፡ በአኩስምና አካባቢው በተገኙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ነገሥታቱ የሚገዙትን ሀገር ሕዝቦች ስም ይዘረዝራሉ፡፡ እጅግ የሚገርመው ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካና የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የምንሻኮተው ብዙዎቹ ጎሳዎች/ነገዶች ስማችን የለም፡፡ ሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ከተለያየ ቦታ መጥተን የሠፈርንበት ላይ ረግተን ነው ዛሬ የምንገኘው፡፡ የሕዝብ የሥፍራ ንቅናቄ የታሪኳ አንዱ መገለጫ በሆነቺው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ሌላውን ሀገርህ አይደለም፣ ክልልህ አይደለም፣ መሬትህ አይደለም እንደማለት ያለ ታሪካዊ ኃጢአት የለም፡፡ ትንሽ በታሪክ ወደኋላ ስንጓዝ ዛሬ ክልልና መንደር በመሠረትንበት ቦታ ሌሎች ሲኖሩበት እናገኛለን፡፡ አሁን የያዝነው ቦታ ከምእተ ዓመታት በፊት የሁላችንም አልነበረም፡፡ ሁሉም ሠፋሪ ነው፡፡ ነባር መሬቱ ብቻ ነው፡፡  ኢትዮጵያ የምታዋጣን የሁላችን እንድትሆን አድርገን ከሠራናት ነው፡፡ እንደ አጥር ሠሪ እንስሳት(territorial animals)  ከዚህ በመለስ ማንም አይገባብኝም፡፡ እኔን ያልመሰለውን በዚህ አካባቢ ላየው አልፈልግም
Posted in Ethiopian News, Religion

ሦስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተጀመረ

 click here for pdfለሁለት ተከታታይ ጊዜ የተካሄደው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት የ2007 የምርጫ ሂደት የካቲት 12 ቀን 2007 ዓም በካፒታል ሆቴል በተዘጋጀ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተጀመረ፡፡  ጋዜጠኞች፣ የቀድሞ ተሸላሚዎችና እጩዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተከናወነው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ስለ በጎ ሰው ሽልማት ያለፉት ዓመታት ክንዋኔዎችና ያመጣቸውን በጎ ተጽዕኖዎችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል፡፡ የሽልማት ኮሚቴው አካላት እንደገለጡት 2007 ዓም የሽልማት ሂደት ካለፉት ዓመታት በተለየ በ10 ዘርፎች የሚከናወን ሲሆን ሂደቱ ተጠናቅቆ ሽልማቱ የሚሰጠው በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡ከጥቆማው በኋላ የእጩዎችን ዝርዝር መግለጫ የማዘጋጀት ሥራ የሚሠራ ሲሆን፣ በመቀጠልም በየሞያው ዕውቀትና ብስለት ባላቸው ሰዎች በተቋቋ ቡድኖች የመጀመሪያ አላፊዎች የመረጣ ሥራ ይከናወናል፡፡ በመቀጠልም ማጣሪያውን ላለፉት የሕይወት ታሪክ ዝግጅት ሥራ ይከናወናል፤ በማስከተልም ቦርዱ የመጨረሻዎቹ ተሸላሚዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ለጠቋሚዎች የተሻለ ዕድል ለመፍጠር የኢሜይል፣ የስልክ፣ የፖስታና የገጸ ድር የመጠቆሚያ መንገዶች የተዘጋጁ ሲሆን፣ የበጎ ሰው ገጸ ድር እዚያው በእዚያው(አውቶማቲክ) የሆነ የእጩ መጠቆሚያ ቅጽ ዝርዝር መረጃዎችን
Posted in Ethiopian News, Religion

እስኪ እንያችሁ

 click here for pdfከቀናት በፊት ሬዲዮ ማዳመጥ እስኪሰለቸን ድረስ ሁሉም ጣቢያዎችና ፕሮግራሞች ስለ ‹ቫላንታይን ደይ› ነበር የሚወተውቱን፡፡ ልክ ፍቅር በዚህች ሀገር እንዳልተወለደ፣ ድኾ እንዳላደገ፣ ለወግ ለመዓርግ ደርሶ ጎጆ እንዳልቀለሰ ይመስል ነበር፡፡ ቀይ ልብስ ያልለበሰ፣ አበባ ያልያዘ፣ በምሽት በሚደረጉት ጭፈራዎች ያልተገኘ፣ ማታም ጥንድ ሆኖ አልጋ ያልያዘ ሰው ሁሉ ፍቅርን እንደማያውቅ ተደርጎ ነበር የሚተረክልን፡፡ ዝንጀሮ ጠባቂ ላያድር ያመሻል፣አፌ ፈራሽ እንጂ ልቤስ ከጅሎሻል፤ዝንጀሮ ጠባቂ ላያድር ካመሸ ከፈራህኝማ ነገር ተበላሽ፡፡                      ተብሎ ያልተገጠመ፤አቡኪ ወእምኪ ኢይፈቅዱ እንግዳሰዐምኒ ንሑር በሳንቃው ቀዳዳ፤ ያልተባለ ይመስል ነበር በዚህች ሀገር፡፡ ‹ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር› አለ ኤፍሬም ሥዩም፡፡ መቼም ፈገግ ካለባቸው አጋጣሚዎች መካከል አንዱ በቀደም ጋዜጠኞቻችን ‹ፍቅር የመጣውኮ ከውጭ ሀገር ነው› ሊሉን ሲደርሱ ሰምቶ መሆን አለበት፡፡ ምዕራባውያን በአንድ ነገር ጎበዞች ናቸው፡፡ ባሕላቸውን ወደ ሸቀጥነት መቀየርና የገበያ ማሟሟቂያ ማድረግ ይችሉበታል፡፡ የካፒታሊስት ሥርዓት አንዱ መገለጫውም ሁሉን ነገር ሸቀጥ ማድረግ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ለእነርሱ ሃይማኖት እንኳን ቢሆን ሲታመንበት ሳይሆን ሸቀጥ ሆኖ ሲሸጥ ነው የሚያዋጣው፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የአማርኛ ሞክሼ ሆሄያት

በአማርኛ ቋንቋ ዕድገትና ብልጸጋ ጎዳና ላይ ከሚገኙት ተግዳሮቶች አንዱ ተገቢ የሆነ፣ ሁሉም የሚቀበለው፣ በቀላሉ የሚገኝና ደረጃውን የጠበቀ የአማርኛ ሥርዓተ ጽሕፈት አለመኖር ነው፡፡ የአጻጻፍ መንገዶችን፣ መልክዐ ፊደልና ሥርዓተ ፊደልን፣ በቃላት አጻጻፍ የሆሄ መረጣን፣ የፊደል መጠንን፣ የስያሜ ቃላት አሰጣጥን፣ የትርጎማ መንገድን፣ ወዘተ የተመለከተ ሥርዓተ ጽሕፈት ያስፈልገናል፡፡ ለዛሬው ግን ብዙዎቻችን የምንስትበትንና የምንምታታበትን የሞክሼ ሆሄያት (ሀ፣ ሐ፣ ኀ፣ ኸ፤ ሠ፣ሰ፣ አ፣ ዐ፤ ጸ፣ ፀ) አጻጻፍን በተመለከተ ታዋቂው ሊቅ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ(ነፍሳቸውን ይማርና) አዘጋጅተውት ሻማ ቡክስያሳተመውን ‹‹የአማርኛን ሞክሼ ሆሄያት  ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግርና መፍትሔ›› የሚለው መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ፡፡ መጽሐፏ የኪስ መጠን ብትሆንም እስከዛሬ በጉዳዩ ከተዘጋጁት የተሻለች፣ በአመክንዮ የቀረበችና በጥናት ላይ የተመሠረተች ናት፡፡ በተለይም ለደራስያን፣ ለቢሮ ጸሐፊዎች፣ ለፖለቲካ ሰዎች፣ ለጋዜጠኞች፣ ለማስታወቂያ ባለሞያዎች፣ ለአርታዕያን፣ ለፌስ ቡክ ደንበኞችና ለሌሎቻችንም በሞክሼ ቃላት ዙሪያ መመሪያ የምትሆን ናት፡፡ እባካችሁ ነገራችን ወጥ እንዲሆን በሊቁ መንገድ እንሥራ፡፡ ዋጋው 25 ብር ነው ገዝተን በጠረጴዛችን ላይ እናስቀምጥና እንመራባት፡፡ ከምር ሁላችንም ቤትና ቢሮ መጥፋት የሌለባት ናት፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

የተፈተነው ማነው?

እስኪ ይኼንን በአንድ ትምህርት ቤት ለሦስተኛ ክፍል ተማሪ የቀረበ ፈተና ተመልከቱት፡፡ አሁን የሚወድቀው ማነው? ተማሪው ወይስ ራሱ ትምህርቱ? እስኪ የስሕተቱን ብዛት እዩት? ወይ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ተምረን ጽንሰ ሐሳቡን አልተረዳነው፣ ወይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተምረን ቋንቋውን በሚገባ አላወቅነው፤ ከሁለት ያጣን ሆንኮ፡፡ ለመሆኑ ፈተናው እንዲህ ከሆነ ትምህርቱማ ምን ሊሆን ነው? እንዲህ እያስተማርንና እየፈተንንስ ምን ዓይነት ትውልድ ይሆን የምናወጣው? ‹አለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል› አለ ያገሬ ሰው፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ጎንደሬው የጃማይካ ሰው

ዶ/ር በርናንድ ብራድሊ አንደርሰን ልደቱ ቅድስት ካትሪን ደብር ጀማይካ ዉስጥ ነዉ፡፡ ወሩ መስከረም፣ ቀኑ 21፣ ዓመተ ምሕረቱ 1944፣ አቆጣጠሩ በአዉሮጳውያን፡፡ ቅድስት ካትሪን አጥቢያ ከእርሻዉ መካከል ነበር ያደገዉ፡፡ ዕድሜዉ ለትምህርት ሲደርስ ካሪቢያን ዉስጥ አንጋፋ ከሚባለዉና ከተከበረዉ ዎልማር የወንዶች ትምህርት ቤት ገባ፡፡ ወደ አሜሪካ ምድር የዘለቀው በ1960ዎቹ ሲሆን በዋሽንግተን ዲሲ ዝነኛዉ ሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ማዕረግ የመጀመሪያዉን የባችለር ዲግሪ አገኘ፡፡ ከክፍሉ ቀዳሚ ሆኖም ወደ ሕክምናዉ የትምህርት ዘርፍ ተሻገረ፡፡ ቀን ቀን ትምህርቱን እየተከታተለ፤  ሌሊቱን እየሠራና ራሱን እየረዳ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ላይ በቀዶ ጥገና ሕክምና በከፍተኛ መዓርግ ተመረቀ፡፡ በትምህርትና በሥራ የበለጸገዉና ገና በለጋነቱ በትጋቱ የታወቀዉ፣ የቅርብ ጓደኞቹ በርኒ የሚሉት በርናንድ፤ የሕክምና ትምህርቱን ጨርሶ እንደተመረቀ ወደ ትዉልድ ሀገሩ ጃማይካ ተመልሶ በኪንግስተን የሕዝብ ሆስፒታል ማገልገል ጀመረ፡፡ ኪንግስተን የሕዝብ ሆስፒታል ነጻ ሕክምና የሚሰጥበት፣ ለተቸገሩና ዐቅም ለሌላቸዉ የሚለገስበት በመሆኑ ቀልቡን ገዛዉ፡፡ ወትሮም የሕክምና ሙያ ለአምሳያ ፍጡር የመድረስ መንፈስ አለዉና ከዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ዉስጣዊ ተፈጥሮና ተልዕኮ ጋር ገጠመ፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ታሪክ ሠሪ ታሪክ አሻጋሪ ሲያገኝ

 click here for pdfአበው ሲመርቁ ‹‹ወይ መልካም ልጅ፣ ወይ መልካም ደቀ መዝሙር ይስጥህ›› ይላሉ፡፡ የሚረከብህ ማለታቸው ነው፡፡ ብዙ ታሪክ ሠሪዎች ታሪካቸውን የሚያስተላልፍላቸው አጥተው ሳናውቃቸው ቀርተናል፡፡ ዛሬ ታሪካቸውን ከፍ አድርገን የምንናገርላቸው ታላላቆቻችን ታሪካቸውን የሚጽፍ፣ የሚጠብቅና ለትውልድ የሚያስተላልፍ ያገኙትን ነው፡፡ ስማቸውን ሰምተን ታሪካቸው ያጣን፣ ሥራቸው ደርሶን ታሪካቸው የጠፋብን አያሌ ጀግኖች አሉን፡፡ አንዳንድ አባቶች እንዲያውም ሰው ሲያጡ ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን ለወንዞችና ለተራሮች በአደራነት ሰጥተው ነበር፡፡ ይሄው በየዘመኑ እየተቆፈረ የሚወጣው ቅርስ መሬት አደራ የተቀበለችውን እያስረከበች ነው፡፡በዘመናዊ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጎልተው ከሚጠቀሱት ታላላቅ ሰዎች መካከል ሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ትርፌ አንዱ ናቸው፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ትርጓሜ(1948)፣ የሐዋርያት ሥራ ትርጓሜ፣ የሰባቱ መልእክታትን ትርጓሜ፣ የዮሐንስ ራእይን ትርጓሜ(1951) ያገኘነው በእርሳቸው ድካም ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹ርትዕት ፍኖት ዘባስልዮስ በባሕረ ጣና›(1948)፣ ‹መጽሐፈ በቁዔት ዘጾም ወዘበዓል›(1946)፣ ቃለ ምዕዳን(1948)፣ መዝገበ ሃይማኖት(1950) ይህንንም መጻሕፍቱ በመጀመሪያ ገጻቸው ‹ከሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ትርፌ› በማለት ያስታውሱናል፡፡ በዚያ ዘመን  ጵጵስና ከሊቅነት በኋላ የሚመጣ መዓርግ ነበርና ቅዱስ ሲኖዶስ እኒህን
Posted in Ethiopian News, Religion

ወንድሟ

click here for pdfመቼም ከጓደኞቹ ጋር ምሳ እንደመብላት የሚያስደስተው ነገር የለም፡፡ ከየትም ቦታ ተሯሩጦ ወደ ቀጠሮው ቦታ ይመጣል፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ ያቺ ያረጀች መኪናው ድንገት እየቆመች ብታስቸግረውም ቀጠሮውን ግን አይሰርዝም፡፡ አሁን የመኪና ማቆሚያ እየፈለገ ነው፡፡ አዲስ አበቤ ሁሉ ለሦስት ቀን ነነዌ ቅበላ ሀገሪቱን በቀንድ ከብት ሀብት አንደኛ ከመሆን ገፍትሮ ሊጥላት በየ ሥጋ ቤቱ ተጠቅጥቋል፡፡ መንገዱም አጥንት እንዳየ ጉንዳን በሚተራመሱ መኪኖች ተሞልቷል፡፡ እዚህ ነው ጓደኞቹ የቀጠሩት፡፡ በዋናው መንገድ በኩል ለመግባት ሞከረና ያለ ማስጠንቀቂያ የሚቆፈረው መንገድ ተዘግቶ አገኘው፡፡ እለፉም አትለፉም የማይል የአፈር ክምር መንገዱን ዘግቶታል፡፡ በታችኛው በኩል ዞረና መጣ፡፡ እንደ ደብረ ዕንቁ አንድ መውጫ ብቻ የቀረለት መንደር በግራ በቀኙ በቆሙት መኪኖች ተጣብቦ ጉርሻ እንዳነቀው ጉሮሮ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ ይላል፡፡ በወዲህና በወዲያ ምንም መቆሚያ አልተረፈም፡፡  ‹በተወደደ ቁጥር ደንበኞቹን የሚጨመር ነገር ቢኖር ሥጋ ቤት ነው› ይላሉ አንድ በላተኛ የታጠቡትን እጃቸውን እያራገፉ ከሥጋ ቤት ወጥተው፡፡ ‹በዚህ የሥጋ ፍቅራችን የጾም ወቅት ባይኖር ምን ይውጠን
Posted in Ethiopian News, Religion

