Blog Archives

የኢህአፓ አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ «ለህዝብ መብት መሞት አኩሪ ታሪክ ነው»

ከተመሠረተ ከአራት አሰርት ዓመት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) አመራሮች ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደሚገቡ  የአቀባበል ስነ ስርዓት አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት 46 ዓመታት በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር በሚገኙ አባላቱ አማካኝነት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ሲታገል መቆየቱን የገለፀው ኢህአፓ፣ አሁን የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ በመጠቀም፣ አመራሮቹ ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን አስታውቋል። “በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን እየታየ ያለው የለውጥ ብልጭታ፣ ለዘመናት ስታገልለት የቆየሁለት አቋሜ ውጤት ነው” ያለው ኢህአፓ፤ ይህን የለውጥ ሂደት ለመደገፍና የተጀመረውን የሰላም የዴሞክራሲና የአንድነት ጭላንጭል እንዳይደበዝዝ፣ የድርሻቸውን ሊወጡ፣ አመራሮቹ ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስታውቋል፡፡ ኢህአፓ በዋናነት የሚታገልላቸው አላማዎችም፤ የአዲሱ ትውልድ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባና  ነው ብሏል ለህዝብ መብት መሞት አኩሪ ታሪክ መሆኑን በተግባር ማሳየት ጠቁሟል፡፡ ዛሬ ለረጅም ዓመታት በስደት ከኖሩበት ወደ ሃገር ቤት ከሚመለሱ ከፍተኛ አመራሮቹ መካከል ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሐመድ ጀሚል፣ ሊቀመንበሩ አቶ መርሻ ዮሴፍና ኢ/ር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ኢትዮጵያን እንገነባለን፣ አፍሪካን እንገነባለን ማንም ኃይል አያስቆመንም” ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ከተመሠረተ ከአራት አሰርት ዓመት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) አመራሮች ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደሚገቡ  የአቀባበል ስነ ስርዓት አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት 46 ዓመታት በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር በሚገኙ አባላቱ አማካኝነት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ሲታገል መቆየቱን የገለፀው ኢህአፓ፣ አሁን የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ በመጠቀም፣ አመራሮቹ ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን አስታውቋል። “በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን እየታየ ያለው የለውጥ ብልጭታ፣ ለዘመናት ስታገልለት የቆየሁለት አቋሜ ውጤት ነው” ያለው ኢህአፓ፤ ይህን የለውጥ ሂደት ለመደገፍና የተጀመረውን የሰላም የዴሞክራሲና የአንድነት ጭላንጭል እንዳይደበዝዝ፣ የድርሻቸውን ሊወጡ፣ አመራሮቹ ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስታውቋል፡፡ ኢህአፓ በዋናነት የሚታገልላቸው አላማዎችም፤ የአዲሱ ትውልድ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባና  ነው ብሏል ለህዝብ መብት መሞት አኩሪ ታሪክ መሆኑን በተግባር ማሳየት ጠቁሟል፡፡ ዛሬ ለረጅም ዓመታት በስደት ከኖሩበት ወደ ሃገር ቤት ከሚመለሱ ከፍተኛ አመራሮቹ መካከል ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሐመድ ጀሚል፣ ሊቀመንበሩ አቶ መርሻ ዮሴፍና ኢ/ር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሁለት ወራት ውስጥ በግጭትና ዘር ተኮር ጥቃት የ215 ዜጐች ህይወት ጠፍቷል

በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በግጭና  ብሔር ተኮር ጥቃቶች፤ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የ215 ዜጐች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ከትናንት በስቲያ ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ብሔር ተኮር ግጭቶችና በቡድን የተደራጁ ኃይሎች እየፈፀሟቸው ያሉትን ከባድ ጥቃቶች መንግስት በአስቸኳይ ሊያስቆም እንደሚገባ ሰመጉ አሳስቧል። በተለያዩ አካባቢዎች ግድያዎች፣ ዘርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችና ግጭቶች፣ የመንጋ ፍትህና ሥርዓት አልበኝነት እየተንሰራፋ መሆኑን የጠቆመው የሰመጉ ሪፖርት፤ በአደባባይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችም በባህሪያቸው ዘግናኝ ናቸው ብሏል፡፡ ካለፈው ሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች 215 ያህል ዜጐች በግጭትና በጥቃት መሞታቸውን ያስታወቀው ሪፖርቱ፤ እነዚህ ግጭቶችና ጥቃቶች በከፍተኛ መስዋዕትነት የተገኘውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል ያጨልም ስር የሰደዱ ችግሮች እየተገዳደሩት ይገኛሉ ብሏል፡፡ በግጭት በቃትና በመንጋ ፍትህ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉባቸው አካባቢዎች መካከልም፤- በደቡብ ክልል ፔፒ ከተማ 5 ሰዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ባሌ-ጐባ 10 ሰዎች፣ በደቡብ ክልል የም ወረዳ 6 ሰዎች፣ እንዲሁም ዳውሮ ዞንሪ ተርጫ ከተማ 5 ሰዎች፣ በሻሸመኔ 4 ሰው፣ በድሬዳዋ 15 ሰዎች፣
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮ-ኤርትራን ስምምነት ተከትሎ የንግድ እንቅስቃሴ ተጠናክሯል

- ሲሚንቶ ወደ ኤርትራ፤ አልባሳት ወደ ኢትዮጵያ …               - ኤርትራ በድንበር አካባቢ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች    በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ባለፈው ሳምንት ሚኖረውን ግንኙነት የሚደነግግ ባለ 7 አንቀጽ ስምምነት፣ የሁለቱ ሃገራት መሪዎች የተፈራረሙ ሲሆን፤ በሳዑዲ አረቢያ ጂዳ የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ፣ በሁለቱ ሃገራት ድንበር ከወዲሁ የንግድ እንቅስቃሴ መጧጧፉ ታውቋል፡፡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ ነው የተባለው ስምምነት፤ በሁለቱ ሃገራት መካከል የጋራ የኢኮኖሚ ትስስር እንዲፈጠር የሚያግዝ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ ሁለቱ ሃገራት በጋራ የኢኮኖሚ ዞን ለመመስረት፣ የንግድ እንቅስቃሴውም ነፃ እንዲሆን የተስማሙ ሲሆን ስምምነቱን ተከትሎም፣ በድንበር አካባቢ ከሰሞኑ የንግድ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መታየቱን ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ሲሚንቶ የኤርትራን ገበያ ማጥለቅለቁን፣ በአንፃሩ የኤርትራ የአልባሳት ምርት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ፣ የኤርትራ መንግስት፤ ለደህንነት ሲል ድንበር ማቋረጥ የሚቻለው ከጠዋቱ 12 ሠዓት እስከ ምሽቱ 12 ሠዓት ብቻ እንዲሆን የሰዓት እላፊ ገደብ መደንገጉን ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡ የሁለቱ ሃገራትን ነፃነት፣ ሉአላዊነትና የድንበር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ለቀጣዩ ብሔራዊ ምርጫ ሁሉን አሳታፊ ቅድመ ዝግጅት እንዲጀመር ተጠየቀ

በመጪው ዓመት 2012 ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ አጋዥ የሆኑ ተቋማትን የመመስረትና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል አስቸኳይ ድርድር ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር እንዲጀመር በፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው “የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ” ጠየቀ፡፡ ፓርቲው በወቅታዊ መግለጫው፤ የተጀመረው ለውጥ ህዝቡ የሚፈልገውን መቋጫ እንዲያገኝ፣ በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ ከወዲሁ ድርድር መጀመር አለበት ብሏል፡፡ “በምርጫ ጉዳይ ለሚደረገው ድርድር ጊዜ ሊሰጠው አይገባም” ያለው ፓርቲው፤ “በገዥው ፓርቲ እየተደረገ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ጊዜያዊ ማስታገሻ ከመሆን የዘለለ አይደለም፤ ሁሉን አሳታፊና ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር ሥርዓት በምርጫ መመስረት ያስፈልጋል” ብሏል።በሃገሪቱ መሠረታዊ በሆኑ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እጅግ የተራራቁ ሃሳቦችን የሚያራምዱ ኃይሎችን የሃሳብ ልዩነቶቻቸውን ለማቀራረብና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉ ውይይቶች መካሄድ አለባቸው ብሏል - ፓርቲው። በሃገሪቱ መሠረታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ድርድሮች ተካሂደው ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኢሶዴፓ፤ የተጀመረውን የለውጥ ሂደትም በገዥው ፓርቲ አመራርነት ብቻ ማሳካት አይቻልም ብሏል። ለዚህም የሃገሪቱን ፖለቲካዊ ለውጥ ወደፊት ሊያሸጋግር የሚችል የብሔራዊ አንድነት መንግስት በአስቸኳይ ተመስርቶ፣ የለውጡን ሂደት መምራት አለበት ሲል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በግጭት ምክንያት በተፈናቀሉ ሰዎች ብዛት ኢትዮጵያ ከዓለም የመሪነት ደረጃን ይዛለች

በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ኢትዮጵያ ከዓለም በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሪፖርት አመልክቷል፡፡ሰሞኑን ይፋ በሆነው በዚህ ሪፖርት በ2018 እ.ኤ.አ. ግማሽ ዓመት በእርስ በርስ ግጭት ምክንያት ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ዜጐች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን፣ ይህም በዓለም ሃገራት ያልተለመደ መሆኑን ጠቁሟል - ሪፖርቱ፡፡ ዜጐች የተፈናቀሉባቸው ግጭቶችም በደቡብና በኦሮሚያ ድንበር አዋሳኝ፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ፣ በቤኒሻንጉልና በአማራ ክልል እንዲሁም በደቡብ ክልል የወረዳ ለወረዳ ግጭቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ ለግጭቶቹ መበራከትና መስፋፋት በኢህአዴግ መካከል የተፈጠረው አለመግባባትና የመንግስቱን ድክመት በምክንያትነት የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ለተፈጠሩት ግጭቶችና መፈናቀሎች የመንግስትን ስልጣን የያዘው ኢህአዴግ ቀዳሚ ተጠያቂና ተወቃሽ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ የተፈናቃዮች ጉዳይ አስቸኳይ እልባት ካላገኘ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል ያለው ሪፖርቱ፤ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ በተፈጠረ ግጭት 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ከቀዬአቸው የመፈናቀላቸውን ጉዳይ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በቸልታ መመልከታቸው አግባብ አይደለም ሲልም ወቅሷል፡፡ በአሁን ወቅት ውስን የእርዳታ ድርጅቶችና መንግስት ለተፈናቃዮች እርዳታ ለማቅረብ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን የመንግስታቱ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ብአዴን” ስያሜውን ለመቀየር አራት አማራጮችን አቅርቧል

ላለፉት 27 ዓመታት የአማራ ክልልን ሲያስተዳድር የቆየው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፤ ስያሜውንና አርማውን እንደሚቀይር አስታወቀ፡፡ የአማራ ህዝብ ትግል የደረሰበትን ደረጃ መሠረት በማድረግ፣ አርማና ስያሜውን ለመቀየር መወሰኑን የገለፀው ብአዴን፤ አዲሱን መጠሪያውንና አርማውን ከሳምንት በኋላ በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤው ይፋ ያደርጋል ተብሏል፡፡ የድርጅቱን ቀጣይ ስያሜና አርማ በተመለከተም አማራጮችን አቅርቦ እስከ ወረዳ ባለው መዋቅሩ እያወያየበት መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ ለድርጅቱ መጠሪያነት አራት አማራጮችን ለውይይት ማቅረቡም ታውቋል፡፡ለውይይት የቀረቡት አማራጮችም፤ “የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” (አህዴፓ)፣ “የአማራ ክልል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ” (አህዴፓ)፣ “የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት” (አህዴድ)ና “የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (አህዴን) የሚሉ ናቸው፡፡ የአርማ አማራጮችም ተዘጋጅተው ለንቅናቄው አባላት ውይይት ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ፤ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስያሜውን፣ አርማውንና ድርጅታዊ መዝሙሩን ለመቀየር እንዳቀደና ይህም ከመስከረም 8 እስከ 10 በጅማ ከተማ በሚካሄደው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ውሣኔ እንደሚያገኝ ተገልጿል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ኢትዮጵያ መላውን ዓለም ያስደመመ ለውጥ ላይ ነች” አርበኞች ግንቦት 7

ኢትዮጵያ መላውን ዓለም ያስደመመ ፖለቲካዊ ለውጥ እያደረገች መሆኑን ሰሞኑን አመራሮቹ ወደ አገር ውስጥ የገቡት “አርበኞች ግንቦት 7” ባወጣው የአቋም መግለጫው አስታወቀ፡፡ የንቅናቄው አመራሮች ወደ ሃገር ቤት ከገቡ በኋላ ባወጣው በዚህ የመጀመሪያው የአቋም መግለጫው፤ ዛሬ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴና የለውጡ ሂደት ቀጥተኛ ባለቤት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ብሏል፡፡ “በሃገሪቱ የተካሄደው ለውጥም የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የናፈቀውን መላውን የዓለመ ህዝብ ያስደመመ ነው” ብሏል - ንቅናቄው፡፡ ባለፉት ሁለትና ሦስት ወራት ውስጥ ለውጡን በመደገፍ፣ ለውጡን ወደፊት ለማራመድ የሚፈልጉ የሰብአዊ መብት ታጋዮች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሃይማኖት አባቶች ለብዙ ዓመታት በስደት ከኖሩባቸው ሃገሮች ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውን ያስታወሰው የንቅናቄው መግለጫ፤ ለተመለሱት ሁሉ እኩል ክብር እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ በዜግነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካን አራምዳለሁ ያለው አርበኞች ግንቦት 7፤ “ለወደፊት የምንገነባው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከሚፈልጋቸው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱና ትልቁ የፖለቲካ አካሄዳቸው ከማይገጥመንና በሃሳብ ከምንለያያቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ተከባብሮና ተቻችሎ መኖር መቻል ነው” ሲል አስገንዝቧል፡፡ህዝቡ ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ በመከባበርና በፍቅር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በአርማና ባንዲራ ጉዳይ ለሚፈጠር ውዝግብ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

በመላ ሃገሪቱ ከአርማና ባንዲራ ጋር በተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ ውዝግቦች ዘላቂ ሕጋዊ መፍትሄ እንደሚያሻቸው የገለፁት ሰማያዊ ፓርቲና ኦፌኮ፤ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከማምራታቸው በፊት መንግስት አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል። ከአርማና ሠንደቅ አላማ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ሁከቶችን ለማስቆም የሃይማኖት አባቶችና፣ አባገዳዎች፣በየአካባቢው ወጣቶችን  የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩም ፓርቲዎቹ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቀዋል፡፡ “የለውጡን ሂደት መደገፍና አገሪቱን እንደ አገር የማስቀጠል ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ሲገባ፤ በየአካባቢው የሚታዩ ግጭቶችና ሥርአት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል” ያሉት ፓርቲዎቹ፤ “በተለይ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከባንዲራ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ውዝግብ ከምንም በላይ አሳሳቢ ነው፤ አስቸኳይ እልባት ያስፈልገዋል” ብለዋል፡፡ ሁሉም አካል የሌላውን ባከበረ መልኩ የየራሱን አርማ መያዝ እንደሚችል የተረጋገጠ ሁኔታ መፈጠሩን የጠቀሱት ፓርቲዎቹ፤ በዚህ ሰበብ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በፅኑ እናወግዛለን ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ በአሁን ወቅት እየታየ ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ ተስፋ ሰጪ መሆኑን የጠቆሙት «ሰማያዊ» እና «ኦፌኮ»፤ ሁሉም የፖለቲካ ቡድን ይህን ተስፋ ወደተሻለ ለውጥ የማሸጋገር ኃላፊነት አለበት ብለዋል፡፡ ወደ ሃገር ውስጥ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን የአሜሪካ መንግስት አደነቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታን ለመቀየር የወሰዷቸውን እርምጃዎችና ለውጡን ለማምጣት የሄዱበትን ርቀት የአሜሪካ መንግስት አደነቀ፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ቲቦር ናጋይ፤ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ አመራር በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች አድናቆት የሚቸራቸው ናቸው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የሃገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ የሚያደርጉ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆኑን የጠቆሙት ቲቦር ናጋይ፤ በዚህም ለበርካታ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ የተጠራቀሙ ፖለቲካዊ ችግሮችም እልባት እያገኙ መሆኑን መረዳታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ፤ ለመጣው ለውጥም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአመራር ሚና አድናቆት የሚቸረው ነው ብለዋል፡፡ መንግስታቸውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን በአድናቆት እንደሚመለከተው ጠቁመው፤ ለዘላቂነቱም ድጋፍ  ይቸረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵና በኤርትራ መካከል ላለፉት 20 ዓመታት የዘለቁ  ችግሮን በሰላም ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያከናወኑት የዲፕሎማሲ ሥራ የሚደነቅና ያልተለመደ መሆኑን የጠቀሱት  ኃላፊው፤ በቀጣይ አፋኝ የሚባሉ አዋጆችን በማሻሻል የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያሰፋ ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወስዱም ጠይቀዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በህዳሴ ግድብ ግንባታ ምዝበራ የፈፀሙ ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

ከህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ጋር ተያይዞ “ስለተፈፀመው ከፍተኛ ዘረፋ” ለህዝብ ማብራሪያ እንዲሰጥ የጠየቀው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፤ በዘረፋውና ምዝበራው የተሳተፉ የመንግስት ኃላፊዎች በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡ ለሃገሪቱ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማት ዘርፍ ብዙ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለተደራጀ ዘረፋ ተጋልጦ እንደነበር ከቀረቡ ዘገባዎች መረዳት መቻሉን የጠቆመው አብን፤ መንግስት የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ዝርዝር መረጃ መስጠት እንዳለበት ገልጿል፡፡ በግድቡ ግንባታ ወቅት መጓተትን የፈጠሩ፣ በህዝብ ሃብትና ገንዘብ ምዝበራ የተሳተፉ እንዲሁም ምዝበራው ሲፈፀም ማስቆም ሲገባቸው ያላስቆሙ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ተጠያቂ እንዲደረጉ ንቅናቄው ጠይቋል፡፡ በቀጣይም ግልፅ የፋይናንስ ሥርዓት ተዘርግቶ፣ ግንባታው በአስቸኳይ እንዲጠናቀቅ መደረግ አለበት ብሏል አብን ባወጣው መግለጫው፡፡ የግድቡን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ኮንትራት የወሰደው ሜቴክ፤ ስራውን በአግባቡ ባለማከናወኑ “ለኪሳራ ተዳርጌያለሁ” ያለው የሲቪል ግንባታ ኮንትራክተሩ ሳሊኒ መንግስትን 3.5 ቢሊዮን ብር እና 338 ሚሊዮን ዩሮ መጠየቁ ይታወቃል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

መቐለ በምጽዋ አገልግሎት መጀመሯ “የአዲስ ዓመት ገጸበረከት ነው” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ    ሰሞኑን በአስመራ ተገናኝተው በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች፤ በአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዚደንት ሙሐመድ ፎርማጆ ስለ ውይይታቸው በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ማስታወሻ፤ሶስቱን ሃገራት በኢኮኖሚ ለማስተሳሰርና በፀጥታ ጉዳይም በጋራ ለመስራት ታሪካዊ ስምምነት ተፈርሟል ብለዋል፡፡ የኤርትራ መንግስት በበኩሉ፤ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን በሙሉ አቅሙ ለመጠቀም እንዲያስችላት በሚል ከወደቡ እስከ ቡሬ ከተማ የሚደርስ የ71 ኪሎ ሜትር ዘመናዊ አስፓልት መንገድ መገንባት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ መንገዱ በአንድ ጊዜ አራት ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ አስፓልት መሆኑን የጠቆመው የኤርትራ መንግስት፤ይህም የሁለቱ ሃገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ወደተሻለ ደረጃ ያሻግራል ብሏል፡፡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ በኤርትራ ባደረጉት ጉብኝትም “መቐለ” የተሰኘችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ፣ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከምፅዋ ወደብ የኤርትራን የወጪ ንግድ እቃ በመጫን፣ ወደ ቻይና ያደረገችውን ጉዞ አስጀምረዋል፡፡ መርከቧ በምጽዋ አገልግሎት መስጠት መጀመሯ በእጅጉ ያስደሰታቸው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ፤ ለመላው
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ብሔራዊ እርቅና መግባባት ያስፈልጋል”

ሰሞኑን ከ15 ዓመታት የውጭ አገር ስደት በኋላ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹና የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኙ አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ብሔራዊ እርቅና መተማመን ያስፈልጋል አሉ፡፡ አቶ ኦባንግ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ወደ ሃገር ቤት የተመለሱት በዋናነት የጀመሩትን የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የበለጠ ለማጠናከር መሆኑን ተናግረዋል፡፡  “ላለፉት 27 ዓመታት ከገባንበት መከፋፈል፣ መጠፋፋትና የጨለማ ጊዜ እየወጣን ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ፤አሁን የሚታየው ለውጥ የብዙዎች ደም ፈሶ፣ በርካቶች ለአካል ጉዳትና፣ ለስደት ተዳርገው ያመጡት እንደመሆኑ፣ ሁሉም ሰው ለውጡ እንዳይቀለበስ ሊጠብቀው ይገባዋል” ብለዋል፡፡  “ሰው መሆናችን ብቻ በቂ ነው፤ ደማችን አንድ ነው” ያሉት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ፤ በዘር መከፋፈል ቀርቶ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር መሰባሰብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ “ከገባንበት የጐጠኝነት ፖለቲካ ወጥተን ወደተሻለው አገራዊ አንድነት አስተሳሰብ መሻገር አለብን” ብለዋል፡፡  የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚሉ ወገኖች በሙሉ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው፣ “ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ምን ትምሰል? ምን አይነት ኢትዮጵያን ነው ለአዲሱ ትውልድ የምናሻግረው?” በሚለው ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግና መወሰንም እንደሚገባ አሳስበዋል - አቶ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ለግንቦት 7 አመራሮች አቀባበል ከተማዋ ደምቃለች

ነገ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ 250 አመራሮች ይገባሉ    ነገ ማለዳ አዲስ አበባ ለሚገቡት የ”አርበኞች ግንቦት 7” ንቅናቄ አመራሮች፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ያደርጉላቸዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን መዲናዋ ለዚሁ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት፣በባንዲራና በፖስተሮች ደምቃለች፡፡ ለአመራሮቹ የሚደረገው አቀባበል ከጠዋቱ 12፡30 እስከ ቀኑ 9 ሰዓት በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚፈፀምም ታውቋል፡፡ የንቅናቄው አመራሮች ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአሜሪካና አውሮፓ ሃገራት በተለያዩ በረራዎች ከጠዋቱ 12፡30 ጀምሮ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚደርሱ ለአዲስ አድማስ የጠቆሙት የአቀባበል ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፤ ሁሉም አመራሮች ከገቡ በኋላ ዋናው የአቀባበልና የዕርቅ ማብሰሪያ ሥነ ሥርዓት ወደ ሚካሄድበት አዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያመሩ አስታውቀዋል፡፡ በነገው ዕለት በመላው ዓለም የሚገኙ የንቅናቄው አመራሮች ተጠናቀው ወደ ሃገር ቤት እንደሚገቡ ያመለከቱት አስተባባሪው፤ ንቅናቄውም ቀደም ሲል ሲያራምድ የነበረውን በትጥቅ የታገዘ ሁለገብ ትግል ፈትሾ፣ በሃገር ውስጥ በሠላማዊ መንገድ ለመታገል የሚያስችለውን ስትራቴጂ ነድፏል ብለዋል፡፡ በቅርቡም ንቅናቄው በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለምርጫ ውድድር እንደሚቀርብ የጠቆሙት አቶ ብርሃኑ፤ ወደ ሃገር ቤት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የፀረ ሽብር አዋጁ እየተሻሻለ ነው ተባለ

- ተቃዋሚዎች ስድስት አንቀፆች እንዲሠረዙ ጠይቀዋል - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የመድረክ አመራሮችን ሊያነጋግሩ ነው    ለበርካታ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እስር ምክንያት የሆነው የፀረ ሽብር አዋጅ እንደሚሻሻል መንግስት ያስታወቀ ሲሆን ተቃዋሚዎች ስድስት አንቀፆች ከአዋጁ ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲሠረዙ ጠይቀዋል፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ ማሻሻያ በህግ ባለሙያዎች እየተሠራ መሆኑን የገለፀው መንግስት፤ ሊካተቱ የሚችሉ አዳዲስ አንቀፆችም ይኖራሉ ተብሏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎችም አምስት አንቀፆች እንዲጨመሩ፣ ስድስት ነባር አንቀፆች እንዲሠረዙና አራት አንቀፆች ማሻሻያ እንዲደረግባቸው የጠየቁ ሲሆን ኢህአዴግም በአብዛኛው መስማማቱ ታውቋል፡፡ ይሠረዛሉ ተብለው ከሚጠበቁት አንቀፆች መካከል አንቀፅ 14 ላይ የተደነገገው “ተጠርጣሪዎች አሻራ በግዳጅ መስጠት” የሚለውን ጨምሮ የግለሠቦችን ስልክና ማናቸውንም የግንኙነት አውታር የመጥለፍ ስልጣን ለደህንነት ሃይሉ የሚሠጠው አንቀፅ ይገኝበታል፡፡  በፀረ ሽብር አዋጁ ይሻሻላሉ ተብለው ከሚጠበቁት አንቀፆች መካከልም የቅጣት አወሣሠን ጉዳይ ይገኝበታል፡፡ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚዎች ባደረጉት ድርድር ላይ በአዋጁ ከእድሜ ልክ እስከ ሞት የተደነገገው የቅጣት ደረጃ ተሻሽሎ፣ “አንድ በእስር የሚፈረድበት ሰው ከ10 ዓመት በማይበልጥ እስራት ብቻ እንዲቀጣ” የሚለው ሃሣብ ጎልቶ መውጣቱ ታውቋል፡፡በአዋጁ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ሊፈቀድ ነው

ሁሉም አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት እድል ሊመቻች እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለፁ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሰሞን በኢትዮጵያ የ2 ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ካደረጉት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ሩዋንዳ ሁሉም አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ሃገሯ እንዲገቡ ያስተላለፈችውን ውሣኔ አድንቀው፣ ኢትዮጵያም በቅርቡ የሩዋንዳን በጎ ተሞክሮ ትከተላለች ብለዋል፡፡ የአፍሪካ መዲና ወደ ሆነችው አዲስ አበባ፣ አፍሪካውያን ያለ ቪዛ እንዲገቡ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሃገሪቱን የቱሪስት ፍሠት የሚጨምር ከመሆኑም በላይ ለኢኮኖሚዋም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም አፍሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቪዛ እንዳይጠየቁ ሊደረግ እንደሚችል ከመጠቆማቸው ውጭ እንዴትና መቼ ተግባራዊ ይደረጋል በሚለው ላይ ያሉት ነገር የለም፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ህገወጥ በሚል ቤት ለፈረሰባቸው መፍትሄ እንዲሠጣቸው የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስተዳደሩን አሣሠበ

ሠኞ ከንቲባው ቅሬታ አቅራቢዎችን ያነጋግራሉ በከተማዋ በሁለት አመት ውስጥ 36 ሺህ ህገወጥ ቤቶች ፈርሠዋል     በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሃና ማርያም አካባቢ ከሁለት አመት በፊት “ህገ ወጥ ናችሁ” በሚል ቤት ለፈረሠባቸው ነዋሪዎች የአዲስ አበባ አስተዳደር መፍትሄ እንዲሠጥ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሣሠበ፡፡በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 እና ወረዳ 11 ውስጥ በሚገኙ ቀርሳ ኮንቶማ፣ ማንጎ በሚባሉ አካባቢዎች ቤታቸው በሃይል የፈረሠባቸው ዜጎች፤ ላለፈው አንድ አመት ተኩል ለአስተዳደሩ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ቢቆዩም ምላሽ ባለማግኘታቸው፣ በሠላማዊ ሠልፍና በደብዳቤ ከሠሞኑ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢ፤ የቅሬታ አቅራቢዎቹን ተወካዮች ከትናንት በስቲያ በፅ/ቤታቸው ያጋገሩ ሲሆን እስካሁን መፍትሄ ሳያገኙ መንገላታታቸው ተገቢ አለመሆኑንና አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመው፤ ለዚህም ከንቲባው ከነገ በስቲያ ሠኞ ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ.ም አቤቱታ አቅራቢዎቹን ሰብስበው እንዲያነጋግሩ ቀጠሮ ማስያዛቸውን እንደነገሯቸው ተወካዮቹ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሁለት አመት በፊት በከተማዋ የሚገኙ 36 ሺህ ህገ ወጥ ቤቶችን ማፍረሡን በመግለፅ፤ ለዚህ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚኒስትሩ በሰ.አሜሪካ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዳይገኙ ተወሠነ