ከአኩስምና ከቻይና ግንብ በፊት

ማክሰኞ ለም ሆቴል አካባቢ ለመንገድ የተቆፈረ ገደል ውስጥ የገባው መኪና(ፎቶ ፡- ጽላት ጌታቸው)ከግንባታዎች ጋር ተያይዞ እየደረሰ ያለው አደጋ አሳዛኝ እየሆነ ነው፡፡ ይኼ አደጋ በሦስት ነገሮች ምክንያት እየደረሰ ያለ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያው ግንባታዎች ሲከናወኑ ተገቢ የሆነው ቅድመ፣ጊዜና ድኅረ ግንባታ ጥንቃቄ ስለማይወሰድ ነው፡፡ ታላላቅ ክሬኖች አገር ደርምሶ የሚሄድ ቋጥኝ አንጠልጥለው እየታዩ፣ በሥራቸው ሰውና መኪና እንዲያልፍ ይደረጋል፡፡ ለግንባታ ሠራተኞች በቂ የሆነ የአደጋ መከላከያ ሥልጠናና መሣሪያ አይሰጣቸውም፡፡ አማራጭ መንገዶችና የእንቅስቃሴ ቦታዎች ቀድመው ስለማይዘጋጁ ግንባታና ኑሮ ጎን ለጎን ይካሄዳል፡፡ መታጠር ያለባቸው ሳይታጠሩ፣ መሸፈን ያለባቸው ሳይሸፈኑ፣ መከደን ያለባቸው ጉድጓዶች ሳይከደኑ፣ ምልክት መደረግ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ሳይደረጉ ግንባታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚህም የተነሣ በተገቢ ጥንቃቄ ሊተርፉ ይችሉ የነበሩ ሕይወቶች ይቀጠፋሉ፣ አካል ይጎድላል፣ ንብረት ይወድማል፡፡ግንባታዎች በመንደሮች መካከል ሲከናወኑ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና ሕጻናት የሌሉበት መንደር ይመስላል፡፡ በየቦታው ጉድጓዱ አፉን ከፍቶ ማየት የተሳናቸውን ሊውጥ አሰፍስፏል፤ አረጋውያንን ‹እስኪ ትዘልና› ይላል፡፡ ሕጻናትን ዋኝተው እንዲያልፉበት ይጋብዛል፡፡ በዊልቼር ለሚጓዙ፣ በከዘራ ለሚራመዱ፣ በክራንች ለሚታገዙ ቦታ የለውም፡፡ አንድ ግንባታ ከመከናወኑ
Posted in Ethiopian News, Religion

ጎርፍና ግፍ

 click here for pdf ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢው ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ እየዞረ ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም ተቀየረሳ›› እያለ ዝም ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ እንዳይነበብ አሳስባለሁ)  ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር እየጨመረ ሄደ፡፡ እየቆየም በግመልና በግመል ወተት ከሚታወቁት የሀገሩ ነጋዎች በላይ እኔ ነኝ ያለ፣ ቢጠሩት የማይሰማ ሀብታም ሆነ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ይኼ ሰው ትናንት ምንም አልነበረውም፡፡ የጠፋ ግመል ሊፈልግ ጫካ ገባ፤ ተመልሶ መጣ፤ ከተማ ገባ፤ በአንድ
Posted in Ethiopian News, Religion

እሳት በዳጋ እስጢፋኖስ

በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ተነሥቶ የነበረው እሳት በደቅ ደሴት ሕዝብ፣ በገዳማውያኑና በፖሊስ ትብብር መጥፋቱ ተነገረ፡፡ እሳቱ ቁጥቋጦዎችን ከማጥፋት በቀር ደኑን እንዳላወደመው ተነግሯል፡፤ የደቅ ደሴት ሕዝብ ላደረገው አስቸኳይ ርብርብ ገዳማውያኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የክልሉ መንግሥትም ሄሊኮፕተር ለመላክ እስከመዘጋጀት ድረስ ያሳየውን ትብብር ገዳማውያኑና ሕዝቡ አድንቀዋል፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ቀጣይ ዜና – እሳት በዳጋ እስጢፋኖስ

እሳቱ ከደኑ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳያልፍ መነኮሳቱ፣ ፖሊስና ሕዝቡ ቆርጠውታል፡፤ በአፈር ከተር በመሥራት የእሳቱን ተሻጋሪነት ቀንሰውታል፡፡ አሁን እሳቱን ለማጥፋት እየተረባረቡ ነው፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

እሳት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም

በጣና ሐይቅ ውስጥ በሚገኘው የዳጋ እስጢፋኖስ እሳት መነሣቱን የገዳሙ ምንጮች ተናግረዋል፡፤ እሳቱ የተነሣው ከደኑ አካባቢ ሲሆን ወደ ገዳሙ ገና አልደረሰም፡፡ የክልሉ ፖሊስ ወደ ቦታው በፍጥነት መድረሱ ተሰምቷል፡፡ አባቶች እሳቱን ቆርጦ ለመከላከል እየሞከሩ ነው፡፡ በሰው ኃይል ለመከላከል የማይቻል ከሆነ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ክልሉ ገልጦላቸዋል፡፡  
Posted in Ethiopian News, Religion

ጉርብትና

ጉርብትናችንን እንደ ጣይቱ ሆቴልና እንደ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ ድርጅት  ጉርብትና አያድርግብን፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ተዋሕዶ በተዐቅቦ

click here for pdfስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በሚነሡ መድረኮች ላይ አንድነትና ኅብር ዋና መከራከሪያዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቻችን የብሔረሰቦች ተናጥላዊ መብትና ማንነት እየጎላ መምጣት፣ ሰዎችም ለአካባቢያዊ ማንነታቸው፣ ቋንቋቸውና ባሕላቸው ይበልጥ እያሳሱ መሄድ ኢትዮጵያዊ የሚባለውን ማንነት እንዳያጠፋውና ቆይቶም ኢትዮጵያ የምትባለውን አንዲት ሀገር እንዳይበታትናት እንሰጋለን፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሚባለው ባሕል፣ ማንነት፣ ታሪክና ግዛት በውስጡ የሚገኙትን ልዩ ልዩ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ታሪክ፣ ማንነት፣ያላቸውን ብሔረሰቦች እንዳይውጣቸው፣ ህልውና እንዳይነፍጋቸው፣ መብታቸውን እንዳይነፍጋቸው እንፈራለን፡፡በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድነትንና ልዩነቶችን(ኅብርን) አስታርቆና አስማምቶ እንደመጓዝ ያለ ፈታኝ የቤት ሥራ የለም፡፡ ሁለቱም የሀገሪቱ እውነታዎች ናቸውና፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሁላችንንም እንደሰበዝ ያያያዘችና የያዘች ሀገር አለችን፡፡ ከነ ልዩ ታሪኳ፣ ማንነቷ፣ ባሕሏና ስሜቷ፡፡ ደግሞም እያንዳንዳችን ቀየ፣ ጎጥ፣ ጎሳ፣ ነገድ፣ ብሔረሰብ አለን፡፡ ከነ ልዩ ታሪኩ፣ ባሕሉ፣ ቋንቋው፣ ልማዱና ወጉ፡፡ ጥያቄው እንዴት ሳይጣሉና ሳይጠፋፉ እናስኪዳቸው ነው፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ኢትዮጵያዊ የምንለው የሁላችንም የሆነው፣ ማንነት፣ ታሪክ፣ ባሕል፣ ሀገር፣ ዜግነትና ክብር ብሔረሰባዊ ማንነትን፣ ታሪክንና ባሕልን ሳይድጠው፣ ሳይውጠው፣ ሳያጠፋውና ሳይመጠው፣ ሳይጨፈልቀውና ሳይጠቀልለው፤ የብሔረሰብ
Posted in Ethiopian News, Religion

ከሳምንታት በኋላ ይወጣል

Posted in Ethiopian News, Religion

ስለ ገና በዓል እና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች

  (በብዙ አንባቢያን ጥያቄ በድጋሚ የታተመ) የገና እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህን እና መሰል የሕዝቡን የዘወትር ጥያቄዎች መልስ የያዘ የማያዳግም ጥራዝ ማውጣት ከሊቃውንት ጉባኤ የሚጠበቅ ነው፡፡ አብዛኞቹ ጉዳዮች አበው ቀድመው ሥርዓት የሠሩባቸው እና ማብራርያ ብቻ የሚያስፈልጋቸው ናቸውና፡፡ ለዛሬ ሦስቱን ብቻ እንመልስ፡፡ ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋል ወይስ ይጾማሉ?ፍትሐ ነገሥት፡ ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር /ዐንቀጽ 15፣ ቁ566/የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 603/የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?ፍትሐ ነገሥት፡ ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይሆን ዘንድ አዘዙ /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 595/ልደት ጋድ አለው?ፍትሐ ነገሥት፡ የልደት እና የጥምቀት በዓላት ጋድ አላቸው /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 566/     ትንታኔ፡ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል፡፡                    40 ጾመ ነቢያት                     3 ጾመ
Posted in Ethiopian News, Religion

እንደ ሰው ወይስ እንደ እንስሳ

click here for pdf The Indian Folktales በተሰኝ ከዛሬ 100 ዓመት በፊት በ1919 እኤአ በታተመ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ይላል፡፡ አንድ የሕንድ ጠቢብ ደቀ መዝሙሮቹን ሥራ እንዲሠሩ አዘዛቸውና ራቅ ብለው በከፍታ ቦታ ላይ ይመለከታቸው ጀመር፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተመልሶ ደቀ መዝሙሮቹን ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም እንዲህ አላቸው ‹‹ከእናንተ መካከል የተወሰናችሁ እንደ ሰው የተወሰናችሁት ደግሞ እንደ እንስሳ ስትሠሩ ነበር›› ተማሪዎቹም ተገርመው ጠየቁት፡፡ መምህሩም ‹‹እንደ እንስሳ መሥራት ማለት አንድን ነገር መጎተት፣ መሸከም፣ መግፋት፣ ማዞር ወይም የሚደርስበት ቦታ ማድረስ ማለት ነው፡፡ ምን እየሠራ እንደሆነ፣ ለምን እየሠራ እንደሆነ፣ የሚመጣው ውጤት ምን እንደሆነ፣ ዓላማው ምን እንደሆነ አያስብም፡፡ በሥራው ላይም ከራሱ አስቦ አንዳች አይጨምርም፡፡ የዛሬ ሺ ዓመት አንድ ዝሆን የሠራውን ዛሬም ሌላ ዝሆን በተመሳሳይ መልኩ ይሠራዋል፡፡(አንድ ሊቅ ‹ዕብደት ማለት አንድ ውጤት እንደማያመጣ እየታወቀ በተደጋጋሚ መሥራት ነው› ብሎ ነበር) አያሻሽለውም፡፡ ምናልባት ከሰው በላይ ተሸክሞ፣ ስቦ፣ ገፍቶ፣ ቆፍሮ፣ ሮጦ፣ ደክሞ፣ ይሆናል፡፡ ያ ግን እንስሳውን ጠንካራ ያስብለዋል እንጂ ጎበዝ አያስብለውም፡፡ጉብዝና አእምሮ አለበት፡፡ እንደ
Posted in Ethiopian News, Religion

በልዩ ቅናሽ የመጻሕፍት ሽያጭ ወር

ጥርበልዩ ቅናሽ የመጻሕፍት ሽያጭ ወርአግዮስ ኅትመትና ጠቅላላ ንግድ ሥራ ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ያሳተማቸውንየዲያቆን ዳንኤል ክብረትና የሌሎችንም መጻሕፍት፤ የንባብ ባህላችንን ለማሳደግ እና አንባብያንን ለማበረታታት፤ ከ25% እስከ 50% (ከሃያ አምስት እስከ ሃምሣ በመቶ) ቅናሽ በማድረግ፤ ከጥር 1 እስከ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ውስጥ ለአንድ ወርየሚቆይ ልዩ የመጻሕፍት ቅናሽ ሽያጭ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል፡፡ቦታ፡- አግዮስ መጻሕፍት መደብርአድራሻ፡- መገናኛ ለም ሆቴል አጠገብ፣ ማትያስ ሕንፃ ምድር ቤት (G – 06)              ስልክ ቁጥር፡- 011 663 9902 / 0930098254በተለይ ‹አራቱ ኃያላንን ላልገዛችሁ ይኼ መልካም አጋጣሚ ነው ውድ አንባብያን መጻሕፍቱን በአዲስ አበባ ሌሎችም አካባቢዎች በወኪሎቻችን አማካኝነት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ፤-      ለጉርድ ሾላ፣ ሲ ኤም ሲ ሚካኤል እና አካባቢው፤መዝገቡ መጻሕፍት መደብር፤ ጉርድ ሾላ ቴሌ ፊት ለፊት፣ ዲ ኤም መንጃ ፈቃድ ት/ቤት ሕንፃ ሥር፤                                ስልክ ቁጥር፡- 0912 951732-      አራት ኪሎ / ቅድስት ማርያም / አካባቢ፤ፍሬው መጻሕፍት መደብር፤ ዐፄ ናዖድ ት/ቤት አጠገብ ስልክ ቁጥር፡- 0911 685232 -      ፒያሳ አራዳ
Posted in Ethiopian News, Religion

የትልቁ ዋርካ ትልቁ ቅርንጫፍ

 click here for pdfታኅሣሥ 19 ቀን 2007 ዓም በቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከታወቁት ሊቃውንት መካከል አንዱን አጥተናል፡፡ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየን፡፡ ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመቆርቆር፣ በማስተማርና በመጻፍ የምናውቃቸው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያገለገሉ፤ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ ጥያቄዎቹን በመመለስና አስረግጠውም በማስረዳት የምናደንቃቸው ነበሩ፡፡ ዜማ፣ አቋቋም፣ የአማርኛ ሰዋስው፣ ቅኔና የግእዝ አገባብ፣ ብሉይ፣ ሐዲስ፣ ነገረ መለኮት፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በዘመናዊ ትምህርት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን ስናይ፤ በአንባቢነታቸው ጥንታውያንና ዘመናውያን መጻሕፍትን የሚያገላብጡ ብቻ ሳይሆኑ በላዔ መጻሕፍት እንደነበሩ በሌሎቹ ሊቃውንት ሲመሰከርላቸው፤ በምሥራች ድምጽ ሬዲዮ ትምህርት በመስጠት፣ በታሪክና ድርሰት ክፍል ለዐሥር ዓመታት በማገልገል፤ የመዝሙር ክፍልን በመምራት፣ የዜና ቤተ ክርስቲያንን በምክትልና በዋና አዘጋጅነት  በማገልገል፣ እንዲያውም ጋዜጣውን የጋዜጣ መልክ በማስያዛቸው በ1962 ዓም መሸለማቸውን  እያዘከርን የተጓዙበትን የዕውቀት ጎዳና ስንመረምር ያጣነው አንድ ሰው ብቻ ባለመሆኑ፡- አራት ሰው ሞተ ተቀበረ ዛሬድጓ ጾመ ድጓ መዋሥዕት ዝማሬተብሎ ለሊቁ የተገጠመው ሙሾ ለእርሳቸውም ይስማማቸዋል እንላለን፡፡  የየረርና ከረዩ አውራጃ ቤተ
Posted in Ethiopian News, Religion

ራትን ቁርስ ላይ

 click here for pdfአፍሪካውያን ቀደምት አያቶቻችን እንዲህ የሚል ትንቢት አዘል አባባል ነበራቸው፡፡ ‹‹የዚህ ትውልድ ትልቁ አደጋ ራታቸውን በቁርስ ሰዓት ለመብላት መፈለጋቸው ነው››፡፡ ሰው እንደ መላእክት አይደለምና በሂደት እየበሰለ፣ በሂደት እየተገነባ፣ በሂደትም የበለጠ እየተማረ የሚሄድ ፍጡር ነው፡፡ ይኼ ደግሞ የመንፈስ፣ የአካል፣ የስሜትና የአእምሮ ዕድገትና ለውጥን ይጠይቃል፡፡ ሰው ሲወለድ ለማደግና ለመለወጥ ከሚያስችል ዐቅም ጋር ነው፡፡ ይህንን ዐቅም ተጠቅሞ ለማደግና ለመለወጥ ግን ልምድ፣ ትምህርትና የሰውነት ግንባታ ያስፈልጉታል፡፡ ልምድ የሚባለው ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ በሕይወት ውጣ ውረድ የሚደርስበት ተሞክሮ ነው፡፡ ይህም የሕይወት ተጋድሎ ይባላል፡፡ ትምህርት ከሰዎች፣ ከትምህርት ቤት፣ ከመጻሕፍት፣ ከአካባቢውና ከሌሎችም የዕውቀት ምንጮች የሚያገኘው ጥበብ ነው፡፡ የሰውነት ግንባታ የሚባለው ደግሞ በምግብና በእንቅስቃሴ የሚያበለጽገውን አካል ነው፡፡እነዚህ ነገሮች የሚመጡትና የሚከናወኑት በሂደት ውስጥ በመሆኑ ሰዎች ለተለያዩ የኑሮ ደረጃዎች የሚበቁበት ጊዜ ይለያያል፡፡ በልጅነት፣ በወጣትነት፣ በዐዋቂነትና በአረጋዊነት ጊዜ የሚከናወኑት ተግባራት በዚያው በየዘመናቸው እንዲከናወኑ የሚያስገድዱት ሰዎች እነዚህን ነገሮች ለማከናወን የብስለታቸው ደረጃ እንደ ዕድሜያቸውና በዚያ ዕድሜ የተነሣ እንደሚያገኙት ልምድና ዕውቀት ብሎም አካላዊ
Posted in Ethiopian News, Religion

የተሰበሰበ ድንች (ካለፈው የቀጠለ)

click here for pdf እኔና ባለቤቴ ልክ እንዳንቺ ሆነን ነበር፡፡ ነገራችን ሁሉ ችኮ ሆኖ፡፡ ያ ድሮ እንደ መልካም ሙዚቃ ጆሮሽን አዘንብለሽ የምትሰሚው የባልሽ ድምጽ ፍሬን እንደያዘ መኪና ድምጽ ሲሆንብሽ ይሰማሻል፡፡ ይናፍቅሽ የነበረው ድምጽ ሲደውል ሐሳብ ውስጥ ይጥልሻል፡፡ ደግሞ ምን ሊል ይሆን? ትያለሽ፡፡ ስልክ ከማንሳት ይልቅ ስልኩን ለመዝጋት ትቸኩያለሽ፡፡ ለመሆኑ ባል ማለት ምንድን ነው? ለእኔ ከባልሽ ጋር ብቻ የምታደርጊያቸው ነገሮች ስላሉ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትቀልጃቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምታወሪያቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትሠሪያቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትወስኛቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትባልጊያቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምታኮርፊያቸው፡፡ ለአንቺ ብቻ የሚቀጸሉ፣ለአንቺ ብቻ የሚውሉ፣ ለአንቺ ብቻ የሚነገሩ፣ ለአንቺ ብቻ የሚገለጡ፣ ለአንቺ ብቻ የሚደረጉ፣ ለአንቺ ብቻ የሚሰሙ የተለዩ ነገሮች ከሌሉ ምኑን ሚስት ሆንሺው፡፡ ባልሽ ደግ፣ ሩኅሩኅ፣ ትዕግሥተኛ፣ የማይሰክር፣ ገንዘብ የማያባክን፣ ታማኝ፣ መልከ ቀና  ቢሆን እጅግ የታደልሽ ትባያለሽ፡፡ ይኼ ሁሉ ግን መልካም ሰውነቱን እንጂ መልካም ባልነቱን አያሳይም፡፡ ደግ ሰው፣ ቆንጆ ሰው፣ ትጉኅ ሰው፣ ፍጹም ሰው ያሰኘዋል እንጂ
Posted in Ethiopian News, Religion

‹የተሰበሰበ ድንች›

click here for pdfከለም ሆቴል ወደ ካዛንቺስ የሚሄድ ታክሲ ውስጥ ገብቼ ከኋላ ወንበር ተቀመጥኩ፡፡ ከጎኔ ሁለት በዕድሜ ወደ ሠላሳዎቹ አጋማሽ የሚሆኑ ሴቶች ተቀምጠዋል፡፡ ታክሲው ሲንቀሳቀስ ‹‹ለመሆኑ ምን ዓይነት ነገር ቢገጥምሽ ነው ለመንገር ያስቸግራል የምትይኝ›› አለቻት መካከል ያለቺዋ ወደ መስኮቱ ጥግ የተቀመጠችውን፡፡ እንደ ታክሲ መቼም ማኅበራዊ ኑሯችንን የምናውቅበት ምቹ መድረክ የለምና ጆሮዬን ጣል አደረግኩ፡፡ ‹‹ባክሽ ችግሩን ከመሸከሙ ችግሩን መግለጡ ይከብዳል›› አለች ያችኛዋ፡፡ አንድ ሊቅ ‹‹እጅግ አስቸጋሪው ችግር ሊገልጡት የሚያስቸግር ችግር ነው›› ያሉትን አስታወሰኝ፡፡ ምን እንደገጠማት ባላውቅም አንዳንድ ችግር ግን የሕመሙን ያህል መግለጫ ነገር አይገኝለትም፡፡ ሲናሩት ተራ ወይም ቀላል ይሆናል፡፡ ሰሚውም ‹‹አሁን ይኼ ችግር ነው?›› ይላል፡፡ ተናጋሪውም ንግግሩ ቀላል ስለሚሆንበት ከችግሩ በላይ ያመዋል፡፡ ‹‹ግዴለሽም እንደምንም ብለሽ ንገሪኝ›› አለቻት፡፡ ‹‹አንቺና ባለቤትሽ ስታወሩ እንዴት ነው?›› ስትል ጥያቄዋን በጥያቄ መለሰችው፡፡‹‹እንዴት?በቃ ማውራት ነዋ፡፡››‹‹ስታወሩ ምን ይሰማሻል?››‹‹ፊዚክስ አደረግሽዋኮ›› አለች እየሳቀች፡፡‹‹እኔ ግን ከእርሱ ጋር ሳወራ ያመኛል፡፡››‹‹እንዴት? ይሰድብሻል፤ ይቆጣል፤ ምን ዓይነት ክፉ ቃል ቢናገርሽ ነው›› በመስኮቱ ጥግ ያለችው ሴት አንገቷን ስትነቀንቅ በዚህኛው
Posted in Ethiopian News, Religion

መጀመሪያ ሰው ነኝ

click here for pdfአንድ ወዳጄ በየገጸ ድሩና በየውይይት መድረኩ የሚሰማውን ‹መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ፣ መጀመሪያ ትግሬ ነኝ፣ መጀመሪያ አማራ ነኝ› የሚል ክርክር አየና ‹አንተ መጀመሪያ ምድንነህ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ እኔ መጀመሪያ ሰው ነኝ፡፡ የተፈጠርኩትም ሰው ሆኜ ነው፡፡ አምላክም የፈጠረው ሰውን ነው፡፡ ቡድን፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ጎሳ፣ ነገድ የሚባሉ ነገሮችን ፈጠረ የሚል መጽሐፍም ትምህርትም አላገኘሁም፡፡ ክብርም፣ ሥልጣንም፣ ጥበብም፣ ፈጣሪውን መምሰልም የተሰጠው ለሰው ነው፡፡ መላእክት ሲፈጠሩ በማኅበር ነው የተፈጠሩት፡፡ አንድ ላይ ነው የተገኙት፡፡ ሰው ግን ሲፈጠር በየተራ ነው፡፡ መጀመሪያ አዳም፣ ከዚያ ሔዋን፣ ከዚያ ቃየል፣ ከዚያ አቤል እያለ ተራ በተራ፡፡ ቡድኖቹን ሰው በኋላ ራሱ ፈጠራቸው እንጂ አብረውት አልተፈጠሩም፡፡ መጀመሪያ ሰውነቴ ነበረ፡፡ በኋ ቡድኔ መጣ፡፡ በኋላ የመጣው ቡድኔ በፊት የነበረውን ሰውነቴን ከዚህ አትለፍ ከዚህ አትውጣ፣ ከዚህ አትዝለል ከዚህ አትሻገር አለው፡፡ ቡድኔ በእኔ መጠራት ሲገባው እኔ በቡድኔ ተጠራሁ፡፡ ለእርሱ ህልውና ሲል እኔን ሰዋኝ፡፡ እርሱ ሳይመጣ በፊት ግን እኔ ሰውዬው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ ሰው ስለነበርኩ መጀመሪያ ሰው ነው መከበር ያለበት፣ መጀመሪያ
Posted in Ethiopian News, Religion

‹ሐተታ ዘርአ ያዕቆብ›

‹ሐተታ ዘርአ ያዕቆብ› የተሰኘውን መጽሐፍ በተመለከተ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ(እድሜያቸውን ያርዝምና) ከመልካም ሐተታ ጋር አዘጋጅተውታል፡፡ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ማን ጻፈው? ዘርአ ያዕቆብ ማነው? ትውልዱስ የት ነው? ፍልስፍናው ከየት መጣ? እውነት ኢትዮጵያዊ ነው ወይስ የውጭ ሰው? ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ ለመከራከር በመጽሐፉ ውስጥ ማስረጃዎች አሉን? የሚሉትንና ሌሎች ጥያቄዎችን አንሥተው ይተነትናሉ፡፡ መጽሐፉንም ተርጉመውና አትተው አቅርበውታል፡፡ የሚከተለውን ሊንክ ተጫኑና በነጻ አንብቡት፡፡http://www.ethiopiawin.com/wp-content/uploads/2014/10/Hateta-Ze-Zera-Yaiqob.Amharic.pdf 
Posted in Ethiopian News, Religion

የማያለቅስ ልጅ

ፎቶ - ሐራ ተዋሕዶ click here for pdf ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን ሕግ በተመለከተ አሠረ ሐዋርያትን የተከተለ ሆኖ እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡ አባቶቻችን በቤተ ክርስቲያን ላይ ግለሰባዊ አምባገነንነትን አልፈቀዱም፡፡ ጸሎተ ሃይማኖቱም ‹ነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት›› በማት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ዘሐዋርያት መሆንዋን ያመለክታል፡፡ በ50/51 ዓም በኢየሩሳሌም የተሰበሰበችው ሲኖዶስም ‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› አለች እንጂ  ‹እኔ› የሚል ግለሰባዊ ድምጽ አልተሰማባትም፡፡ኢትዮጵያውያን አበው የቅዱስ ሲኖዶስን ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ሌሎችን የቤተ ክርስቲያን የአመራር ሥርዓቶች ከግለሰብ አምባገነንነት ለማውጣት መልካም የሆነ ሥርዓት ሠርተዋል፡፡ ቅዳሴው በአምስት ልዑካን እንዲሆን፣ አጥቢያው በሰበካ ጉባኤ እንዲመራ፣ ገዳማት በምርፋቅ (ጉባኤ አበው) ወይም በማኅበር እንዲመሩ፣ ጵጵስናን አንድ ጳጳስ (ፓትርያርክ እንኳን ቢሆን) ብቻውን እንዳይሰጥ፣ ቢያንስ ሦስት አበው ሊኖሩ እንደሚገባ፤ አንድ አባት ብቻውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንዳይለውጥ፤ አድርገው የሠሩበት አንዱ ምክንያት ግለሰባዊ አምባገነንነትን ለመቋቋም እንዲቻል ነው፡፡ይህንን ማኅበራዊና ጉባኤያዊ የሆነ የቤተ ክርስቲያን አሠራርና አመራር ለማስወገድ በየዘመናቱ ጥረት ተደርጓል፡፡ የዚህም ምክያቱ ግልጽ ነው፡፡ ግለሰባዊ የሆነ አመራር
Posted in Ethiopian News, Religion

‹‹የነ እንትና ታቦት››

click here for pdfዓርብ ዕለት የተከበረውን የአቡነ አረጋዊ በዓል ለማክበር አውስትራልያ አደላይድ ነበርኩ፡፡ እዚያ ከተማ የሚገኝ አንድ የድሮ ወዳጄ በፌስ ቡክ አገኘኝና አደላይድ መሆኔን ነገርኩት፡፡ ‹‹የት እንገናኝ›› ሲለኝ ‹‹ነገ (ቅዳሜ) የአቡነ አረጋዊን በዓል ለማክበር ስለምሄድ እዚያ እንገናኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹አንተም እርሱን በዓል ታከብራለህ?›› አለኝ፡፡ በዓይነ ኅሊናየ ራሱን እየነቀነቀ ታየኝ፡፡ ‹‹እንዴት?›› አልኩት፡፡ ‹‹የእነ እንትና ታቦት አይደል እንዴ›› አለኝ የሆነ የኢትዮጵያ አካባቢ ጠርቶ፡፡ ‹‹ማን እንደዚያ አለ?›› ስል ጠየቅኩት፡፡ ‹‹ምን፣ የታወቀኮ ነው›› አለኝ፡፡ እየገረመኝ ተለያየን፡፡ በማግሥቱ በዓሉ ላይ ተገኘሁ፡፡ በዓሉን እኩለ ቀን ላይ ጨርሼ ስወጣ ሌላ የጥንት ዘመዴን አገኘሁት፡፡ ያ ትናንት ማታው ጓደኛዬ እዚህ ከተማ እንዳለ የማላውቅ መስሎት ይኼኛው ነገረኝ፡፡ እኔም ሰው ላለማጋጨት ብዬ ያለኝን ሳልዘረዝር እንዴው በደፈናው ደውዬለት መምጣት አልችልም እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ ይኼኛውም እኔ እንዳልነግረው የደበቅኩትን እርሱ ገልብጦ ነገረኝ ‹‹የኛ ታቦት ሲሆንኮ እነ እንትና አይመጡም›› አለኝ ፈገግ እያለ፡፡ ‹‹ማን ነው የእናንተ ታቦት ያደረገው›› አልኩ በአግራሞት›› ‹‹ያው አቡነ አረጋዊ የኛ ሀገር ሰው አይደሉ›› አለኝ
Posted in Ethiopian News, Religion

የአውስትራልያ ትምህርት በረከቶች ለአፍሪካ፡- ዕድሎችና ተግዳሮቶች(ሪፖርታዥ)

click here for pdfርብራብኃይለ ልዑልና ዶ/ር ብርሃነ ከቀድሞው የአውስትራልያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኬቪ ሩድ ጋርበየሀገሩ ስዞር ለሀገራቸውና ለወገናቸው ልዕልና ያለው ሥራ የሚሠሩ፣ ወግ ያለው ታሪክ ያላቸው፡፤ ከመንደርተኛነትና ወንዘኛነት ድንበር ተነጥቀው በሉላዊነት መንበር ላይ የተቀመጡ፣ ከምድጃ ሥር ወሬ ርቀው ዓለም ተኮር ነገር ውስጥ የሚዘውሩ ዜጎቻችንን ሳይ ትፍትፍ እላለሁ፡፡ እሥራኤሎች በልዩ ልዩ ሀገር ሆነው ለሀገራቸው የሠሩ ዜጎችን ታሪክ ሲጽፉ ‹የኛ ሰው በዚህ ቦታ› የሚሉት ዓይነት ርእስ ይሰጣሉ፡፡ ‹የኛ ሰው በደማስቆ› እንዲል ማሞ ውድነህ፡፡ ባለፈው ኀሙስ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓም እናንተ አቦን ስታከብሩ እኔ ደግሞ እዚህ ሜልበርን ለየት ያለ ግብዣ ደረሰኝ፡፡ የጋበዘኝ የአፍሪካና አውስትራልያ ማኅበር(African Australian Association - AAA ) ዋና ዳይሬክተሩ በሆነው ኃይለ ልዑል ገብረ ሥላሴ በኩል ነው፡፡ ኃይለ ልዑል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ካበረከተቻቸው አዳጊ የማኅበረሰብ መሪዎች አንዱ ነው፡፡ ከ ላ ቶቤ የኑቨርሲቲ በ2000 በዓለም አቀፋዊ ልማት ማስተርስ ያገኘ፣ በ2008 ከሜልበርን ዩኒቨርሲቲ በማኅበረሰባዊ ፖሊሲና አስተዳደር በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ ሰው ነው፡፡ የኢትዮጵያ
Posted in Ethiopian News, Religion