ከአንድ ወር በኋላ በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ፣ ለ35ኛ ጊዜ በሚካሄደው በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለመገኘት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም ተባለ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሣምንት በፊት ለስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጁ ፌዴሬሽን፤ “በፕሮግራማችሁ ላይ ከኢትዮጵያውያን ጋር ልገናኝ” የሚል ደብዳቤ መፃፋቸው የታወቀ ሲሆን ፌዴሬሽኑም ይገኙ አይገኙ የሚለውን የወሠነው በአባላቱ ድምፅ ነው ተብሏል፡፡ 14 የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት “ዶ/ር አብይ መገኘት የለባቸውም” የሚል ድምፅ ሲሠጡ፣ “11 ደግሞ ይገኙ” ብለዋል፡፡ 8 ድምፀ ተአቅቦ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በድረ ገፁ በሠጠው መግለጫ፤ “አብዛኛው አመራር አይገኙ የሚል ውሣኔ ያሣለፉት እንዳይገኙ ከመፈለግ ሣይሆን ጥያቄው የቀረበበት ጊዜ አጭር በመሆኑ፣ ሁኔታዎች አገናዝቦ ለመወሰን አመቺ ባለመሆኑ ነው” ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፤ በቀጣይ በሚደረገው ተመሣሣይ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የመገኘት እድል እንዲሰጣቸው መመቻቸቱንና ጥያቄያቸው ለቀጣይ መሸጋገሩንም ፌደሬሽኑ አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ በሠሜን አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚሰባሰቡበት የስፖርት መድረክ ላይ ልገኝ ብለው የጠየቁ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሃገሪቱ 1.5 ሚሊዮን ዜጎች ለጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች ተጋልጠዋል ተባለ

የመሬት መንሸራተት አስጊ ሆኗል    በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየጣለ ባለው መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ በሆነ ዝናብ ምክንያት በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት 39 ሰዎች መሞታቸው የታወቀ ሲሆን በቀጣዩ ክረምት 1.5 ሚሊዮን ዜጎች ለጎርፍ አደጋ ተጋልጠዋል ተባለ፡፡ ከሠሞኑ በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን፣ ከባድና ተከታታይ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት 7 ሰዎች፣ በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ በተመሣሣይ አደጋ ዘጠኝ ሰዎች እንዲሁም በደቡብ ክልል በሲዳማና በአርሲ ዞን አዋሳኝ አካባቢ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን፣ ከፌደራል የአደጋ መከላከልና ስጋት አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ምን መልክ ይኖረዋል በሚለው ጉዳይ ለአዲስ አድማስ መረጃ የሰጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ፤ በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት የመሬት መንሸራተት አንዱ የአደጋ ዘርፍ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡ ችግሩም አሣሣቢ ደረጃ መድረሡን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ የሰዎች ህይወትም እየቀጠፈ ነው ብለዋል፡፡ ለመሬት መንሸራተት አስጊ እየሆነ መምጣት በአካባቢ ጥበቃ ጉድለት ደን መራቆት መከሠቱ፣ ሠዎች ተዳፋታማ አካባቢዎች መስፈር መጀመራቸው እንዲሁም የአፈር አይነት ምክንያት መሆናቸውን አቶ ምትኩ ለአዲስ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“በትግራይ የፖለቲካ እስረኞች አልተፈቱም” – አረና

ከ50 በላይ አመራሮቹና አባላቱ በትግራይ ክልል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ የገለፀው አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት (አረና) ፓርቲ፤ የክልሉ መንግስት እስካሁን ዋነኛ የፖለቲካ ሰዎችን ከእስር አለመልቀቁን አስታወቀ፡፡ በቅርቡ ከ2 ሺህ በላይ እስረኞች በክልሉ መለቀቃቸውን ያስታወሡት የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ፤ ከተለቀቁት መካከል አንድም ፖለቲከኛ አለመኖሩን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ከ50 በላይ የሚሆኑ በፓርቲው ውስጥ ሠፊ ተሣትፎ የሚያደርጉ አባላትና አመራሮች በተለያየ ሰበብ በእስር ላይ እንደሚገኙ የገለፁት አቶ ጎይቶም፤ ፓርቲያቸው ታሣሪዎች እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ቀና ምላሽ አለማግኘቱን ጠቁመዋል፡፡ ከፓርቲው አባላት በተጨማሪም መሠረቱን ኤርትራ አድርጎ፣ የኢትዮጵያን መንግስት በመቃወም ከሚንቀሳቀሰው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሠሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ከእስር አለመፈታታቸውን አቶ ጎይቶም አስታውቀዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ፖለቲካችን ወደ አዲስ ምዕራፍ

- “ኢትዮጵያ እንዲህ ይቅር ባይ መሪ ያስፈልጋታል” - ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ- “የኢትዮጵያ ትንሣኤ መቅረብ ምልክት ነው” - ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ- “ይህቺ ሃገር ሊያልፍላት ይሆን እንዴ?” - ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሃይሉ   ከእስር የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተገናኝተው መወያየታቸው ብዙዎችን ያስደሰተ ሲሆን የአውሮፖ ህብረትና የእንግሊዝ መንግስት የሚበረታታ እርምጃ ነው፤ እንደግፈዋለን ብለዋል፡፡ ማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2010. ዓ.ም ከ4 ዓመት እስር በኋላ በይቅርታ ተፈትተው  ቤተሠቦቻቸውን የተቀላቀሉት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፤ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡በውይይታቸውም የተለያዩ ፖለቲካዊና ሃገራዊ ጉዳዮች መነሣታቸውን በጥቅሉ የገለፁት አቶ አንዳርጋቸውም የተወያዩባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በብሄራዊ ቤተ መንግስት የተነሱትና በጠ/ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ድረገፅ የወጣው ፎቶ ግራፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከተሠራጨ በኋላ በርካቶች የተሠማቸው ደስታ ገልፀዋል፡፡የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህሩና የመብት አራማጁ ስዩም ተሾመ በፌስ ቡክ ላይ ባሰፈረው አስተያየት፤ የቂም በቀልና
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

መንግስት የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይልን እንዲበትን ተጠየቀ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ውስጥ የሠብአዊ መብት ጥሰቶችን እየፈፀመ ነው ያለውን የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ መንግስት በአስቸኳይ እንዲበትን የሠብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ፡፡ አምነስቲ ትናንትና ባወጣው መግለጫው፤ የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ ተደጋጋሚ የሠብአዊ መብት ጥሠትና ግድያዎችን እየፈፀመ መሆኑን ጠቅሶ፤ ከሠሞኑም በክልሉ 48 ቤቶችን በማቃጠል፣ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ጥለው እንዲሠደዱ አድርጓል ብሏል፡፡ መንግስት ይህን ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ በአስቸኳይ በመበተን፣ ለአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ተገዥ የሆነ መደበኛ የፖሊስ ሃይል እንዲደራጅ ጠይቋል፡፡ “ከዚህ በኋላ የሶማሌ ልዩ ሃይል አባላት እንዳሻቸው በህዝብ ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ መፈቀድ የለበትም” ያለው ተቋሙ፤ “መንግስት ይሄ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያበቃ ማድረግ አለበት” ብሏል፡፡ በአከባቢው ላለው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠትም ልዩ ሃይሉን በማፍረስ፣ የክልሎችን ድንበር በተገቢው ሁኔታ ማካለል ያስፈልጋል ብሏል- አምነስቲ፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ቤታቸው የፈረሰባቸው አስር ሺህ አባወራዎች ለጠ/ሚሩ አቤቱታ አቀረቡ

ህገ ወጥ ግንባታ ነው በሚል ከሁለት አመት በፊት በአዲስ አበባ ቤታቸው የፈረሠባቸው አስር ሺህ ያህል አባ ወራዎች፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቤቱታቸውን በደብዳቤ አቀረቡ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ገቢ በተደረገው የአቤቱታ ደብዳቤ ላይ፤ አባወራዎቹ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ማንጎ ጨፌ ግራር በተባለ አከባቢ በተለያየ አግባብ መኖሪያ ቤት ሠርተው መኖር መጀመራቸው ተገልጿል፡፡ በወቅቱ ነዋሪዎቹ ያለ ማስጠንቀቂያ በቡልዶዘር ቤታቸው በጅምላ እንዲፈርስ ተደርጎ ጎዳና ላይ መበተናቸውን የሚጠቅሰው ደብዳቤው፤ በኋላም በአካባቢው በነበረው የቤቶቻቸው ፍርስራሽ ላይ በላስቲክና በሸራ ድንኳን ወጥረው መኖር እንደጀመሩ ደብዳቤው ይጠቁማል፡፡ ይሁን እንጂ ሠሞኑን (ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 3) ወደ ፕላስቲክ መኖሪያ ቤቶቻቸው እንዳይገቡ ተከልክለው ሜዳ ላይ መውደቃቸውን፤ ልጆቻችውም ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን አቤቱታ አቅራቢዎቹ ገልፀዋል፡፡ህብረተሠቡ መብቱን ሲጠይቅ በዱላ እየተደበደበ ይታሠራል የሚሉት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ የውጭ ሃገር ስደተኞችን ተቀብላ በክብር የምታኖር ሃገራችን፣ እንዴት ለኛ ለዜጎቿ ቦታ ታጣለች ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ በ2005 ዓ.ም ገንዘብ አዋጥተን፣ መንገድ፣ መብራትና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተርን ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናትና ባለሃብት ከእስር ይፈታሉ

የግል ኩባንያዎች የሙስና ክስም ተቋርጧል    ከአምስት አመት በፊት በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት የገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ ምክትላቸው አቶ ገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስና ባለቤታቸው ኮ/ል ሃይማኖት ተስፋዬን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ክሳቸው ተቋረጠ፡፡ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክሱን ያቋረጠው የግንቦት 20ን በአል ምክንያት በማድረግ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ክሣቸው ከተቋረጠላቸውም መካከልም አቶ መላኩ ፋንታ፣ አቶ ገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስ እንዲሁም አብረዋቸው ታስረው የነበሩት የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሄር፣ የኬኬ ኩባንያ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ፣ የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት አቶ ስማቸው ከበደ እንዲሁም ባለሃብቱ አቶ ጌቱ ገለቴና፣ አቶ ገብረስላሴ ገብሬ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በቅርቡ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የኢሊሊ ሆቴል ባለቤት አቶ ገምሹ በየነም ክሳቸው ተቋርጧል፡፡ ከባለስልጣናትም የኢንዱስትሪ ሚ/ር ዴኤታ የነበሩ አቶ አለማየሁ ጉጆ፣ አቶ ዋሲሁን አባተ፣ አቶ አክሎክ ደምሴ፣ አቶ ዛይድ ወ/ገብርኤል (የቀድሞ የመንገዶች ባለስልጣን ዳይሬክተር)፣ አቶ መስፍን  ወርቅነህ፣ ወ/ሮ ሰኙን ጎበና፣ አቶ ጌታቸው ነገሪ፣ አቶ ነጋ መንግስቱና አቶ ሙሣ መሃመድ ክሳቸው ተቋርጧል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ጂኤች
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በአማራና ኦሮሚያ፣ ከ2ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች ታስረዋል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣቱን ተከትሎ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ከ2ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮማንድ ፖስት፣ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች 1600 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በአማራ ክልል፣ ጎንደር 93 ሰዎች በገዛ ፍቃዳቸው እጃቸውን ለፖሊስ ሰጥተዋል ብሏል - ኮማንድ ፖስቱ፡፡ በሰበታ ከተማ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ላይ ለደረሰው ቃጠሎና ውድመት እጃቸው አለበት የተባሉ 1 ሺ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ባለፈው ሳምንት ፖሊስ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡  ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ ብቻ 450፣ በአካባቢው ባሉ ወረዳዎች 670 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የገለጸው ኮማንድ ፖስቱ፤ በቄለም ወለጋ ዞን 110 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብሏል። በኦሮሚያ ከተዘረፉት 513 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች 384 ያህሉ መመለሳቸውን አመልክቷል፡፡ ሌሎች በግጭቱ ወቅት የተዘረፉ የመንግስትና የግለሰብ ንብረቶችም በስፋት እየተመለሱ ነው ብሏል - ኮማንድ ፖስቱ፡፡ በአማራ ክልል በጎንደር ከተማና አካባቢው “ሸፍተው” ጫካ የገቡና ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ከነበራቸው መካከል 93 ሰዎች እጃቸውን የሰጡ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ህዋዌ፤ ለመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ አደረገ

በቴሌኮም ማስፋፋትና በኔትወርክ ዝርጋታ ስራ የተሰማራው ህዋዌ፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለ‹‹መሰረት በጎ አድራጎት›› ድርጅት የትምህርት መሳሪያ ድጋፍ አደረገ፡፡  ድርጅቱ 4500 ደብተሮችን፣ 1500 እርሳሶችን፣ 1500 እስክርቢቶዎችንና ላጲሶችን ለግሷል፡፡ በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አዛገ ህዋዌ ስላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፣ ድጋፉ  ‹‹አንድ እሽግ ለአንድ ልጅ›› በሚል የሚያካሂዱትን የትምህርት ቁሳቁሶች አቅም ለሌላቸው የማከፋፈል ፕሮጄክት፣ በእጅጉ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ ከህዋዌ ያገኙት ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ50 ሺህ ብር በላይ እንደሆነ የገለፁት ወ/ሮ መሰረት፤ ድጋፉ ሌሎችም ድርጅቶች ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡ከድጋፉ ጎን ለጎን መሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት የተመሰረተበትን አምስተኛ ዓመት ያከበረ ሲሆን በአምስት አመት ጉዞው ያከናወናቸውን፣ ያሳካቸውንና ያለፋቸውን ፈተናዎች በዘጋቢ ፊልም ለታዳሚዎቹ አቅርቧል፡፡ የህዋዌ ተወካዮችም ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ በዕለቱ ቃል ገብተዋል፡፡ በመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ ድርጅቱ አምባሳደር አርቲስት ሩታ መንግስተአብና አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቱሪዝም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው›› – አስጎብኚ ድርጅቶች

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ የውጭ አገር ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ የመጓዝ ፍላጎታቸው በእጅጉ መቀነሱን የገለፁ አስጎብኚ ድርጅቶች፤ ለችግሩ መላ ካልተገኘ አዋጁ በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ተናገሩ፡፡ ‹‹አገር የማስጎብኘት ሥራ እንደ ማኑፋክቸሪንግ አይደለም፤ አንድ ፋብሪካ ቢቃጠል ወይም ሌላ ጉዳት ቢደርስበት በዓይን ይታያል። የቱር ኦፕሬሽን ሥራ፣ አገልግሎት ስለሆነ ጉዳት ሲደርስበት በዓይን አይታይም፡፡ አሁን በአገሪቱ በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ዘርፉ ጉዳት ደርሶበታል›› ብለዋል፤ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት፤ አቶ ያዕቆብ መላኩ፡፡አስጎብኚ ድርጅቶች ከመስከረም ጀምሮ እስከ ታህሳስ፣ ጥርና የካቲት ያሏቸውን ገበያዎች ሸጠው እንደጨረሱና ደንበኞችም ክፍያ መፈጸማቸውን ጠቅሰው፣ ለሆቴሎችና ለሌላ አገልግሎት አቅራቢያዎችም ክፍያ መፈፀማቸውን ይገልፃሉ። ሆኖም በተፈጠረው ችግር ምክንያት ቱሪስቶች ወደ አገራችን  ለመምጣት  ፍላጎት አላሳዩም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አንዳንድ ቱሪስቶች የከፈሉት እንዲመለስላቸው እየጠየቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  የተለያዩ የጉዞ አማካሪዎችና ኤምባሲዎች የሚያሰራጩት ወደ ክልከላ ያደገ ማስጠንቀቂያ፣ ለጉብኝት ፕሮግራሞች መሰረዝ ዋነኛ ምክንያት እንደሆኑ የጠቀሱት አቶ ያዕቆብ፣ ‹‹አንዴ ፕሮግራም አድርጌአለሁ፤ ሄጄ ያለውን ነገር አያለሁ›› ብለው የሚመጡ ጥቂት ቱሪስቶች ቢኖሩም
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ከፕሬዚዳንቱ ፅ/ቤት የተሰጠ ማስተባበያ

“የሰመጉን ሪፖርት አንቀበልም አላልንም”   ባለፈው ጥቅምት 5 ቀን 2009 ዓ.ም ታትሞ በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ከሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ብፅአተ ተረፈ ጋር በተደረገው ቃለ ምልልስ፤ ‹‹ከፕሬዚዳንቱ ፅ/ቤት ሁለተኛ ሪፖርታችሁን ወደ ፅ/ቤታችን እንዳትልኩ ተብለናል›› ሲሉ የተናገሩት የፕሬዚዳንቱን ፅ/ቤት ስም የሚያጠፋና ፈፅሞ ያልተባለ ነገር ነው፤ አንድም ቀን ሪፖርታችሁን አንቀበልም ብለናቸው አናውቅም፤ ልንልም የምንችልበት ምክንያት የለንም፡፡ የፕሬዚንዳንቱ ፅ/ቤት ሁሉንም የሃገሪቱን ዜጎችና ተቋማት በእኩልነት የሚያገለግል ተቋም ነው፡፡ አቶ አለምነህ ረጋሳ  የፕሬዚዳንቱ የፅ/ቤት የፕሮቶኮልና ኮሚኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የህትመት ኢንዱስትሪው በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ነው ተባለ

ለሚዲያዎች መስፋፋትና እድገት ማነቆ ሆኗልበሃገሪቱ ያለው የህትመት ኢንዱስትሪ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ መሆኑን አንድ ጥናት ያረጋገጠ ሲሆን ለሚዲያዎች መስፋፋትና እድገትም ማነቆ እየፈጠረ ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ አሳታሚዎች አታሚዎች ማህበር ከትናንት በስቲያ በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጀው የግማሽ ቀን ወርክሾፕ ላይ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የቀድሞው ፕሬዚዳንት በአቶ ጌታቸው በለጠ የቀረበ ጥናት እንዳመለከተው፤መንግስት ለህትመት ኢንዱስትሪው ምንም አይነት ድጋፍ ስለማያደርግ ዘርፉ ከማደግ ይልቅ እየቀጨጨ ነው፡፡  በጥናቱ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ የኢንዱስትሪ አንቀሳቃሾች በተሰባሰበ መጠይቅ፣ለህትመት ኢንዱስትሪው የሚደረግ የመንግስት ድጋፍ 0 % መሆኑ ተመላክቷል፡፡ መንግስት በሁለቱም የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዶቹ ኢንዱስትሪውን በተመለከተ ያስቀመጠው እቅድ፣ ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል ብለዋል - ጥናት አቅራቢው፡፡ የህትመት ኢንዱስትሪው ትልቁ ተግዳሮት፣ ተደራራቢ ታክስ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡ በንጉሡ፣ በደርግና በአሁኑ መንግስት በህትመት ኢንዱስትሪው ላይ የታዩ ለውጦች በጥናቱ የተዳሰሱ ሲሆን በንጉሡ ዘመን የተሻለ የህትመት ኢንዱስትሪ መስፋፋት ታይቶ ነበር ተብሏል፡፡ በተለይ እንደ ማክሚላን ቡክስ፣ ኦክስፎርድ የመሳሰሉ የውጭ ትላልቅ የህትመት ኩባንያዎች በኢንዱስትሪው ተሳታፊ የነበሩ መሆናቸው መልካም አጋጣሚ እንደነበር በጥናቱ ተጠቁሟል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ለ3 የግል ቴሌቪዥንና ለ3 የኤፍኤም ሬዲዮ ፈቃድ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለሁለት “ሴት ቶፕ ቦክስ” አምራቾች፣ ለሦስት የግል ቴሌቪዥንና ለሦስት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስተር ድርጅቶች ፈቃድ ሰጠ፡፡  ባለፈው ረቡዕ በሸራተን አዲስ በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት፣ “ሴት ቶፕ ቦክስ” ለማምረት ከባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ዘርዓይ አስገዶም ጋር የተፈራረሙት ጣና ኮሙኒኬሽን ኃ.የተ. የግ.ማ እና ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሃይቴክ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ናቸው፡፡ የግል የቴሌቪዥን ብሮድካስት ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስት ድርጅቶች፡- ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ኃ.ተ. የግ.ማ ናቸው፡፡ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ብሮድካስቲንግ ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስት ድርጅቶች ደግሞ ኤዲስቴለር ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ (አሐዱ 94.3)፣ አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስና ዋን ላቭ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ኃ.የተ. የግ.ማ (ሉሲ 107.8) ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ናቸው፡፡ በዕለቱ የተሰጠው ሦስት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ፈቃድ፣ አሁን በአዲስ አበባና አካባቢያዋ አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ሰባት ጣቢያዎች ጋር ቁጥር ወደ 10 እንደሚያደርሰው ታውቋል፡፡ “ሴት ቶፕ ቦክስ” ማለት አሁን ያለው አናሎግ የቴሌቪዥን ስርጭት ወደ ዲጂታል ሲቀየር ስርጭቱን መቀበል የሚያስችል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“በእርቀ ሰላም በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ የተደረገው ጥረት ከሽፏል”

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበሩን ተከትሎ፣ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ የተደረገው ጥረትና መንግስት ተገዶ ወደ እርቀ ሰላም እንዲገባ በማድረግ፣ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ የተደረገው ጥረት መክሸፉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጌታቸው አምባዬ አስታወቁ፡፡ አዋጁ ያስፈለገበትን ምክንያትና እስካሁን ያለውን አፈፃፀም ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ከትናንት በስቲያ በስፋት ያብራሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ፤ አዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ በአገሪቱ ላይ መረጋጋት እየተፈጠረ፣ የሰዎች ደህንነትና ቁሳዊ ሀብቶች ከውድመት እየተጠበቁ ነው ብለዋል፡፡ በተቃውሞ ወቅት በጦር መሳሪያ የታጀቡ ትንንሽ ቡድኖች ራሳቸውን በማደራጀት፣ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ፊት ለፊት ፍልሚያ የጀመሩበት ሁኔታ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጌታቸው፤ ሀገሪቱ የበለጠ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ በማሰብ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጁ ሀገሪቱ የተጋረጠባትን ስጋት እየቀለበሰ ነው ብለዋል፡፡ በኢሬቻ በአል ላይ የተፈጠረውን ግጭትና የህይወት መጥፋት ተከትሎ ከበአሉ የተበተነው ኃይል፣ በአዲስ አበባ  ዙሪያ ባሉ ከተሞች ሰፍሮ እንደነበር የገለፁት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ፤ የተለያዩ ቡድኖችን በማደራጀት ሃዋሳን፣ አዳማንና አዲስ አበባን ወደ መሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች እንዲገቡ ጥረት ሲደረግ ነበር ብለዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢንተርኔት መቋረጥ ዲቪ የሚሞሉትንም አስቸግሯል

ኢትዮ ቴሌኮም “ከደንበኞቼ ቅሬታ አልደረሰኝም” ብሏል    በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ የኢንተርኔት ካፌ ከፍቶ መስራት ከጀመረ 7 ዓመታት ያስቆጠረው ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ወጣት፤ በየዓመቱ በዚህ ወቅት የአሜሪካን ዲቪ ሎተሪ በማስሞላት ዳጎስ ያለ ገቢ ያገኝ እንደነበር ይናገራል፡፡ ዘንድሮ ግን በከተማዋ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ፣ የተለመደውን አገልግሎት ለደንበኞቼ መስጠት እንዳልቻለ ይገልፃል፡፡ በአማራጭነት የዋይ ፋይ አገልግሎት መስጫ ቢኖረውም በአግባቡ የሚሰራ ባለመሆኑ፣ እንኳን ዲቪ ለማስሞላት ይቅርና  የኢንተርኔት አገልግሎት በቅጡ ለመስጠት አዳግቶኛል ብሏል፡፡የኢንተርኔት አገልግሎት በመስጠት ብቻ በቀን በአማካይ ከ300-500 ብር ገቢ ያገኝ እንደነበር የሚናገረው የኢንተርኔት ካፌ ባለቤት፤ የኢንተርኔት መቋረጥ የሥራ ዘርፉን እንዳስቀየረው ይናገራል። “የኮምፒውተር ፅሁፍ፣ መጠረዝና፣ የፎቶ ኮፒ ስራዎችን ብቻ ለመስራት ተገድጄአለሁ” ብሏል። በየአመቱ ጥሩ ገቢ ያስገኝለት የነበረው ዲቪ የማስሞላት ስራም በኢንተርኔት መቋረጥ ሳቢያ መስተጓጎሉን ገልጿል፡፡  የዲቪ አመልካቾች በኢንተርኔት መቋረጥ የገጠማቸውን ችግር በተመለከተ ለአሜሪካ ኤምባሲ ላቀረብነው ጥያቄ፤ ችግሩ ከዲቪ ማመልከቻ ድረ ገፁ ሳይሆን ከኢንተርኔት መንቀራፈፍና መቆራረጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል፡፡“አመልካቾች የ2018 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ማመልከቻን በኢንተርኔት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

1 ሺህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን እስር ቤት አመለጡ

- የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች እስረኞቹ እንዲያመልጡ ትብብር አድርገውላችዋል     በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ገብተዋል በሚል በደቡባዊ የመን በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩ 1 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ባለፈው ረቡዕ ሌሊት አምልጠው መጥፋታቸውን አንድ የአገሪቱ የደህንነት ሃላፊ ማስታወቃቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡በህገወጥ መንገድ ወደ የመን ገብተዋል በሚል ሻባዋ በተባለቺው የአገሪቱ ግዛት ውስጥ ታስረው ከነበሩትና ወደ አገራቸው ሊመለሱ ከተዘጋጁት 1 ሺህ 400 ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል አንድ ሺህ የሚሆኑት ባለፈው ረቡዕ ሌሊት እስር ቤቱን ሰብረው በመውጣት መጥፋታቸውን ዘገባው ገልጧል፡፡የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ስደተኞቹ እንዲያመልጡ ትብብር እንዳደረጉላቸው ተረጋግጧል ያለው ዘገባው፤ ስደተኞቹ በተቀናበረ መንገድ ካመለጡ በኋላም በተዘጋጀላቸው መኪና በቡድን በቡድን እየሆኑ በአቅራቢያ ወደሚገኙት ማሪብ እና ባይዳ የተሰኙ ግዛቶች መሄዳቸውን አስታውቋል፡፡ የየመን መንግስት ባለፈው ወር ብቻ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ገብተዋል በሚል ከ220 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ አገራቸው እንደመለሰ ያስታወሰው ዘገባው፤ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ጠቁሟል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

‹‹በጌዴኦ የደረሰው ችግር የብሔር ግጭት አይደለም››

(ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲን፤ የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ)   የችግሩ ምክንያት በዲላ የንግዱ ማኅበረሰብና የጌዴኦ ዞን ሕብረት ሥራ ዩኒየን መካከል የቦታ ይገባኛል ክርክር ነበር፡፡ ባለፉት ጊዜያት ፍ/ቤቱ አክራክሮ ውሳኔም አስተሳልፎ ወደ አፈፃፀም ሂደት ሊገባ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ቦታው ለዩኒየኑ ይገባል በሚል የተወሰኑ አካላት ማኅበረሰቡን አነሳስተው በንግዱ ማኅበረሰብ ላይ ጉዳት ደርሷል። የፍ/ቤቱን ውሳኔ መነሻ አድርጎ ነው ግጭቱ የተከሰተው፡፡ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረትም ወድሟል፡፡ 23 ሰዎች ሞተዋል፤ ቤት ንብረት የተቃጠለባቸውና የወደመባቸው አሉ፤ ጉዳቱ ሰፊ ነው፡፡ በዚሁ ሂደት መካከል ችግሩ ሲከሰት ደንግጦ ከቤቱ የወጣ፤ ቤትንብረቱ ሲቃጠል ከቤቱ የወጣ  ሰው አለ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የብሔር ግጭት ነው ይላሉ፡፡ ግን አይደለም፡፡ ጉዳቱ የደረሰው ከአካባቢው ብሔረሰብ ውጭ ብቻ አይደለም፡፡ ከአካባቢው ተወላጅ ሕይወቱ ያለፈ አለ፡፡ ስለዚህ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ብለን ነው መውሰድ የሚቻለው፡፡ የንግዱ ማኅበረሰብ ውስጥም የአካባቢው ተወላጆች አሉ፡፡ ንብረታቸው የወደመው የሁሉም ነው፡፡ ስለዚህ ግጭቱ የተወሰነ ብሔረሰብ ላይ በፍፁም ያነጣጠረ አይደለም፡፡ ለተጠቂዎቹ ቀድሞ የደረሰላቸውና ሕይወታቸውን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ነገ የኢ/ር ኃይሉ ሻወል መታሰቢያ ይደረጋል

የቀብር ስነ ስርአታቸው ባለፈው ማክሰኞ በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለተፈፀመው አንጋፋው ፖለቲከኛ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል በመኢአድ ፅ/ቤት በነገው እለት የመታሰቢያ ዝግጅት ይደረጋል። በመታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ የፓርቲ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችን ጨምሮ የስራ አጋሮቻቸውና ቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙ ከመኢአድ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ነገ እሁድ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው የመታሰቢያ ስነ ስርአት ላይ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል፤ በተለይ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ባበረከቱት አስተዋፅኦ ላይ ሶስት ምሁራን ፅሁፍ አቅርበው ውይይት ይደረጋል ብለዋል፤ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አደና ጥላሁን፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ የስነ ፅሁፍ ፕሮግራሞችም እንደሚካተቱና ከ200 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ ወጣ

- የሰዓት እላፊ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ቦታዎች አሁንም ይፋ አልተደረጉም- በሁከቱና ብጥብጡ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎችን  በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ እንደጥፋታቸው    መጠን እርምጃ የመውሰድ ሥራ ይሰራል - በስራ ማቆምና በቤት ውስጥ መቀመጥ አድማዎች ላይ ተሳታፊ መሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስቀጣል- በኢንተርኔት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ በአፍራሽ ተግባር ላይ ተሰማርተው የቆዩ በመሆኑ ገድቦ ማቆየቱ ተገቢ ነውየሰዓት እላፊ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ቦታዎች አሁንም ይፋ አልተደረጉም በሁከቱና ብጥብጡ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎችን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ እንደጥፋታቸው መጠን እርምጃ የመውሰድ ሥራ ይሰራል በስራ ማቆምና በቤት ውስጥ መቀመጥ አድማዎች ላይ ተሳታፊ መሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስቀጣል በኢንተርኔት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ በአፍራሽ ተግባር ላይ ተሰማርተው የቆዩ በመሆኑ ገድቦ ማቆየቱ ተገቢ ነው በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተነሳውን ተቃውሞና አመፅ ተከትሎ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የማስፈፀሚያ ደንብ  የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ማውጣቱ ተገለፀ፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የግል ማተሚያ ቤቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሳቢያ ጋዜጣ አናትምም አሉ