‹ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለም፣ ካህናቱ›

click here for pdfቅዱስ ጳውሎስ ተከስሶ በቂሣርያው ገዥ በፊስጦስ ፊት በቀረበ ጊዜ አይሁድ ለብቻቸው ቀርበው በቅዱስ ጳውሎስ ላይ ይፈርድበት ዘንድ ጎትጉተውት፣ እነርሱ ማስረጃ ያሉትንም አቅርበውለት፣ ሕጋቸውንም ጠቅሰው ማሳመኛ አቅርበውለት ነበር፡፡ አሕዛባዊው ገዥ ፊስጦስ ግን እግዚአብሔርን እናውቃለንም፣ እንፈራለንም ከሚሉት አይሁድ ተሽሎ ያሉትን ከማድረግ ራሱን ከለከለ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ጉዳዩን አቀረበላቸው፡፡ ፊስጦስ አይሁድ ያቀረቡትን ስሞታ፣ ውትወታና ክስ ተቀብሎ በቅዱስ ጳውሎስ ላይ ያልፈረደበትን ምክንያት ለአግሪጳ ሲገልጥለት ‹‹ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም፣ ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፣ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም›› ብሎ መሆኑን ነግሮታል (የሐዋ.25÷16)፡፡ ይህ በሮማውያን ዘመን እጅግ የታወቀውን ራስን በእኩል ደረጃ የመከላከል መብት በተመለከተ ሮማዊው ታሪክ ጸሐፊ አፒያን (95-165ዓም) በጻፈው Civil War በተሰኘው መጽሐፉ (3:54) ላይ ‹‹የምክር ቤት አባሎች፣ ሕጉ የተከሰሰ ሰው የተከሰሰበትን ሰምቶ በእርሱ ላይ ከመፈረዱ በፊት መልስ የመስጠት መብት አለው ይላል›› ሲል አሥፍሮት ነበር፡፡ ፊሊክስ የጠቀሰው ይኼንን ነው፡፡ አበው
Posted in Ethiopian News, Religion

አርሴማ

ዐጽሟ ያረፈበት አርመን የሚገኘው ቤተ ክርስቲያንቅድስት አርሴማ በ290 ዓም በአርመን በሰማዕትነት ያረፈች ወጣት ክርስቲያን ሰማዕት ናት፡፡ ትውልዷ ሮም ሲሆን ሰማዕትነት የተቀበለችው አርመን ነው፡፡ እኛ አርሴማ ስንላት እነርሱ Saint Hripsime ይሏታል፡፡ ታሪኳን የፈለገ ሰው በዚህ ስሟ ጎጉል ላይ ቢፈልግ በቀላሉ ያገኘዋል፡፡ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መስከረም 29 ቀን ወይም ኦክቶበር 9 ሰማዕትነት የተቀበለችበትን ቀን ያከብራሉ፡፡ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን በስሟ የተሠራውም አርመን ኤችሚዚን ውስጥ በ395 ዓም ነው፡፡ ይህ የአርሴማ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ሳይፈርሱ ከኖሩት እጅግ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ነው፡፡የዚህች ወጣት ሰማዕት ታሪክ በስንክሳር በመስከረም 29 ቀን ተጽፏል፡፡ በሀገራችን ገድላቸው ከተተረጎመላቸው የውጭ ቅዱሳን አንዷ አርሴማ ናት፡፡ የዚህ ምክንያቱ የታወቀ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ አርመን ከአርመንም ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱና የሚመጡ ቅዱሳን ነበሩ፡፡ በ10ኛው መክዘ አካባቢ በአርመን የደረሰውን የፋርሶችን ወረራ በመሸሽ አያሌ አርመናውያን ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውንና ዛሬ ሐይቅ እስጢፋኖስ በተባለው ቦታ መሥፈራቸውን የአርመን ታሪክ ይነግረናል፡፡ በአርመንኛ ‹ሐይቅ› ማለትም ገዳም ማለት ነው ይላሉ፡፡   
Posted in Ethiopian News, Religion

ፍቅር፣ ቁልፍና ድልድይ

click here for pdfበሜልበርን እምብርት እየተሽረከርን በያራ ወንዝ ዳርቻ ስንዋብ ወደ ሌላ አቅጣጫ የመሻገሪያ የእግረኞች ድልድይ ላይ ደረስን፡፡ የያራ ወንዝ ዓባይን በሰኔ መስሏል፡፡ እዚህ ወንዝ ዳር ነው የዛሬ 179 ዓም እኤአ 1835 የሜልበርን ከተማ የተቆረቆረችው፡፡ ከ242 ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል ያራ ወንዝ፡፡ የመሻገሪያው ድልድይ ወንዙ መካከል በአንዲት አነስተኛ ጀልባ በምትመስል ኮንክሪት መሬት ላይ ቆሟል፡፡ ሀገሬዎቹ ደሴት ብርቃቸው ነው መሰለኝ ‹ፖኒ ፊሽ ደሴት› ይሏታል፡፡ መቼም ፈረንጅ ትንሽን ነገር ታላቅ በማድረግ የሚተካከለው የለም፡፡ ይህንን ድልድይ እያቋረጥን ስንሄድ በግራና ቀኝ በድልድዩ መደገፊያ ላይ የታሠሩና የተቆለፉ ቁልፎችን አየሁ፡፡ ሙሉ የድልድዩን ብረት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይዘውታል፡፡ አንዳንዶቹ በሀገራችን ለስታድዮም በር ብቻ ሊውሉ የሚችሉ ቁልፎች ናቸው፡፡ እነዚህ በፍቅራቸው ላይ ሥጋት ሳይኖርባቸው አይቀርም፡፡ አንዳንዶቹ ቁልፎችም ከቻይኖች ዓይን እንኳን ያነሱ ናቸው፡፡ ይህንን ዓይነት ነገር የገጠመኝ ፓሪስ ነበረ፡፡ በፓሪስ የሚገኙ ድልድዮች በዚያ ስማቸውን ጽፈውና ቁልፋቸውን ቆልፈው በሚያንጠለጥሉ ፍቅረኞች ምክንያት ለአደጋ መጋለጣቸውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ቢጮህ እንኳን ሰሚ አላገኘም፡፡ በተለይ
Posted in Ethiopian News, Religion

ጨረቃና ጨለማ

click here for pdfበ1768 እኤአ የተጻፈና ጥንታዊ አባባሎችን የያዘ አንድ ‹‹AN ETHIOPIAN SAGA›› የተሰኘ መጽሐፍ ሳነብ ‹‹ጨረቃዋን እያየህ፣ ጨለማውን ግን እየተጠነቀቅ ተጓዝ›› የሚል ጥንታዊ ብሂል አየሁ፡፡ ይህ ለጥንቱ መንገደኛ የተሰጠ የጠቢብ ምክር ነው፡፡የጥንቱ ተጓዥ ጤፍ በምታስለቅመው ጨረቃ መጓዙ ሁለት ጥቅሞች ይሰጡት ነበር፡፡ በአንድ በኩል በቀን ከሚገጥመው ሙቀትና የፀሐይ ቃጠሎ ይድናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንገዱን በሩቁ ስለማያየው ‹ለካ ገና ብዙ መንገድ ይቀረኛል› እያለ መንፈሱ እንዳይደክም ያደርገዋል፡፡በተለይም ደግሞ መንገደኞቹ በዛ ካሉ፣ ሰብሰብ ብለው በአንድ ቤት ታዛ ሥር ወይም በአንድ ዛፍ ጥላ ሥር ያርፉና በአራተኛው ክፍለ ሌሊት(ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት በኋላ) ተነሥተው የጨረቃዋን ብርሃን እየተከተሉ መጓዝ ነው፡፡ ያን ጊዜ  ነው እንግዲህ ‹ከጨለማው እየተጠነቀቁ፣ ነገር ግን ጨረቃዋን እያዩ›› የሚጓዙት፡፡መንገደኞቹ ጨረቃዋን የሚያዩዋት ለሁለት ነገር ነው፡፡ በአንድ በኩል ጨረቃዋ መጀመሪያ እየደመቀች፣ በኋላ ደግሞ እየደበዘዘች መጓዟ የሌሊቱን ማለፍና የቀኑን መምጣት ይነግራቸዋል፡፡ በተለይ የበረሐ መንገደኞች ከሆኑ የጨረቃዋ እየደበዘዘች መሄድ ለእነርሱ መልካም ዜና አይደለም፡፡ የሙቀቱን መምጣት እያረዳቸው ነውና፡፡ የፀሐዩን ግለትም
Posted in Ethiopian News, Religion

እምቢታ (የቃቄ ወርድወት)

click here for pdfደራሲ - እንዳለ ጌታ ከበደዋጋ - 49 ብርአታሚ - ኤች ዋይ ማተሚያ ቤትእንዳለ ጌታ የጻፈውን እምቢታ መጽሐፍ ከአዲስ አበባ ወደ አውስትራልያ እየተጓዝኩ አውሮፕላን ውስጥ ነው ያነበብኩት፡፡ መጽሐፉ ለገበያ ሲቀርብ እንደማልኖር ስላወቀ ቀድሜ እንዳገኘው በማድረጉ አመሰግነዋለሁ፡፡ ይኼ በታሪክና በሥነ ቃል(ፎክሎር) ላይ የተመሠረተ ልቦለድ በአንዲት ብዙዎቻችን በማናውቃት ከዘመን የቀደመች ሴት ጀግና ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡ቃቄ ወርድወት ትባላለች፡፡ በነገራችን ላይ ቃቄ የአባቷ ስም ነው፡፡ የእርሷ ስም ወርድወት ነው፡፡ በጉራጌ ባሕል የአባትን ስም ከልጅ የሚያስቀድም ጥንታዊ ሥርዓት ነበረ ማለት ነው፡፡ ምናልባትም በዕውቀቱ ስዩም ‹በኢትዮጵያ ከልጅ ስም በፊት የአባት እንደሚቀድም ማስረጃ አለኝ› ያለው አንዱ ይኼንን ሳይሆን አይቀርም ብዬ ገምቻለሁ፡፡ የመጽሐፉን ረቂቅ መመልከቱን መግቢያው ላይ ያሳያልና፡፡ ቃቄ ወርድወት በ1840ዎቹ አካባቢ ከጉራጌ ማኅበረሰብ የፈነጠቀች ኢትዮጵያዊት ኮከብ ነበረች፡፡ በሴቶች ላይ የነበረውን አድሏዊ ልማዳዊ ሥርዓት ለመታገል፣ በጋብቻ ሥርዓት ወንዶቹ ከሴቶቹ ይልቅ ሥልጣን ለማደላደል፤ ሴቶች ከለፉበት ትዳራቸው ያለ አንዳች ንብረት በፍቺ መባረራቸውን ለማስቀረት የታገለች ጀግና፡፡ ዛሬ እንኳን ለብዙ
Posted in Ethiopian News, Religion

ሰነቦ

click here for pdfነሐሴ 23 ቀን 2006 ዓም ማለዳ 10 ሰዓት ነው ከዕንቅልፌ የነቃሁት፡፡ ዲያቆን  ሙሉቀን ብርሃን ከጎንደር፣ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ ከፍኖተ ሰላም መንገድ ላይ ይጠብቁኛል፡፡ ለመንገዱ የሚሆነውን የቱሪስት መኪና ያዘጋጀልኝ የኦሪጂንስ ኢትዮጵያ አስጎብኝ ድርጅትባለቤት ሳምሶን ተሾመ ነው፡፡ ክብር ይስጥልኝ ብያለሁ፡፡ የምተርክላችሁን ታሪክ ስትጨርሱ ትመርቁታላችሁ ብየ አምናለሁ፡፡ የምጓዘው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ለማደርገው ጥናት ተጨማሪ መረጃዎችን ፍለጋ ነው፡፡ ሾፌራችን ደምስ ይባላል፡፡ ዝምታና ትኩረት ገንዘቦቹ የሆኑ፣ በሁሉም ነገር ለመንገድ የተዘጋጀ፡፡ ለተራራ ቢሉ ለቁልቁለት፣ ለበረሐ ቢባል ለደጋ የሚሆኑ መሣሪያዎችን ሸክፎ የያዘ ልምድ ያለው ሾፌር ነው፡፡ ዓባይ በረሐ መግቢያ ላይየምንጓዘው ከምድር ሥር ከሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎቻችን ወደ አንዱ ነው፡፡ በጎጃም በር በኩል ወጥተን ፍቼና ጎሐ ጽዮንን አቋርጠን በክረምት ውበቱ እጥፍ ድርብ ወደሚሆነው ዓባይ በረሐ መንደርደር ቀጥለናል፡፡ ዓባይ በረሐ የሚባል ቦታ መቼም አያልፍለት፡፡ አበሻ ቢሠራው፣ ጣልያን ቢሠራው፣ ጃፓን ቢሠራው መሬቱ እንደሆነ ድንጋይ ላይ እንዳስቀመጡት ሰው ሲንቀሳቀስ ይኖራል፡፡ይንሸራተታል ተጠንቀቁተሻገርንና ደጀንን አለፍናት፡፡ ከደጀን እስከ ደብረ ማርቆስ
Posted in Ethiopian News, Religion

ጳጉሜን – አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት

click here for pdfየመግቢያ ማስታወሻበጽሑፉ ውስጥ በግእዝ ቁጥሮች በቅንፍ ውስጥ የተጻፉት ሐሳቡን እንዲወክሉ ብቻ ነው፡፡ በኋላ (ቁጥር ፭ ተመልከት ቢል ያንን ሐሳብ መልሶ ለማየት እንዲረዳ ነው፡፡የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ጳጉሜ የምትባል አሥራ ሦስተኛ ወር ስላለችን ነው፡፡ የቤት ኪራይና የወር ደመወዝ የማንከፍልባትና የማንቀበልባት፤ መብራትና ውኃ ግን ከነሐሴ ወር ጋር ጨምረው የሚያስከፍሉባት፤ ሲሻት አምስት፣ ሲያስፈልጋት ስድስት፣ ስትፈልግ ደግሞ ሰባት የምትሆን ወር ናት፡፡ እንዲያውም ከአሥራ ሁለቱ የኢትዮጵያ ወሮች ጳጉሜ በብዙ መንገድ የተለየች ናት፡፡በአንድ በኩል በጣም ትንሿ ወር ናት፡፡ ሲቀጥልም ወርኃዊ በዓላት የማይውሉባት ወር ናት፡፡ እንዲያም ሲል ደግሞ ከሌሎች ወሮች በተለየ የቀኖቿ መጠን የሚቀያየሩ ብቸኛ ወር ናት፡፡ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወሮች በተለየም ስሟ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ወር ናት፡፡ በሁለት ዘመናት መካከልም እንደ መሸጋገሪያ የምትታይ ወርም ናት፡፡  ጳጉሜ ማለት በግሪክ ‹ጭማሪ› ማለት ሲሆን ዓመቱን በሠላሳ ቀናት ስንከፍለው የሚተርፉትን ዕለታት ሰብስበው የሰየሟት ተጨማሪ ወር ናት፡፡ ወይም በየዕለቱ በፀሐይና በጨረቃ አቆጣጠር መካከል የሚፈጠረውን ልዩነት ሰብስበው ያከማቹባት
Posted in Ethiopian News, Religion

ዝሆን (ክፍል ሦስትና የመጨረሻው)

click here for pdfዝሆኖች አንድ የታመመ ወይም የቆሰለ ወገን ካላቸው እስኪድን ድረስ ይከባከቡታል፡፡ ምግብ ያቀርቡለታል፤ ከአደጋም ይጠብቁታል፡፡ ለዚህ ሁሉ ድካማቸው በኩምቢ የሚገለጥ ‹እግዜር ይስጥልኝ› በቂያቸው ነው፡፡ አንድ ቀን ግማሽ ኪሎ ብርቱካን ይዘን የጠየቅነውን በሽተኛ ሁሉ ውለታችንን ካልመለሰ ለምንል ሰዎች ከእኛ የሚሻሉ እንስሳት መኖራቸውን ማወቅ እንዴት መልካም መሰላችሁ፡፡ ዝሆኖች ይቅር ባዮች ናቸው፡፡ ዝሆን አደጋ የደረሰበትንም ያደረሰበትንም አይረሳም ይባላል፡፡ ጊዜ ጠብቆ የመበቀል አመል አለው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ችግር የፈጠረባቸው ኅብረተሰብ ወይም ግለሰብ ሲከባከባቸውና ለእነርሱ መልካምን ነገር ሲያደርግ ከተመለከቱ በቀላቸውን ሁሉ ለመተውና ይቅር ለማለት ፈጣኖች ናቸው፡፡ ይቅርታ ለመበቀል አለመቻል አይደለም፡፡ አለመፈለግ እንጂ፡፡ ይቅርታ ከዐቅም ማጣት ሳይሆን ከዐቅም ማግኘት የሚፈጠር ነው፡፡ በዝሆኖች መንጋ መካከል ችግር ፈጣሪ ከተገኘና ከተቀጣ ሁሉም ዝሆኖች ያገሉታል፡፡ ተስተካክሎ ከመጣ ግን ኩምቢያቸው በማነካካት ይቅር ማለታቸውንና መተዋቸውን ይገልጡለታል፡፡ ከዚያ በኋላ አለቀ፡፡ ሰውን ‹እንስሳ› ብለን የምንሳደብ እኛ ለይቅርታ የተዘጋጀ ልብ የለንም ማለት ከዝሆን ያነስን ነን ማለታችን ነው፡፡ ጉልበተኛነት ነውር ነው፡፡ በዝሆኖች ዘንድ ከባዱን
Posted in Ethiopian News, Religion

ዝሆን (ክፍል ሁለት)

click here for pdfዝሆኖች ለቤተሰባዊ ሕይወት ልዩ ቦታ አላቸው፡፡ የዝሆን መንጋ በእናት የሚመራ ነው፡፡ የሰው ልጅ ሴቶችን ወደ መሪነት ሳያመጣ፣ እነ ንግሥተ ሳባና ንግሥት ሕንደኬም ሀገር ሳይመሩ በፊት ዝሆኖች የእናቶችን መሪነት ተቀብለዋል፡፡ በዝሆኖች መንጋ ውስጥ ታላቅ መሆን ክብርንም ያመጣል ኃላፊነትንም ያስከትላል፡፡ እኛ ሀገር ብዙ ጊዜ ‹ታላቅነት› ክብርን ብቻ እንዲያመጣ ይታሰባል እንጂ ኃላፊነትን እንዲያስከትል አይፈለግም፡፡ በዝሆኖች ዘንድ ግን ታላቅ እናት ትከበራለችም፣ ኃላፊነት ትወስዳለችም፡፡ በማለዳ የዝሆኖች ውሎ ሲጀመር የዝሆን ቤተሰብ ለተግባር ሥምሪት ይወጣል፡፡ ብዙ ጊዜ አንድ ቤተሰብ ከ12 አባላት በላይ አይበልጥም፡፡ ይህም ልጆችንና የቅርብ ዘመዶችን ያካትታል፡፡ እናት ዝሆን ይህን ቤተሰብ በመምራት ወደ ምግብ ሥምሪት ስትነቃነቅ አመራርዋን የሚፈልጉ ሌሎች ዝሆኖች ይቀላቀሏታል፡፡ ወደ ረፋድ ላይ የመንጋው ቁጥር ወደ 25 ይደርሳል፡፡ ፀሐይ ልታቆለቁል ስታስፈራራ የመንጋው ቁጥር ወደ አንድ መቶ ያሻቅባል፡፡ ሲመሽ የመንጋው ቁጥር እየቀነሰና ሁሉም በየቤቱ እየገባ ይሄድና ወደ ቀደመው አሥራ ሁለት የቤተሰብ አባላት ይመለሳል፡፡ ይህ ሁሉ የሚመራው በአንዲት አረጋዊት ታላቅ እናት ነው፡፡ አንዳንድ የዝሆንን
Posted in Ethiopian News, Religion

ዝሆን

click here for pdf(ክፍል አንድ)የዝሆን ሥዕል፣ ወሎ ገነተማርያም ቤተ ክርስቲያንበሰው ልጆች የአደን፣ የጦርነት፣ የንግድ፣ የባሕልና የሃይማኖት ታሪክ ውስጥ ቦታ ካላቸው እንስሳት አንዱ ዝሆን ነው፡፡ ዝሆን ማደን የጀግንነት መገለጫ ሆኖ አዳኞቹን ሲያስመሰግንና ሲያስወድስ ኖሯል፡፡ በቀደምት ዘመናት በተደረጉ ጦርነቶችም ዝሆኖች የዛሬዎቹን ታንኮች ቦታ ተክተው አገልግለዋል፡፡ የአኩስሙ አብርሃ ከደቡብ የመን ወደ መካ ባደረገው የጦርነት ጉዞ አያሌ ዝሆኖችን ተጠቅሞ ስለነበር ዘመኑ ‹የዝሆኖች ዓመት› እየተባለ እስከ መጠራት ደርሶ ነበር፡፡ በበጥሊሞሳያን ዘመንም ግብጻውያን ከኢትዮጵያና አካባቢዋ ዝሆኖችን በመውሰድ ለጦርነት ተጠቅመውባቸዋል፡፡ የዝሆን ጥርስ ለጌጣጌጥ መሥሪያ መዋል የጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በነበሩ ጥንታውያን ሥልጣኔዎች ዘመን ነው፡፡ ይህ የዝሆን ጥርስ ንግድ ዝሆኖችን ከልዩ ልዩ አካባቢዎች እንዲጠፉና ዛሬም ቁጥራቸው እንዲመነምን ዋናውን ክፉ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ ዝሆን በልዩ ልዩ ባሕሎችና ሃይማኖቶች ዘንድ የጥንካሬ፣ ወድቆ የመነሣት፣ ታላቅን የማክበርና የማስታወስ ተምሳሌት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ ላይ የምናገኘው የ‹ዐቢይ ነጌና የውርዝው ነጌያት› ምሳሌ ለዚህ ማሳያ ይሆናል፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍልም ‹ሔርማዝ› የሚለው ጥንታዊ የዝሆን መጠሪያ  ለ‹ጀግና›
Posted in Ethiopian News, Religion

አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ዋጋ 60 ብር
Posted in Ethiopian News, Religion

ሕግና ሥርዓት – በሐበሻ አሜሪካ

click here for pdfአሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ስዘዋወር ከአስተባባሪዎቹ የምሰማው ተመሳሳይ ሮሮ አለ፡፡ ብዙዎቹ አብያተ ክርስቲያናት የራሳቸው ሕንጻ እስኪያገኙ ድረስ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተከራይተው ይገለገላሉ፡፡ የራሳቸው ሕንጸ ያላቸውም ቢሆኑ ከአሜሪካዊው ማኅበረሰብ ጋር ይጎራበታሉ፡፡ በሰንበት ቅዳሴና የንግሥ በዓላት በሚከበሩባቸው ቀናት በመኪና ማቆሚያ፣ በድምጽ፣ በአካባቢው በብዛት በመገኘትና በጽዳት ጉዳዮች አብያተ ክርስቲያናቱ ካሉባቸው መንደሮች ነዋሪዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡እነዚህ ግንኙነቶች ግን ብዙውን ጊዜ ሰላማውያን አይሆኑም፡፡ አልፎ አልፎ ችግሩ ከሌሎች ወገን ቢመነጭም ዋናው ችግር ግን ከራሳችን የሚመጣ መሆኑን አስተባባሪዎችም ማኅበረሰቡም ያምኑበታል፡፡ ፈታኙ ነገር ችግሩን ለማስተካከል አለመቻሉ ነው፡፡ ‹ከተማ የጉርብትና ሥርዓት ነው› የሚለውን የከተሞችን አንዱን መርሕ በጉልሕ ለማየት ከሚቻልባው ሀገሮች አንዷ በሆነችው አሜሪካ የመንደርተኞች ሕጎችና ባሕሎች ጥብቅ ናቸው፡፡ በተለይም ግለሰባዊ ኑሮን መሠረት ባደረገው የአሜሪካ የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ በአንድ መንደር የሚከናወኑ ተግባራት የግለሰቦችን መብቶች እንዳይነኩ ጥንቃቄ ይደረግባቸዋል፡፡አንድ የመንደሩ ነዋሪ የራሱን መብት አስጠብቆ፣ በሌሎቹ መብት ላይ ሳይደርስ፣ ነገር ግን ደግሞ አካባቢያዊ ግዴታውን ተወጥቶ የሚኖርበት የመንደር ሕግ
Posted in Ethiopian News, Religion

ንሥር (ክፍል ሁለት)

click here for pdf ንሥር ሳይፈትን አያምንም፤ አይተማመንምም፡፡ ሴቷ ንሥር ባል ማግባት ስትፈልግ አንድ እንጨት ታነሣና ወንዱ እየተከተላት ወደ ላይ ትመጥቃለች፡፡ እስከ ሰማይ ጥግ ከደረሰች በኋላም ያንን እንጨት ትለቀዋለች፡፡ ያን ጊዜ ወንዱ እንጨቱ መሬት ከመድረሱ በፊት በፍጥነት በመወርወር መያዝና ለሴቷ መልሶ ማምጣት ይጠበቅበታል፡፡ ሴቷም እንጨቱን ተቀብላ እንደገና ወደ ቀጣዩ ከፍታ ትመጥቅና እንጨቱን መልሳ ትጥለዋለች፡፡ አሁንም ወንዱ ንሥር ከእንጨቱ የውድቀት ፍጥነት ቀድሞ ያንን እንጨት በመያዝ ለሴቷ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ እንዲህ ያለው ፈተና ወንዱን ለሰዓታት ያህል ይጠብቃዋል፡፡ ከፍታው እየጨመረ፣ እንጨቱም ይበልጥ እየተወረወረ ይሄዳል፡፡ ሴቷ ንሥር ወንዱ ንሥር ፈጣንና የተወረወረለትን ለመያዝ ያለውን ቆራጥነት እስክታረጋግጥ ድረስ ፈተናው ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻም ቆራጥና ፈጣን፣ ማንኛውም ችግር የማይበግረው መሆኑን ስታረጋግጥ ባልነቱን ትፈቅድለታለች፡፡ንሥርም እንዲህ ትልሃለች፡- በግላዊ ሕይወትህ፣ በንግድህም ሆነ በሌላው ኑሮህ ከሰዎች ጋር መወዳጀት፣ አብሮ መሥራትና መንገድ መጀመር ያለብህ ለዓላማቸው ምን ያህል ጽኑና ቆራጥ፣ ትጉና አይበገሬ መሆናቸውን አረጋግጠህ መሆን አለበት፡፡ ሳታረጋግጥ መግባት ትርፉ ፀፀት ነው፡፡ እንኳን ሌሎችን ራስህንም ለአዲስ ተልዕኮ ከማሠማራትህ
Posted in Ethiopian News, Religion

ንሥር

click here for pdf ንሥር እጅግ ግዙፍ ከሆኑ የአዕዋፍ ዝርያዎች አንዱ ነው፡፡ ክብደቱ እስከ 6.7 ኪሎ ሲደርስ ቁመቱ ደግሞ ከአንዱ ክንፉ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ 2 ሜትር ተኩል ይደርሳል፡፡ በዓለም ላይ እስከ ስድሳ የሚደርሱ የንሥር ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡በኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ንሥር የትንሣኤ ሙታን፣ አርቆ የማሰብ፣ ወደ ላይ የመምጠቅና የመነጠቅ፣ የጥበቃና የምናኔ ተምሳሌት ሆኖ ተገልጧል፡፡ ግብጻውያን ደግሞ የተቀበሩ ሰዎችን አጋንንት እንዳይደርሱባቸው በመቃብራቸው በር በድንጋይ ላይ የንሥርን ምስል ያስቀርጹ ነበር፡፡ ይጠብቃቸዋል ብለው፡፡ በግሪክ አፈ ታሪክ የአማልክት ንጉሥ የሚባለው ዜውስ በንሥር የሚመሰል ነበር፡፡ ጥንታውያን የአሜሪካ ሕዝቦች እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው የንሥርን ላባ በመስጠት ክብራቸውንና ፍቅራቸውን ይገልጡ ነበር፡፡ ሞቼ የተባሉት የፔሩ ሕዝቦችም ንሥርን ያመልኩት ነበር ይባላል፡፡ ንሥር ይህንን ያህል ቦታ በሕዝቦች ባሕል ውስጥ ሊይዝ የቻለው በተፈጥሮው በታደላቸው የተለያዩ ጸጋዎች የተነሣ ነው፡፡  ንሥር ከእንስሳት ሁሉ ወደ ሰማይ በመነጠቅ የሚተካከለው የለም፡፡ እርሱ የሚደርስበትን የሕዋ ከፍታ የትኛውም ዓይነት ወፍ አይደርስበትም፡፡ አንዳንድ አዕዋፍ እስከ ተወሰነ ድረስ
Posted in Ethiopian News, Religion

እንደገና እንጋባ(የመጨረሻ ደብዳቤ)

click here for pdfይኼ የመጨረሻዬ ደብዳቤ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ወይ እንደገና እንጋባለን አለበለዚያም እኅትና ወንድም ሆነን እንቀጥላለን፡፡ አሁን ‹እኅትና ወንድም ሆኖ መቀጠል›› ሲባል ቀላል ነገር ይመስላልኮ፡፡ የተለያዩ ባልና ሚስቶች ‹እኅትና ወንድም› ሆነው ለመቀጠል ሦስት ነገሮች ሳያስፈልጋቸው አይቀርም፡፡ ጠላትነትን ማጥፋት፣ ሌላ ዓይነት ወዳጅነትን መቀጠልና በአዲሱ መንገድ የሚመጡትን አስከፊ ነገሮች ሁሉ ለመቀበል መቻል፡፡ አንዳንድ ተጋቢዎች ሲለያዩ በጋብቻ ምትክ ጠላትነትን ተክተው ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ እንኳን ከዚህ በፊት አንድ ሆነው የኖሩና አንድ ሆነው ያደሩ፣ የተዋወቁም አይመስሉ፡፡ አንዱ ሌላውን ሲያስበው ያንገሸግሸዋል፡፡ ‹‹በለው በለው፣ ግደለው ግደለው› የሚለው ስሜት ይመጣበታል፡፡ ከፍቺ በኋላ ለሚፈጠሩ አሰቃቂ ወንጀሎች አንዱ ምክንያትም ይኼው ነው፡፡ ንብረት ክፍፍል ላይ ‹‹ይህንንማ አትገኛትም፣ አያገኛትም›› እየተባባሉ ምርኮ ስብሰባ የሚያስመስሉትም ለዚህ ነው፡፡‹ሌላ ዓይነት ወዳጅነት› ያልኩሽ ቢያንስ ለመጠያየቅ፣ ተገናኝቶም ቢሆን ሻሂ ለመጠጣት፣ ስለ ልጆች ለመነጋገር፣ ቤተሰቦቻቸውን ለመጠያየቅ መግባባት ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡ በትዳሩ ጉዳይ ለጊዜው ባይግባቡም ሌላ የሚያግባባቸው ነገር አያጡም፡፡ ትዳሩ ቢፈርስ እንኳን ትውውቁና ዝምድናው እንዲቀጥል ለማድረግ መጣር አስፈላጊ
Posted in Ethiopian News, Religion

ጳውሎስ ኞኞ (1926-1984)