መንግስት ድርጊቱ ከአዋጁ መንፈስ ጋር አይገናኝም ብሏልየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ የግል ማተሚያ ቤቶች፤ ጋዜጣና መፅሄት አናትምም በማለታቸው ህትመታቸው መስተጓጎሉን የ “ኢትዮ ምህዳር” ጋዜጣ እና “የሀበሻ ወግ” መፅሄት አሳታሚዎች ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአጠቃላይ አቃቤ ህግ ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ሃይማኖት ከሃይማኖት፣ ብሄርን ከብሄር የሚያጋጩና አመፅና ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ፅሁፎችን ማተም፣ ማሳተምና ማሰራጨት ሊከለከል ይችላል መባሉን መነሻ በማድረግ የግል ማተሚያ ቤቶች በተለይ ፖለቲካ ነክ ፅሁፎች ያሉባቸውን ጋዜጦች አናትምም ማለታቸውን አሳታሚዎቹ ተናግረዋል፡፡ ዘወትር ቅዳሜ ታትሞ የሚወጣው ሳምንታዊው “የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ባለቤት አቶ ጌታቸው ወርቁ፤ ቀድሞ ጋዜጣው ይታተምበት የነበረውን ማተሚያ ቤት ጨምሮ ከ3 በላይ ማተሚያ ቤቶች አዋጁ እንዳስፈራቸው በመግለፅ፣ ለማተም ፍቃደኛ እንዳልሆኑላቸው አስረድቷል፡፡ አዋጁ ገና ዝርዝሩ ወጥቶ እንዳልፀደቀና ጋዜጣቸው በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚሰራ ሚዲያ መሆኑን በመግለፅ ማተሚያ ቤቶቹን ለማግባባት ሞክረው እንደነበር የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ ማተሚያ ቤቶቹ ግን ፍቃደኛ ሊሆኑ እንዳልቻሉ ገልፀዋል፡፡ ማተሚያ ቤቶቹ ጋዜጣውን አናትምም ማለታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ወዳሏቸው
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አሜሪካና ካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አሳስቧቸዋል

“ነፃና ትችት ያዘሉ ድምፆችን ማፈንና ማሰር በራስ ላይ ውድቀትን መጋበዝ ነው”   በቅርቡ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞና አመፅ     ተከትሎ መንግስት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በእጅጉ እንዳሳሰባትና አዋጁ በዚህ ሁኔታ ተፈፃሚ የሚሆን ከሆነ ለተቀሰቀሰው የፖለቲካ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እንደማያስችል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቁ፡፡ ቃል አቀባዩ ጆን ኪርቢ ከትናንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ መንግስት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች የማይጥስ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰርና የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋት ጨምሮ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን መገደብ፣ ህዝባዊ ስብሰባን መከልከል፣ የሰዓት እላፊ ገደብን መጣል  እንዲሁም የመናገር መብትን መገደብ የመሳሰሉ ተፅዕኖዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ የቃል አቀባዩ መግለጫ ያመለክታል፡፡ የተቃውሞ ሰልፈኞቹና የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ተገቢ የሆኑ ብሶቶች ማዳመጥና ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው ያለው መግለጫው፤ መንግስት የዜጎቹን መብት እንዲያከብር፣ ህገ-መንግስቱ ያረጋገጠውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅና የመደራጀት መብት እንዲያረጋግጥ እንዲሁም መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢ/ር ኃይሉ ሻውል በ80 ዓመታቸው አረፉ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መስራችና ፕሬዚዳንት እንዲሁም በ97 ምርጫ የቅንጅት ሊቀመንበር የነበሩት አንጋፋው ፖለቲከኛ ኢ/ር ሃይሉ ሻወል በ80 አመታቸው ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል አስክሬናቸው ዛሬ አዲስ አበባ የሚገባ ሲሆን፡፡ የቀብር ስነስርዓታቸው መቼ እንደሚፈፀም አልተወሰነም ተብሏል፡፡ ኢ/ር ሀይሉ ሻወል በ1997 ምርጫ ማግስት በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ታስረው ከተፈቱ በኋላ የጀርባና የእግር ህመምን ጨምሮ በተለያዩ ህመሞች ሲሰቃዩ እንደነበር ያስታወቀው ፓርቲያቸው፤ በተለይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ህመማቸው ፀንቶ በታይላንድ ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ትናንት እዚያው ታይላንድ አርፈዋል ብሏል፡፡ ኢንጀነር ኃይሉ በ1984 ዓ.ም የመላው አማራ አንድነት ድርጅትን (መአዕድ) ከፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ ጋር በመሆን ከመሰረቱ በኋላ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለ10 ዓመት መርተውታል፡፡ መአዕድ ወደ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት  በ1995 (መኢአድ) ከተቀየረ በኋላ እስከ 2005 ዓ.ም ለ10 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ማገልገላቸው ይታወቃል። በ1997 አራት ድርጅቶች ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የተሠኘውን ስብስብ ሲፈጥሩ ኢ/ር ሃይሉ ሊቀ መንበር በመሆን ከምርጫ ጋር ተያይዞ ለተለያዩ አለማቀፍ መገናኛ  ብዙሃን በሚሠጧቸው መግለጫዎች የሚታወቁ ሲሆን ከታሰሩት የቅንጅት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ተቃውሞ – ግጭት – እልቂት- ውድመት – ቀውስ

የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው- ትላንት በአርሲ - ኦጄ፣ ከ30 በላይ ሰዎች ሞተዋል    በኢሬቻ በዓል ላይ በደረሰው እልቂት በተቀሰቀሰው ቁጣ ምክንያት ሳምንቱን በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከፍተኛ ተቃውሞና ግጭት ተከስቶ የበርካቶች ህይወት ጠፍቷል፡፡ በትላንትናው ዕለት በአርሲ ነገሌና አርሲአጄ አካባቢ፣ በተከሰተ ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ “በክልሉ በዚህ ሳምንት የሞቱ ሰዎችን በተመለከተ የሚደርሱን መረጃዎች አስደንጋጭና እርስ በእርስ የማይጣጣሙ ናቸው” ያለው የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ የበለጠ ማጣራት “አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው ቁጥሩን ከመግለፅ እንታቀባለን” ብሏል፡፡ በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች በተነሳው ግጭት የሞቱ ሰዎችን አስመልክቶ ከክልሉ መንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ያገኘነው መረጃ፤ ከሰኞ ጀምሮ በተለያዩ ወረዳዎች በተፈጠሩ ሁከቶች የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የዜጎች ህይወት መጥፋቱን ቢገልፅም የሟቾች ቁጥርን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል፡፡ የቢሾፍቱ እልቂት የቀሰቀሰው ቁጣ፤ በምዕራብ ጎጂ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሆሮጉድሩ፣ ጊምቢ፣ በጅማ፣ በቦረና ያቤሎ፣ በቡሌ ሆራ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በአምቦ፣ ወሊሶ፣ በዝዋይ፣ በአርሲ -ነገሌና አርሲአጄ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ውስጥ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በተቃውሞ በቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል

“ለደህንነታችን ዋስትና የሚሰጠን አካል የለም” ባለሀብቶች- “ቢሻን ጋሪ ሎጅ” ላይ በደረሰው ዘረፋና ቃጠሎ ፖሊስ ጥቃቱ እንዳይደርስ ከመከላከል ተቆጥቧል- ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ማዘጋጃ ቤቶችና የመንግስት ተቋማት ወድመዋልበኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት የተከሰተውን የበርካቶች ህልፈተ ህይወት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመፅ እያደረሰ ያለው የንብረት ውድመት ከመንግስት ጥበቃና ቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች በተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመፅ በቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር ንብረት ወድሟል ተብሏል፡፡ ሰሞኑን በቡራዩ፣ በሰበታ፣ በአዋሽ መልካሳ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በአለምገና እና ሌሎች የኦሮሚያ ክልሎች በተቀሰቀሰው ተቃውሞ፣ በሚሊዮኖች በሚቆጠር ገንዘብ የተቋቋሙ ፋብሪካዎች፣ የህዝብና የጭነት ማመላለሻ መኪኖች፣ የመንግስት ተቋማት፣ ፖሊስ ጣቢያዎችና የአበባ እርሻዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ በላንጋኖ አካባቢ በ100ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በተገነባው ቢሻን ጋሪ ሎጅ ባለፈው እሮብ በደረሰበት ዘረፋና ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋትም ሆነ ንብረቱን ከአደጋ ለመከላከል የተደረገ ሙከራ አለመኖሩ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው የድርጅቱ ባለቤት አቶ ዑመር ባገርሽ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡ ሎጁ ላለፉት 17
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የጀርመን መራሄ መንግስት ማክሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ

የጀርመን መራሄ መንግስት አንጌላ መርኬል ማክሰኞ አዲስ አበባን እንደሚጎበኙና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ከስደት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የፊታችን ዘግቧል፡፡ከሶስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር በስደትና ሽብርተኝነትን በመታገል ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ለማድረግ ያቀዱት መርኬል፤ ነገ ወደ ማሊ እንደሚያቀኑና ከዚያም በኒጀርና በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንደሚቀጥሉ የጠቆመው ዘገባው፤ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤትን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡አንጌላ መርኬል በአፍሪካ አገራት ለቀናት የዘለቀ ጉብኝት ሲያደርጉ ከአምስት አመታት ወዲህ የአሁኑ የመጀመሪያው እንደሚሆን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ኤክሰል አሬንጁስ” እና “ማርች ማንጎጁስ” ለጤና ጎጂ መሆናቸው ተገለጸ

ፓሲፊክ ኢንዱስትሪዎች ኃ.የተ.ማ የሚያመርታቸው “ኤክሰል አሬንጅ ጁስ”ና “ማርች ማንጎ ጁስ” ለጤና ጎጂ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ ባለሥልጣኑ ሰሞኑን ለዝግጅት ክፍላችን ለድርጅታችን በላከው ደብዳቤ፣ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት፤ ምርቶቹ ላይ በተደረገ የላቦራቶሪ ፍተሻ ለጤና ተስማሚ አለመሆናቸው በመረጋገጡ፣ ለኅብረተሰቡ ጤና ጎጂ መሆናቸውን ጠቁሞ፣ ድርጅቱ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ችግር ምርቱ ገበያ ላይ እንደይውል መደረጉንና ከገበያም እንዲሰበሰብ መደረጉን፣ አሁንም ተመሳሳይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አመልክቷል፡፡ አምራች ድርጅቱ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ምንም ዓይነት የብቃት ማረጋገጫ ያልተሰጠው በመሆኑ ምርቱ ተመርምሮ የሀገሪቱን የምግብ ደህንነትና የጥራት መስፈርት የማያሟላ፣ እንዲሁም ለጤና ጎጂና አደገኛ መሆኑን በማረጋገጥ እነዚህን ምርቶች ማንኛውም ሰው እንዳይጠቀም አበክሮ አሳስቧል፡፡ ባለሥልጣን መ/ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት፤ እነዚህን የተከለከሉ ምርቶች ሲሸጥ፣ ሲያጓጉዝ፣ ሲያከፋፍል የተገኘ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ እርምጃ እንደሚወስድና አጥፊዎቹን በሕግ የሚጠይቅ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ኅብረተሰቡ ይህን መሰል ሕገ-ወጥ ተግባራትና ማንኛውም ሕገ ወጥ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና አገልግሎቶች ሲያጋጥሙት፣ በአካባቢው ላለ የሕግና የጤና
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሦስት ዘርፎች መጻሕፍት ተወዳድረው ሊሸለሙ ነው

ኖርዝ ኢስት ኢንቨስትመንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚካሄድ ‹‹ሆሄ የኢትዮጵያ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት›› ፕሮግራም ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡የሽልማት ዝግጅቱ ዓላማ በሀገራችን የንባብ ባህል እንዲጎለብት ማስቻል፣ በየዓመቱ የሚታተሙ መጽሐፍትን እንዲተዋወቁና የተሻሉት ደግሞ በተሸላሚነት እውቅና እንዲያገኙ እንዲሁም በልጆች ንባብ ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ድጋፍ መስጠት ነው፡፡ የፈጠራ ፅሁፍ ስራዎቻቸውን ላበረከቱ ደራሲያንና ጸሐፍት እውቅና ከመስጠት ባለፈ የንባብ ባህል እንዲስፋፋ፣ በተፃፉ መፅሃፍት ላይ ህብረተሰቡ እንዲወያይባቸው ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ የንባብ ክበባት እንዲፈጠሩ እንዲሁም በየጊዜው የሚታተሙ መፅሀፍት ላይ ሂስና ትንታኔ በመስጠት ለመላው ህብረተሰብ የንባብ ትሩፋቶችን በማጋራት ለሚሰሩ ሀያሲያን የሽልማት ፕሮግራሙ እውቅና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ “ሆሄ የስነፅሁፍ ሽልማት” ፕሮግራም በዋነኛነት ሶስት የውድድር ዘርፎች የሚኖሩት ሲሆን እነዚህም የረጅም ልብ ወለድ መጻህፍት፣ የስነ ግጥም መድበሎችና የልጆች መጻህፍት ናቸው። ተወዳዳሪ መፃህፍት በዳኞች ኮሚቴ አማካይነት በተዘጋጀላቸው መስፈርቶች መሰረት የሚመዘኑ ሲሆን ውድድሩ በዳኞች ኮሚቴ ከሚሰጠው ውጤት በተጨማሪ በአንባቢያን ነፃ የስልክ መልእክትና በድረ ገፅ ኦን ላይን ከአንባቢያን የሚሰጠው ድምፅ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ውይይት በተቃውሞ ተቋረጠ

የትምህርት መጀመሪያ ቀን እስካሁን አልታወቀም      ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ዘግይቶ ከትላንት በስቲያ የተጀመረውና ለ5 ቀናት እንደሚካሄድ የተጠበቀው የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመምህራን ውይይት፤ ትላንት ሐሙስ ጠዋት በተቃውሞ የተቋረጠ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ጉዳይ መምህራኑ ውይይት አድርገዋል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል ከመስከረም 9 ጀምሮ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ውይይት፤ መምህራኑ በውይይቱ ሥፍራ ሳይገኙ በመቅረታቸው አለመካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በድጋሚ በዩኒቨርሲቲው በወጣ ማስታወቂያ መሰረት ውይይቱ ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 24 እንደሚካሄድ ተገልፆ ነበር፡፡ ሁሙስ እለት የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል፤ “የሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት” በሚል ርዕስ ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ የመድረክ መሪውን የመነሻ ፅሁፍ ተከትሎ መምህራን በሶስት አዳራሽ ተከፋፍለው በቡድን ውይይት  እንዲያደርጉ ቢሞከርም፣ በሁለቱ አዳራሾች የነበሩ መምህራን ራሳቸውን ከንግግር በማቀባቸው ውይይቱ ተበትኗል፡፡ በሌላኛው አዳራሽ ከነበሩ መምህራን አንደኛው ድንገት ተነስቶ፤ ‹‹ሰው እየተገደለ፣ ንብረት እየተቃጠለ ምን እንድንል ነው የምትፈልጉት?›› የሚል ዱብ ዕዳ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን የመድረኩ መሪ ንግግሩን ውይይቱ መበተኑ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ለአዲስ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የጋዜጦች የማተሚያ ቤት ችግር እስከ መስከረም 30 ይዘልቃል

ሳምንታዊ የግል ጋዜጦች ከማተሚያ ቤት ችግር ጋር በተያያዘ ከሚወጡበት መደበኛ ቀናቸው እስከ 5 ቀን ዘግይተው እየወጡ ሲሆን ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፤ የጋዜጦችን ዘግይቶ የመውጣት ችግር ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ነኝ ብሏል። ችግሩን ለመፍታት የጋዜጣ አሳታሚዎች እስከ መስከረም 30 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲታገሱትም ጠይቋል-ማተሚያ ቤቱ፡፡ “አዲስ አድማስ” ን ጨምሮ ቅዳሜ ለአንባቢያን መድረስ የነበረባቸው ጋዜጦች እሁድ መውጣት የጀመሩ ሲሆን የእሁድ ሳምንታዊ ጋዜጦች እስከ 4 እና 5 ቀናት እየዘገዩ እንደሚወጡ የገለፁት አሳታሚዎች፤ መዘግየቱ ከማስታወቂያ ደንበኞቻቸው ጋር ቅራኔ ውስጥ እየከተታቸው መሆኑን ጠቁመው ለአንባቢያን በጊዜና በሰአቱ መድረስ ያለባቸው መረጃዎችም እየዘገዩ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተካ አባዲ፤ ጋዜጦች ለምን በዕለታቸው እንደማይወጡ ከአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ ‹‹ማተሚያ ቤቱ በ22 ሚሊዮን ብር የገዛውና በሰአት እስከ 20 ሺህ ኮፒ ጋዜጦች የማተም አቅም ያለው ዘመናዊ ማሽን የቴክኒክ እክል ስለገጠመው ነው›› ብለዋል፡፡ ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት ድርጅቱ ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ ተካ፤ ማሽኑ ወደ ሀገር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሳምንቱ በኦሮሚያ 4 ወጣቶች መገደላቸውን ኦፌኮ አስታወቀ

ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የኦሮሚያ ወረዳዎች የ4 ሰዎች ህይወት በፀጥታ ኃይሎች ማለፉን ኦፌኮ ገለፀ፡፡ በነቀምት ላይ አንድ ወጣት መገደሉንና በምዕራብ መንዲ ወረዳ በመስቀል ደመራ ላይ የ15 ዓመት ታዳጊ መገደሉን የገለፀው ኦፌኮ፣ ነጆ በምትባል ከተማም አንድ ሰው ተገድሎ 5 ሰዎች በጥይት እንደቆሰሉ ጠቁሟል፡፡ በምዕራብ አርሲ አጄ፣ አንድ ሰው መሞቱን የተናገሩት የኦፌኮ ም/ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ፤ የማስፈራራትና ማዋከብ ዘመቻም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ የኦህዴድ ሊቀ መንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ለማ መገርሳ፤ ከህዝብ ጎን እንደሚቆሙና ሰላም እንደሚፈጥሩ ቃል መግባታቸውን የጠቀሱት አቶ ሙላቱ፤ ይህ በተባለ ማግስትም በሰው ህይወትና አካል ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ካልቆሙ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡ ከክልሉ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች አቡነ አብርሃምን አነጋገሩ

በባህርዳር ከተማ መስቀል አደባባይ በተካሄደው የደመራ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙትና የሰሞኑ አገራዊ የመወያያ አጀንዳ የሆኑት የባህርዳር ምዕራብ ጎጃም አዊና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አቡነ አብርሃምን የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ከትናንት በስቲያ አነጋገሯቸው፡፡ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሰረት፤ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ከሆኑት የመንግስት ባለስልጣናት መካከል የፌደራል አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃንና በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ህላዊ ዮሴፍ ናቸው፤ ጳጳሱን ያነጋገሩዋቸው፡፡ የንግግራቸው አጀንዳም በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይና መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሆነም ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በባለስልጣናቱና በአቡነ አብርሃም መካከል የተካሄደውን ውይይት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ባንችልም፣ ባለስልጣናቱ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መንግስት ምን ማድረግ እንደሚገባው አባታዊ ምክራቸውን እንዲሰጡ አቡነ አብርሃምን መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በባህርዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ላይ በተከናወነው የደመራ በአል ላይ ለምዕምኑ ንግግር ያደረጉት አቡነ አብርሃም፤ ‹‹የምናገረው ፖለቲካ አይደለም፤ እንደዛ ነው የሚል እንደፈለገ ይተርጉመው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ችግር የሚፈጠረው በመሪ እንጂ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡ ወታደሩ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የምሁራኑ ውይይት በባህርዳርና በጎንደር ዩኒቨርስቲዎች እክል ገጠመው

በዲላ ዩኒቨርስቲ ‹‹የህሊና ፀሎት›› ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም   በአገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መንግስት ከመምህራን ጋር እያካሄደ ያለው ውይይቶች በተቃውሞና በውዝግብ የታጀቡ ሆነዋል፡፡ በጎንደርና በባህርዳር ውይይቱ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት አለመካሄዱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡መስከረም 4 በተጀመረው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የመምህራን ውይይት ለ2 ቀናት ብቻ ብቻ የተሳተፉ አንድ መምህር፤ እንደገለፁልን፤ መምህራኑ ተቀምጦ ከማዳመጥ ባለፈ ጥያቄም ሆነ አስተያየት በቀጥታ ማቅረብ አትችሉም መባላቸውን ተከትሎ ቅሬታዎች ተፈጥረው ነበር፡፡ በትግራይ ክልል ም/ርዕሠ መስተዳደር ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ አጋፋሪነት በተመራው ውይይት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው በየኮሌጆቹ ተወካዮች በኩል እንጂ መምህራን በቀጥታ ማቅረብ ተከልክለው ነበር።  የሚሉት መምህሩ፤ ጥያቄዎች ለኮሌጅ መሪዎች ከተሰጡ በኋላ ተጨምቆ ለመድረክ ይቀርብ ነበር ብለዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው ስብሰባው ላይ ተሳታፊ የነበሩ አንዳንድ ያነጋገርናቸው  መምህራንም በቀሪ መቆጣጠሪያ መዝገብ ላይ እየፈረሙ ወጣ ገባ ከማለት በስተቀር ውይይቱን በአግባቡ እንዳልተከታተሉ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪና የዲላ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል ሰብሳቢነት ከመስከረም 5 ጀምሮ እስከ ትናንት በተካሄደው ስብሰባ ላይ እንደ አዲስ አበባ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

‹‹ማልታ ጊነስ›› የ‹‹ስኬት ቦርድ›› ውድድር አካሄደ

ማልታ ጊነስ በአይነቱ ልዩ የሆነ የስኬት ቦርድ ውድድር ሰሞኑን በአዲስ ስኬት መዝናኛ ውስጥ አካሄደ፡፡ በ15 ተወዳዳሪዎች መካከል የተካሄደው የስኬት ቦርድ ውድድር፤ በአገራችን አምብዛም ያልተለመደውን የስኬት ስፖርት በስፋት እንዲለመድና ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለማፍራት የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል። ከአልኮል ነፃ በሆነው የማልታ ጊነስ ምርት ታጅቦ በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ከ1-3 የወጡ ተወዳዳሪዎች የማልታ ጊነስ ምርት አምራች በሆነው ዲያጆ ኢትዮጵያ የተዘጋጀላቸውን ሽልማቶች ተቀብለዋል፡፡ ውድድሩ በራሳቸው የሚታማመኑና ብቃት ያላቸው የስኬት ቦርድ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል የማልታ ጊነስ ብራንድ ማናጀር አቶ አቤል አናጋው በውድድሩ ወቅት ተናግረዋል፡፡ በዚሁ የስኬት ቦርድ ስፖርት ውድድር ወቅትም ዲያጆ ኢትዮጵያ ለአዲስ ስኬት ፓርክ የ50ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ተቃዋሚዎች፤ የባለስልጣናት ለውጥ የህዝብ ጥያቄን አይመልስም አሉ

‹‹የህዝቡ ጥያቄ የስርአትና የፖሊሲ ለውጥ ነው››   በተሃድሶ ግምገማ ላይ ከሚገኙት አራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች ኦህዴድ ሊቀመናብርቱን ሰሞኑን ከሃላፊነት ያነሰ  ሲሆን  ተቃዋሚ ፓርቲዎች  በየትኛውም ደረጃ የሚደረጉ የአመራር ለውጦች ለህዝብ መሰረታዊ ጥያቄ ምላሽ አይሆኑም ብለዋል፡፡ህዝብ የጠየቀው የስርዓትና የፖሊሲ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች መቀያየርን አይደለም፤ ይላሉ ተቃዋሚዎች፡፡የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፤ የገዥውን ፓርቲ ተሃድሶ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አስተሳሰቦች የተካተቱበት የፖሊሲ ለውጦች ነው የጠየቅነው ብለው፡፡ አሁን  ባለው ፖሊሲ ላይ ግለሰቦችን መለዋወጥ ተሃድሶ እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡ ‹‹የህዝቡ ጥያቄም የአመራሮች መለዋወጥ›› አይደለም ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ ተሃድሶው በዚህ መልኩ ከቀጠለ ምንም ለውጥ አያመጣም፤ የህዝቡንም ጥያቄ በዚህ መንገድ መመለስ አይቻልም ብለዋል፡፡ በኦሮሚያ የኦህዴድ አመራሮች መቀያየራቸው ሌሎቹ ድርጅቶችም ከዚህ የተለየ አጀንዳ እንደሌላቸው ያሳያል፡፡ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በኢዴፓ እምነት ይህ አካሄድ የበለጠ የህዝበን ጥያቄ የማፈኛ መንገድ ነው ብለዋል፡፡ አዴፓ አሁንም ብቸኛው መፍትሄ የብሄራዊ እርቅ መድረክ ማዘጋጀት ነው የሚል አቋም እንዳለውም ዶ/ር ጫኔ ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያም ቢሆን ህዝብ የአመራር ለውጥ አልጠየቀም ያሉት የሠማያዊ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በጎንደርና በባህርዳር የቤት ውስጥ አድማ ሲደረግ ሰንብቷል

በአማራ ክልል በተለይ በጎንደርና  በባህርዳር ከተሞችና በአካባቢያቸው ባሉ ወረዳዎች ሠሞኑን ከቤት ያለመውጣት አድማ ሲደረግ መሠንበቱን የጠቆመው መኢአድ፤ በሌላ በኩል ወጣቶች በፀጥታ ሃይሎች እየተለቀሙ መታሠራቸው አስታውቋል፡፡ የፓርቲው ዋና ፀሃፊ አቶ ኪዳነ በጎንደር ከሠኞ መስከረም 9 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ አንድም የንግድ ተቋም ሳይከፈት የቤት ውስጥ አድማ ሲደረግ መሰንበቱንና በደብረታቦር  ማክሰኞ አድማው የተደረገ ቢሆንም በሃይል ህዝቡ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ነዋሪዎችም ደብረታቦር መታሰራቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጋይንት፣ ንፋስ መውጫ፣ ሊቦ ኮምኮምና አዲስ ዘመን በተባሉ የጎንደር ከተሞችም እስከ ትናንት ድረስ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል ተብሏል፡፡ ባህርዳር  እስከ ሃሙስ እለት የንግድ መደብሮች ዝግ ቢሆኑም የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት አልተቋረጡም ብለዋል ዋና ፀሃፊው፡፡ በወገራና ኮሶዬ በተባሉ ወረዳዎች ሠሞኑን የፀጥታ ሃይሎች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መጋጨታቸውን መኢአድ አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል፤ በባህርዳርና በወልቂጤ ዩኒቨርስቲዎች በተደረጉ የመምህራን ስብሰባዎች ለመንግስት ሃላፊዎች ጠንካራ ጥያቄዎች እንደቀረበላቸው መኢአድ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በኮንሶ አካባቢ የተከሰተው ቀውስ አለመረጋጋቱን የጠቆመው መኢአድ፤ በአካባቢው ሰዎች
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢሬቻ በአል ከፖለቲካ ነፃ እንዲሆን ኦፌኮ አሳሰበ

የኩሽ ህዝቦች በተለይም አሮሞዎች ፈጣሪያቸውን በሚያመሠግኑበት ሃይማኖታዊና ባህላዊ የኢሬቻ ስነስርአት ላይ ማናቸውም የፖለቲካ ሃይሎች ከዋዜማው ጀምሮ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ የኦሮም ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አሣሠበ፡፡መስከረም 22 የሚከበረው የኢሬቻ በአል የራሱ ሃይማኖታዊ ባህልና የአከባበር ስርአት እንዳለው በመግለጫው የጠቀሰው ኦፌኮ፤ የተለያዩ አካላት በዋዜማው ‹‹የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ›› እና ሌሎች ከባህሉ ጋር የማይገናኙ ፕሮግራሞችን ለማካሄድ ማቀዳቸው ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡ በአሉ የምስጋና ቀን በመሆኑ በመልከ መውረጃ መንገዶች ላይ የኪነት ቡድን አደራጅቶ ማስጨፈር፣ የፖለቲካ ንግግር ማድረግ የመሣሰሉትን ፓርቲው እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡ በአሉ ከፖለቲካም ሆነ ባህሉን ከሚፃረር ማንኛውም ድርጊት ነፃ እንዲሆንና የህዝብ በአልነቱ እንዲከበር አሳስቧል ኦፌኮ፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ወጋገን ኮሌጅ ዛሬ ተማሪዎቹን ያስመርቃል

ወጋገን ኮሌጅ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአካውንቲንግ፣ በፊልምና በቴአትር ጥበባት ያሰለጠናቸውን 120 ተማሪዎች ዛሬ ቦሌ አሮሚያ ታወር ላይ በሚገኘው ሰራዊት ሲኒማ አዳራሽ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃል፡፡ ኮሌጁ ከተቋቋመበት ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ሲያሰለጥን የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ የሚያስመርቅ መሆኑን የኮሌጁ ሬጅስትራር ኦፊሰር ወ/ሪት ሀመልማል በላይ አሞኘ ለአዲ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ወጋገን ኮሌጅ በ2008 የበጀት ዓመት የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 66 ያህል የግል ኮሌጆች መካከል የሰልጣኞቹን የብቃት መረጋገጫ ውጤት 81 በመቶ በማምጣት ለ2009 ዓ.ም የእውቅና ፈቃዳቸውን ካደሱ 12 ኮሌጆች የመጀመሪያው ሆኖ ማለፉንም ወ/ሪት ሀመልማል ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ኮሌጁ ዛሬ በሚያስመርቃቸው ሰልጣኞች የምረቃ በዓል ላይ የዩኒቨርስቲ ምሁራን፣ ታዋቂ የኪነ- ጥበብ ባለሞያዎች የተመራቂ ቤተሰቦችና የኮሌጁ ማህበረሰቦች እንደሚታደሙም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ሠማያዊ ፓርቲ ያቀደው ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ መደናቀፉን ገለፀ

አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በነገው እለት በመኢአድ ፅ/ቤት ግቢ ሊያከናውን ቀጠሮ ይዞ የነበረው ሠማያዊ ፓርቲ፤ ከህግ አግባብ ውጪ በምርጫ ቦርድ ጉባኤውን እንዳያካሂድ መከልከሉን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ፤ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ የነበረበትን የውስጥ ፓርቲ ችግር ለመፍታት አቅዶ እንደነበር ጠቅሶ፤ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት፤ ‹‹በፓርቲው ላይ የሚጣሩ ጉዳዮች በመኖራቸው የጉባኤው ቀን እንዲራዘም›› በሚል የማሳሰቢያ ደብዳቤ መላኩን አመልክቷል፡፡ የምርጫ ቦርድ ሃላፊነት ተወካይ በመላክ ሂደቱን መታዘብ እንጂ የጉባዔ ቀን መወሠን አለመሆኑን የጠቀሰው ፓርቲው፤ ጉባኤው በዚህ ምክንያት ከመደናቀፉ ባሻገር ለጉባኤው ፓርቲው ያወጣቸው ወጪዎች ለኪሣራ እንደዳረገው አስታውቋል፡፡ ለደረሰው ኪሣራም ፓርቲው ምርጫ ቦርድን በህግ እንደሚጠይቅ አስታውቆ፤ የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል ጌትነትና  ሌሎች አካላት ጉባኤውን ከማደናቀፍ ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡ ጉባኤውንም በቅርቡ በድጋሚ እንደሚጠራም የፓርቲው ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሠጡን የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ፤ ‹‹የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ለማሠናከል አይደለም፤ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ይልቃል ጌትነት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኮንሶ ቀውስ

“ጥያቄያችን በኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል” አቶ ገመቹ ገንፌ፤ - የኮንሶ ኮሚቴ አባል“ጥያቄው የህዝብ ሳይሆን የጥቂቶች ነው” - የክልሉ መንግስት    ከኮንሶ የዞንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት የበርካቶች ህይወት ጠፍቶና በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለው ዜጎች የተፈናቀሉሲሆን የኮንሶ ህዝብ ኮሚቴ፤ ጥያቄያችን ወደ ኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል ብለዋል፡፡ በአካባቢው እስከ ትናንት ድረስ ግጭቶች መቀጠላቸውንና የታጠቁ የመንግስት ኃይሎች የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የኮንሶ ኮሚቴ አባል አቶ ገመቹ ገንፌ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን በሰሞኑ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና አስክሬናቸው እስከ ትናንት ድረስ ለቤተሰብ እንዳልተሰጠ ተገናግረዋል። የደቡብ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ አይረዲን በበኩላቸው፤ ግጭቱን ያስነሱትና በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉት የኮሚቴው አባላት ናቸው ይላሉ፡፡ “የፀጥታ ኃይሉ ጥፋቱ ከደረሰ በኋላ ነው ህዝቡን ለመታደግ ወደ አካባቢው የገባው፤ በአሁን ወቅት ግን በኮንሶ ምንም ግጭት የለም፤ ሰላማዊ ነው”፤ ብለዋል ኃላፊዋ፡፡ የኮሚቴው አባል አቶ ገመቹ፤ ጥያቄያችን በፌደሬሽን ምክር ቤት ተቀባይነት ካላገኘ በሪፈረንደም ወደ ኦሮሚያ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአገሪቱ ምሁራን የት ገቡ? ፍርሃት?…አድርባይነት?… ከሃላፊነት መሸሽ??