አዘጋጅ፡- ደረጀ ትእዛዙኅትመት፡- 2006 ዓምየገጽ ብዛት፡- 308ዋጋ፡- 84 ብርስለ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና የታሪክ ሰው ጳውሎስ ኞኞ ታሪክ፣ ሥራዎችና ሀገራዊ አስተዋጽዖ የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ደረጀ የጳውሎስ ጎረቤት ነበረ፡፡ ያደገውም እነ ጳውሎስ ሠፈር ነው፡፡ የልጅነቱ ትዝታ ስለ ጳውሎስ እንዲያጠና እንዳደረገው ይነግረናል፡፡ የጳውሎስን ሥራዎችና ስለ እርሱ የተጻፉ መዛግብትን አገላብጦ፤ ዛሬም በሕይወት ለታሪክ ቆይተው ያገኛቸውን የቅርብ ሰዎቹን አናግሮ ዙሪያ መለስ የሆነ ሥራ አቅርቦልናል፡፡ የጳውሎስን ጉዞ ከትውልድ መንደሩ እስከ ተጓዘባቸው የዓለም ክፍሎች፣ ከትውልድ ሥፍራው ቁልቢ እስከ መቀበሪያው ቀራንዮ መድኃኔዓለም ደረጀ ስለ ጳውሎስ የሚመሰገንበትን ብቻ ሳይሆን የሚወቀስበትን፣ የሚደነቅበትን ብቻ ሳይሆን የሚነቀፍበትን፣ ብርታቱን ብቻ ሳይሆን ድክመቱንም እንድናየው አድርጎናል፡፡ ከጠባዩ እስከ ችሎታው፣ ከእምነቱ እስከ ፍልስፍናው፣ ከኩርፊያው እስከ ደግነቱ ያሳየናል፡፡ በጳውሎስ ኞኞ ታሪክ በኩል የኢትዮጵያን ፕሬስ ጉዞ፣ የነበሩትን ዋና ዋና ተዋናዮች፣ የነበረባቸውን ፈተና፣ አስተዳደራዊ፣ ፖለቲካዊና ፍልስፍናዊ ተግዳሮት፣ በየዘመናቱ የተነሡ ጋዜጠኞች ለፕሬስ ነጻነት እንዴት ይጋደሉ እንደነበር፣ ከንጉሥ እስከ ሰካራም፣ ከአንባቢ እስከ አለቃ ይደርስባቸው የነበረውን መከራ ያሳየናል፡፡ጳውሎስ ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆን ራሱን በራሱ ያስተማረ፣ ታሪካችንን
Posted in Ethiopian News, Religion

እንደገና እንጋባ

click here for pdf(ሁለተኛ ደብዳቤ)ምን ብዬ ጠርቼሽ ልቀጥልለካስ እስካሁን የተዋደዱና የተጣሉ ሰዎች የሚጠራሩበት የቅጽል ስም እንጂ የተለያዩ፣ ግን ያልተጣሉ ሰዎች የሚጠራሩበት የቅጽል ስም የለንም፡፡ መቼም አንዳንዱን  ነገር የምንረዳው ሲገጥመን ብቻ ነው፡፡ በኑሯችን ውስጥ የሚጎድሉ፣ ነገር ግን ልብ የማንላቸው ጥቃቅን ነገሮች ብቅ የሚሉት ታላላቅ ነገሮችን አጥተን ቦታው ክፍት መሆኑን ስናረጋግጥ ብቻ ነው፡፡ ‹ውዴ› ብዬ እንዳልጠራሽ ተለያይተናል፤ ‹አንቺ ምናምን› ብዬ እንዳልጠራሽ ደግሞ እኔና አንቺ ተለያይተናል እንጂ ልቤና ልብሽ መለያየቱን እንጃ፡፡ ብቻ ለማንኛውም ዝም ብዬ ሐሳቤን ልቀጥል፡፡ሰሞኑን ካንቺ ለመጨረሻ ጊዜ ተለያይቼ ከሌላ ሰው ጋር ስለ መኖር ሳስብ ነበር፡፡ ነገር ግን እስከ ዛሬ አስቤያቸው የማላውቅ ሐሳቦች ወደ ልቡናዬ እየመጡ ይሞግቱኝ ጀምረዋል፡፡ አንዱ ሞጋች እንዲህ አለኝ፡፡ ወደህ፣ ፈቅደህ፣ አፍቅረህ ካገባሃት፣ አብረሃትም ለዚህን ያህል ዓመት ከኖርካት፣ ከምታውቅህና ከምታውቃት፣ ካነበበችህና ካነበብካት ሴት ጋር አብረህ ለመኖር ካልቻልክ ከሌላዋ ጋር አብረህ ለመኖርህ ምን ዋስትና አለህ? ይህችንምኮ ያገባሃት አንተው ነህ፤ እንደ ጥንቱ ወላጆችህ አጭተውልህ ቢሆን ኖሮ በእነርሱ ታመካኝ ነበር፤ ያመጣሃትም
Posted in Ethiopian News, Religion

ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬ ዳዋ

(አርቲስቱና ሽቅርቅሩ የድሬዳዋ ሕዝብ)click here for pdfደራሲ፡- አፈንዲ ሙተቂየገጽ ብዛት፡-191ዋጋ፡- 46 ብር የኅትመት ዘመን፡- 2006 ዓምአፈንዲ ሙተቂ ያበረከተልንን መጽሐፍ አነበብኩት፡፡ ከአዋሽ ወዲያ ማዶ ያለውን ሀገራችንን ሙልጭ አድርገን ለማወቅ የሚጎድለን ነገር መኖሩን የምንረዳው የእርሱን መጽሐፍ ስናነብ ነው፡፡ እንኳን እንደ እኔ በጎብኝነት የሚያውቀው ቀርቶ ተወልጄበታለሁ አድጌበታለሁ የሚለው ሁሉ የቀበሌ መታወቂያውን እንደገና እንዲያወጣ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው፡፡ሰው የሚያውቀውን ሲጽፍ ወይም የሚጽፈውን ሲያውቅ እንዲህ ያለ መጽሐፍ ይገኛል፡፡ ባሕሉ አልቀረ፣ ትውፊቱ አልቀረ፣ አባባሉ አልቀረ፣ ታሪኩ አልተዘለለ፣ መልክዐ ምድራዊ መረጃው አልተዘነጋ፣ አፈ ታሪኩ ቦታውን አልሳተ፣ ሁሉም በመልክ በመልኩ ተሰድሮ እንደ መልካም የወታደር ሠልፍ የቀረበበት መጽሐፍ ነው፡፡ አፈንዲ ለአካባቢው ወግና ታሪክ ቅርበት ብቻ ሳይሆን ፍቅርም እንዳለው፣ ፍቅር ብቻም ሳይሆን ጥናትም እንዳለው፣ ጥናትም ብቻ ሳይሆን ትኩረትም እንዳለው መጽሐፉ ያሳየናል፡፡ የሕዝቡን ፍቅርና አንድነት፣ መተሳሰብና አብሮነት፣ የቆየውን የመተጋገዝ ልማድና ተግባቦት ያሳየባቸው ወጎቹ የመለያየት ጥላ ላጠላበት ህልውናችን ፈዋሾ ናቸው፡፡ በተለይም የሐረርጌ ኦሮሞን ትውፊትና ባሕል፣ የአስተዳደር ታሪክና ዕምቅ ብቃት ያሳየበት ጹሑፉ እዚያው ሕዝቡ
Posted in Ethiopian News, Religion

ድኻው ምን አረገ

click here for pdfሰሞኑን ከአንድ ሰው ‹የማጭበርበር› ነገር ጋር በተያያዝ ከዚህም ከዚያም አስተያየት ይሰጣል፡፡ አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙኃንም ትኩረታቸውን በሰውዬው ላይ አድርገው እንዴት እንዲህ ሊያደርግ ቻለ? ለምን እንዲህ አደረገ?ምን ነክቶት ነው? እያሉ ጉዳዩን ከማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ከሥነ ልቡና፣ ከእምነትና ከባሕል አንጻር እየተነተኑ ይገኛሉ፡፡ እኔ ግን ይህን ጉዳይ ስከታተል ትዝ የሚለኝ አንድ የሀገራችን ተረት ነው፡፡ ሰውዬው መንገድ ላይ ሲሄድ በሩ ወለል ብሎ የተከፈተ ቤት ያገኛል፡፡ ለጥቂት ቆም ብሎ ሁኔታውን ሲያይ ማንም በአካባቢው ዝር የሚል አልነበረም፡፡ ነገሩ የተከፈተ በር ብቻ ሳይሆን ‹የተከፈተ ዕድልም› የሆነለት ሰውዬ የተከፈተው ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ማንም አልነበረም፡፡ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደ ቤቱን ቃኘና ዓይኑ ያረፈበትን ዕቃ ይዞ ላጥ አለ፡፡ መንገድ ላይ ያዩት ሰዎች የሚያውቁትን ዕቃ አንድ ሰው ይዞ ሲሸመጥጥ በማየታቸው ይጠራጠሩና ያስቆሙታል፡፡ ፖሊስም በነገሩ ይገባበታል፡፡ ሰውም ከዚህም ከዚያም ይወርድበታል፡፡ ግርግሩ በዚህ መልክ እየቀጠለ ዕቃቸው የተሰረቀባቸው ሰዎች ኡኡ እያሉ ይደርሳሉ፡፡ ሲደርሱም የቤት ዕቃቸው በአንድ በማያውቁት ሰው ትከሻ ላይ ያገኛሉ፡፡ ግርግሩን ሰንጥቀው
Posted in Ethiopian News, Religion

የታጋዩ የልጅ ልጅ

click for pdf<<ስኩል ኦፍ ኖርዘርን ስታር›› ከሚባለው ውድ ትምህርት ቤቱ የአያቱ ሾፌር ወደ ቤቱ ሲያመጣው ልቡ ከመኪናው ፍጥነት በላይ ነበር ወደ ቤቱ የሚሮጠው፡፡ ያየውንማ ለአያቱ መንገር አለበት፡፡ አያቱ እንዲህ ታዋቂ  አክተር መሆናቸውን አያውቅም ነበር፡፡ ፊልሙን ሲመለከት አያቱን በመሪ ተዋናይነት በማግኘቱ ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ ጋር በኩራት ነበር ያወራው፡፡ እነርሱም የታዋቂ ሰው የልጅ ልጅ በመሆኑ ከፊልሙ በኋላ እንደ ንብ ነበር የከበቡት፡፡ ብዙዎቹ እንዲያውም በወረቀት ላይ አያቱን አስፈርሞ እንዲያመጣላቸው፣ ከተቻለም ፎቷቸውን እንዲሰጣቸው ለምነውታል፡፡  ቤቱ ሲገባ አያቱ የሉም፡፡ ደወለላቸው፡፡ እየመጡ መሆናቸውን ነገሩት፡፡ መክሰስ ለመብላት እንኳን ሆድ አልቀረለትም፡፡ ይህን አስገራሚ ነገር ከአያቱ ጋር ማውራት እጅግ አጓጉቶታል፡፡ እየደጋገመ ‹ፐ› ይላል፡፡ አባቱና እናቱ ራሳቸው ይህንን የሚያውቁ አልመሰለውም፡፡ ይህንን ነገር ያወቀ የመጀመሪያ ሰው እርሱ ብቻ ሊሆን እንደሚችል ገምቷል፡፡ ‹ፐ›፡፡አያቱ መጡ፡፡ ‹‹አያቴ ቴክ ፋይቭ›› አለና በአምስት ጣቱ አምስት ጣታቸውን ገጨ፡፡‹‹ምን ተገኘ ዛሬ›› አሉ አያትዬው ደንቋቸው፡፡‹‹እኔኮ አክተር መሆንህን አላውቅም ነበር፡፡ ጓደኞቼ ሁሉ አያቴ አክተር መሆኑን ሲያውቁ ሪስፔክት አደረጉኝ›› አላቸው በሳቅ
Posted in Ethiopian News, Religion

የሁለት ፈረሶች ጥያቄ

click here for pdfሁለት ፈረሶች እንደነበሩ ተነገረ፡፡ አንደኛው እጅግ ለምለም በሆነ ሰፊ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ፣ ሲያሻው ደግሞ በግራ በቀኝ ገብስ ፈስሶለት፣ ሲጠማው የሚጠጣው ውኃ በሜዳው መካከል ኩልል ብሎ እየወረደለት፣ አውሬ እንዳይተናኮለው ዙሪያውን በውሻ እየተጠበቀ ይኖር ነበር፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሣር ዘር ለአመል ያህል ብቻ እዚህም እዚያም በበቀለበት፣ ጭው ባለ ደረቅ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ ያገኛትን እየነጨ፣ ከዕለታት በአንድ ቀን ከደጋ የዘነበ ዝናብ በአካባቢው ሲያልፍ የሚያገኘውን ጥፍጣፊ ውኃ እየተጎነጨ፣ ሌትና ቀን ምን ዓይነት አውሬ መጥቶ ይዘነጥለኝ ይሆን? እያለ በሥጋት ይኖር ነበር፡፡ምንም እንኳን ሁለቱም ፈረሶች በኑሮ በማይቀራረብ ሜዳ ላይ በመከራና በቅንጦት ተለያይተው ቢኖሩም የኑሮ ጥያቄ ግን አገናኝቷቸው ኖሯል፡፡ ያ እንዲያ በለመለመ መስክ ተሠማርቶ እምብርቱ እስኪነፋ ሆዱ እስኪቆዘር እየበላ ሲተኛ ሲነሣ የሚውለው ፈረስ ‹‹ይኼ ሣር ያለቀ ዕለት፣ ይኼም ውኃ የነጠፈ ጊዜ፣ እነዚህም ውሾች እኔን መጠበቅ ትተው የሄዱ ጊዜ፣ ይኼስ ገብስ የጠፋ ቀን ምን ይውጠኝ ይሆን? ያስ ቀን መቼ ይሆን? ይል ነበር፡፡ ይኼ ጥያቄ ምንጊዜም ይረብሸው
Posted in Ethiopian News, Religion

‹ትዕግሥት› – የቴሌ ሶፍትዌር

click here for pdfቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በእንግዶች ተጨናንቋል፡፡ በአዲስ አበባ ለሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚመጡ እንግዶች አሁንም አሁንም የፍተሻውን መሥመር እያለፉ ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ይሰለፋሉ፡፡ ብዙዎቹ የሞባይል ስልክ ለማግኘት የተሰለፉ ናቸው፡፡ የቪዛ አገልግሎት ለማግኘት እንኳን ያንን ያህል አልተሰለፉም፡፡ አንዳንዶቹ ያማርራሉ፣ አንዳንዶቹም ያመራሉ፡፡ ሰልፉ እየተቃለለ መጥቶ ሁሉም እንግዶች ወደየማረፊያቸው ተጓዙ፤ ጉባኤው የሚጀመረው ነገ ነው፡፡ በማግሥቱ የሀገሩም የውጭውም ሰው በአዳራሹ ከተተ፡፡ መርሐ ግብሩ እስኪጀመር ድረስ ንዴትና ብስጭት፣ ቁጣና ርግማን የተቀላቀለባቸው ንግግሮች ከእንግዶቹ እዚህም እዚያም ይሠነዘሩ ጀመር፡፡ ‹‹እንዴት ለሀገራቸው ሰው ብቻ የሚሠራ ስልክ ይሰጣሉ፤ ነውር አይደለም እንዴ›› ይላሉ እዚህም እዚያም፡፡ አንዳንዱ ስልኩን መሬት ላይ ቢፈጠፍጠው ንዴቱ የሚበርድለት ይመስል አሥር ጊዜ ይሠነዝረዋል፡፡ ወዲያው አንድ አካባቢ ሰዎቹ ከበው ቆሙ፤ ቀጥሎም ቁጣ ቀላቅሎ የሚዘንብ የውግዘት ዝናብ አወረዱ፡፡ ለካስ ከጉባኤው አስተናጋጆች መካከል አንዱን አግኝተውት ነው፡፡ ‹‹እንዴት ከስልክ ዐቅም የሀገር ሰውና የውጭ ትለያላችሁ፤ ሌላ ሀገርኮ ስልክ በሳንቲም ከሱቅ የሚሸመት ነው፤ የኛ ሳይሠራ እንዴት የናንተ ብቻ ተለይቶ ሠራ›› ባለሥልጣን
Posted in Ethiopian News, Religion

የዓመቱ በጎ ሰው መጽሔት

ሁለተኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሲከናወን ከተፈጸሙት ነገሮች አንዱ የተሸላሚዎችን ታሪክ የያዝ መጽሔት መታተሙ ነው፡፡ መጽሔቱን በፒዲኤፍ ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ የመጽሔቱን ጠንካራ ቅጅ የምትፈልጉ ካላችሁ ለም ሆቴል ማትያስ ሕንጻ በሚገኘው የአግስዮ መጻሕፍት መደብር በነጻ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ በተለይም አብያተ መጻሕፍት፣ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶችና የወጣት ማኅበራት መጽሔቱን እንዲወስዱ ይበረታታሉ፡፡የመጽሔቱ ሽፋን(cover page)የመጽሔቱ ይዘት(bego sew bulletin pdf)
Posted in Ethiopian News, Religion