ባለፈው ዓመት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሱት ተቃውሞዎች ወደ ግጭትና የፖለቲካ ቀውስ ሲሻገሩ ነበር አዲስ አድማስ የመፍትሄ ሃሳቦችን ከተለያዩ ወገኖች ማሰባሰብ የጀመረችው፡፡  ባለፉት ጥቂት ወራት የሃይማኖት መሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የተለያዩ ዕውቅ ኢትዮጵያውያንን አነጋግረን ለፖለቲካ ቀውሱ መፍትሄ ነው የሚሏቸውን ሃሳቦች ስናስተናግድ ቆይተናል፡፡የአገሪቱ ምሁራንም በችግሮቹ ዙሪያ ሀሳባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫ ይሰጡን ዘንድ ጥረት ብናደርግም ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ ከሶስት ምሁራን ውጭ አብዛኞቹ “ትንሽ ይቆየን፤ አሁን ይለፈን” በሚል ራሳቸውን አግልለዋል፡፡ ምሁራን በአገራቸው እንዲህ ያለ ፖለቲካ ቀውስ ተከስቶ፣ ለምን ራሳቸውን አገለሉ? ብዙዎች ፍርሃት ስላለባቸው ነው በሚለው ይስማማሉ፡፡ አገር በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ስትገባ፣ ምሁራን ቀዳሚ ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚናገሩት ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፤ ምሁራኑ ከማንም በፊት ለህዝብ መቆም አለባቸው ይላሉ፡፡ ችግሩ ግን በፍርሃት ተቀፍድደዋል ባይ ናቸው፡፡ በየትኛውም አገር ለህዝብ መብቶች በመታገል ጉልህ ሚና የሚጫወቱት ምሁራን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ሚዲያው እንደሆኑ የሚናገሩት ፕሮፌሰሩ፤ ሦስቱም ግን በፍርሃት ተሸብበዋል ይላሉ፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ፅሁፍ መምህሩ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራም የፕሮፌሰሩን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የግል ት/ቤት መምህራን በስልጠናው አልተካፈሉም

የስልጠናው ዋነኛ አጀንዳ ፌደራሊዝም ነው      በአገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 4 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት ለመምህራን ሊሰጥ የታሰበው ስልጠና ውዝግብ አስነሳ፡፡ የግል ት/ቤት መምህራን ስልጠናው ከሙያቸው ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ ከመሆኑም በላይ ለመንግስት ት/ቤቶች መምህራን የሚሰጠው የአበል ክፍያ የማይታሰብላቸው በመሆኑ ስልጠናውን አንካፈልም በማለት ጥለው ወጥተዋል ተብሏል፡፡ ሰሞኑን ተዘዋውረን ባየናቸው የግል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ መምህራኑ ስልጠናውን ለመካፈል የማይፈልጉ መሆናቸውን በመግለፅ አቋርጠው ወጥተዋል፡፡ በባሸዋም አንደኛ ደረጃና የፕሪፓራቶሪ ት/ቤት ውስጥ ስልጠናውን ለመካፈል ተሰባስበው የነበሩ የአምስት የግል ት/ቤቶች መምህራን፤ ስልጠናውን ለመካፈል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ተበትነዋል፡፡ ለመምህራኑ ስልጠናውን ለመስጠት በሥፍው ለተገኙት የመንግስት ተጠሪ፤ ስልጠናውን የሚካፈሉት ለመንግስት መምህራን የተሰጠው የአበል ክፍያ ለእነሱም ሲታሰብ መሆኑን በመግለፅ ስልጠናውን አንሣተፍም ብለዋል፡፡ የመንግስት ተጠሪዋ ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመግለፅ፤ የግል ት/ቤቶች መምህራን የአበል ክፍያውን ከየትምህርት ቤቶቻቸው ያገኛሉ ተብሎ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “ስልጠናው ባይኖርም ሥራ ላይ መሆናችሁ አይቀርም ነበር፡፡ ስለዚህም አበል ሊከፈላችሁ አይገባም” መባላቸውን የሚናገሩት መምህራኑ፤ ከሥራችን ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሳምንቱ ከ11 ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ገብተዋል

ከ292 ሺህ በላይ የአገሪቱ ስደተኞች በኢትዮጵያ ይገኛሉ      ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ11 ሺህ በላይ የሚሆኑ ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች በጋምቤላ ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው ግጭትና ውጥረት በርካታ ዜጎች አገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት አገራት እንዲሰደዱ እያስገደዳቸው ነው ያለው ኮሚሽኑ፤ ባለፈው ሳምንት በስደት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከ11 ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳናውያን በኢትዮጵያ የሚገኙ የአገሪቱ ስደተኞችን ቁጥር ከ292 ሺህ በላይ እንዳደረሱት አስታውቋል፡፡አብዛኞቹ ስደተኞች ናስር፣ ማባን፣ ማቲያንግና ማዩት በተባሉት የደቡብ ሱዳን አካባቢዎች የተጠናከረ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በማየታቸውና አዲስ ግጭት ይከሰታል ብለው በመስጋት ስደትን የመረጡ ደቡብ ሱዳናውያን እንደሆኑም አስረድቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በጋምቤላ ክልል ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች፤ አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው ያለው ኮሚሽኑ፣ ብዙዎቹም የኑዌር ጎሳ ተወላጆች እንደሆኑና 500 ያህሉ ስደተኞች ያለ ወላጅ ብቻቸውን ስደት የወጡ ህጻናት እንደሆኑ ገልጧል፡፡በደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ሳቢያ ወደ ጎረቤት አገራት የተሰደዱ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር ከአንድ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያዊው ኢኮኖሚስት የአይኤምኤፍ የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆኑ

የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስቲያን ላጋርድ፣ ኢትዮጵያዊውን ኢኮኖሚስት አቶ አበበ አእምሮን የተቋሙ የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ተቋሙ ከትናንት በስቲያ በድረ-ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ ላለፉት 22 አመታት በአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የሰሩት አቶ አበበ አእምሮ በተቋሙ፣ በነበራቸው ቆይታ፣ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን የገለጸው ተቋሙ፤ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ባከናወኗቸው ውጤታማ ተግባራት የካበተ ልምድ እንዳላቸውም ጠቁሟል፡፡“አቶ አበበ በተቋሙ በነበራቸው ቆይታ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ከአህጉሪቱ ፖሊሲ አውጪዎች ጋር በቅርበት ሲሰሩ እንደመቆየታቸው የአፍሪካን ፈተናዎች በተመለከተ ጥልቅ ግንዛቤ አላቸው፡፡ በአመራር፣ በማስተባበርና በሌሎች መስኮች ያላቸውን ብቃት በተግባር ማረጋገጣቸው ለዚህ የስራ ሃላፊነት እንዲመረጡ አድርጓቸዋል” ብለዋል የተቋሙ ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ ክርስቲያን ላጋርድ፡፡አቶ አበበ አእምሮ በተቋሙ ቆይታቸው፣ የአፍሪካ ክፍል የኡጋንዳ ከፍተኛ ተወካይና የደቡብ አፍሪካ ተልዕኮ ሃላፊ ሆነው ከመስራታቸው በተጨማሪ የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ትንበያን ጨምሮ በኮትዲቯር፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያና ሴራሊዮን በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ስኬታማ ስራ ማከናወናቸውንም ተቋሙ አስታውቋል፡፡በተቋሙ የስትራቴጂ፣ ፖሊሲና ግምገማ ክፍሎች በተለያዩ ሃላፊነቶች ላይ በነበራቸው የስራ ቆይታ የአመራር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ለዓመት በዘለቀ ተቃውሞ ከ1ሺ በላይ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል

በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ቃጠሎ 40 ሰዎች ሞተዋልበኢህአዴግ የሚመራው መንግስት የዘንድሮውን ያህል ህዝባዊ ተቃውሞ ደርሶበት አያውቅም ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ህዳር ወር የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም የተነሳው ተቃውሞ ማስተር ፕላኑ መሰረዙን መንግስት ቢያስታውቅም ተቃውሞው ግን አልበረደም። በርካታ የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ ወጣቶች የሚበዙባቸው የተቃውሞ ጎርፎች የኦሮምያ ጎዳናዎች አጥለቀለቁት፡፡  ከ10 ወራት በላይ በዘለቀው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞና ግጭት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ብዙ ሺዎችም ለእስር እንደተዳረጉ የተለያዩ ሪፖርቶች ጠቁመዋል፡፡በአማራ ክልለ ህዝባዊ ተቃውሞዎቹ ከ3 ወር የማይበልጥ ዕድሜ ቢኖራቸውም በእጅጉ የተጠናከሩና በህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ናቸው፡፡የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን መረጃ መዝግቦ መያዙን የገለፁት የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን፤ በአማራ ክልል ውስጥ እስከ ሐሙስ ድረስ 173 ሰዎች ሞተው፣ 130 መቁሰላቸውን ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ሐምሌ 30 ተጠርቶ በነበረ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በአንድ ቀን የሞቱትን 60 ሰዎች ጨምሮ ከነሐሴ 18 እስከ 27 ድረስ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“በኦሮሚያ የተጠራው የንግድ አድማ ተሳክቷል” – ኦፌኮ – “አድማው በህብረተሰቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከሽፏል” – መንግሥት

ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 2 በኦሮሚያ በማህበራዊ የንግድ አድማ መጠራቱን ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ተግባራዊ መደረጉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያስታወቀ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ የአድማ ጥሪው በህብረተሰቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከሽፏል ብሏል፡፡ የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለአዲስ አድማስ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ “በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች የንግድም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፤ ሁሉም ነገር እንደታገደ ነው” ብለዋል፡፡ ሆቴል ቤቶች፣ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችና የገበያ ስፍራዎች ዝግ ሆነው መሰንበታቸውን ኦፌኮ አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል በነቀምትና ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ባለፈው ሰኞና ማክሰኞ 4 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው አቶ ሙላቱ ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሠኢድ ስለጉዳዩ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠሩት ችግሮች ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጣጣሙ እንደሆኑ ጠቁመው ሁከቱ በዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ ጥፋት ማስከተሉን አስታውቀዋል፡፡ “ህዝቡ በቅንነት የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከህዝቡ ከራሱ ጋር ተመካክሮ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነቱን መንግስት በመግለጫዎቹ አሳይቷል” ያሉት አቶ መሃመድ፤ ከዚህ በመነሳት የህብረተሰቡን አጀንዳ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ተመድ በተቃውሞው የታሰሩ በአፋጣኝ እንዲፈቱ ግፊት እንዲያደርግ 15 ተቋማት ጠየቁ

- የሞቱ ዜጎች ጉዳይ በገለልተኛ አካል ይጣራ፤ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ በህግ ይጠየቁ ብለዋል   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በአማራና ኦሮምያ ክልሎች ከተቀሰቀሱ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ የታሰሩ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲፈታ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርግ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ 15 የተለያዩ ታዋቂ አለማቀፍ እና ብሄራዊ ተቋማት ጠየቁ፡፡ ተቋማቱ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በላኩት የጋራ ደብዳቤ፣ ምክር ቤቱ በቀጣዩ ሳምንት በሚያካሂደው አመታዊ ጉባኤው በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ቀዳሚ አጀንዳው እንዲያደርግና ጉዳዩን በተመለከተ መግለጫ እንዲያወጣ ጠይቀዋል፡፡መንግስት ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላትና ተቃዋሚዎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔ በአፋጣኝ እንዲፈታ እንዲሁም የጸጥታ ሃይሎች በሁለቱም ክልሎች ሆነ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በተቃዋሚዎች ላይ ያልተመጣጠነና ተገቢ ያልሆነ የሃይል ጥቃት መፈጸማቸውን እንዲያስቆም ግፊት እንዲያደርግም ምክር ቤቱን ጠይቀዋል፡፡መንግስት ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የተገደሉና የሰባዓዊ መብቶች ጥሰቶች የደረሱባቸው ዜጎች ጉዳይ በአለማቀፍ ገለልተኛ ተቋማት እንዲጣራ እንዲፈቅድ፣ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ አካላት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አባገዳዎች፤ መንግሥት እንዲያነጋግረን እንፈልጋለን አሉ

“ያለ ህግ አግባብ የታሰሩ ሰዎች በአስቸኳይ ይፈቱ”ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የተሠባሠቡ አባገዳዎች በክልሉ ባለው ተቃውሞና ግጭት ሳቢያ የበርካታ ሰዎች ህይወት እየጠፋ መሆኑን በመግለፅ ችግሩን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ በውይይት መንግስት እንዲያነጋግራቸው ጠይቀዋል፡፡ከነሐሴ 23 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሶደሬ ሆቴልና ሪዞርት ከ2 ሺ በላይ የሀገር ሽማግሌዎችና ሴቶች ባካሄዱት የ3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤ በክልሉ ባለው ተቃውሞና ግጭት ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ባለ 13 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የፌዴራል መንግስት ጦር የሃገሪቱን ዳር ድንበር የመጠበቅ ስራውን ትቶ በክልሉ መስፈሩን የጠቆሙት አባገዳዎች፤ ጦሩ የህዝቡን ቋንቋ የማያወቅ በመሆኑ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን በመግለፅ በአስቸኳይ ከክልሉ እንዲወጣ ጠይቀዋል። ሰላማችንን ራሳችን እንጠብቃለን በማለት፡፡“የጦር ሰራዊቱ ኦሮሚኛ ቋንቋን ስለማያውቅ ከህብረተሰቡ ጋር በቅጡ እየተግባባ አይደለም፤ ክልሉን በአፋጣኝ ለቆ እንዲወጣ እንጠይቃለን” ብለዋል የቱለማ አባገዳ በየነ ሰንበቶ፡፡ አብዛኛው የኦሮሞ ማህበረሠብ አባገዳዎች ጋር እየቀረበ፣ የደረሰበትን በደል እየተናገረ መሆኑን የጠቀሱት አባገዳው፣ ግጭቶችን ተከትለው የኦሮሞ ልጆች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ “በኦሮሞ ባህል እንኳን የሰው ልጅ የበሬ ደም እንኳ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለደረሰው የህይወት መጥፋት መኢአድ መንግስትን ተጠያቂ አደረገ

የእርቅ መንግስት እንዲመሰረት ፓርቲው ጠይቋልባለፈው ሳምንት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ለደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት መንግስትን  ተጠያቂ ያደረገው የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፤ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል፡፡ ፓርቲው ሰሞኑን በፅ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤መንግስት በአደጋው 23 ታራሚዎች መሞታቸውን ቢናገርም ቁጥሩ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለኝ ብሏል፡፡ መንግስት ለታራሚዎች ህገ መንግስታዊ ከለላ በመስጠት ደህንነታቸውን መጠበቅ ሲገባው፤ ይህ ሳይፈፀም መሞታቸውም ሆነ ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ለታሳሪ ቤተሰቦች ግልፅና የማያሻማ ፈጣን መልስ በመስጠት ፈንታ በቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጭንቀትና አሳዛኝ መጉላላት እንዲደርስ መደረጉን በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል መኢአድ፡፡ በጉዳቱ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት ማዘኑንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በመግለጫው፤ በማረሚያ ቤቱ የደረሰውን ጉዳት ጨምሮ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የደረሡ ጉዳቶች በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ለጠፋው ህይወት መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና የደም ካሣና የዜጎች ማቋቋሚያ ካሣ እንዲከፍል  ጠይቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ ነሀሴ 24 የሠጡት መግለጫ ‹‹ጦርነት ከማወጅ የማይተናነስ አሳዛኝም አስደንጋጭም ተግባር ነው›› ያለው ፓርቲው፤ በአስቸኳይ ትዕዛዙ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢዴፓን ጨምሮ የ16 ፓርቲዎች ‹‹ጥምረት›› አስቸኳይ እርቅ ጠየቀ

በሃገሪቱ ያለው ውጥረት ይረግብ ዘንድ ብሄራዊ እርቅ እንዲፈጠር ኢዴፓን ጨምሮ 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሠባሠቡበት ‹‹ጥምረት ለብሄራዊ መግባባትና አንድነት›› ሰሞኑን ጥሪ ያቀረበ ሲሆን መንግስት እርቁን ካልተቀበለ ሃገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላታል ብሏል፡፡ ኢህአዴግ አሁን በጀመረው መንገድ ግጭቶቹ ሊፈቱ እንደማይችሉ የጠቆመው ጥምረቱ፤ የሃይል እርምጃዎች ከቀጠሉ ሃገሪቱ ከኢህአዴግ ቁጥጥር ውጭ ልትሆን ስለምትችል በጊዜ የብሔራዊ እርቅ መድረክ ተፈጥሮ ሠላምና መግባባት እንዲሰፍን ጠይቋል፡፡ የተፈጠረውን የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ ለማረጋጋት ብሄራዊ እርቅ ወሳኝ ነው ያለው የፓርቲዎች ጥምረት፤ እርቁ ለዘመናት ስር እየስደደ የመጣውን የጥላቻ፣ የመናናቅ፣ ያለመተማመን፤ የቂም በቀልና የመገዳደል ስሜትን ለማስወገድ ወሳኝ ነው ብሏል፡፡ በዋናነት በተቃውሞዎች የተንፀባረቀው ‹‹የህወሃት የበላይነት የተረጋገጠበትና የታየበት አሰራር እንዲለወጥ›› የቀረበ ጥያቄ ነው ያለው ጥምረቱ፤ የአንድ ፓርቲ የበላይነት ሠፍኗል የሚለው አመለካከት እንዲቀረፍ ከተፈለገ፤ በጉዳይ ላይ የመድረክ ላይ ክርክር ውይይት ወሳኝ ነው ብሏል፡፡ የፖለቲካ እስረኞች ተፈተው ብሄራዊ እርቁ እንዲከናወን የጠየቀው ጥምረቱ፤ በእርቅ መድረኩ የተለያዩ ሃገራት መንግስታት፣ ታዋቂ አለማቀፍ ድርጅቶችና የዲፕሎማቲክ ተቋማት የታዛቢነት ድርሻ እንዲኖራቸው ጠይቋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በአማራ ክልል በ1 ወር ውስጥ ከ80 ሰዎች በላይ ሞተዋል – መኢአድ

“በመተማ ከ1ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሏል” አረና ፓርቲ- ከሠኔ ወዲህ በአማራና በኦሮሚያ ከ500 በላይ ሰዎች ሞተዋል” የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችበአማራ ክልል ከተፈጠረው ተቃውሞና ግጭት ጋር በተያያዘ በሁለት ሳምንት ውስጥ የ51 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 63 ሰዎች በፅኑ መቁሠላቸውን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ያስታወቀ ሲሆን የክልሉ መንግስት በበኩሉ፤ በአሁን ሰዓት ህግ የማስከበር ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁሞ በሰዎች ህይወት ላይ የደረሰው ጉዳት በኋላ ይገልጻል ብሏል፡፡ከነሐሴ 8 እስከ ረቡዕ ነሐሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም በጎንደርና በጎጃም ከተሞች የተካሄዱ ተቃውሞዎችን ተከትሎ በተከሰቱ ግጭቶች የ51 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለፀው መኢአድ፤ ከሐምሌ 29-ነሐሴ 1 በነበረው ተቃውሞ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉንና በድምሩ 81 ሰዎች መሞታቸውን አመልክቷል፡፡ የመኢአድ ዋና ፀሐፊ አቶ ኪዳነ ጥላሁን ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ የአማራ ክልል ከተሞች በሆኑት፤ ማጀቴ-ሠሜን ሸዋ 1 ሰው ሞቶ 2 ሠው ቆስሏል፣ ጎንደር  8 ሠው ሞቷል፣ ኮሶ በር (እንድባራ) 3 ሠው ሲሞት፣ 8 ሠው ቆስሏል፣ ዱርቤቴ 6 ሠው ሞቷል፣ ፍኖተ ሰላም 1 ሠው ሞቷል፣
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ጳጉሜን ለጤና” ነጻ የምርመራ አገልግሎት ሊጀመር ነው

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ሴንተር በየዓመቱ የሚያከናውነውና “ጳጉሜን ለጤና” የተሰኘው ነፃ የምርመራ አገልግሎት የፊታችን ማክሰኞ ይጀምራል፡፡ማዕከሉ ከትናንት በስቲያ በሸራተን አዲስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫና የፓናል ውይይት ላይ የማዕከሉ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ኃይሉ እንደተናገሩት፤ ማዕከሉ ያለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ላለፉት ሰባት ዓመታት የሲቲስካን፣ ኤምአርአይ እና ሌሎች የተለያዩ የምርመራ አገልግሎቶችን ገንዘብ ከፍለው መታከም ለማይችሉ ህሙማን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች እና ከአዲስ አበባ ከተማ የሚመጡና የሲቲስካንና የኤምአርአይ ምርመራዎች በሀኪሞቻቸው ታዞላቸው በገንዘብ ማጣት ምክንያት ምርመራውን ለማግኘት ያልቻሉ ህሙማን፤ ከጳጉሜ 1-5/ 2008 ዓ.ም ድረስ በማዕከሉ በሚሰጠው ነፃ የምርመራ አገልግሎት ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማዕከሉ ላለፉት ሰባት ዓመታት በየዓመቱ በሚሰጠው በዚህ ነፃ የምርመራ አገልግሎት፣ ከ15ሺህ በላይ ህሙማን ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለፁት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፤ በቀጣይም አገልግሎቱን በስፋት ለመስጠት ዕቅድ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ በማዕከሉ ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ ከፍለው አገልግሎቱን ማግኘት ለማይችሉ ወገኖች ከሚሰጠው ነፃ የምርመራ አገልግሎት በተጨማሪ “ጳጉሜን ለጤና” በሚል መሪ ቃል፣ በየዓመቱ በሚሰጠው ነፃ የምርመራ አገልግሎት ከ800-1000 ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ገልጸዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአመቱ የለዛ ሽልማት እጩዎች ይፋ ሆኑ

በየአመቱ የሚካሄደውና በለዛ የሬዲዮ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ብርሀኑ ድጋፌ የሚዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ የለዛ የኪነ-ጥበብ እጩዎች ይፋ ሆኑ፡፡ ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ሽልማት ላይ በሰባት ዘርፎች ማለትም በምርጥ ዋና ተዋናይ፣ በምርጥ ዋና ተዋናይት የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ፣ የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ፊልምና የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ የተመረጡ እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡ በየአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይ አለምሰገድ ተስፋዬ በ‹‹እውነት ሀሰት›› ፊልም ደሞዝ ጎሽሜ በ‹‹ዩቶጵያ›› ፊልም፣ ፈለቀ የማር ውሃ አበበ በ‹‹ፍሬ›› ፊልም፣ ደረጀ ደመቀ በ‹‹አንድ ጀግና›› ፊልም፣ ሰለሞን ቦጋለ በ‹‹የፀሀይ መውጫ ልጆች›› ፊልም፣ ከሳሁን ፍስሀ (ማንዴላ) በ‹‹ሀ እና ለ›› ፊልም አማኑኤል ሀብታሙ በ‹‹መባ›› ፊልም፣ ሄኖክ ወንድሙ በ‹‹ፍቅር ተራ›› ፊልም፣ ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) በ‹‹ሀገርሽ ሀገሬ›› ፊልም እና አብርሀም በላይነህ በ‹‹ለኔካለሽ›› ፊልም እጩ ሆነዋል፡፡ የዓመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይት የሽልማት ዘርፍ ደግሞ በ‹‹ወፌ ቆመች›› ፊልም ፍርያት የማነ፣ በ‹‹መባ›› ፊልም እድለ ወርቅ ጣሰው፣ ብርቱካን በፍቃዱ በ‹‹የፀሀይ መውጫ ልጆች›› ፊልም፣ ቃልኪዳን ጥበቡ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት የኃይል እርምጃ አቁሞ ህዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ሰመጉ አሳሰበ

በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የሚወሰድ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ እንዲቆምና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት እንዲከበር የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) የጠየቀ ሲሆን የመብት ጥሰቶችን በማጣራት ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎቹም በመንግስት እየታሰሩበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ ተቋሙ ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የደረሱ የመብት ጥቃቶችን አጣርቶ ማቅረቡን በመጥቀስ፤ አሁንም በአማራ ክልል በጎንደርና  ባህር ዳር ከተሞች ጨምሮ ተቃውሞና ግጭት በተፈጠረባቸው የክልሉ ከተሞች የበርካታ ሰው ህይወት ማለፉን ባገኘው መረጃ አንዳረጋገጠ መቁሞ መንግሥት የኃይል እርምጃ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስቧል፡፡ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ወደ ግጭት እየቀየረ ያለው በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የሚወሰድ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ መሆኑን የጠቀሰው ሰመጉ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ኃይማኖትና ብሄርን አላማ ያደረገ ግጭት ለመፍጠር የሚደረጉ ሙከራዎች መኖራቸውን ጠቁሞ ሁሉም ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል፡፡ መንግስት፤ የፀጥታ ኃይሎችን ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ አስቁሞ ህዝብን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ የተፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራና አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ እንዲሁም ህይወታቸው ላለፈ ዜጎች ቤተሰብና በግጭቱ ለተጎዱ ካሳ እንዲከፈል፣ ከህግ አግባብ ውጪ የታሰሩ እንዲፈቱ ሰመጉ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢህአዴግ “እታደሳለሁ” ማለቱን ተቃዋሚዎች አጣጣሉት