የ2006 ዓም የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች ተሸለሙ

 click here for pdfከ120 ተጠቋሚ ኢትዮጵያውያን መካከል በበጎ ሰው ዳኞች የተመረጡት ሰባት ኢትዮጵያውያን ‹በጎ ሰዎች› ቅዳሜ ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓም በኢሊሊ ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ተሸለሙ፡፡የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ከየትምህርት ቤቱ የተጋበዙ ወጣቶችና ሌሎችም በተገኙበት በተከናወነው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ ወ/ሮ ቤተ ልሔም ጥላሁን፣ በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ብጹዕ አቡነ ዮናስ፣ በርዳታና ሰብአዊ ሥራ ዘርፍ ዶክተር በላይ አበጋዝ፣ መንግሥታዊ  የሥራ ኃላፊነትን በመወጣት ዘርፍ አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ፣ በጥናትና ምርምር ዘርፍ አምባሳደር ዘውዴ ረታ፣ በቅርስ፣ ባሕልና ቱሪዝም ዘርፍ አብዱላሂ ሸሪፍ፣ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ደግሞ አባባ ተስፋዬ ሣሕሉ ተሸልመዋል፡፡ሽልማቶቹን የተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የሸለሙ ሲሆን ከተሸላሚዎቹ መካከል አምባሳደር ዘውዴ፣ አምባሳደር ቆንጂትና  ወ/ሮ ቤተ ልሔም ጥላሁን ለሥራ ከሀገር ውጭ በመሆናቸው በተወካዮቻቸው በኩል ተቀብለዋል፡፡ለሀገር በጎ ሥራ መሥራትንና ያለውንም በጎ ተጽዕኖ በተመለከተ ዶክተር እሌኒ(የ2005 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ) እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋየ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ገጣሚ አበባው መላኩና ገጣሚ
Posted in Ethiopian News, Religion

ያልሰማኸው ነገር

click here for pdfይሄ ልጅ ለምን እዚህ እንደመጣ ግልጽ አልሆነላቸውም፡፡ ከሃያ ዓመት በኋላ ነው እንዲህ ቤት ውሎ ቤት ሲያድር ያዩት፡፡ ሥራ አለው፣ በትምህርት ተወጥሯል፤ ንግዱን እያጧጧፈ ነው ሲባል ነበር የሚሰሙት፡፡ በቤቱ ውስጥ የተሻለ የተማረ ሰው እርሱ በመሆኑ ሠርግና ልቅሶ ለምን አልመጣህም ብሎ የሚወቅሰው ቤተ ዘመድ አልነበረም፡፡ አንዳንዶቹም ስሙን ሰምተው እንዲሁ ያደንቁታል እንጂ አይተውት አያውቁም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድሮ በልጅነቱ እንዳዩት ናቸው፡፡አሁን ግን ነገር ዓለሙን ሁሉ ትቶ እዚህ አያቱ ቤት መዋል ማደር ከጀመረ ሰነባበተ፡፡ አያቱ ደግሞ ይሳቀቃል ብለው ለምን መጣህ? ሥራና ትምህርትህንስ የት ተውከው? ብለው መጠየቅ ከብዷቸዋል፡፡ እጅግ በጣም የገረማቸው ደግሞ መቀመጫው ላይ ወስፌ እንደተተከለበት ሁሉ ለአፍታ ቁጭ ማለት የማይችለው ሰውዬ ደርሶ ቀኑን ሙሉ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ሲቆዝም መዋሉ ነው፡፡ አንድ ቀን ግን ደፍረው መጠየቅ እንዳለባቸው ወሰኑና ወደ እልፍኛቸው አስጠሩት፡፡ ‹‹ልጄ በደኅህ ነው? እንደዚያ ለምግብ እንኳን ጊዜ የለኝም የምትለው ሰውዬ ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብለህ የምትውለው›› አሉና ጠየቁት፡፡ አንገቱን ደፍቶ መሬቱን በመነጽሩ ጫፍ
Posted in Ethiopian News, Religion

‹‹የዓመቱ በጎ ሰው›› የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች

click here for pdfየ2006 ዓም ‹‹የዓመቱ በጎ ሰው›› ሽልማት በሰባት ዘርፎች የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ታውቀዋል፡፡ በልዩ ልዩ ዘርፎች ዕውቀትና ተሞክሮ ያላቸው፣ በሞያው ለረዥም ዘመን ያገለገሉ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ደራስያን፣ የዜማ ሰዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ የባሕል ባለሞያዎች፣ የሚገኙበት 21 ዳኞች የመጨረሻዎቹን ሰባት ተሸላሚዎች ለመለየት ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡ ዳኞቹ እርስ በርሳቸው የማይተዋወቁ ሲሆን በዘርፋቸው የራሳቸውን ድምፅ ብቻ ይሰጣሉ፡፡ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች የሚታወቁት በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ነው፡፡የሽልማቱ ዲዛይን የታዋቂው ሰዓሊ የእሸቱ ጥሩነህ ነው፡፡ ‹‹ጀ›› ፊደል ኢትዮጵያዊ ፊደል በመሆኑ ኢትዮጵያዊነትን የሚወክል ሲሆን ‹በ› ና ‹ሰ› የሚሉ ፊደላት ተቀጣጥለውበታል፡፡ ይህም የበጎ ሰው ሽልማትን የሚገልጥ ነው፡፡ ከላይ ደግሞ የ‹ሽ› ምልክት አለው፡፡ ይህም ሽልማትነቱን ያሳያል፡፡ ከላይ ያለው የፊደሉ ቅጥያ የቁልፍ መክፈቻ ምልክት ያለው ይኼም የተሸላሚዎቹን ቁልፍ ማኅበረሰባዊ ሚና ያመለክታል፡፡ ከፊደሉ ሥር የሚገኘው ደረጃ ደግሞ ተሸላሚዎቹ ደረጃ በደረጃ የደረሱበትን የሰብእና  ልዕልና ያሳያል፡፡ዕጩዎች በየዘርፉኪነጥበብ ዘርፍሙላቱ አስታጥቄተስፋየ አበበአባባ ተስፋየ ሳሕሉይልማ ሀብተየስታደሰ መስፍን ማኅበራዊ አገልግሎት 1.         ዶ/ር አበበ በጂጋ2.       ዶ/ር ሚናስ ኅሩይ3.       ቄስ አሰፋ ሰጠኝ(ትግራይ)4.       ብጹዕ
Posted in Ethiopian News, Religion

ሃይማኖታውያን ያልሆኑ የግእዝ ጽሑፎች (ግንቦት 2006 ዓም አኩስም ትግራይ)

click here for pdf ክፍል አንድ1.1 አጠቃላይ የግእዝ ሥነ ጽሑፋዊ ሀብትየግእዝ ቋንቋ ከሁለት ሺ ዓመታት በላይ ጊዜ ያስቆጠረ የሥነ ጽሑፍ ሀብት ያለው ቋንቋ ነው፡፡ እስካሁን የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የግእዝ ሥነ ጽሑፍ በተጻፉበት ቁስ በሦስት መልኮች ቀርበዋል፡፡ በድንጋይ ላይ፣ በብራና ላይና በወረቀት ላይ፡፡ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፡- በድንጋይ ላይ የተጻፉት የግእዝ ሥነ ጽሑፎች በአኩስም አካባቢ የተገኙትንና የነገሥታቱን የጦርነት ታሪኮችንና ሌሎች ዘገባዎችን የያዙትን ጽሑፎች ይመለከታል፡፡  የተገኙት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ከአራተኛው መክዘ(ቅልክ) እስከ 8ኛው መክዘ(ድልክ) የሚደርሱ ናቸው፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ጥንታዊው የሚባለው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በመጣራ ኤርትራ በሐውልቲ የተገኘው(5ኛው መክዘ ቅልክ) ጽሑፍ ነው፡፡‹‹ዝ ሐውልት ዘአገበረ አገዘ ለአበዊሁ ወሰሐበ ሙሓዛተ አውዐአለፈነ ወጸበለነ›› የሚለው ነው፡፡እነዚህ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች አብዛኞቹ ዘገባዎችና ታሪኮች ሃይማኖታውያን አይደሉም፡፡ የብራና ላይ ጽሑፎች፡- ሁለተኛው የግእዝ ሥነ ጽሑፍ የብራና ሥነ ጽሑፎች መልክ ነው፡፡ የብራና ላይ የግእዝ ጽሑፍ ከ6ኛው መክዘ እስከ አሁን ዘመን የቀጠለ ሲሆን በማይክሮፊልም በተነሡት የብራና መጻሕፍት ቁጥር የሄድን እንደሆነ ቁጥራቸው እስከ 12,000 ይደርሳል፡፡
Posted in Ethiopian News, Religion

ሀገር አቀፍ የግእዝ ዐውደ ጥናት

click here for pdfከግንቦት 9 እስከ 11 ቀን ድረስ በትግራይ ክልል አኩስም ከተማ ‹ሀገር አቀፍ የግእዝ ዐውደ ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡ ይህ በዓይነቱ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ሲዘጋጅ የመጀመሪያ የሆነው ዐውደ ጥናት የትግራይ ክልል ባሕል ቱሪዝም ኤጀንሲ ከፌዴራል ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን ያዘጋጀው ነበር፡፡የክልሉ ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች እንደገለጡት ይህ ዐውደ ጥናት በትግራይ ክልል ደረጃ ሲከናወን ለስድስተኛ ጊዜ ነው፡፡ የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው በሀገር አቀፍ ደረጃ መከናወኑ ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ከጎንደርና ከሌሎችም አካባቢዎች የተጋበዙ ጉምቱ ጉምቱ ሊቃውንት የተገኙ ሲሆን እስከ ዛሬ ትውፊታውያን ሊቃውንት እንዲህ በብዛትና በዓይነት ተገኝተው ከዘመናውያን ምሁራን ጋር ሲገናኙ ዕድል ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ በዚህም የክልሉ ባሕል ቱሪዝም ኤጀንሲና የፌዴራሉ ባሕል ቱሪዝም ሚኒስቴር ተመስጋኞች ናቸው፡፡ከልዩ ልዩ ቦታ የተጋበዙ ምሁራንና ሊቃውንትከተለያዩ ዩኒቨረሲቲዎች ባለሞያዎች እንዲጋበዙ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም እንዲገኙ መደረጉ፤ መርሐ ግብሩ ግንቦት 11 ከሚከበረው የቅዱስ ያሬድ በዓል ጋር እንዲሠምር መደረጉ፣ ለበዓሉም የተሰጠው ቦታ ሊቃውንቱ ሁሉ ቅኔ ሲያዘንቡበት የዋሉት ጉዳይ ነው፡፡ ቅኔ ልብስ ቢሆን
Posted in Ethiopian News, Religion

የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር

click here for pdfየበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓም በኢሊሊ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ‹‹በጎ ሰዎችን በመሸለምና በማክበር፣ ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፍራ›› በሚል ሐሳብ የተጀመረው መርሐ ግብር ወደ ማጠናቀቂያው እየተጓዘ ነው፡፡ በሰባቱ ዘርፎች የሚወዳደሩት 35 ዕጩዎች የታወቁ ሲሆን ማክሰኞ ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓም በኢሊሊ ሆቴል ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ይሆናሉ፡፡መርሐ ግብሩን ለማገዝ አያሌ ድርጅቶችና ባለሞያዎች ከኮሚቴው ጎን ቆመዋል፡፡ ዳሽን ቢራ ለዝግጅቱ የሚሆነውን ወጭ ለመሸፈን ግንባር ቀደሙን ቦታ የያዘ ሲሆን ሸገር ሬዲዮና ኢ ቢ ኤስ ቴሌቭዥን የዝግጅቱ አጋር በመሆን ማስታወቂያዎችንና የዝግጅቱን መርሐ ግብሮች በነጻ ለማስተላለፍ ወስነዋል፡፡ ኢሊሊ ሆቴል ደግሞ አዳራሹን በነጻ በሚባል ዋጋ በመስጠት ትብብሩን ለግሷል፡፡ የሽልማቱን ምስል ታዋቂው ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ አዘጋጅተውታል፡፡መርሐ ግብሩን ለመሳተፍ ለሚፈልጉ 100 የዚህ ጦማር ተከታታዮች ካርድ ተዘጋጅቷል፡፡ ካርዱን ለማግኘት በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ ይመዝገቡ፡፡ [email protected] ሥራው የሁላችሁንም ጸሎትና እገዛ ይጠይቃል፡፡ 
Posted in Ethiopian News, Religion

‹‹የሚገሥጹንን ሁሉ መቅጣት የለብንም››

click here for pdfብጹዕ አቡነ ዮሐንስ በሊቅነታቸው፣ በቆራጥነታቸው፣ ለየት ባለ አስተሳሰባቸውና ለነገሮች በሚሰጡት አስደናቂ ምላሽ የሚታወቁ የትግራይ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ እስካሁንም እርሳቸውን በተመለከተ የሚተረኩ እጅግ አስገራሚ ታሪኮች አሏቸው፡፡ አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አቡነ ዮሐንስ በዓላትን በተመለከተ የነበራቸው አስተሳሰብ ከብዙው ሰው ለየት ያለ ነበር፡፡ ‹‹በዓል መከበር ያለበት በሥራ ነው›› ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት እንዲያውም በቀዳሚት ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ያያቸው ሰው ‹‹እንዴት ጌታ ባረፈበት ቀን ይሠራሉ›› ቢላቸው ‹‹እርሱኮ ያረፈው ሥራውን ጨርሶ ነው፡፡ እኔ መች ሥራዬን ጨረስኩ ብለህ ነው›› ብለው መመለሳቸው ይነገራል፡፡ ‹‹የበዓላትን ቀናት ለበዓሉ የሚስማማ ሥራ በመሥራት እንጂ እጅና እግርን አጣጥፎ በመቀመጥ፣ መጠጥ ቤትና ጭፈራ ቤት በመዋል ማክበር ከማክበር አይቆጠርም፡፡ ሰው ምንጊዜም መቦዘን የለበትም፡፡ በየዕለቱ ለዕለቱ ተስማሚ የሆነ ሥራ መሥራት አለበት›› ብለው ያም ይህንንም ያስተምሩ ነበር፡፡ ታድያ በአንድ ወቅት በበዓል ቀን ቤተ ክርስቲያን ሲያሠሩ ውለው ለጉዳይ ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳሉ፡፡ ለአቤቱታ ወደ እርሳቸው ዘንድ ከገጠር የመጣ አንድ ካህን እርሳቸውን ፍለጋ ወደሚያሠሩት ሕንፃ
Posted in Ethiopian News, Religion

መሟላት

click here for pdfእሥራኤላውያን እንዲህ ይተርካሉ፡፡በኢየሩሳሌም ከተማ የሚኖሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንደኛው ባለ ትዳርና የቤተሰብ አስተዳዳሪ፣ ሌላኛው ደግሞ ላጤ ነበሩ፡፡ ሁለቱም የሚተዳደሩት በአንድ የእርሻ መሬት ነው፡፡ ጠንክረው በጋራ በመሥራት ያመርቱና ምርቱን በእኩል ይካፈላሉ፡፡ በሥራና በኑሮ ያላቸው መተጋገዝና መጠቃቀም ለአካባቢው ሰዎች ሁሉ እጅግ የሚያሰቀና ነበር፡፡ አንደኛው ለሌላኛው የሚያስበውን ያህል ለራሱ አያስብም ነበር፡፡ አንድ ቀን ላጤው ለባለ ትዳር ወንድሙ እንዲህ አሰበ፡፡ ‹‹ወንድሜ የቤተሰብ ኃላፊ ነው፡፡ ባለቤቱን፣ ልጆቹን፣ የባለቤቱን ወላጆችና የቤቱን ሠራተኞች ማስተዳደር አለበት፡፡ ምርቱን ከእኔ ጋር እኩል መካፈል የለበትም፡፡ እርሱ ከእኔ የሚበልጥ ምርት ማግኘት አለበት፡፡ ነገር ግን አሁን ከእኔ የተሻለ እህል ውሰድ ብለው አይቀበለኝም፡፡ ስለዚህ በሌላ መንገድ መርዳት አለብኝ፡፡››አውጥቶ አውርዶም በጎተራ ካለው የእርሱ እህል እየወሰደ ማታ ማታ ተደብቆ በወንድሙ ጎተራ ውስጥ ለማስቀመጥ ወሰነ፡፡ ማታ ማታ ተደብቆ በመውጣት ከራሱ ጎተራ ወደ ወንድሙ ጎተራ እህል ይገለብጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ጠዋት ጎተራውን ሲያየው እንኳንስ ሊጎድል ካለፈው የበለጠ ሞልቶ ያገኘው ነበር፡፡ ይህም እጅግ ይገርመው ነበር፡፡ ፈጣሪ
Posted in Ethiopian News, Religion