“መንግሥት የሀገሪቱን መሰረታዊ ችግር አልተገነዘበም”   የሰሞኑ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ መግለጫ፤ የወቅቱን የሀገሪቱን ችግሮች በአግባቡ የፈተሸና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አለመሆኑን የገለፁት ተቃዋሚዎች፤ በሀገሪቱ በተከሰቱት ችግሮች ዙሪያ ያስቀመጧቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ ያስገባ የሰጠ አይደለም ብለዋል፡፡ መንግስት የአገሪቱን መሰረታዊ ችግር ባለመገንዘቡ፣ አሁንም መፍትሄ ለማምጣት ቁርጠኛ አለመሆኑን ከተሰጠው መግለጫ መረዳታቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታውቀዋል፡፡ በሀገሪቱ በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሄው ውይይትና ብሄራዊ እርቅ ማካሄድ ብቻ እንደሆነ ሲወተውቱ መቆየታቸውን የጠቆሙት ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፤ መንግስት የመፍትሄ ሃሳቦቹን አለመቀበሉን እንዳልተቀበላቸው ከመግለጫው አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ “ኢህአዴግ እታደሳለሁ ማለቱ ጊዜውን ያልጠበቀ ነው፤ ከዚህ በኋላ ቢታደስም ለውጥ አያመጣም” ሲሉ ፓርቲዎቹ የተሃድሶ ፕሮግራሙን ነቅፈውታል። የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፤ በሀገሪቱ ለተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶች የብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማካሄድ መፍትሄ እንደሆነ ፓርቲያቸው በተደጋጋሚ ሲያሳስብ እንደነበር አስታውሰው፤ መንግስት እንደተለመደው ማሳሰቢያዎቹን ችላ ማለት ውጤቱ የከፋ ነው ብለዋል፡፡ ኢዴፓ፤ የግጭት መንስኤዎች እንዲጠኑ፣ የኃይል እርምጃ እንዲቆም በተደጋጋሚ መጠየቁን የጠቀሱት ዶ/ር ጫኔ፤ መንግስት የመፍትሄ ሃሳቦቹን ያልተቀበለው አሁንም በጉልበት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዛሬ አዲስ ኮሌጅ 520 ተማሪዎችን ያስመርቃል

አዲስ ኮሌጅ በዲግሪ ለ5 ዓመት በቲኢቪቲ ለ3 ዓመት ያስለጠናቸውን 520 ተማሪዎች ዛሬ በአምባሳደር ቴአትር ያስመርቃል፡፡በቲኢቪቲ ፕሮግራም በአይቲ በአካውንቲንግ፣ በሰርቬይ፣ በድራፍቲንግ፣ በኮንስትራክሽንና በኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የሚያስመርቅ ሲሆን በዲግሪ ፕሮግራም ደግሞ በአርኪተክቸርና በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና በማኔጅመንት  ያሠለጠናቸው ናቸው፡፡የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ለማረጋገጥ በ2009 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል በማደራጀት በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በሮድ ኤንድ ትራንስፖርትና በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት ለመጀመር ለመንግሥት ጥያቄ አቅርቦ በመጠባበቅ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

እስራኤል ዜጎቿ ተቃውሞ ካለባቸው አካባቢዎች እንዲርቁ አስጠነቀቀች

የሆላንዱ ኩባንያ በባህር ዳር ተቃውሞ የ11.1 ሚ. ዶላር የአበባ እርሻ ተቃጠለብኝ አለ   የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ ተቃውሞ ወደተስፋፋባቸው የአማራና የኦሮምያ ክልል አካባቢዎች እንዳይጓዙና ህዝብ ከተሰበሰበባቸውና ተቃውሞ ከተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች እንዲርቁ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አስጠነቀቀ፡፡ተቃውሞ ወደተቀሰቀሰባቸው የአማራና የኦሮምያ ክልል አካባቢዎች መሄድ ለአደጋ ያጋልጣል ያለው ሚኒስቴሩ፤ ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳንና ከኬንያ ጋር በምትዋሰንባቸው የድንበር አካባቢዎች በ10 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ውስጥ መገኘት እጅግ አደገኛ ነው ሲል ለዜጎቹ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡በተያያዘ ዜናም፣ ባለፈው ሰኞ በባህር ዳር በተቀሰቀሰው ተቃውሞ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች የአበባ እርሻ ኢንቨስትመንቱን በእሳት በማጋየት፤ ሙሉ ለሙሉ እንዳወደሙት “ኢስሜራልዳ ፋርምስ” የተባለው የሆላንድ ኩባንያ በድረገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡11.1 ሚሊዮን ዶላር ያወጣሁበት የአበባ እርሻ ኢንቨስትመንት በእሳት ወድሞብኛል ያለው ኩባንያው፣ ሌሎች በአካባቢው የሚገኙና ንብረትነታቸው የእስራኤል፣ ጣሊያን፣ ህንድና ቤልጂየም ኩባንያዎች የሆኑ ዘጠኝ ያህል የአበባ እርሻዎችም በተቃዋሚዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡ የኩባንያው ረዳት ስራ አስኪያጅ ሬምኮ ቤርካምፕ ለአልጀዚራ በሰጡት መግለጫ፣ ኩባንያው የተቃጠለውን እርሻ እንደገና አቋቁሞ፣
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አቤል ተስፋዬ 2 የዓለም የክብረ-ወሰኖችን አስመዘገበ

በርካታ ታላላቅ ዓለማቀፍ የሙዚቃ ሽልማቶችን በማስገባት ስኬታማ የሙዚቃ ጉዞውን የቀጠለው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ፤ በ2017 የዓለም የክብረወሰን መዝገብ በሁለት ክብረ ወሰኖች መመዘግቡን ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ዘ ዊክንድ በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የ26 አመቱ ድምጻዊ፤ “ቢዩቲ ቢሃይንድ ዘ ማድነስ” በሚለው የሙዚቃ አልበሙ ባለፈው የፈረንጆች አመት በ“ስፖቲፋይ” ድረገጽ ተጠቃሚዎች በብዛት በመታየቱና ሙዚቃዎቹ በቢልቦርድ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ለረጅም ተከታታይ ሳምንታት በምርጥ አስር ዝርዝር ውስጥ በመቆየታቸው፣ በአለም የክብረ ወሰን መዝገብ ላይ በሁለት ክብረ ወሰኖች ስሙን ማስፈሩ ተገልጧል፡፡“ቢዩቲ ቢሃይንድ ዘ ማድነስ” የተሰኘው የአቤል የሙዚቃ አልበም ከታህሳስ 2014 እስከ ታህሳስ 2015 ባለው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ በ60 ሚሊዮን የ“ስፖቲፋይ” ተጠቃሚዎች በመታየት ክብረ ወሰን ማስመዝገቡን የጠቆመው ተቋሙ፣ የድምጻዊው ዘፈኖች ከመጋቢት 2015 እስከ ጥር 2016 ባሉት ጊዚያት፣ ለ45 ተከታታይ ሳምንታት በቢልቦርድ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ምርጥ አስር ደረጃ ውስጥ ተካትተው መቆየታቸውን ገልጧል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ትላንት በጎጃም ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

በጎንደር ለ2ኛ ጊዜ ከቤት ያለመውጣት አድማ እየተካሄደ ነው      ተቃውሞውን ለማስቆም እርምጃ እወስዳለሁ”- የክልሉ መንግስት        ትላንት በባህር ዳር አንዳንድ የንግድ ተቋማት ታሸጉ                    ትናንት በተለያዩ የጎጃም ከተማዎች የተቃውሞ ሠልፍ የተደረገ ሲሆን በጎንደርና አካባቢው ባሉ ከተሞች ባለፈው ረቡዕ ለ2ኛ ጊዜ የተጀመረው የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ እንደቀጠለ ነው ተብሏል። በምዕራብ ጎጃም ዳሞት ወረዳ ቡሬ ከተማ ላይ በትናንትናው ዕለት ህዝቡ የአደባባይ ተቃውሞ ማድረጉን የጠቆሙት የመኢአድ ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን፤ በተቃዋሚዎችና በፀጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት መፈጠሩንና የተኩስ ድምፅም ሲሰማ እንደነበር ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በቡሬ በተካሄደው ተቃውሞና ግጭት በሰዎች ህይወት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሠዓት ድረስ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡በሰሜን ጎንደርና በጎጃም ባህርዳርና ፍኖተ ሰላም ከተሞች ሰሞኑን  አድማዎችና የአደባባይ ተቃውሞዎች የተደረጉ ሲሆን በጎንደር ከተማና በተለያዩ ወረዳዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከቤት  ያለመውጣት አድማ እየተካሄደ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት፤ ከዚህ በላይ እንደማይታገስ ጠቁሞ፣ ተቃውሞውን ለማስቆም እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።  በባህር ዳር ከተማ ደግሞ ከእሁድ ነሐሴ 14 እስከ ማክሰኞ ነሐሴ 16 የቆየ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ

ፓርቲው በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቷል                           ሰማያዊ ፓርቲ በወቅቱ የሀገሪቱ ችግር ላይ መንግሥት፣ ተቃዋሚዎች፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ተፅዕኖ ፈጣሪ አካላት በጋራ ህዝባዊ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡ በሌላ በኩል በፓርቲ የውስጥ ችግር ሲናጥ የቆየው ሰማያዊ፤ የፓርቲውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለመስከረም 14 ቀን 2009 ዓ.ም መጥራቱን አስታውቋል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤውን የጠራው ከፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ባገኘው ይሁንታ መሰረት፣ የፓርቲው የኦዲት ምርመራ ኮሚሽን መሆኑን የሰማያዊ  ም/ፕሬዚዳንት አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በጠቅላላ ጉባኤው የኦዲትና ኢንስፔክሽን እንዲሁም ብሄራዊ ም/ቤቱ ሪፖርት የሚያቀርቡ ሲሆን ከሪፖርቱ በመነሳት ውይይቶች እንደሚደረጉ ያስረዱት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ተጠሪ አቶ አበራ፤ የፓርቲው የወደፊት አቅጣጫ በጉባኤው  የሚወሰን ይሆናል ብለዋል፡፡ የአመራር ምርጫ ይካሄድ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ አበራ ገብሩ፤ ምርጫ ይካሄድ አይካሄድ የሚለው በጠቅላላ ጉባኤው እንደሚወሰን ተናግረዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣በአሁኑ ወቅት  የሚገኙት በአሜሪካ ሲሆን ለጉባኤው ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆሙት አቶ አበራ፤ ሆኖም እሳቸው ቢገኙም ባይገኙም ጠቅላላ ጉባኤው መደረጉ አይቀርም ብለዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ሜዳልያው ፀደቀለት

በኢንተርኔት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰባስቦለታል           መንግስት የፖለቲካ አቋሙን እንደሚያከብርለት ገልጾ ነበር                      አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ ያሳየው የተቃውሞ ምልክት በውድድሩ 2ኛ በመውጣት ያገኘውን የብር ሜዳልያ እንዳያሰርዝበት ተፈርቶ ነበር፡፡ ከትናንት በስቲያ አለማቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ፤ አትሌት ፈይሣ በውድድር መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውን ትግል ለመደገፍ እጁን በማጣመር ላሳየው ምልክት እንደማይቀጣ መወሰኑን አስታውቋል፡፡  የኢትዮጵያ መንግስት አትሌቱ ወደ ሀገሩ ቢመለስ የተለየ ችግር እንደማያጋጥመው ያስታወቀ ቢሆንም ወደ አገር ቤት ከመመለስ ይልቅ እዚያው ብራዚል ሪዮ ከተማ መቅረትን መርጧል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከአሜሪካ የሄዱ 3 ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጠበቆች የህግ ድጋፍ እያደረጉለት ነው ተብሏል፡፡ ቢቢሲና አልጀዚራን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አትሌቱ ባሳየው የተቃውሞ ምልክት በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልል ያለውን ተቃውሞና ግጭት ለዓለም አጋልጧል የሚሉ ዘገባዎችን ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡ ሮይተርስ ያነጋገራቸው የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወላጅ እናት፤ ልጃቸው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደሌለበትና ባለበት እንዲቆይ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ባለቤቱ በበኩሏ፤ ፈይሣ ይሄን ማድረጉ ብዙም እንዳላስደነቃትና ወትሮም
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ትርጉም የሌለው እርዳታ” ወይስ “ለትርጉም የምታስቸግር አገር”?

አምናና ዘንድሮ፣ ከፍተኛ እርዳታ ካገኙ ሦስት አገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።       ለረሃቡ 1.4 ቢ ዶላር (30 ቢ. ብር) እርዳታ ተገኝቷል። ግማሹ ከአሜሪካ! (የዩኤን መረጃ)፡፡       3ቱ ትልልቅ ለጋሾች፣ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝና የጀርመን መንግስታት ናቸው።       ረሃብ የሚከሰተው፣ የእህል ምርት ምን ያህል ሲቀንስ ነው?       በ1966 ዓ.ም፣ የእህል ምርት 13 ሚ. ኩንታል ቀንሶ ነበር። በ77ም እንዲሁ            (የዓለም ባንክመረጃ)፡፡       በ2007 ዓ.ም? ረሃብ የተከሰተው፣ የእህል ምርት በ5ሚ ኩንታል ስለቀነሰ ነው።                    (ስታትስቲክስ ኤጀንሲ)።    አዴግ ሰሞኑን ያወጣውን ረዥም መግለጫ ሰምታችኋል? ከመግለጫው ውስጥ ጥቂት ዓረፍተ ነገሮችን በመመልከት፣ የአገራችን ፖለቲካ ምን እንደሚመስል መታዘብ እንችላለን። እንደተለመደው፣ እንደወትሮው፣ ተቃዋሚም፣ ደጋፊም እንደሚያደርገው፣ ለፕሮፓጋንዳ እስከጠቀመ ድረስ፣ ፍሬ እና ገለባውን እያደበላለቁ የመንጎድ ፖለቲካ፣ የአገራችን ባህል ነው፡፡  በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ኃይለኛ ድርቅ መከሰቱን ይጠቅሳል መግለጫው። ከዚያስ? “ትርጉም ያለው እርዳታ” ባናገኝም፤ የረሃብ አደጋውን በራሳችን አቅም መቋቋም ችለናል ብሏል ኢህአዴግ፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ስለተሻሻለ የረሃብ አደጋው እጅግ የከፋ ጥፋት እንዳላደረሰም ተናግሯል፡፡ እስቲ፣ እውነተኛውን መረጃ … እውነተኛውን ፍሬ ከገለባው ለመለየት እንሞክር፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

23 ደቡብ ሱዳናውያን 10 ኢትዮጵያውያንን በመግደል ተከሰሱ

ግድያውን የፈጸሙት ለበቀል ነው ተብሏልባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ በጋምቤላ ክልል በሚገኝ የስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ የሚሰሩ 10 ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል የተባሉ 23 ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ባለፈው ሰኞ በግድያ ወንጀል መከሰሳቸውን ሮይተርስ ዘገበ፡፡በጋምቤላ ጀዊ የስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ሁለት ደቡብ ሱዳናውያን ህጻናት በመኪና አደጋ ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ እነዚሁ 23 ደቡብ ሱዳናውያንም የህጻናቱን ሞት ለመበቀል በማሰብ፣ በስደተኞች ጣቢያው ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 10 የግንባታ ሰራተኞችን በአሰቃቂ ሁኔታ ደብድበው በመግደላቸው ክስ እንደተመሰረተባቸው ጠቁሟል፡፡በተከሳሾቹ የግድያ ሰለባ የሆኑት አስሩ ኢትዮጵያውያን በህጻናቱ ግድያ ላይ እጃቸው እንደሌለበት የክስ መዝገቡ መግለጹን የጠቆመው ዘገባው፤ ግድያው መፈጸሙን ተከትሎ በአካባቢው ብጥብጥ መፈጠሩንና አንዳንድ ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞችም ጥቃት እንደደረሰባቸው አስታውሷል፡፡ በደቡብ ሱዳንያውያኑ ስደተኞች ከተገደሉት 10 ንጹሃን ኢትዮጵያውያን መካከል ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ በጋምቤላ ክልል ከ270 ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች እንደሚገኙም ዘገባው አስታውሷል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአለም አብያተ ክርስቲያናት ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ህገ-መንግስታዊ መብቶች ይከበሩ ብሏል   የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችና ውጥረቶች ምክንያት በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንዲያደርጉ ለኢትዮጵያ መንግስት፣ ለጸጥታ ሃይሎችና ለተቃዋሚዎች ጥሪ አቀረበ፡፡በኢትዮጵያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በላኩልኝ መረጃ፣ ተቃውሞውን ተከትሎ በአገሪቱ የተፈጠረው ውጥረት አሁንም አለመርገቡንና በተቃዋሚዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች እንደቀጠሉ መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ ብሏል - ምክር ቤቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ፡፡ የፀጥታ ሃይሎች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ሃይል እንዳይጠቀሙ የጠየቀው ምክር ቤቱ፣  ተቃዋሚዎችም ለግጭቱ መንስኤ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ጋር ግልጽ ውይይት የሚደረግበትን መንገድ መሻት አለባቸው ብሏል፡፡“በተቃውሞዎቹ ለህልፈተ ህይወት በተዳረጉት ዜጎች እንዲሁም በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተቃዋሚዎች ላይ በተፈጸመው እስርና ድብደባ ማዘናችንን እንገልጻለን” ብለዋል፣ የምክር ቤቱ የአለማቀፍ ጉዳዮች ኮሚሽን ዳይሬክተር ፒተር ፕሮቭ፡፡በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲና እርዳታ ኮሚሽነር ባረቤል ኮፍለር በበኩላቸው ባለፈው ረቡዕ ባወጡት መግለጫ፣ በአገሪቱ የተከሰቱት ግጭቶች በእጅጉ እንደሚያሳስቧቸው ጠቁመው፣ ሁሉም ወገኖች ከቀጣይ ግጭቶች
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የድሬዳዋ 10ኛ ዓመት የጎርፍ አደጋ መታሰቢያ ስነ- ስርዓትን አስመልክቶ ከድሬደዋ አስተዳደር የተሰጠ ምላሽ

ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 7 ቀን 2008 ዓ.ም በወጣው የጋዜጣችሁ እትም ላይ ‹‹የድሬዳዋ 10ኛ ዓመት የጎርፍ አደጋ አከባበር ከፍተኛ ቅሬታ አስነሳ›› በሚል ርዕስ በትክክለኛ መረጃ ላይ ሳይመሰረት ለቀረበው ዘገባ እንደሚከተለው ምላሽ ለመስጠት እንወዳለን፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ሐምሌ 28 ቀን 1998 ዓ.ም ሌሊት በከተማው ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት የቀጠፈና በሺዎች ለሚቆጠሩ ነዋሪዎች መጠለያ ማጣትና ንብረት መውደም ምክንያት የሆነበትን ቀን ከዚህ በፊት በሐይማኖት ተቋማት፣ በበጎ አድራጊ ግለሰቦችና ማህበራት በየዓመቱ ሲከበር መቆየቱ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ የዘንድሮውም የአደጋውን 10ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ፤ አስተዳደሩ ለተጎጂዎች ያለውን አጋርነት  በልዩ ሁኔታ እንዲታሰብ ለማድረግና የጎርፍ አደጋውን በዘላቂነት ለመፍታት በአስተዳደሩ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ህብረተሰቡ እንዲያውቃቸው በማድረግ፣ከአደጋው ስጋት ተላቆ የተረጋጋ ሕይወት እንዲመራ ማድረግን ያለመ ተግባር በመሆኑ፣ ይህን ቅዱስ ዓላማ ከሚደግፉ ድርጅቶች ጋር በመሆን አክብሯል፡፡ በዚሁ የተቀደሰ አላማ መሰረት ነው፤‹‹በጎርፍ የተጎዱ ወገኖቻችን ሁሌም እናስባለን፤ስጋቱንም ለመቀነስ ተግተን እንሰራለን›› በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንዲከበር የተደረገው፡፡ በመታሰቢያ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ፕሬዚዳንት ሙላቱና የመኢአድ አመራሮች በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ተወያዩ

በ25 ዓመት ውስጥ መሰል ውይይት ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው‹‹ፕሬዚዳንቱ ሁሌም በሬ ክፍት ነው ብለውናል›› - ዶ/ር በዛብህ ደምሴፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፤ በአማራና በኦሮሚያ ክልል በተፈጠሩ ተቃውሞዎችና ግጭቶች እንዲሁም በአዲስ አበባ ቤት በፈረሠባቸው ነዋሪዎች ጉዳይ ዙሪያ የመኢአድ አመራሮችን በቤተመንግስታቸው ጠርተው አነጋገሩ፡፡ የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ለፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ፣ ለህዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤዎች በፃፈው ደብዳቤ፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተፈጠሩ ተቃውሞዎችና ግጭቶች እንዲሁም በአዲስ አበባ ቤት በፈረሠባቸው ነዋሪዎች ጉዳይ ዙሪያ መንግስት ችግሩን መርምሮ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያበጅ መጠየቁ ይታወሳል፡፡ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ፤ ለፓርቲው ማሳሰቢያዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ደብዳቤው በደረሳቸው በ4ኛው ቀን ወደ ፓርቲው ፅ/ቤት ስልክ አስደውለው ለውይይት እንደጋብዟቸው የመኢአድ ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ ደምሴ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ በተያዘላቸው ቀጠሮ መሠረትም የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ ደምሴና ተ/ም/ፕሬዚዳንት አቶ አሠፋ ሃብተወልድ፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ለ1 ሰዓት ተኩል የቆየ ውይይት በቤተ መንግስት አድርገዋል፡፡በውይይታቸውም በተለይ በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ህገ ወጥ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ያረጀ ቲቪ እና አገር፤ መንግስት እና ‘ሕዝብ’…

• ዘረኝነት፣ … ማብሪያና ማጥፊያ የለውም። ዛሬ ‘ኦን’፣ ነገ ‘ሳይለንት’ ማድረግ አይቻልም።• በዘፈቀደ ማበላሸትና ማፍረስ እንጂ፣ በዘፈቀደ መገንባትና ማስተካከል አይቻልም። ያረጀ ቴሌቪዥን፣ ብዥ ብዥ፣ እያለ ሲያስቸግር ምን እናደርጋለን? ‘ግራና ቀኝ’ ማንገራገጭ፣ መደለቅ! ነቅነቅ ነቅነቅ ሲደረግ፣ ይስተካከል ይሆናል። መቼም፣ ምኞት አይከለከልም። ግን፣ ምኞት ብቻውን፣ አያዘልቅ። ያለ እውቀት፣ ያለ ሞያና ያለ ጥረት፣... ሌጣ ምኞት ብቻውን፣ እያሳሳቀና እያታለለ ገደል ይከታል። ግራ ቀኝ በማንገራገጭና በመነቅነቅ፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማስተካከል ቢቻል ኖሮ፣... የተበላሹ ኮምፒዩተሮችና ቴሌቪዥኖች፣ መጋዘን ባላጣበቡ ነበር። ቴሌቪዥን መጠገኛ ቤት ሂዱ፣... ከወለል እስከ ጣሪያ ድረስ ተደራርበው አቧራ የለበሱ የቴሌቪዥን አይነቶችን ታያላችሁ። ማንገራገጭና መነቅነቅ፣ አልፎ አልፎ ብልሽትን ያስተካክል ይሆናል። ግን ብልሽትንም ሊያባብስ ይችላል። ለዘለቄታው፣ የዘፈቀደ ንቅናቄ... መፍትሄ አይሆንም። አሳዛኙ ነገር፣ አገራችን ኢትዮጵያ፣ እንደ ተበላሸ ቲቪ፣ ግራና ቀኝ የሚደልቅና የሚያንገራግጭ እንጂ፣ በእውቀት፣ በሙያና በጥረት፣ ላይ ተማምኖ፤ አሳምሮ የሚጠግንና የሚያስካክል ብልህ፣ ጥበበኛና ጀግና አላገኘችም። አንዱ፣ እንደመጣለት ሲደልቅ፣ ሌላኛው በተራው ለማንገራገጭ እየተነሳሳ፣ በዙር እየተቀባበሉ ያጦዙታል፡፡ በእርግጥ ይሄ፤ የኛን አገር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢዴፓ የመንግስት ሚዲያዎችንና የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትን አስጠነቀቀ

የጋራ ም/ቤቱን ሊለቅ እንደሚችል ፓርቲው ገልጿልበኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶችን አስመልክቶ የሚሰጧቸውን መግለጫዎች የመንግስት ሚዲያዎች አዛብተው ለህዝብ እያቀረቡ ነው ሲል የተቸው ኢዴፓ፤ የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትም ከፓርቲው እውቅና ውጪ አቋሞችን በማንፀባረቅ ደንብ እየጣሰ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው ለአዲስ አድማስ በላከው ደብዳቤ እንዳመለከተው፤ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 6 በሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን የሰጠውን መግለጫ ኢዜአ፣ ፋና፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣና የአማራ ብሄራዊ ክልል ቴሌቪዥን ይዘቱን አዛብተው በማቅረብ፣ ህዝብ ስለ ፓርቲው ያለው አቋም እንዲናጋ ማድረጋቸውን ጠቁሞ፤ የሚዲያ ተቋማቱ አሰራራቸውን እንዲፈትሹና እንዲያስተካክሉ አሳስቧል፡፡ በእለቱ ኢዴፓ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶች፣ በውይይት ሰላማዊ መፍትሄ ማግኘት አለባቸው የሚል አቋም ማንፀባረቁን የጠቆሙት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ፤ የተጠቀሱት የመገናኛ ብዙኃን ግን “ፓርቲው ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ የሚደረግ ጥረት ተቀባይነት የለውም” ብሏል በማለት በመግለጫው ላይ ፈፅሞ ያልተጠቀሰ ዘገባ አስተላልፈዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ ሰንደቅ አላማን በተመለከተም ኢዴፓ ሰልፈኞቹ የያዙትን ሰንደቅ አላማ እንዳወገዘ ተደርጎ በዘገባዎቹ ቀርቧል ያሉት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሰሞኑ ተቃውሞና ግጭት 142 ሰዎች መሞታቸውን መኢአድ አስታወቀ

ቅዳሜና እሁድ በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተደረገ ህዝባዊ ተቃውሞና ግጭት 142 ሰዎች መገደላቸውን መኢአድ አስታወቀ፡፡“መንግስት በሀገራችን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ በአስቸኳይ ያቁም” በሚል ርዕስ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጠው የመላ ኢትዮጵያውን አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፤ በአማራ ክልል አርብ ሐምሌ 29 እና እሁድ ነሐሴ 1 በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ 82 ሰዎች መሞታቸውንና 67 ሰዎች መቁሰላቸውን እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሐምሌ 30 በአንድ ቀን ብቻ ከ60 በላይ ዜጎች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሁለቱ ክልሎች በተፈጠሩ ተቃውሞዎችና ግጭቶች በኦሮሚያ 67 ሰዎች፤ በአማራ ክልል 30 ሰዎች በድምሩ 97 ሰዎች በቀጥታ ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት፤ ቢቢሲ እና አልጀዚራን ጨምሮ የዓለም ዋና ዋና ሚዲያዎች ሲዘግቡ ሰንብተዋል፡፡ መኢአድ በበኩሉ ትላንትና በሰጠው መግለጫ የ142 ሰዎችን ህልፈት ያረጋገጥኩት በየዞኑና ወረዳው ባሉ መዋቅሮቼ ከተሰበሰበና ከተጠናከረ መረጃ መሆኑን ጠቅሶ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም ብሏል፡፡ መንግስት ያልተመጣጠነ ሃይል ከመጠቀም እንዲቆጠብና የመከላከያ ሃይል ከግጭት አካባቢዎች እንዲወጣ ፓርቲው ጠይቋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ በአልማዝ ወርቅ የድል ጉዞዋን ጀምራለች

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ትናንት በሪዮ ዲ ጄኔሮ ማራካኛ ስታዲዬም በተካሄደው የ31ኛው ኦሎምፒያድ በሴቶች የ10ሺህ ሜትር የዓለምና የኦሎምፒክ ሪኮርዶችን በማስመዝገብ የወርቅ ሜደልያ ተጎናፅፋለች፡፡ አልማዝ በ10 ሺ ሜትር ውድድሩ ተፎካካሪዎቿን በሰፊ ርቀት ቀድማ ስታሸንፍ የተደነቀው የውድድሩ ኮሜንታተር “በጣም ጎበዝ” ሲል አድንቋታል፡፡ አዲስ የዓለምና የኦሎምፒክ ሪከርድ ሆኖ የተመዘገበው ሰዓት 29 ደቂቃዎች ከ17.45 ሰከንዶች ነው፡፡37 የተለያዩ የአለማችን አገራት አትሌቶች በተሳተፉበት በዚህ ውድድር፣ ብዙ ዙር ሲቀራት ቀድማ የወጣችው አልማዝ አያና፣ ተፎካካሪዎቿን እስከ መጨረሻው ድረስ በሰፊ ርቀት በመምራት የወርቅ ሜዳልያውን አጥልቃለች፡፡ ከአራት ቀናት በኋላ በ5 ሺ ሜትር ማጣሪያ ቋሚ ተሰላፊ ስትሆን ስኬታማ ሆና አስቀድሞ እንደተሰጣት ግምት የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት ከቻለች በ2008 በቤጂንግ ኦሎምፒክ ጥሩነሽ ዲባባና ቀነኒሳ በቀለ እንዲሁም በ1980 በሞስኮ ኦሎምፒክ ምሩፅ ይፍጠር ድርብ የወርቅ ሜዳሊያ በማስመዝገብ የሰሩትን ታሪክ ትጋራለች፡፡ዘንድሮ በ5ሺህ ሜትር የዓመቱን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው አልማዝ፣ በ2015 በርቀቱ የአለም ሻምፒዮን ለመሆን በቅታለች፡፡ በ10 ሺህ ሜትር የዓለም ሻምፒዮኗ ኬንያዊቷ አትሌት ቪቪያን ቺሮይት፣ በውድድሩ ሁለተኛ በመውጣት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የእርቀ ሰላም ጥሪ አቀረቡ

መድረክ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠይቋልመንግስት በዜጎች ላይ የኃይል እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ አሳሰቡሰሞኑን በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተደረጉ የህዝብ ተቃውሞዎችን ተከትሎ በተከሰተ ግጭት በርካቶች ህይወታቸውን እንዳጡ የገለፁት ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ሀገሪቱ ልትበታተን ትችላለች የሚል ስጋት እንዳላቸው ጠቁመው፣ በአስቸኳይ ሁሉንም ወገን ያካተተ የእርቀ ሰላም ጉባኤ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ መኢአድ፤ ኢዴፓና መድረክ ሰሞኑን ባወጡት የአቋም መግለጫ፤ መንግስት ለህዝብ ተቃውሞ የኃይል አፀፋ በመውሰዱ፤ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው በእጅጉ እንዳሳዘናቸው የገለፁ ሲሆን መንግስት በዜጎች ላይ የኃይል እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ አሳስበዋል፡፡ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አቅጣጫቸውን እየሳቱ፣ በህዝቡ አብሮ የመኖርና የመቻቻል እሴቶች ላይ እንቅፋት እየሆኑ ነው ያለው ኢዴፓ፤ ሁኔታው በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተጋረጠ አደጋ በመሆኑ በእጅጉ ያሳስበኛል ብሏል፡፡ ፓርቲው አክሎም፤ ከነዚህ ተቃውሞዎችና ግጭቶች ጋር በተያያዘ ለእስር የተዳረጉ ዜጎች፤ ሰብአዊ መብታቸው እንዲጠበቅ፤ አላግባብ የታሰሩም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ መኢአድና መድረክም ተመሳሳይ አቋም ያንፀባረቁ ሲሆን መንግስት የሚወስዳቸውን የኃይል እርምጃዎች አቁሞ፣ ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፍልና በሀገር ውስጥም
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የመንግስት የውጭ እዳ እየከበደ ነው

የኢትዮጵያ መንግስት፣ በግማሽ ዓመት 670 ሚ.ዶላር ለእዳ ክፍያ አውጥቷልየውጭ እዳ በፍጥነት እየተከማቸበት የመጣው የኢትዮጵያ መንግስት፣ በ2006 ዓ.ም የብድር እዳ ከነወለዱ 570 ሚ. ዶላር መክፈሉ የሚታወስ ሲሆን፣ ዘንድሮ ክፍያው በእጥፍ ጨምሮበታል። ዘንድሮ እስከ መጋቢት ድረስ፣ 670 ሚ.ዶላር እንደከፈለ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ገልጿል።ከአራት አመት በፊት፣ የመንግስት ጠቅላላ የውጭ እዳ ወደ 9 ቢሊዮን ገደማ እንደነበረ የገንዘብ ሚኒስቴር ጠቅሶ፣ ዘንድሮ እስከ መጋቢት ወር ድረስ፣ የእዳው ክምችት 20.6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቋል።በተለይ፣ በባቡር መስመር ግንባታ፣ በቴሌኮም እና ለአመታት በተጓተቱት የስኳር ፕሮጀክቶች ሳቢያ በፍጥነት እየተከማቸ ከመጣው ብድር ጋር፣ ለእዳና ለወለድ ክፍያ የሚውለው የውጭ ምንዛሬም እየከበደ እንደመጣ የሚኒስቴሩ ሪፖርት ያሳያል።በ2004 እና በ2005 ዓ.ም፣ ለእዳና ለወለድ ክፍያ የሚውለው የውጭ ምንዛሬ ግማሽ ቢሊዮን ገደማ ነበር። አምና የክፍያው ሸክም ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ተጠግቷል (980 ሚ.ዶላር)።የወለድ ክፍያው ለብቻው ሲታይም እንዲሁ፣ ከአመት አመት እየጨመረ መጥቷል። ከአራት አመት በፊት፣ 100 ሚሊዮን ዶላር የነበረው የወለድ ክፍያ፣ አምና ከ250 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የድሬደዋ 10ኛ ዓመት የጎርፍ አደጋ አከባበር ከፍተኛ ቅሬታ አስነሳ

የዛሬ 10 ዓመት ሐምሌ 28 ቀን 1998 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የደረሰውን ጉዳት ለማስታወስ የተዘጋጀው በዓል የጉዳቱን ሰለባዎች የዘነጋነው በሚል የተተቸ ሲሆን በአደጋው ተጎጂዎች ዘንድም ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል፡፡ከ500 በላይ ሰዎች የሞቱበትና 10 ሺ የሚደርሱ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉበት አስከፊ የጎርፍ አደጋ የተከሰተበትን 10ኛ ዓመት አስመልክቶ ሰሞኑን በከተማዋ 13 ሚ. ብር ወጪ የተደረገበት በዓል ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና የመንግስት ባለስልጣናት የተጋበዙበት ይሄው በዓል፤ ለሶስት ቀናት የዘለቀ ሲሆን አርቲስቶችን በባለ 5 ኮከብ ሆቴል ሰብስቦ በማስጨፈር መከበሩ አሳዝኖናል ብለዋል ተጎጂዎች፡፡  በጎርፍ አደጋው ሁለት ልጆቹንና ባለቤቱን ማጣቱን የገለፀልን አንድ የአደጋው ሰለባ፤ በወቅቱ በቤቱ ውስጥ ባለመኖሩና በጥበቃ ሥራው ላይ አዳሪ ተረኛ ስለነበር ከአደጋው መትረፉን ገልፆ አሁን ያለሁበትን ዓይነት ህይወት ከመኖር በጎርፍ አደጋው ከሚስቴና ልጆቼ ጋር ብሞት ይሻለኝ ነበር ሲል አማሯል፡፡ ‹‹ሚስቴንና ሁለት ልጆቼን በድንገተኛ አደጋ በአንድ ቀን ማጣቴ ያደረሰብኝ ሐዘንና የህሊና ጉዳት ቀላል አልነበረም፡፡ ከአደጋው በኋላ ወደ ህሊናዬ ለመመለስና  ራሴን ለማረጋጋት አመታት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ያባረራቸው ሰራተኞች ወደ ስራ ሊመለሱ ነው

የአዲስ አበበ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን፤ አዲስ በሰራው መዋቅር መስፈርቱን አታሟሉም በሚል ያበረራቸው 600 ሰራተኞች በአንድ ሳምንት ውስጥ ድልድል ሰርቶ ወደ ስራ እንደሚመለሱ ተገለፀ፡፡ ትላንት ከቀትር በፊት ሳር ቤት በሚገኘው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተደረገው ስብሰባ፤ የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ያብባል አዲስ፤ የሰራተኛውን አቤቱታ ካደመጡ በኋላ የሰራተኛው ጥያቄ አግባብ መሆኑን አምነው፣ ከ58 ሰራተኞች በስተቀር ሌሎቹ ድልድል ተሰርቶ ወደ ስራቸው ይመለሳሉ ማለታቸውን ምንጮች ገለፁ፡፡ 58ቱ ሰራተኞች በስራቸው ላይ በነበሩበት ወቅት ባሳዩት የስነ ምግባር ግድፈትና ተደጋጋሚ ስህተት በህግ እንደሚጠየቁና ከጥፋት ነፃ መሆናቸውን ካረጋገጡ ወደ ስራቸው እንደሚመለሱም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ንብረት አስረክባችሁ ውጡ የተባሉ ከ600 በላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ  ሰራተኞች፤ አፍሪካ ህብረት ጎን የሚገኘውን አዲሱን የባለስልጣኑን መስሪያ ቤት በተቃውሞ አጨናንቀውት ሰንብተዋል፡፡ ሰራተኞቹ ከዋና ስራ አስፈፃሚው ጋር “የመዋቅር አሰራሩ ግልፅነት የጎደለው፣ መስፈርት ያልወጣለት፣ በዘመድ አዝማድ የተሰራና የመስሪያ ቤቱን ሰራተኞች የረጅም ጊዜ ውለታ መና ያስቀረ ነው” በማለት ተቃውሞአቸውን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ትናንት በጎንደር በተከሰተ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ

በጎንደር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉትን የወልቃይት ኮሚቴ አባላት የፍርድ ጉዳይ ለመከታተል ትናንት ፍ/ቤት አካባቢ ተሰብስበው በነበሩ ነዋሪዎችና የፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን የፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል ጎንደር ፒያሣ አካባቢ በሚገኘው ፍ/ቤት በጠዋቱ በሺዎች የሚቆጠሩ  የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰብስበው የነበረ  ሲሆን ፍ/ቤቱ የተጠርጣሪዎቹን ጉዳይ ለነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ እንደተሰማ ግርግር መፈጠሩን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ ተቃውሞ የሚያሰሙትን ነዋሪዎች ለመበተን ሙከራ ማድረጉን የጠቆሙት ምንጮች፤ ከቆይታ በኋላ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመሳሪያ ተኩስ መሰማቱንና ተኩሱ በየአቅጣጫው እስከ አመሻሹ ድረስ መዝለቁን ተናግረዋል፡፡  የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በድንጋይ መዘጋጋታቸውንና ወጣቶች በቡድን እየሆኑ ተቃውሞ ሲያሰሙ መዋላቸውንና ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የከተማዋን ከንቲባ ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት የሞባይል ስልካቸው ዝግ በመሆኑ ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ በግጭቱ የሰዎች ህይወት ማለፉን ምንጮች ቢጠቁሙም ከፖሊስ ለማረጋገጥ አልቻልንም፡፡ ባለፈው እሁድ በከተማዋ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በአገሪቱ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ

በሀገሪቱ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንና በችግሮቹ ላይ አስቸኳይ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች አሳሰቡ፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች እየተቀሰቀሱ ያሉ ተቃውሞዎችና ግጭቶችን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡንት አቶ ልደቱ አያሌውና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ በሀገሪቱ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ችግር ሀገሪቱን ሊበታትን የሚችል አደጋ መሆኑን አስጠንቅቀው፣ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻዎች ለውይይት በጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጥ አለባቸው ብለዋል፡፡ “ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት፤ አሁን የተፈጠረውን ችግር ብቻውን ሊፈታው አይችልም” ያሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ አሁን የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ወዳልሆነ አቅጣጫ ሄደው የሀገሪቱን ህልውና ከመፈታተናቸው በፊት ሁሉም አካላት ሊያስቡበት ይገባል ብለዋል፡፡ አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው በበኩላቸው፤ አሁን ያለው ስርአት የለውጥ እርምጃዎችን ካልወሰደ፤ ሀገሪቱን ለከፋ የመበታተን አደጋ ሊያጋልጣት እንደሚችል አሳስበዋል፡፡ በወቅታዊ የፖለቲካ ችግሮችና ግጭቶች ዙሪያ ያነጋገርናቸው የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው፤ መንግስትና ህዝብ በተፈጠሩት ችግሮች ላይ የጋራ ውይይት ሊደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡     
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በባህርዳርና በኦሮሚያ ለተጠሩ ሰልፎች፣ ኦፌኮና ሰማያዊ ፓርቲ ድጋፋቸውን ገለፁ

በኦሮሚያ ከተሞችና በባህርዳር፤ ዛሬና ነገ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማህበራዊ ድረ ገፆች ጥሪዎች የተሰራጩ ሲሆን፣ ኦፌኮ ሰልፉን እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ፤ በባህርዳር ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ፈቃድ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ ባለፈው እሁድ በጎንደር ከተማ ሰፊ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን ተከትሎ በማህበራዊ ድረ ገፅ፤ በኦሮሚያ ከተሞች “በመንግስት የተወሰዱ የሀይል እርምጃዎችን እናወግዛለን” የሚል የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ተሰራጭቷል፡፡የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ ለሰላማዊ ሰልፉ ድጋፍ በመስጠት ተሳታፊ እንደሚሆን የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንቱ አቶ ሙላቱ ገመቹ ተናግረዋል፡፡ ግድያና እስራት እንዲቆም፣ ወታደሮች እንዲወጡና የታሰሩ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ፣ እንዲሁም ለሟች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል ይጠየቃል ብለዋል - አቶ ሙላቱ፡፡ የፓርቲያችን ፍላጎት፣ በክልሉ ያለው ችግር በሰላም እንዲፈታ ነው ያሉት አቶ ሙላቱ፤ መንግስት በቁርጠኛ አቋም በሩን ለውይይት ክፍት እንዲያደርግ አጥብቀን እንጠይቃለን ብለዋል፡፡ በክልሉ ተቃውሞና ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ ፓርቲው ከየአካባቢው መረጃዎችን እያጣራ ሲገልፅ መቆየቱን አቶ ሙላቱ ጠቅሰው፣ ከ300 በላይ ሰዎች መሞታቸውን በተሟላ መረጃ አረጋግጠናል ብለዋል። ነገር ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ እጥፍ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ያሉት አቶ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአቶ ሀብታሙ የውጪ የህክምና ፈቃድ ለመስከረም ተቀጠረ

ቤተሰቡ ዳግመኛ ጥያቄውን አናነሳም ብሏል  ወደ ውጭ ሃገር ሄደው ለመታከም የጉዞ እግድ እንዲነሣላቸው ለጠቅላይ ፍ/ቤቱን ያመለከቱት ፖለቲከኛው አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ የጠየቁትን ፈቃድ ያላገኙ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጉዳያቸውን ለቀጣዩ አመት መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጥሮታል። የአቶ ሀብታሙ ቤተሰብ፤ ከእንግዲህ የጉዞ እገዳ እንዲነሳላቸው ለመጠየቅ ወደ ፍ/ቤት እንደማያመሩ ተናግረዋል፡፡ ጉዳያቸውን የሚመለከተው የጠቅላይ ፍ/ቤት ትናንት የመጨረሻ ውሳኔ ያሣልፋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ከካዲስኮ ሆስፒታል ሃኪሞች የቀረበው የህክምና ማስረጃ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጥበትና ህክምናው ሃገር ውስጥ እንደማይሠጥ እንዲያረጋግጥ በመግለፅ ፍ/ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ካዲስኮ ሆስፒታል በሰጠው የሃኪሞች ቦርድ ውሳኔ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ  ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ አቶ ሃብታሙ በአሁን ወቅት በአልጋ ላይ ሆነው በማደንዘዣ ብቻ ህመማቸውን እያስታገሱ እንደሚገኙ የገለፁት የቤተሰቡ ተወካይና የአቶ ሀብታሙ የቅርብ ወዳጅ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፤ ከዚህ ቀጠሮ በኋላ ቤተሰቡ ፍ/ቤት የጉዞ እገዳውን እንዲያነሳለት ላለመጠየቅ ከውሳኔ ላይ ደርሷል፤ ብለዋል፡፡ አቶ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩ ሲሆን በተከሰሱበት የሽብር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በአወዳይ ግጭት ስድስት ሰዎች ሞተዋል፤ የከተማዋ ኑሮ ተናግቷል

- 26 ሰዎች ቆስለዋል፤ የከተማዋ ስራ ቆሟል- የነዋሪዎች ዋና መተዳደሪያ የጫት ንግድ ተቋርጦ፤ ወደ ሃረር አቅራቢያ ሸሽቷል- ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ገበያውን ለማስመለስ እየጣሩ ነው  በጫት ንግድ ማዕከልነቷ በምትታወቀው አወዳይ ከተማ፣ ባለፈው እሁድ በተቀሰቀሰው ረብሻ ስድስት ሰዎች መሞታቸውንና 26 ሰዎች መቁሰላቸውን የገለፁ ምንጮች፤ የአገሪቱ ዋነኛ የጫት ንግድ መቋረጡ የከተማዋን ኑሮ እንዳናጋ ተናግረዋል፡፡መንገድ ላይ ጎማዎች በማቃጠል ተቃውሞ ሲያካሂዱ በነበሩ ወጣቶችና በፖሊስ መካከል ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን፤ በግጭቱ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ፖሊስ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ በከተማዋ የነዋሪዎች እለታዊ ስራና የንግድ እንቅስቃሴ ክፉኛ መጎዳቱን፣ የከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች እንዲሁም የኢንዱስትሪና የንግድ ቢሮ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡ ከቡና በመቀጠል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በሚያስገኘው የጫት ንግድ በዋና መነሃርያነት የምትጠቀሰው አወዳይ  ከተማ ትልቅ ድርሻ በመያዟ፣  12 የባንኮች ቅርንጫፎች ተከፍተዋል፡፡ በከተማዋ ይካሄድ የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ ሰሞኑን በመቋረጡ፣ ባንኮችን ጨምሮ፣ ጫት አምራቾችና ላኪዎች፣ የጭነት አገልግሎት ሰጪዎችና አብዛኞቹ የከተማዋ ስራዎች፣ ኪሳራና ችግር ደርሶባቸዋል።  ከምስራቅ ሃረርጌ ወረዳዎች የሚመረተውን ጫት እየሰበሰበ፤ ለአገር ውስጥና ለውጭ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮ-ኬንያ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ ግንባታ ተጀመረ

ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ የያዘቺው እቅድ ዋነኛ አካል የሆነውና 1.2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግበት የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ በዚህ ሳምንት መጀመሩን ስታንዳርድ ሚዲያ ዘገበ፡፡1 ሺህ 45 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውንና 2 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው የተነገረለትን የዚህን የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ የሚያከናውነው ቻይና ኤሌክትሪክ ፓዎር ኢኩፒመንት ቴክኖሎጂ የተባለው ኩባንያ እንደሆነ የጠቆመው ዘገባው፣ ግንባታው በታህሳስ ወር 2018 ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡ኬንያ ከኢትዮጵያ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት ስምምነት መፈጸሟን የዘገበው ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ፣ በቀጣይም የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ሃይል መጠን በብዙ እጥፍ ለማሳደግ ማሰቧን አስነብቧል፡፡በሁለቱ አገራት መካከል የሚዘረጋው ይህ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመር፣ በ2018 ዓ.ም ለ870 ሺህ አወዎራዎች የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ያሟላል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአፍሪካ ልማት ባንክ ማስታወቁንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡በተያያዘ ዜናም ግልገል ጊቤ ሶስት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ፣ 800 ሜጋ ዋት ሃይል ማመንጨት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ተናግረዋል፡፡ የግልገል ጊቤ ሶስት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዲማ ልዩ የዓይን ህክምና ማዕከል ስራ ጀመረ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአይን ህክምና መምህሮች የተቋቋመው “ዲማ” የአይን ህክምና ክሊኒክ፤ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ክሊኒኩ ከሌላው የአይን ህክምና በተለየ በአይን ቆብና በእንባ መፍሰስ ህክምና ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራና በአገሪቱ ሁለቱ ህክምናዎች ላይ ስፔሻላይዝድ ያደረጉ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዶክተሮች ብቻ እንዳሉ የክሊኒኩ መስራች አባል ዶ/ር መሰረት እጅጉ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ በአሁኑ ወቀት የእንባ መፍሰስ፣ የአይን ቆብና የአይን ቆብ አካባቢዎችን በማከም ትኩረት ያደረገው ክሊኒኩ፣ ሌሎችንም የአይን ህክምናዎች እግረ መንገዱን እንደሚሰጥና በተለያዩ አደጋዎች አይናቸውን ያጡ ሰዎች፣ በቀዶ ጥገና አርቴፊሻል አይኖችን እንደሚተክሉ ዶ/ር መሰረት ተናግረዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ለ33ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመረቀ

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 798 ተማሪዎች የዛሬ ሳምንት በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል፡፡ በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዕድን ምህንድስና ተማሪዎችን ማስመረቁም በእለቱ ተገልፆል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በማስተርስ ኦፍ አድምኒስትሬሽን፣ በመጀመሪያ ዲግሪ ደግሞ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ፣ በቢዝነስ ኢኮኖሚክስ፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሳይንስ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ በአርክቴክቸር ኤንድ አርባን ፕላኒንግ፣ በሶሲዮሎጂና በሶሻል አንትሮፖሎጂ፣በክሊኒካል ነርሲንግና በሌሎችም ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የሚድሮክ ሊቀመንበር ዶ/ር ሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲንና የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰርና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው በተገኙበት አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል፤በየአመቱ ከማህበረሰቡ ውስጥ በአርአያነት የሚመረጡ ግለሰቦችንም ይሸልማል፡፡ ዘንድሮም የቱሪዝም አባት ተብለው የሚጠሩት አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ፣ የማስታወቂያ ባለሙያው የትውልዱ አምባሳደር አቶ ውብሸት ወርቃለማሁና በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ፣ የዩኒቨርሲቲው አርክቴክቸርና ኸርባን ዴቨሎፕመንት መምህር  ዶ/ር ፈረደ በፍቃዱ የሊቀመንበሩን ዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ከሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲ እጅ ተቀብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በደሴ ልዩ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከመቶ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዜድቲኢ ለሶስተኛ ጊዜ በጉለሌ ከተማ ዛፍ ተከላ አካሄደ

ዓለምአቀፉ የቴሌኮምና የኔትወርክ ኩባንያ ዜድቲኢ፤ ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ በጉለሌ ክ/ከተማ ከ2 ሺ በላይ ዛፎችን ተከለ፡፡ በዛፍ ተከላው ላይ በኢትዮጵያ የቻይና የንግድና ኢኮኖሚ አማካሪ  ወ/ሮ ሊዮ ዩን እና የዜድቲኢ ኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ሚስተር ሊ ጉዋንግ ዮንግን ጨምሮ ከ200 በላይ የኩባንያው የውጭና የአገር ውስጥ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ ‹‹Green Action Tree Planting›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ የዛፍ ተከላ ላይ ምክትል ዳሬክተሩ ባደረጉት ንግግር፤ ዜድቲኢ ባለፉት 16 ዓመታት በቴሌኮም ማስፋፋት፣ በኔትወርክ ዝርጋታና በተለያዩ ማህበራዊና በጎ አድራጎት ስራዎች በመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት አጋር መሆኑን ጠቅሰው ባለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ለመደገፍ የዘንድሮን ጨምሮ ከስድስት ሺህ በላይ ዛፎችን መትከሉን ገልፀዋል፡፡  የቻይና ብሄራዊ ቀን በየአመቱ ማርች 12 እንደሚከበር ጠቁመው፣ የቻይና ህዝብ ተፈጥሮን ለመጠበቅ ዛፍ እንደሚተክል የተናገሩት ምክትል ዳሬክተሩ፤ይህ አይነት ተግባር በኢትዮጵያም ሊበረታታ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡ የዛሬው የዛፍ ተከላ ቀን ለቻይናም ሆነ ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ነው ያሉት አማካሪዋ፤ኢትዮጵያ በጣም ቆንጆ አገር እንደመሆኗ ውበቷንና ተፈጥሮዋን በመጠበቅ ይበልጥ እንድትዋብ፣ ዛፍ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የጤፍ ዱቄትን ከጀሶና ሰጋቱራ ጋር ቀላቅለው እንጀራ የሚጋግሩ በየአካባቢው እየተያዙ ነው

- ትላንት በልደታ ክ/ከተማ 5 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል- ወንጀሉ ላለፉት 5 ዓመታት በከተማዋ በድብቅ ሲፈፀም ቆይቷል- እንጀራው 30 በመቶ ጤፍ፣ 70 በመቶ ጀሶና ሰጋቱራ ተቀላቅሎ ይጋገራል- ሀኪሞች፤ ጀሶና ሰጋቱራ በጉበትና ኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል አሉ- በሁሉም ክፍለ ከተሞች ድርጊቱ እንደሚፈፀም ለማወቅ ተችሏል  በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ጥቂት የጤፍ ዱቄትን ከጀሶ፣ ከሰጋቱራና ከደረቀ እንጀራ ዱቄት ጋር በመቀላቀል እየጋገሩ፣ ለገበያ የሚያቀርቡ ሰዎች ከየአካባቢው በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው፡፡ እስከ አሁን በአቃቂ ቃሊቲ፣ በልደታ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በሰበታ ከተማ ውስጥ በተመሳሳይ ድርጊት ላይ የተሰማሩ ህገወጦች መያዛቸው ታውቋል፡፡ በትላንትናው ዕለት በልደታ ክ/ከተማ በተመሳሳይ ድርጊት ላይ የተሰማሩ 5 ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ ህገወጦቹ 30 በመቶ የጤፍ ዱቄት፣ ቀሪውን 70 በመቶ ደግሞ ጀሶ፣ ሰጋቱራና የደረቅ እንጀራ ዱቄት በመቀላቀል እየጋገሩ ለሆቴሎች፣ ለሱፐር ማርኬቶች፣ ለሱቆችና ለምግብ ቤቶች በስፋት ሲያከፋፍሉ ቆይተዋል፡፡ ድርጊቱ በከተማዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተፈፀመ እንደሚገኝና የተፈጨውን ሰጋቱራና የጀሶ ዱቄት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በመጪው ቅዳሜ የ39 ሺ ቤቶች እጣ ይወጣል

የቤት እድለኞች፤ ከ14 ሺ - 95 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ይጠበቅባቸዋልእጣው የሚወጣው በ97 ዓ.ም ለተመዘገቡ ነውየ10/90 ሁሉም ተመዝጋቢዎች፣የቤት ባለ ዕድል ይሆናሉከ6 ወር በላይ ቁጠባ ያቋረጠ፣ እጣ ውስጥ አይገባም20 በመቶ ቅድመ ክፍያና የቤቶቹ ዋጋ ዝርዝር  የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ 39ሺህ ቤቶች ዕጣ ከሚወጣባቸው ቤቶች መካከል ግማሾቹ በ10/90 ለተመዘገቡ ነዋሪዎች የተገነቡ ቤቶች ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ቤቶች በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው ሲጠባበቁ ለነበሩ ነዋሪዎች የተመደቡ ናቸው፡፡ ለ10/90 የተመዘገቡ ሁለት ሺ ነዋሪዎች የቁጠባ ሂሳብ መክፈል በማቋረጣቸው እጣ ውስጥ አይገቡም ተብሏል፡፡ ቁጠባ ያላቋረጡ 19 ሺ ተመዝጋቢዎች ግን ሁሉም፣ ቤት ያገኛሉ - ለሁሉም የሚበቃ ቤት ተገንብቷል፡፡ ከ850 ሺ የሚበልጠው አብዛኛው ቤት ፈላጊ ግን የ97 ዓ.ም ነባር ተመዝጋቢዎች ናቸው፡፡ ለእነዚህ ወደ ሃያ ሺ ገደማ ቤቶች ቀርበዋል፡፡ ግን ሁሉም ነባር ተመዝጋቢ እጣ ውስጥ አይገባም፡፡ ቢያንስ ለ29 ወራት የቁጠባ ሂሳብ የከፈሉ ተመዝጋቢዎች ናቸው እጣ ውስጥ የሚገቡት ተብሏል፡፡ ለስቱዲዮ 4,379 ብር፣ ለባለ አንድ መኝታ 7,946 ብር፣ ለባለ ሁለት መኝታ 16ሺ269 ብር እንዲሁም ለባለ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

መንግስት ቤት ለፈረሰባቸው ተለዋጭ ቤት መስጠት አለበት – የህግ ባለሙያዎች

“በወረዳ አመራሮች የሚሰሩ ስህተቶች መንግስትን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለው ነው”   መንግስት ‹‹ህገ ወጥ›› ያላቸውን ቤቶች ያፈረሠበት መንገድ በአለማቀፍ የሠብአዊ መብቶች ድንጋጌና በህግ ተቀባይነት እንደሌለው የገለጹ የህግ ባለሙያዎች፤ድርጊቱ የህግ ተጠያቂነትን ሊያስከትል እንደሚችል ተናገሩ፡፡ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ዜጎች፣መንግስት ተለዋጭ ቤት መስጠት አለበትም ብለዋል - የህግ ባለሙያዎቹ፡፡  ዓለማቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት፤ማንኛውም ሰው ደህንነቱ እንዲጠበቅና መኖሪያ ቤቱ እንዲከበር በፅኑ ይደነግጋል ያሉት አለማቀፍ የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ወ/ማርያም፤በተለያዩ የሠብዓዊ መብት ስምምነቶች፣ የመኖሪያ ቤት ጉዳይ በዋናነት ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡   ‹‹ሠዎች ህገ-ወጥ ቤት ቢሠሩ እንኳን ቤቶቹ ሲሠሩ በዝምታ የታለፉ እንደመሆናቸው በድጋሚ አይፈርሱም›› ያሉት ዶ/ር ያዕቆብ፤ ‹‹በተለያዩ ሃገራት በህገ ወጥ መንገድ ቤት የሠሩ ሰዎች ካሳ ከፍለው ቤቱ ህጋዊ ይሆንላቸዋል” ሲሉ የሌሎች አገራትን ተመክሮ ጠቅሰዋል፡፡ በቅርቡ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያፈረሳቸው ቤቶች አፈራረስም የኢትዮጵያንም ሆነ ዓለማቀፍ የሠብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን የጣሰና ዜጎችን ያለ አግባብ ለእንግልት የዳረገ ነው የሚሉት የህግ ባለሙያው፤ ‹‹የከተማ አስተዳደሩ የግድ ማፍረስ አለብኝ ካለም በቅድሚያ ቤት ሊያዘጋጅላቸው ወይም ቤት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞና ግጭት አገርሽቷል