ዴር ሡልጣን፡- ዐሥር ነገሮች (ክፍል አምስትና የመጨረሻው ክፍል)

click here for pdfባለፈው ጊዜ በተከታታይ የዴር ሡልጣንና ከዚያም ጋር የሚያያዙ ጉዳዮችን ስናነሣ ነበር፡፡ ምን መደረግ አለበት በሚለውም ዙሪያ ስድስት ነጥቦችን አንሥተናል ዛሬ የመጨረሻውን ክፍል እነሆ፡፡ 7. ዲያስጶራውን ማንቀሳቀስወደ ኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናትን በመሳለም ረገድ ዲያስጶራ ኢትዮጵያውያን ብዛታቸው እየጨመረ ነው፡፡ በውጭ የሚገኙት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትም ቁጥር ከዓመት ዓመት እጨመረ ይገኛል፡፡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እንዲሆን ለኢትዮጵያ ታሪክ፣ ቅርስና ዝና ተቆርቋሪ የሆኑትን ሌሎች ወገኖች በማስተባበር ዲያስጶራው የዴር ሡልጣንን  ይዞታ በማስጠበቅ፣ ዲፕሎማሲያዊ ሥራ በመሥራትና የሕግ ድጋፍ በማድረግ ተግባራት ላይ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ይገባል፡፡ አንዳንድ በአሜሪካን ሀገር የሚገኙና ከሲኖዶሱ የተለዩ ወገኖች ክፍፍሉን ወደ ኢየሩሳሌም ለማዝመትና በቅድስቲቱ ሀገር እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ማኅበረሰቦችን ለመፍጠር፣ ጥንታዊው ቦታም ተረስቶ እንዲቀር የሚያደርጉትን ጥረት በመግታት በኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናት ጉዳይ የተባበረ እና የማይከፋፈል የኢትዮጵያውያን ድምጽ እንዲኖር ማድረግ ያሻል፡፡ በእሥራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያ ቅዱሳት መካናትን በተመለከተ ዓለም ዐቀፋዊ ሲምፖዝየምና የውይይት መድረክ በማዘጋጀት፣ ዐውደ ርእዮችን በማቅረብ፣ ግብጾች በገዳሙ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በዓለም ዐቀፍ መድረኮች
Posted in Ethiopian News, Religion

የ2006 የበጎ ሰው ሽልማት ደረሰ

click here for pdfከዚህ በፊት በዚሁ ጦማርና በልዩ ልዩ ሚዲያዎችም በተነገረው መሠረት ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው መልካም ሠርተዋል የተባሉ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ተጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እጅግ የተሻሉትን ለመምረጥ የመጨረሻው ሂደት እየተከናወነ ነው፡፡ መርሐ ግብሩ የሚካሄደው ቅዳሜ ግንቦት 30 ቀን ከቀኑ በ 8 ሰዓት አዲስ አበባ ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው እሊሌ ሆቴል ሲሆን፣ ተሸላሚዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም በተገኙበት ይከናወናል፡፡ ሽልማቱ የሚከናወነው በሰባት ዘርፎች ነው፡፡የሀገራዊ ዕርቅና ሰላም ዘርፍየበጎ አድራጎት(ሰብአዊነት) ዘርፍየኪነ ጥበብ/ ሥነ ጥበብ ዘርፍግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፍመንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት የመወጣት ዘርፍቅርስ ጥበቃ፣ ባሕልና ቱሪዝም ዘርፍሳይንስና ቴክኖሎጂ/ ጥናትና ምርምር ዘርፍበእነዚህ ዘርፎች የተመረጡ ተሸላሚዎች በመጨረሻ መራጮች ድምጽ ከተሰጠባቸው በኋላ ይታወቃሉ፡፡ የሽልማቱ ዋና ዓላማ ገንዘብ አይደለም፡፡ በጎ ሰዎችን በማበረታታት፣ ለበጎ ሰዎችም ዕውቅና በመስጠት ለሀገር ሰው ማትረፍ እንጂ፡፡ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑ ጀግኖችን ማሳወቅ ሥራቸውም ለትውልድ አርአያ እንዲሆን ማድረግ እንጂ፡፡ የመመሰጋገንንና የመበረታታትን ባሕልም ማበልጸግ እንጂ፡፡በዕለቱ መገኘት ለሚፈልጉ በቅርቡ የመግቢያ ካርዱ የሚገኝበትን መንገድ እንጠቁማለን፡፡የበጎ ሰው ሽልማት ኮሚቴ
Posted in Ethiopian News, Religion

ዴር ሡልጣን፡- ዐሥር ነገሮች(ክፍል አራት)

click here for pdf5. መዝየምኢትዮጵያውያን አባቶችና ምእመናን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ተጋድሎ ለመፈጸምና መንፈሳዊ ርስትን ለትውልድ ለማኖር ታላቅ መሥዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ይህንን የዘመናት ተጋድሎ የሚያሳይ አንዳች ሙዝየም ግን የለንም፡፡ የገዳሞቻችንን ታሪክ፣ የተጻጻፍናቸውን ደብዳቤዎች፣ በየጊዜው ከሀገር ቤት የተላኩትን መጻሕፍትና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት፣ የዘመናቱን አሻራ የሚያሳዩ የሥዕልና የፎቶ ግራፍ መረጃዎች፣ ካርታዎች፣ ተጓዦችና ታሪክ ጸሐፊዎች የከተቧቸው ማስረጃዎች፣ በየዘመናቱ የተሰጡ ስጦታዎችን የሚያሳዩ መዛግብት፣ የተሾሙ ራይሶችንና ሊቃነ ጳጳሳትን የሚያሳዩ ዝርዝሮችና ፎቶዎች፣ የተሳላሚዎችን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶዎችና መዛግብት የተከማቹበት፤ ከዚያም አልፎ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ማንነት፣ ታሪክና ቅርሶች የሚያሳይ አንድ ታላቅ ሙዝየም በደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት ግቢ ውስጥ ወይም በአካባቢው ያስፈልገናል፡፡ይህ ሙዝየም ሦስት ጥቅሞች ይኖሩታል፡፡ በአንድ በኩል ከሁለት ሺ ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የቅድስት ሀገር ርስታችንን ታሪክ በተጨባጭ የምናሳይበት፣ ከንግግር የዘለለ ማስረጃ እንዲኖረንና ያንንም ለዓለም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንድናሳይ ያደርገናል፡፡ ከኢየሩሳሌም ከተማ አንዱ የቱሪስት መዳረሻ በመሆንም የኢትዮጵያውያንን የተጋድሎ ታሪክ ለጎብኝዎች እናሳይበታለን፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ኢየሩሳሌም የመላው ዓለም አማኞች መናኸሪያ በመሆኗ
Posted in Ethiopian News, Religion

ዴር ሡልጣን፡- ዐሥር ነገሮች(ክፍል ሦስት)

ከመቶ ዓመታት በፊት ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ አባቶችclick here for pdfከዚህ በፊት ለኢየሩሳሌም ገዳማችን ሊደረጉ የሚገቡ ዐሥር ነገሮችን አቀርባለሁ ባልኩት መሠረት ሦስቱን አቅርቤያለሁ፡፤ አራተኛውን እነሆ4. ጠንካራ የምልመላ መሥፈርት ይኑርአባቶቻችን ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ሲያደርጉ ሁለት ሺ ዓመት አልፏቸዋል፡፡ በየዘመናቱ ከአውሮፓና ከእስያ የመጡ ተጓዦችና ታሪክ ጸሐፊዎች የኢትዮጵያውያን መነኮሳትን የፈቃድ ድህነት፣ የጸሎት ትጋት፣ ተአምር አድራጊነት፣ ሊቅነት፣ መንፈሳዊነትና ፍጹማዊ ምናኔ በአድናቆት ጽፈውታል፡፡ እነዚያ መነኮሳት ወደ ቅድስት ሀገር የመጡት ለአራት ዓላማዎች ነበር፡፡ ከቅዱሳን ቦታዎች በረከት ለማግኘት፣ ፍጹም የሆነ ምናኔን ለመኖር፣ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ዕውቀትን ለመገብየትና የኢትዮጵያውያንን ቅዱሳት መካናት ለመጠበቅ፡፡ ያኔ የዐረብ ሀገሮችን፣ የሱዳንንና የሳዑዲን በረሃዎች፣ የዐረቦችንና የቱርኮችን አገዛዝ፣ ውኃ ጥሙንና መከራውን አልፎ ለመምጣት መንፈሳዊ ጽናትና የጸና እምነት ያስፈልግ ስለነበር ለክፉ የሚሰጥ ሰው ይህንን ሁሉ ችሎ ወደ ኢትዮጵያውያን ገዳማት አይመጣም ነበር፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን በመነኮሳቱ መካከል መለያየትና መከፋፈል እንደነበረ እቴጌ ጣይቱ መነኮሳቱን ‹‹እባካችሁ አትጣሉ፣ አንድ ሁኑ›› እያሉ የጻፉት ደብዳቤ ይነግረናል፡፡ ለገዳሙ በጎ የሠሩ አንዳንድ አባቶችም ዕጣ ፈንታቸው መሰደድ፣
Posted in Ethiopian News, Religion

ዴር ሡልጣን፡- ዐሥር ነገሮች(ክፍል ሁለት)

ከዚህ ቀደም ባለው ጽሑፍ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚገኘውን ገዳማችንን በተመለከተ ዐሥር ነጥቦች እንደማነሣ ቀጠሮ ሰጥቼ ነበር ያቆምኩት፡፡ ዛሬ ሦስቱን አነሣለሁ፡፡ብሔራዊ ኮሚቴ ማቋቋምየዴር ሡልጣን ገዳማችን ሁለት ዓይነት ችግሮች ተደቅነውበት ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው የይዞታ ባለቤትነት ያልተፈታ ችግር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ገዳሙ ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ምንም ዓይነት ጥገና ባለማግኘቱ የተደቀነበት የመፍረስ አደጋ ነው፡፡ የሁለቱም ችግሮች መነሻው ግብጾች በገዳሙ ላይ የሚያቀርቡት የይገባናል ጥያቄና እርሱንም ተከትሎ በመተግበር ላይ የሚገኘው ይርጋ ሕግ(states co)ነው፡፡ ይህንን የገዳማችንን ችግር ለመፍታት በዘላቂነት፣ በተጠናና ዓለም ዐቀፍ ደረጃ ባለው መልክ የሚሠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ማቋቋም ያስፈልገናል፡፡ ይህ ኮሚቴ የሃይማኖት፣ የሕግ፣ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም የዴር ሡልጣንን ገዳም ባለቤትነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚፈታ፣ ገዳሙም ጥንታዊነቱንና ደረጃውን ጠብቆ እንዲጠገንና እንዲገነባ የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡ ዛሬ ዓለም በኑሮ ደረጃ የትና የት በደረሰበት ዘመን መብራት፣ ውኃና መጸዳጃ ማግኘት ለዴር ሡልጣን መነኮሳት ፈተና መሆን የለበትም፡፡ በእሥራኤል ሀገር እንስሳ እንኳን በማይኖርበት መልኩ እንዲኖሩ ያስገደዳቸውን የይርጋ ሕግ አስቀርቶ ለደረጃቸውና
Posted in Ethiopian News, Religion

ዴር ሡልጣን፡- ዐሥር ነገሮች

click here for pdf ከ ሁለት ሺ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የተገለጠው ኢየሩሳሌምን ለመሳለም የሚደረገው ጉዞ ዛሬ የሺዎች ጉዞ ሆኗል፡፡ በእግር ተጉዘው ኢየሩሳሌም ለመድረስ ሱዳንን፣ ግብጽና የሲና በረሃን ያቋርጡ የነበሩት፤ ያለበለዚያም በመካ በኩል ተሻግረው በዮርዳኖስ በኩል ይገቡ የነበሩት አባቶቻችን ክብር ይግባቸውና፣ በኢየሩሳሌም ያቆዩትን ቦታ ለመሳለምና የትንሣኤ በዓልንም በትንሣኤው ቦታ ለማክበር ኢትዮጵያውያን ከሰባ ሺ ብር በላይ እየከፈሉ ይጓዛሉ፡፡ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት የኢትዮጵያውያን ምእመናን የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት በአዲስ መልክ የኢየሩሳሌምን ጉዞ ሲጀምር በአንድ ድርጅት ብቻ ይከናወን የነበረው ጉዞ፣ ዛሬ ከሃያ በላይ በሚሆኑ አጓጓዦች በኩል ከመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ይሰባሰባሉ፡፡ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ በሚመጡ ተሳላሚዎች የተጀመረው ጉዞ ዘንድሮ ከ27 ሀገሮች በመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደሚከናወንበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ከዓመታት በፊት በአብዛኛው በሽማግሌዎችና በእናቶች ብቻ ይደረግ የነበረው ጉዞ ዛሬ ከሦስት ወር ጽንስ እስከ 94 ዓመት አዛውንት ተካትተውበት የሚደረግ ሆኗል፡፡ ከዐሥር ዓመታት በፊት የትንሣኤ በዓል በዴር ሡልጣን ሲከበር በአንደኛው የገዳሙ አጥር ጥግ ተሰባስበው ይታዩ የነበሩት ተሳላሚዎች
Posted in Ethiopian News, Religion

የሚከራዩ አማት

click here for pdf(አማትና ምራት በአንድ ላይ የሚያነቡት)አንድ ጊዜ አንዲት እናት ይህንን ታሪክ ነግረውኝ ነበር፡፡እኔና ባለቤቴ የተጋባነው ልጆች ሆነን ነው፡፡ ያኔ እንዳሁኑ ተያይቶ፣ ተጠናንቶ፣ ሰንብቶ፣ ቆያይቶ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም የኛ ጊዜ ዘመናይ ነው ተብሎ የተወሰነ ጊዜ ትተያይና ወላጆቹ ለወላጆቿ ሽማግሌ ይልኩና፣ በስንት መመላለስ፣ አጥንትህ ጉልጥምትህ ተጠንቶ፣ ሀብት ንብረትህ ታይቶ ነበር የሚፈቀድልህ፡፡ ዛሬማ መንገድ ላይ ተንበርክኮ አንዲት የሃምሳ ብር አበባ ይዞ መለመን ነው አሉ፡፡ በኛ ዘመን በሬ ጎትተህ፣ መኪና አንጋግተህ፣ ጥሎሽ አግተልትለህም ከተሳካልህ ነው፡፡ታድያ መጋባት አይቀርም ተጋባን፡፡ የእርሱ ወላጆች የሚያከራዩት ቤት ነበራቸው፡፡ አንዱን ቤት ሰጡንና ኑሮ ጀመርን፡፡ መቼም ፍቅርና ትዳር ለየቅል ነው፡፡ ታድያ እኛ ትዳር እንደጀመርን ባለቤቴ የልጅነት ነገር ሆነበትና ከጓደኞቹ እየተማረ ውኃ ቀጠነ ማለት ጀመረ፡፡ ባልነት ማለት መኮሳተር፣ መጎማለል፣ አንቺ እያሉ መጣራት፣ አምሽቶ መምጣት መሰለው፡፡ ይህን ጠባይ እርሱ እንዳላመጣው ዐውቅ ነበር፡፡ ጓደኞቹ ናቸው ያስተማሩት፡፡ በጊዜ ገብቶ አብረን ነበር ስንስቅና ስንጫወት የምናመሸው፡፡ እንዲያውም የኔ ባልኮ ዘመናይ ነው እያልኩ ነበር ለሰው
Posted in Ethiopian News, Religion