- “አውዳሚ የሆኑ ኃይሎች የፈጠሩት እንጂ የህዝብ ተቃውሞ አይደለም”- “የተደራጀ ጥያቄ ስላልቀረበ በጎንደር ሠላማዊ ሰልፍ አይኖርም” የክልሉ መንግስት   በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ተቃውሞ አገርሽቶ፣ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች አይለው መሰንበታቸው የተጠቆመ ሲሆን መንግስት የማረጋጋት ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በክልሉ አርሲ ዞን ዶዶላ፣ አሣሣ፣ በቆናጂ ከተሞች፣ በምዕራብ ሃረርጌ እንዲሁም በምዕራብ ሸዋ አካባቢ ነዋሪዎች ካለፈው ሠኞ ጀምሮ ወደ የከተሞቹ የሚያስገቡ መንገዶችን በድንጋይ በመዘጋጋት ተቃውሞአቸውን ሲገልፁ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ከአርሲ ወደ ባሌ የሚሄደው ዋናው መንገድም እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ ተዘግቶ እንደነበር ምንጮች ለአዲስ አድማስ የጠቆሙ ሲሆን በተቃውሞው ላይ የክልሉን መንግስት የሚያወግዙ መፈክሮች መስተጋባታቸው ታውቋል፡፡ የፀጥታ ሐይሎች ተቃውሞውን ለማብረድ በአብዛኛው የአስለቃሽ ጭስ ሲጠቀሙ እንደነበር የገለፁት ነዋሪነታቸው በአርሲ ዶዶላ የሆነ ምንጮች፤ በፀጥታ ሃይሎችና በተቃዋሚዎች መካከል የከፋ ግጭት አለመከሰቱን ጠቁመዋል፡፡ከሠሞኑ በተጠቀሱት አካባቢዎች ችግሮችን መፈጠራቸውን ያረጋገጡት የመንግስት ኮሚኒኬሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መሃመድ ሰዒድ፤ “በየአካባቢዎቹ ተደራጅተው አውዳሚ የሆነ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሃይሎች የፈጠሩት ችግር እንጂ የህዝብ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

750 ታክሲዎች አገልግሎት መስጠት ሊጀምሩ ነው

በኪ.ሜ የሚያስከፍሉ ናቸው ተብሏል    በአዲስ አበባ በኪሎ ሜትር የሚያስከፍሉ 750 ታክሲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገለጸ፡፡ መንግስት በትናንሽ ታክሲዎች አገልግሎት ላይ የተሠማሩ ባለንብረቶች፣ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ፣ከ800 በላይ የሆኑ ግለሠቦች በጋራ በመደራጀት፣የተሽከርካሪዎቹን ግዢ ከቻይናው ሊፋን ሞተርስ ጋር መፈጸማቸውን ተወካዮቹ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ እያንዳንዳቸው 4 ተሣፋሪዎችን የመጫን አቅም ያላቸው ሊፋን 530 የተሠኙ 750 ተሽከርካሪዎች ተገዝተው ወደ ሃገር ውስጥ በመግባት ላይ መሆናቸውን የገለፁት ተወካዮቹ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በመላዋ አዲስ አበባ መንግስት በሚያወጣውና በሚቆጣጠረው ታሪፍ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል፡፡ አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችል በዘመናዊ ማዕከል የተደራጀና የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ የጉዞ ደህንነት የሚያረጋግጥ አክሲዮን ማህበር መቋቋሙን የገለፁት ተወካዮቹ፤ተሽከርካሪዎቹ  ኢንሹራንስ የተገባላቸው በመሆኑ ለተሣፋሪዎች ዋስትና ይሰጣሉ ብለዋል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ ዘመኑ የደረሰበትን የታክሲ አገልግሎት እንዲሠጡ ተደርገው የተዘጋጁ መሆኑን ያስረዱት ተወካዮቹ፤መንግስት በሚያወጣው ታሪፍ በኪሎ ሜትር ከማስከፈላቸውም በላይ ጂፒ ኤስ የተገጠመላቸው በመሆኑ በተሽከርካሪዎቹ አገልግሎት ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡ የታክሲ አገልግሎት የሚፈልግ ተጠቃሚ፣ አገልግሎቱ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

መሰቦ ሲሚንቶ ደንበኞቹን ሸለመ

የደንበኞች ቀንን ለ3ኛ ጊዜ ያከበረው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ፤የገበያ ድርሻዬን አሳድገውልኛል ፣አጋርም ሆነውኛል ያላቸውን ደንበኞቹን ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 16 ቀን፣ በባህር ዳር ከተማ ሸለመ፡፡ የሲሚንቶ ምርቶቹን በማጓጓዝና ምርቶቹን በመጠቀም ሁነኛ ደንበኞቼ ናቸው ያላቸውን በርካታ ድርጅቶች ፋብሪካው በተለያዩ ደረጃዎች የሸለመ ሲሆን በትራንስፖርት ዘርፍ የላቀ ተሸላሚ በመሆን ትራንስ ኢትዮጵያ ተጠቃሽ ነው፡፡ ምርቶቹን በማስፋፋት ደግሞ ጉና ትሬዲንግ ተሸልሟል፡፡ ምርቶቹን በመጠቀም የላቀ ሽልማት ከተሰጣቸው መካከል የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፅ/ቤትና የህዳሴውን ግድብ የሚገነባው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡  የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ክብረአብ ተወልደ፤ፋብሪካው ዋነኛ ችግሩ ምርቶቹን በራሱ ትራንስፖርት ማጓጓዝ አለመቻሉ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይ በራሱ ትራንስፖርት ለማጓጓዝ  200 ተሽከርካሪዎችን በ877 ሚሊዬን ብር መግዛቱን ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ፋብሪካው ምርቶቹን የሚያሰራጨው ከግል ትራንስፖርት ሰጪዎች ጋር ውለታ በመግባት እንደነበርም ሥራ አስኪያጁ አውስተዋል፡፡  መሰቦ ሲሚንቶ፤ ግልገል ጊቤ 1, 2 እና 3 እንዲሁም ታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ለመንግስት የተለያዩ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች ምርቶቹን እያቀረበ ሲሆን በሀገሪቱ የገበያ ድርሻውም ወደ 24 በመቶ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

2 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በግብጽ ራሳቸውን አቃጠሉ

ላቀረብነው የጥገኝነት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠንም በሚል በግብጽ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ ፊት ለፊት ባለፈው ማክሰኞ ተቃውሞ ካሰሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል ሁለቱ ራሳቸውን በእሳት ማቃጠላቸውን ‹‹ዴይሊ ኒውስ ኢጂፕት›› ዘገበ፡፡የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ምላሹን ሲጠባበቁ የቆዩ የኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ የተነገረላቸው ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፤ 6ኛው ኦክቶበር ሲቲ በሚባለው አካባቢ ከሚገኘው የኮሚሽኑ ቢሮ ፊት ለፊት ራሳቸውን በእሳት አቃጥለዋል ያለው ዘገባው፣ ኢትዮጵያውያኑ ድርጊቱን የፈጸሙት በግብጽ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች የጥገኝነት መብታቸው እንዲከበር ካደረጉት ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው መባሉን ገልጧል፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ረቡዕ ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ በተቃውሞው ወቅት ለህልፈተ ህይወት በተዳረገቺው አንዲት የኦሮሞ ተወላጅ  ሞት የተሰማውን ሃዘን እንደገለጸ የጠቆመው ዘገባው፤ ይሄም ሆኖ ግን ኮሚሽኑ ሟቿ የሁለት ልጆች እናት መሆኗን ከመጥቀስ ውጭ ለህልፈተ ህይወት የተዳረገቺው ራሷን አቃጥላ ስለመሆኑ በግልጽ ያለው ነገር እንደሌለ ገልጧል፡፡“በግብጽ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ፣ የአቀባበል ስርዓቱ ረጅም ጊዜን የሚወስድ መሆኑ፤ በጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ላይ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፤ በህንጻዎች ተንበሸበሸ

• ከ60 ሚ.ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን 4 ህንጻዎች ተረክቧል• የአዲስ አበባን ጨምሮ በ4 ከተሞች ተጨማሪ ህንፃዎች እያስገነባ ነው  የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የአገልግሎት መስጪያ ጣቢያዎችን ደረጃ ለማሳደግ ባስቀመጠው መርሐ ግብር መሰረት፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ህንፃዎችን በማስገንባት ላይ ሲሆን በአራት ከተሞች ከ60 ሚ. ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን ህንፃዎች መረከቡን አስታውቋል፡፡ በአርባ ምንጭ ባለ ሁለት ወለል፤ በወልቂጤ፣ በነቀምትና በወሊሶ ከተሞች ባለ ሦስት ወለል ህንፃዎች ነው፤የፖስታ አገልግሎት ድርጅት ያስገነባው፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ በቱሪስት ሆቴል አካባቢ ባለ አራት ወለል፤ በሽሬ ባለ ሦስት ወለል፣ በደብረ ታቦር ባለ  ሦስት ወለል፣ በወልዲያ ባለ ሦስት ወለል ህንፃ በአጠቃላይ በ45 ሚ. ብር የ4 ሕንፃዎች ግንባታ በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ግንባታዎቹ በመጪው ዓመት ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ፤በአዳማ ባለ ሰባት ወለል፣ በአሰላ ባለ አምስት ወለል፣ በጂግጂጋ ባለ አራት ወለል ህንጻዎችን ለማስገንባትም በዝግጅት ላይ መሆኑን ያስታወቀው ድርጅቱ፤በቀጣይም በአዲግራት፣ በዝዋይ፣ በአላማጣና በአሰበ ተፈሪ ከተማዎች የሕንፃ ግንባታ ለማካሄድ ማቀዱን ጠቁሟል፡፡  ርክክብ የተፈጸመባቸውም
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ለ9 ቀናት የረሃብ አድማ ላይ የነበሩ የሽብር ተከሳሽ ፖለቲከኞች መመገብ ጀምረዋል

በማረሚያ ቤት አያያዝ ተበድለናል ያሉት የሽብር ተካሳሾቹ የአሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ አመራሮችና የሠማያዊ ፓርቲ አባላት ላለፉት 9 ቀናት የረሃብ አድማ ያደረጉ ሲሆን ከማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ትናንት መመገብ መጀመራቸውን የረሃብ አድማ ካደረጉት አንዱ የሆኑት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለፍ/ቤት አስረድተዋል፡፡መንግስት በኦሮሚያ ከተቀሠቀሰው ግጭትና ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ሲል ክስ ያቀረበባቸውና በቂሊንቶ ማረሚያ ቤት የሚገኙት የአፌኮ ተ/ም/ሊቀ መንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የፓርቲ አመራሮች፡- አቶ ገርሣ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጠፋ እና አቶ አዲሱ ቡላላ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ በሌላ ጉዳይ በሽብር የታሰሩት አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ አቶ ፍቅረ ማርያም አስማማውና ማስረሻ ሰጠኝ በረሃብ አድማ ላይ መሠንበታቸው ታውቋል፡፡ተከሳሶቹ “በማረሚያ ቤቱ ከሌሎች እስረኞች ተለይተን በጨለማ ክፍል ውስጥ መታሠር የለብንም፤ በቤተሰብም እንዳንጠየቅ ተደርገናል” በሚል የረሀቡን አድማ ላለፉት ማድረጋቸውን የአቶ ዮናታን ተስፋዬ ጠበቃ አቶ ሽብሩ በለጠ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ የረሃብ አድማውን ካደረጉት መካከል ትናንት ፍ/ቤት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ከንቲባውን ጨምሮ የከተማዋ ባለስልጣናት በቆሻሻው ጉዳይ በስብሰባ ተወጥረዋል

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን ጨምሮ ዋና ዋና የከተማዋ ባለስልጣናት፤ በተለያዩ አካባቢዎች ከሳምንት ባላይ ሳይነሱ ለቆዩት የደረቅ ቆሻሻ ክምችቶች መፍትሄ ለማግኘት በስብሰባ ተወጥረው መሰንበታቸው ተገለፀ፡፡ በጉዳዩ ላይ የአስተዳደሩን ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ከንቲባው ቢሮ በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም፤ “ኃላፊዎቹ ከቢሮ ውጪ በኦሮሚያ ክልል በስብሰባ ላይ ናቸው” በሚል ሙከራችን ሳይሳካ ቀርቷል፡፡በኦሮሚያ ክልል ሰንደፋ ከተማ አካባቢ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ የአዲስ አበባ ቆሻሻ እንዳይጣል በአካባቢው አርሶአደሮች መከልከሉን ተከትሎ ከሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የከተማዋን ቆሻሻ ወደ ስፍራው ወስዶ መጣል አልተቻለም። ይሄን ተከትሎ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች (ዋና ዋና ጎዳናዎችና አደባባዮችን ጨምሮ) የቆሻሻ ክምር ተቆልሎ ሰንብቷል፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የከተማዋ አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር ሲያደርግ የነበረው ውይይትና ድርድር ሳይሳካ መቅረቱ የተገለፀ ቢሆንም ባለስልጣናቱ ትላንት ድረስ በዚሁ ጉዳይ በስብሰባ ላይ እንደነበሩ ከንቲባው ፀሃፊ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከሳምንት በላይ በየአካባቢው ተጠራቅሞ የቆየው የደረቅ ቆሻሻ፤ ነዋሪውን ለከፍተኛ የጤና ችግር እየዳረገው መሆኑን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአተት ወረርሽኝ በቀጣዮቹ ሳምንታት ይባባሳል ተባለ

- በከተማዋ 80 ሆቴሎችና 12 የጤና ተቋማት ታሸጉ- 10 ሺ ኪሎ ምግብና 1200 ኪሎ ሥጋ ተወገደ   በአዲስ አበባ ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም መከሰቱ በይፋ በተገለፀው የአተት በሽታ የሚያዙ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን በሽታው በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት እንደሚችልና በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚባባስ የዩኤን የረድኤት ማስተባበሪያ አስታወቀ፡፡ በሽታው ከጎርፍ መከሰት ጋር ተያይዞ የሚስፋፋ መሆኑን የጠቆመው መረጃው፤ በመጪው ነሀሴ ወር ሊባባስ እንደሚችል አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል በከተማዋ ለህብረተሰቡ ንፅህና የጎደለው አገልግሎት ሲሰጡ ተገኝተዋል የተባሉ ከ80 በላይ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶችን ማሸጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል፡፡ሰሞኑን በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች ላይ ድንገተኛ ፍተሻና ቁጥጥር ሲያካሄድ መሰንበቱን የጠቆመው ባለሥልጣን መ/ቤቱ፤ የመመገቢያና የማብሰያ ዕቃዎቻቸው ንፅህና በአግባቡ ያልተያዘ፣ በቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓታቸው ላይ ጉድለት የተገኘባቸውና ንፅህናውን የጠበቀ የምግብና መጠጥ አገልግሎት አልሰጡም ያላቸውን ከ80 በላይ ምግብ ቤቶች፤ ሆቴሎችና መጠጥ ቤቶች ማሸጉን አስታውቋል። በፍተሻው ወቅት የተገኙና ከአተት በሽታ ጋር ተያይዞ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ተቃዋሚዎች፤ የሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች አሳሳቢ ሆነዋል አሉ

· ኢዴፓ የብሄራዊ እርቅ መድረክ እንዲፈጠር ጠየቀ    የአገሪቱን ወቅታዊ ችግሮች በመጥቀስ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ማበጀት እንዳለበት የገለፁት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ችግሮቹ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ሲሉ አስጠነቀቁ የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ለፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በፃፈው ደብዳቤ፤ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት መገምገሙን ጠቅሶ፤ መንግስት በመላ ሀገሪቱ ሰላምና ዲሞክራሲ በማስፈን፣ ለህዝቡ የተረጋጋ ህይወት ማስፈን አልቻለም ብሏል፡፡ በኦሮሚያ የተፈጠረው ግጭትና ተቃውሞ፣ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ላደረሰው ጥፋት እስካሁን ዘላቂ መፍትሄ አለመቀመጡን የጠቀሰው ፓርቲው፤ በአማራ ክልልም በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ መነሻነት የተፈጠረው ግጭት በተመሳሳይ መልኩ ለሰው ህይወት መጥፋትና ለብረት መውደም ምክንያት መሆኑ ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክ/ከተሞች ህገ ወጥ እየተባሉ ቤቶች በመፍረሳቸው፣ ዜጎች ያለ መጠለያ መቅረታቸውን ያወገዘው መኢአድ፤ ለእነዚህ ወቅታዊ ችግሮች መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቋል፡፡ ፓርቲው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና ለፌደሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤዎችም ደብዳቤውን እንደላከ ገልጿል፡፡  ፓርቲው እነዚህን በመሳሰሉ ወቅታዊ ችግሮች ላይ ለጠቅላይ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዶሮ የወባ በሽታ መከላከያ ሆናለች

የኢትዮጵያና የስዊድን ሳይንቲስቶች ለወባ በሽታ አማጭ ትንኝ መከላከያ ያገኙት የምርምር ውጤት አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በህይወት ያለች ዶሮ መኝታ አጠገብ ማስቀመጥ የወባ ትንኝን ድርሽ እንዳይል ያደርጋል ብለዋል፤ ተመራማሪዎቹ፡፡ ከዶሮና ከወፎች የሚወጣው የተፈጥሮ ሽታ ለወባ ትንኝ ጠላቷ ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ በየዓመቱ በአፍሪካ ወደ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ለሚገድለው የወባ በሽታ ፍቱን መፍትሄ ይሆናል ብለዋል፡፡ ቢቢሲ ተመራማሪዎቹን ተጠቅሶ እንደዘገበው፤ በምዕራብ ኦትዮጵያ ወባማ አካባቢ ፍቃደኛ በሆኑ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት መኝታ አጠገብ፣ ዶሮ በማስቀመጥ ያደረጉት ሙከራ የተሳካ ነበር ብሏል፡፡ የወባ ትንኝ የሚያባርረው የዶሮ ወይም የወፍ ጠረን መሆኑን ደርሰንበታል ያሉት ተመራማሪዎቹ የምርምር ውጤቱን በሰፊው ለመሞከር በሂደት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ የምርም ቡድኑ አባልና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሀብቴ ተክኤ፤ ከዶሮዎች የሚወጣውን ጠረን በመውሰድ የመከላከያ መንገድ ለማበጀት እየተሞከረ ነው ብለዋል፡፡ ዶሮዎች በብዛት ባሉበት አካባቢ የወባ ትንኝ መጠን እንደሚቀንስ ማስተዋላቸውን ተከትሎ የምርምር ስራቸውን በጥልቀት ማከናወን መቀጠላቸውን ተመራማሪዎቹ ለቢቢሲ ገልፀዋል፡፡  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የታላቁ የቲያትር ባለሙያ አባተ መኩሪያ፣ የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈፀመ

የኢትዮጵያ የቴያትር አባት እየተባለ የሚጠራውና በተወለደ በ72 አመቱ ከትናንት በስቲያ ከዚህ አለም በሞት የተለየው፣ የአንጋፋው የቲያትር አዘጋጅ የአባተ መኩሪያ የቀብር ስነ ስርዓት ትናንት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ቴአትር ፈር ቀዳጅነቱ የሚታወቀው አባተ መኩሪያ፤ ከጥቂት ወራት በፊት በጠና ታምሞ አገር ውስጥ የቀዶ ጥገና ህክምና ቢደረግለትም፣ ጤናው ሊመለስ ባለመቻሉ ለተሻለ ህክምና ወደ ግብጽ ሄዶ ነበር፡፡ ከወር በፊት ህክምናውን ተከታትሎ ወደ አገሩ የተመለሰው አባተ መኩሪያ፣ በቅርቡ በገጠመው የፕሮስቴት እጢ፣ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ቢደረግለትም ህይወቱን ማትረፍ ባለመቻሉ ከትናንት በስቲያ ሐምሌ 13 ቀን 2008 ዓ.ም ምሽት ላይ ህይወቱ አልፏል፡፡  ህዳር 10 ቀን 1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ አቧሬ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር አካባቢ የተወለደው ፀሃፌ-ተውኔት፣ የፊልም ዳይሬክተርና የቴአትር አዘጋጅ የነበረው አባተ መኩሪያ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ለአምስት ዓመታት በመምህርነት ያገለገለ ሲሆን፣ በብሄራዊ ቲያትር በአርት ዳይሬክተርነት፣ በአዲስ አበባ ባህል ማዕከል በዋና ሥራ አስኪያጅነትና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመዝናኛ ክፍል፣ በከፍተኛ አዘጋጅነት ሰርቷል፡፡ ሀሁ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“በአቃቂ 15 ሺህ ቤቶች ይፈርሳሉ”

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች፣ “ሜዳ ላይ ወድቀናል” ሲሉ እያማረሩ ሲሆን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከረቡዕ ጀምሮ “ህገ ወጥ” የተባሉ ቤቶች እየፈረሱ ነው፡፡ በላፍቶ ከሚፈርሱ 20 ሺህ ቤቶች በተጨማሪ በአቃቂ 15 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱም ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በህገወጥ የመሬት ወረራ የተሰሩ ናቸው በሚል በንፋስ ስልክ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ እንደሆነ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ በርካታች ተፈናቃዮች እዚያው የፈራረሰ ሰፈር ውስጥ፣ የፕላስቲክና ቆርቆሮ ዳሶችን በመስራት ለመኖር መገደዳቸውን ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን በአቃቂ ቃሊቲ በተጀመረው የማፍረስ ዘመቻ 15 ሺ መኖሪያ ቤቶች እንደሚፈርሱ ምንጮች ለአዲስ አድማስ የጠቆሙ ሲሆን፤ ቤቶቹ እንደ ንፋስ ስልክ ላፍቶዎቹ በግሬደር ሳይሆን በአፍራሽ ግብረሃይል እንዲፈርሱ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡  ትናንት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፤ በህገወጥ ወረራ የተመሠረቱ ሠፈራዎችን የማፍረስ ስራ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ መንግስት እስከ 1997 በህገ ወጥ እንቅስቃሴ የተሠሩ ቤቶችን ተቀብሎ ማጽደቁን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ “ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም አንዳንድ ባለሃብቶች በርካታ ሰው አሰማርተው ሰፈራ ካቋቋሙ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በጎንደሩ ግጭት የበርካቶች ህይወት አልፏል ተባለ

ባለፈው ማክሰኞ በጎንደር ከተማ በነዋሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የበርካቶች ህይወት ማለፉ የተገለፀ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ በግጭቱ የ3 ፖሊሶችና 2 ነዋሪዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡ የሟቾችን ቁጥር በተመለከተ በተለያዩ (የሚዲያዎች የተገለፁ መረጃዎች ይለያያሉ፡፡ አልጀዚራ የአይን እማኞችን ጠቅሶ 10 ሰዎች መሞታቸውን ሲዘግብ፤ ሌሎች ሚዲያዎች የሟቾች ቁጥር እስከ 20 ሊደርስ እንደሚችል ዘግበዋል፡፡ማክሰኞ ዕለት 6 የወልቃይት ማንነት ጉዳይ ኮሚቴ አባላትን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ ግጭቱ መቀስቀሱ የተገለፀ ሲሆን ፖሊስ 4ቱን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና 2ቱ እስካሁን እንዳልተያዙ አስታውቋል፡፡ በተለይ አንደኛውን ተጠርጣሪ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ፖሊስ ለመያዝ ሙከራ ባደረገበት ወቅት በተከፈተ ተኩስ የነዋሪዎችና የፖሊስ አባላት ህይወት ጠፍቷል ተብሏል፡፡ ትናንት ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ የሠጡት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ‹‹ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ፖሊስ ሁለቱን ለመያዝ ጥረት ሲያደርግ ቦንብ በመወርወር፣ አውቶማቲክ መሣሪያዎችን ተጠቅመው በፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ በመክፈት በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ገድለዋል›› ብለዋል፡፡ማክሰኞ እለት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ረቡዕ እለት በርካታ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ቤታቸው የፈረሰባቸው፣“የመንግስት ያለህ!” እያሉ ነው

በቅርቡ በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ‹ማንጎ› በተባለው አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች “መውደቂያ፣ መድረሻአጥተናል፤ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እየተጋፋን ለመኖር ተገድደናል” ሲሉ እያማረሩ ይገኛሉ፡፡ እስካሁን የት ናችሁ ብሎ ያነጋገራቸውየመንግስት አካል እንደሌለና አስታዋሽ አጥተው እንደተጣሉ እኚሁ ተፈናቃዮች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ከነልጆቻቸው በክረምትዝናብና ጭቃ ሜዳ ላይ ወድቀው እየተሰቃዩ መሆኑን በምሬት የሚያስረዱት አባወራና እማወራዎቹ፤መንግስት የኤርትራ ስደተኞችን እንኳንካምፕ አዘጋጅቶ እየተቀበለ መሆኑን ጠቁመው ለዜጎቹ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል፡፡ ቤታቸው ፈርሶ በማንጎ ጫካ ከተጠለሉነዋሪዎች ሶስቱ ስለቀድሞ አሰፋፈራቸውና አሁን ስላሉበት አስከፊ ሁኔታ እንደሚከተለው ገልጸዋል፡፡ “የመንግስት ያለህ!” እያሉም ነው፡፡ “የሚደርስልን አካል ካለ ይድረስልን!”(አዛውንቱ ሃጂ አብደላ ሁሴን ቤታቸው ከፈረሰባቸው አንዱ ናቸው፡፡ እርጅና የተጫናቸው ሃጂ አብደላ እንባቸውን እያፈሰሱ ያሉበትን ሁኔታ ተናግረዋል፡፡)“---ይፈርሳል ተብለው ቀደም ሲል ተነግሯቸው ሲከራከሩ የነበሩት ቀርሳ ኮንቶማና ኤርቶ ሞጆ የሚባል አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች እንጂ እኛ የማንጎ አካባቢ ነዋሪዎች ይፈርሳል ተብለን አናውቅም፡፡ የነሱን ነበር እየሠማን የነበረው፡፡ እነሱ አመት ከመንፈቅ በዚህ ጉዳይ ሲከራከሩ  ነበር፤ ነገር ግን ቤታችን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት የመልካም ተሞክሮ ቀን አከበረ

ኢየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት፤ የማህበረሰብ ምስረታ ተቋማት የመልካም ተሞክሮ ቀን በዓል አከበረ፡፡ ድርጅቱ ሰሞኑን በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በሚገኘውና የጄክዶ አፖርቹኒቲ ፎር ቼንጅ እየተባለ በሚጠራው የስልጠና ማዕከሉ ውስጥ ባከበረው በዚሁ የመልካም ተሞክሮ ቀን ክብረ በዓል ላይ የማህበረሰብ ምስርት ተቋማቱ ተወካዮች ተገኝተው ከድርጅቱ ጋር በማከናወን ላይ ስለሚገኙት የልማት ስራዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡ “የማህበረሰብ ምስርት ተቋማት አጋርነት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል በተከናወነው በዚህ የመልካም ተሞክሮ ቀን በዓል ላይ ተሞክሮአቸውን ለማካፈል ከተገኙት የማህበረሰብ ምስርት ተቋማት መካከል ዕድሮች፣ ማህበራትና የልማት ድርጅቶች ይገኙበታል፡፡ የእየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ገብሩ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ ከ140 በላይ የማህበረሰብ ምስርት ተቋማት ጋር በአጋርነት የሚሰራ ሲሆን በተለያዩ የልማት መስኮች በሺዎች የሚቆጠሩ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል ብለዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“መመሪያችን፡- ቅንጦትን ሁሉም ሰው እንዲገዛው ማድረግ ነው”

• ሆቴሎች የሰለጠነ ባለሙያ ከሚሰራረቁ በጥምረት ቢሰሩ የበለጠ ያድጋሉ• ዋጋው የቱሪስቶችንና የከተማዋን ነዋሪ አቅም ያገናዘበ ነው     ዓርማው ዘውድ ነው - ስሙም ሞናርክ፡፡ ትርጉሙ “እንግዶች ስትመጡ የንጉሥ መስተንግዶ ይደረግላችኋል” ማለት ነው ይላሉ፤የሆቴሉ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ያየህይራድ የምወደው፡፡ ንጉሥ ፈልጎና ጠይቆ የሚያጣው ነገር እንደሌለ ሁሉ እናንተም ተደስታችሁ እንድትሄዱና በሌላ ጊዜ ሌላ ሰው ይዛችሁ እንድትመጡ የጠየቃችሁትና የፈለጋችሁት ሁሉ ይሟላላችኋል፤ ሲሉም ያብራራሉ - የማርኬቲንግ ዳይሬክተሩ፡፡  እንግዶች ወደ ሆቴሉ ሲገቡ በስተቀኝ የመዋናኛ ስፍራ ያለው ሲሆን አስደሳችና መንፈስ የሚያድስ ግቢም አለው፡፡ በስተግራ ባር ሬስቶራንትና ካፌ ያገኛሉ፡፡ እውስጥ ካለው ጋር ሁለት ባርና ሁለት ሬስቶራንት ማለት ነው፡፡ ደጅ ባለው ሬስቶራንት እንግዶች እያዩ የሚሰናዳው ፒዛና ባርቢኪው ተወዳጅ ነው፡፡ ባርቢኪው የሆቴሉ ተመራጭ ምግብ እንደሆነ አቶ ያየህ ይራድ ይናገራሉ፡፡ ሐሙስና አርብ ላይቭ የሙዚቃ ዝግጅት ያቀርባል፡፡ ሆቴሉ 74 የመኝታ ክፍሎችና 3 የመሰብሰቢያ አዳራሾች አሉት፡፡ 350 ክፍሎች የሚኖሩት የሆቴል ማስፋፊያ በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተነግሯል።  ሆቴሉ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ንብረት ነው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ጥርስን ያለ ድሪልና ያለማደንዘዣ አፅድቶ የሚሞላ መሳሪያ አገራችን ገባ

የአርጀንቲናው አሊሚኔተር ግሩፕ የቬንዳኖቫ ምርት የሆነውና ላለፉት አራት ዓመታት በአርጀንቲና ጥቅም ላይ የዋለውን ጥርስን ያለ መቦርቦሪያ ድሪልና ያለ ማደንዘዣ አፅድቶ የሚሞላው መሳሪያ ሰሞኑን አገራችን ገባ፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና የተሰጠውና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አገር ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ የተሰጠው ይሄው መሳሪያ ከተፈጥሮአዊ እፅዋት በሚሰራ ጄል ያለ ማደንዘዣና ያለ ድሪል ጥርስን በማፅዳት የሚሞላ ሲሆን አንድ ሰው በ10 ደቂቃ ውስጥ ጥርሱ ፀድቶና ተሞልቶ ወደቤቱ እንዲሄድ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ የአምራች ድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ጆርጅ ሌይንና የኢትዮጵያ ወኪሉ ሚረር ‹ትሬዲንግና ሰርቪስ› ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋየየ ወንድሙ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በሂልተን ሆቴል  በሰጡት መግለጫ፤ መጀመሪያ ምርቱ በጥርስ ህመም የሚሰቃዩ ህፃናትን ታሳቢ አድርጎ የተሰራ እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት አዋቂዎችም በስፋት እየተጠቀሙበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡በሁለቱ ኩባንያዎች መካከል በዕለቱ የ50 ሚ. ዶላር ስምምነት የተደረገ ሲሆን መሳሪያውን በዋና በወኪልነት ሚረር ትሬዲንግና ሰርቪስ እንደሚያከፋፍልና ከአርጀንቲና የሀኪሞች ቡድን እንደሚመጣና ለኢትዮጵያዊያን የጥርስ ሀኪሞች ስለመሳሪያው አጠቃቀም ስልጠና እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ አንዱ መሳሪያ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮ ሴራሚክስ 5ኛውን ትልቅና ዘመናዊ ሾውሩም በቦሌ ከፈተ

ላለፉት 20 ዓመታት ከተለያዩ የዓለም አገራት የባኞ ቤት የህንፃ ማጠናቀቂያ (Finishing) የሳውና የጃኩዚና መሰል የሴራሚክ ምርቶችን በማስመጣት ለአገር ውስጥ ገበያ ሲያቀርብ የቆየው ኢትዮ ሴራሚክስ፤ አምስተኛውን ትልቅና ዘመናዊ የሴራሚክስ መሸጫ ማዕከል ቦሌ ኖቪስ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት አዲስ በገነባው ህንፃ ላይ ከፈተ፡፡ ከትላንት በስቲያ በይፋ ስራ የጀመረው ይሄው መደብር፤ ከሌሎቹ መደብሮች በተለየ የተደራጀና እቃዎች ተገጣጥመው ዲስፕሌይ የተደረጉበት ሲሆን ማንኛውም ደንበኛ እቃዎቹን ሲገዛ ምን እንደሚመስሉና ምን ቅርፅ እንደሚኖራቸው በማየት የሚገዛውን ለመወሰን እንዲችል የሚረዱ መሆናቸው በእለቱ ተገልጿል፡፡ከዱባይ፣ ስፔይን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ ጀርመንና ከቻይና የመጡ የሴራሚክስ እቃዎች እንደየመጡበት አገርና ሁኔታ ተለይተው የተቀመጡ ሲሆን በአገራችን የቤት ውስጥ ዲዛይነር ህንፃው ላይ ተሰርተው ተቀምጠዋል፡፡ በ1ኛና 2ኛ ፎቅ ላይ በአይነት በአይነት የተደረደሩ የተለያዩ አገራት የሴራሚክስ ውጤቶች የቀረቡ ሲሆን 3ኛ እና 4ኛ ፎቅ ላይ ደረጃቸውን የጠበቁ ሶፋዎች፣ አልጋዎች፣ የቢሮና የመመገቢያ ወንበርና ጠረጴዛዎች፣ ቁም ሳጥኖች ይገኙበታል “ይህ የሽያጭ ማዕከሉ አደረጃጀት አንድ ሰው ቤት ሰርቶ ሲያጠናቅቅ ቤቱን ለመጨረስና ሁሉንም እቃ በአንድ ቦታ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዜድቲኢ የዘረጋውን የኤሌክትሪክ መስመር ፕሮጀክት አስረክበ

ዜድቲኢ ኢትዮጵያ በመላው አገሪቱ የዘረጋውን የኦፕቲካል ግራውንድ ዋየር (OPGW) ፕሮጀክት አጠናቅቆ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ በሸራተን አዲስ በተደረገ ስነስርዓት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስረከበ፡፡ በ37 ሚሊዮን ዶላር በመላ አገሪቱ የዘረጋው ይሄው ኦፕቲካል ግራውንድ ፓወር በ17 ተኩል ወራት የተጠናቀቀ ሲሆን 1260 ካ.ሜትር መሸፈኑም በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ የፕሮጀክቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ ሥነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከዜድቲኢ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ሚስተር ሊ ጉዋንግ ዮንግ በተረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ዜድቲኢ ስራውን ከተረከበበት ሰዓት አንስቶ በትጋት በመስራት በታቀደው ሰዓት ማስረከባቸውን ተቁመው ፕሮጀክቱን ያለምንም ችግር ማጠናቀቃቸው ስራውን የበለጠ ስኬታማ አድርጎታል ብለዋል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ሚስተር ሊ ጉዋንግ ዮንግ በበኩላቸው ዜድቲኢ ባለፉት 16 ዓመታት የኢትዮጵያ የመንግስት አጋር ሆኖ በትልልቅ የቴሌኮም ፕሮጀክቶች ላይ ሲሳተፍ መቆየቱን ገልፀው ይህ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የአገሪቱን የሀይል አቅርቦት አስተማማኝነት እንደሚያሳድገው ተናግረዋል፡፡በዕለቱ የፕሮጀክቱ ስራተኞችና አስተባባሪዎች ባቀረቡት አጭር ዘጋቢ ፊልሞና ፎቶ ኤሌክትሪክ ሳይቋረጥ 132
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የትምህርት ሚኒስትሩ የፈተና ወረቀት አልተሰረቀም አሉ

ከሰኞ ሐምሌ 4 ቀን የሚጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሰረቀ በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ድረ-ገፆች የተሰራጨው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን የት/ት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡ 26 የፈተና ወረቀቶች ተሰርቀው መውጣታቸውን አንዳንድ ድረ ገፆች ያስታወቁ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎችም የእንግሊዝኛ ፈተና መሰረቁን የሚያመላክት መረጃዎች ተሰራጭተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ፈተናው ተሰርቋል የተባለው “ውሸት ነው፤ የራሳቸውን የውሸት የፈተና ወረቀት አዘጋጅተው ነው ወሬውን ያሰራጩት” ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል ፈተናው ግንቦት 22 ቀን እንዲካሄድ ታስቦ በነበረበት ወቅት የፈተና ወረቀቶች ስለመሰረቃቸው በተለያዩ ድረ ገፆችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡ መንግት መረጃውን እያስተባበለ ቆይቶ፣ በፈተናው መስጫ እለት ነው በድንገተኛ መግለጫ ፈተናው እንዲቋረጥ የወሰነው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የክብር ዶክትሬት ክብሩን እያጣ ነው ተባለ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ለተመረጡ ግለሰቦች የክብር ዶክትሬት ይሰጣል   በሀገሪቱ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዓመቱ ለሁለትና ሶስት ሰዎች የክብር ዶክትሬት መስጠትን እንደ ልማድ መያዛቸው ከክብር ዶክትሬት መሰረታዊ አላማዎች ጋር የሚፃረርና ክብሩን የሚያራክስ ነው ሲሉ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ፡፡ የክብር ዶክትሬት የሚሰጥባቸው መስፈርቶች በመርፌ ቀዳዳ ግመል እንደ ማሽሎክ ያህል ናቸው ያሉት ምሁራኑ፤ በአሁን ወቅት አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር ፉክክር በሚመስል መልኩ ዶክትሬቱን የሚሰጡበት አካሄድ በአስቸኳይ ሊታረም እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ የክብር ዶክትሬቱ የተሰጠባቸው ግለሰቦችም ለስም መጠሪያነት መጠቀማቸው ተገቢ አይደለም ያሉት ምሁራኑ፤ መገናኛ ብዙኃን የክብር ዶክትሬት የተሰጠውን ግለሰብ፤ “የክብር ዶክተር” እያሉ መጥራታቸውም አግባብ ባለመሆኑ ማረም ይኖርባቸል ብለዋል፡፡ የቋንቋና ስነ ፅሁፍ ምሁሩ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፤ ከሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ለተለያዩ ግለሰቦች የክብር ዶክትሬት የሚሰጥበት ሁኔታ፤ ከማዕረጉ መሰረታዊ አላማ ጋር የተቃረነ መሆኑን አለማቀፍ ልምዶችን በማጣቀስ አስረድተዋል፡፡ በአሁን ወቅት በትምህርት በቅተዋል ተብለው ዶክትሬት ዲግሪ የሚሰጣቸው ምሁራን ምን ያህል ችግር ፈቺ ምርምር ሰርተዋል የሚለው ራሱ ጥያቄ ውስጥ እንደገባ የጠቆሙት ዶ/ር በድሉ፤
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የተቃዋሚ አመራሩ አቶ አብርሃ ደስታ ከእስር ተፈቱ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት የአረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃም ደስታ ትናንት ከእስር ተለቀቁ፡፡ አቶ አብርሃ ደስታ ከሁለት አመት በፊት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ከሰማያዊና ከአንድነት ፓርቲ አመራሮቹ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ጋር በሽብር ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሁለት አመት የቆዩ ሲሆን ከቀረበባቸው ክስ በከፍተኛው ፍ/ቤት በነፃ የተሰናበቱ ቢሆንም አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ጉዳያቸው መቋጫ አለማግኘቱ ይታወሳል፡፡በአቶ አብርሃና ሌሎች የፖለቲካ አመራሮች ላይ የቀረበው የሽብር ክስ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና አባል በመሆን በማንኛውም የሽብር ድርጊት ተሳታፊ መሆን የሚል ሲሆን ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የከፍተኛው ፍ/ቤት 19ኛ ወ/ችሎት፤ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱና ከእስር እንዲለቀቁ ማዘዙ ይታወሳል፡፡ይሁን እንጂ አቶ አብርሃ በነበረባቸው የዲሲፒሊን ቅጣት ምክንያት በእስር ላይ ቆይተው በትናንትናው እለት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ከ4 ሚሊዮን አምፖሎች ውስጥ 15 ሚሊዮኑ ለተጠቃሚ ደርሷል”

አዝናኝ እና አሳዛኝ የመንግስት ሪፖርቶች - በአዲስ መፅሀፍስኳር፣ ኮንዶሚኒዬም፣ ወርቅ፣ ኤሌክትሪክ፣ አውቶቡስ …   ባለፈው ዓመት፣ የስኳር ምርትን 22 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ ታቅዶ አልነበር? ለዚህም፤ ከ200ሺ ሄክታር በላይ አዲስ የእርሻ መሬት ተዘጋጅቶ፣ የስኳር አገዳ ይለማል ተብሎ ነበር - በትራንስፎርሜሽን እቅድ፡፡ ግን አልተሳካም፡፡ የለማው ተጨማሪ መሬት፣ 35ሺ ሄክታር ነው፡፡ ከእቅዱ ጋር ሲነፃፀር፣ 15 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከእቅዱ ውስጥ፣ ሩብ ያህሉን እንኳ ማሳካት አልቻለም፡፡ ነገር ግን፣ ይህንን ውድቀት እንደ ስኬት አስመስዬ ማቅረብ ብፈልግስ? በአምስት አመታት ውስጥኮ፣ በድሮው 30ሺ ሄክታር ላይ 35ሺ ሄክታር ተጨምሯል፡፡ ስለዚህ፣ የ115% እድገት ተመዝግቧል ማለት ይቻላል፡፡በእርግጥ፣ በቅርቡ የታተመው አመታዊ የመንግስት ሪፖርት ላይ “215%” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ግን ይሄ አይገርምም፡፡ ለምን ብትሉ፤ “ገና ምኑን አያችሁና!” እላችኋለሁ፡፡ ገና ብዙ ስህተቶችን ታያላችሁ፡፡ ለምን? አገሩን ካጥለቀለቁት ብዙ አይነት እጥረቶች መካከል፣ “የቁጥር እውቀት እጥረት” (የሂሳብ እጥረት) አንዱ ነዋ፡፡ የመጀመሪያው ስህተት፣ ቁጥሩን ማሳሳት ነው (115% መሆን የነበረበት 215% ብሎ መፃፍ)፡፡ ሁለተኛው ስህተት፣ በ200ሺ ሄክታር (በ700%) ለማሳደግ ታቅዶ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በመሃል ከተማ የሚገነቡ ህንፃዎች ከ20 ፎቅ በላይ ይሆናሉ

አዲስ አበባ 300 ሽንት ቤቶች ያስፈልጋታል ተባለ   ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀውና ዝግጅቱ 4 ዓመታትን ፈጅቷል የተባለው የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን በ10 ዓመት ውስጥ በከተማዋ 300 ሽንት ቤቶች እንዲገነቡ፤ ወንዞችን ይበክላሉ የተባሉ ፋብሪካዎች ከመዲናይቱ እንዲወጡ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በአሁን ወቅት በአዲስ አበባ 1 መፀዳጃ ቤት ለ50 ሺህ ነዋሪዎች እያገለገለ ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ በከተማዋ ያሉ ፋብሪካዎች ፍሳሻቸውን ሳያጣሩ ወደ ወንዞች ይለቃሉ ተብሏል፡፡ የከተማዋ ከ70 በመቶ በላይ ፍሳሽ ወደ ወንዝና መንገዶች እንደሚለቀቁ የጠቆመው የፕላኑ ጥናት፤ አብዛኞቹ መንገዶችም ወደ ውሃ መውረጃነት ተቀይረዋል ተብሏል፡፡ በአሁን ወቅት 17 የህዝብ ሽንት ቤቶች በመዲናዋ ቢኖሩም የተሟላ ዘመናዊ አገልግሎት አልሰጡም ያለው መሪ ፕላኑ በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ቁጥሩ አሁን ካለበት 3.3 ሚሊዮን ወደ 5 ሚሊዮን ከፍ ለሚለው የመዲናዋ ነዋሪ 300 ሽንት ቤቶች በዋና ዋና የህዝብ መተላፊያዎች መገንባት እንዳለባቸው ያመላክታል፡፡ የሚገነቡት ሽንት ቤቶች ባለሁለት ፎቅ ህንፃ ሲሆኑ በሁለተኛው ወለል ላይ ሬስቶራንት ይኖራቸዋል ይላል -
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ፤ 136 ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከኤቢኤች ሰርቪስ ጋር በመተባበር በሁለት የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 136 ተማሪዎች ነገ በሸራተን አዲስ ያስመርቃል፡፡በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽንና በማስተርስ ኦፍ ፐብሊክ ኸልዝ የሚመረቁት እነዚሁ የድህረ ምርቃ ተማሪዎች፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ ኤቢኤች ካምፓስ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የረጅም ዓመታት ሙያዊ እውቀትና ልምድ ያላቸውን መምህራን በመመደብ ተማሪዎቹን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ለሜሳ፤ አሁንም አዳዲስ ፕሮግራሞችን በመክፈት የመንግስትና የግል ዘርፉን አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ የኤቢኤች ሰርቪስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ በበኩላቸው፤ የጅማ ዩኒቨርሲቲን ወደ አዲስ አበባ መምጣት ተከትሎ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ጠቁመው፤ በቀጣዩ በሁለት የድህረ ምርቃ ፕሮግራሞ በፐብሊክ ሪሌሽንና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን እንዲሁም በኸልዝ ሞኒተሪንግና ኢቫሉዬሽን አዳዲስ ተማሪዎን እንደሚቀበል ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በነገው ዕለት ከሚያስመርቃቸው የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መካከል 42ቱ ሴቶች ሲሆኑ ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ 97 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ አስተምሮ ማስመረቁ አይዘነጋም፡፡ 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

20 ሺ ቤቶች በሚፈርሱበት ክ/ከተማ የሰዎች ህይወት አልፏል

በግጭቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ከ200 በላይ ሰዎች ታስረዋልነዋሪዎች መውደቂያ አጥተናል ሲሉ እያማረሩ ነውበላፍቶ ክ/ከተማ ቀርሳ ከንቱማና ማንጎ ሰፈር በተባሉ አካባቢዎች ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች ከትላንት በስቲያ ጀምሮ በአፍራሽ ግብረ ኃይል እየፈረሱ ሲሆን በአጠቃላይ 20 ሺ ገደማ ቤቶች ሊፈርሱ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ባለፈው ረቡዕ በደንብ ማስከበርና በክ/ከተማው ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ የወረዳ ሥራ አስፈፃሚና የሁለት ፖሊስ ኃላፊዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል፡፡ ሟቾቹ የላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታሪኩ ፍቅሬ፣ የለቡ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ባህሩ፣ እንዲሁም የለቡ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ  ም/ኢንስፔክተር ሚካኤል ሽፈራው ናቸው ተብሏል፡፡ ግጭቱ በተከሰተበት በዚያው እለት ከሰዓት በኋላ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው በመሰማራት በግጭቱ ላይ ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ከ200 በላይ ነዋሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋሉ፣ በመኪና በመጫን ወደ ፖሊስ ጣቢያዎች ሲያጓግዙ እንደነበር የአይን እማኞች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ቤታቸው ከፈረሰባቸው ነዋሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ግለሰብ፤ በቀን ሥራ እንደሚተዳደሩ ገልፀው፤ በ1998 ዓ.ም 150
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአቶ ሀብታሙ አያሌው ከሀገር የመውጣት ጥያቄ በፍ/ቤት ተቀባይነት አላገኘም

አምነስቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እግዱ እንዲነሳ መንግስትን ጠይቀዋል   በውጭ ሀገር ሄደው ለመታከም በህግ የተጣለባቸው ከሀገር የመውጣት እገዳ እንዲነሳላቸው በጠበቃቸው አማካይነት ትናንት ለጠቅላይ ፍ/ቤት ያመለከቱት የቀድሞው የአንድነት አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ “በቂ ምክንያት አላቀረቡም” በሚል ፍ/ቤቱ ጥያቄያቸውን አልተቀበለም፡፡ ፍ/ቤቱ ትናንት ከሰዓት በኋላ የቀረበለትን ጥያቄ ከተመለከተ በኋላ “ዛሬውኑ እግዱን ለማንሳት የቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም፤ ታማሚው ህክምናቸውን ሀገር ውስጥ እንደማያገኙና ህይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ከሆስፒታሎች ማስረጃ ከቀረበ ወዲያውኑ እግዱ እንዲነሳ ይደረጋል” የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው የአቶ ሀብታሙ ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በሽብር ክስ ይግባኝ የተጠየቀባቸው ጉዳይ በመጪው ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በቀጠሮ መሰረት የሚታይ ሲሆን ፍ/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥና ምናልባት የአቶ ሀብታሙ ጉዳይ እልባት ሊያገኝ እንደሚችል ጠበቃው ተናግረዋል፡፡  የሃብታሙን የህክምና ጉዳይ የሚከታተሉት የቅርብ ወዳጃቸው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ አቶ ሀብታሙ ስር በሰደደ ከፍተኛ የኪንታሮት ህመም እየተሰቃዩ ሲሆን በሀገር ውስጥ እስካሁን በ4 ሆስፒታሎች ለመታከም ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር መረራ ጉዲና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከሰሱ

የፕሮፌሰርነት ደረጃዬን ያለአግባብ ከልክሎኛል ብለዋል300 ሺ ብር የሚጠጋ የገንዘብ ክስም አቅርበዋል     አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት የደረጃ እድገቴን ያለ አግባብ ከልክሎኛል ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከዩንቨርስቲው ማግኘት የሚገባኝን የአገልግሎትና ልዩ ልዩ ክፍያዎችም ነፍጎኛል ሲሉ ክስ አቀረቡ፡፡ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ መናገሻ ምድብ ሥራ ክርክር ችሎት የቀረበው የዶክተር መረራ የክስ ማመልከቻ፤ በዩንቨርስቲው ውስጥ ከግማሽ በላይ ዕድሜዬን ያገለገልኩና ብርቱ፣ ብቁና ተጠያቂ ዜጐችን ሳፈራ የቆየሁ ሲሆን ለፕሮፌሰርነት ደረጃና የሙያ እድገት ብቁ የሚያደርገኝን መስፈርቶች ሁሉ ያሟላሁ ቢሆንም፣ የፕሮፌሰርነት ደረጃውና እድገቱ በ3 ወር ጊዜ ወስጥ ሊፈቀድልኝ ወይም ሊሰጠኝ ሲገባ፣ ያለ ሕግ አግባብ መብቴን ተነፍጌአለሁ ይላል፡፡ ዩኒቨርሲው ያለ ህግ የነጠቀኝን መብቴን እንዲሰጠኝና የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ እንዲፈቀድልኝ፣ እንዲሁም በዩንቨርስቲው ውስጥ ለረዥም ዓመት የሰራሁበት የአገልግሎት ክፍያም 282 ሺ 960 ብር እንዲከፈለኝ እጠይቃለሁ ብለዋል - ለፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የደሞዝ፣ የኪራይ እና “የጥቃቅን ተቋማት”፣ የግብር ማሻሻያ ለፓርላማ ቀርቧል

ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት፣ ግብር ተቀንሶላቸዋል ከኪራይ ገቢ ውስጥ፣ ግማሹ ከግብር ነፃ ይሆናል ተብሏል የተቀጣሪ ሰራተኞች የግብር ማሻሻያም ለፓርላማ ቀርቧል     የስድስት መቶ ብር ደሞዝተኛ፣ ከ40 ብር በላይ ነበር ግብር የሚከፍለው፡፡ በአዲሱ ማሻሻያ አዋጅ፣ የግብር ክፍያው ይቀርለታል፡፡ የጡረታ መዋጮ ከተቀነሰ በኋላ አንድ ሺ ብር የሚያገኝ ደሞዝተኛ ደግሞ፤ 62 ብር የግብር ቅናሽ ያገኛል፡፡በተመሳሳይ ስሌት የሶስት ሺ ብር ደሞዝተኛ 208 ብር የግብር ቅናሽ ይኖረዋል፡፡ (ሰንጠረዥ ይመልከቱ)የቤት ኪራይ ገቢ ላይ የተደረገው ለውጥ ሁለት አይነት ነው፡፡ በ1750 ብር ቤት ያከራየ ሰው፣ በድሮው አሰራር፣ ሃያ በመቶ የጥገና ወጪ ታስቦለት 1400 ብር ገቢ እንዳገኘ ነበር የሚቆጠረው፡፡ ከዚያ ልክ እንደ ወር ደሞዝተኛ ግብር ይከፍላል 160 ብር ገደማ፡፡ አዲስ በተሻሻለው አዋጅ ግን፣ ከ1750 ኪራዩ ውስጥ ሀምሳ በመቶው ወይም ግማሹ ለጥገና እንደሚያወጣ ይታሰብበታል፡፡ እናም 875 ብር ገቢ እንዳገኘ ደሞዝተኛ ይቆጠራል፡፡ ከዚህም ውስጥ 28 ብር ግብር ይከፍላል፡፡ ለምን ቢባል፣ ቤት አከራይ እንደ ደሞዝተኛ፣ በአዲስ የግብር ማስከፈያ ስሌት ቅናሽ ተደርጎለታል፡፡ ትልቁ ለውጥ ግን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአዲስ አበባ መስተዳድር ለታክሲ እጥረት መፍትሄ አገኘ – 300 ብስክሌቶችን ገዛ

የአንድ ብስክሌት ዋጋ - 35 ሺ ብር!    የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ በታክሲ እጥረት መንገላታታቸውና መማረራቸውን እንርሳው - ሁሉንም ችለውና ተሸክመው ኑሯቸውን ይገፋሉ እንበል፡፡ ግን፣ ከአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ሩብ ያህሉን የምታመነጭ ከተማ፣ በትራንስፖርት እጥረት ስትጨናነቅ ጉዳቱ ቀላል ይሆናል?የከተማዋ ትራንስፖርት ባለስልጣናት፣ “ነዋሪዎችን ከታክሲ ተፅእኖ ነፃ ለማውጣት ነው አላማችን” ብለው ሲናገሩ፤ ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ግራ ያገባል፡፡ ከትራንስፖርት እጥረት ነጻ የማውጣት አላማ ሳይሆን “ከታክሲ ነፃ የማውጣት” አላማ መያዝ ምን ማለት ነው? ጉዳዩ፣ ቀልድና ጨዋታ እንዳልሆነ በቅጡ ባይገባቸው ይሆናል፡፡ ነዋሪዎች በተለያዩ እውነተኛ የኑሮ ችግሮች በቤት እጦት፣ በትራንስፖርት እጥረት፣ በኑሮ ፈተናዎች ተወጥረዋል፡፡ ባለስልጣናት ደግሞ በመግለጫና በፕሮፓጋንዳ፣ ሁሉንም ችግሮች ብን አድርገው ማጥፋት የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ የምናብ ዓለም ይፈጥራሉ፡፡ ህገ ወጥ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻዎች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ተመልከቱ፡፡ በአንድ ክፍለ ከተማ ብቻ 20 ሺህ ቤቶችን ለማፍረስ ነው የታቀደው፡፡ በሌሎች ክፍለ ከተማዎችም እንዲሁ፡፡ ቤቶችን ማፍረስ ከመቶ በላይ ሰዎችን እንደሚያፈናቅልና ህይወታቸውን እንደሚያናጋ ለመገንዘብ ይከብዳል? አብዛኞቹ ከአካባቢው ገበሬ ትንንሽ መሬት በመግዛት፣
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዓለም አቀፉ ክራውን ፕላዛ ሆቴል በመጪው ዓመት ይጠናቀቃል

ፀሜክስ ሆቴሎችና ቢዝነስ ማኅበር በዓለም ታዋቂ ከሆነው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ግሩፕ ጋር ለ15 ዓመት ባደረገው የአስተዳደር ሽርክና መሰረት፣ክራውን ፕላዛ ሆቴልና ሬስቶራንት በአዲስ አበባ እየገነባ ነው፡፡ ልደታ አካባቢ በፀማይ ግሎባል ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ባለቤት በአቶ ረዘነ አያሌው እየተገነባ ያለው ባለ 5 ኮከቡ ክራውን ፕላዛ ሆቴልና ሬስቶራንት 212 ክፍሎች ሲኖሩት ሁለቱ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ፕሬዚደንሻል ሱትስ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ይህን ሆቴል ልዩ የሚያደርገው ለግንባታ የሚውለው 37 ሚሊዮን ዶላር የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) በብድር የተገኘ ሲሆን እስካሁን በ18.6 ሚ. ዶላር ብድር ግንባታው እየተፋጠነ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ሌላው ልዩ ነገር ሆቴሉ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ግንባታውን በ18 ወራት ለማጠናቀቅ የኢጣሊያው ኩባንያ “ሳፖርቲ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ሰርቪስ” የዛሬ ሳምንት በተደረገ የሆቴሉ ክፍል ማሳያ ሞዴል ምረቃ ላይ የፕሮጀክት አስተዳደሩን ተረክቧል፡፡ በሆቴል ክፍሉ ምረቃና በፕሮጀክት አስተዳደሩ ርክክብ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው፣ ከተማችን የአፍሪካ መዲና፣ የበርካታ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

3 ሰዓሊያን ሀበሻ ቢራን አስጠነቀቁ

ጥያቄያችን በ10 ቀን ውስጥ ካልተፈፀመ ወደ ክስ እናመራለን ብለዋል   በብራና እና በጂባ ላይ 4 ሺህ ስዕሎችን ስለው ለማቅረብ ከሀበሻ ቢራ ጋር የ6.6 ሚሊዮን ብር ውል መዋዋላቸውን የገለፁት ሶስት ሰአሊያን፤ በውሉ መሰረት ክፍያ አልተፈፀመልንም፤ ከውል ውጪም ስራውን እንዳንሰራ ተደርገናል በማለት ኩባንያው በ10 ቀን ውስጥ ለጥያቄያቸው ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ ወደ ፍ/ቤት እንደሚያመሩ አስታውቀዋል፡፡ በህግ አማካሪና ጠበቃቸው አቶ ጳውሎስ ተሰማ በኩል ተፅፎ ለሀበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር በተላከው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ፡- ሰዓሊ በልአንተ ብርሃኑ፣ ሰዓሊ አብዱል ቃድር መሃመድና ሰዓሊ መሃሪ ተሾመ በሽርክና ማህበራቸው በኩል በጥር 2008 ዓ.ም 2000 የብራና ላይ እና 2000 የጂባ ላይ ስዕሎችን ስለው እንዲያቀርቡ መስማማታቸውን፣ የአንዱ ስዕል ዋጋ 1500 ብር፤ ጠቅላላ ዋጋው 6 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር መሆኑን ያስረዳል፡፡ ሀበሻ ቢራ በውሉ መሰረት 5 በመቶ ቅድመ ክፍያ 330ሺህ ብር የከፈለ መሆኑንና 200 ስዕሎችን መረከቡን፤ ነገር ግን ለቀጣይ ስዕሎች መስሪያ 10 በመቶ ተጨማሪ ክፍያ ሲጠየቅ አዲስ የስራ ዋጋ በማቅረብ ክፍያውን ለመፈፀም ፍቃደኛ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ፊቴ ተመልሶ እንዲመጣ እፈልጋለሁ”

ባለፈው ፋሲካ አካባቢ ደወለልኝ፡፡ ሀዋሳ ነው ያለሁት አለኝ፡፡ እኛ ጋ የሚሰራ አንድ ጓደኛ አለው፡፡ እሱ ጋ መጥቶ እንዳረፈ በኋላ ነውየሰማሁት፡፡ እኔም የምኖረው እዚያው የምሰራበት ሆቴል ክፍል ተሰጥቶኝ ነው፡፡ የምኖረው ሀዋሳ ነኝ ያለው ለካ እዛ መጥቶ ነው፡፡ ለአንድሳምንት ያህል የምሰራበት ሆቴል መጥቶ ምግብ በልቶ አይቶኝ ይሄድ እንደነበር ቆይቼ ሰምቻለሁ፡፡ እኔ ግን አይቼው አላውቅም፡፡ አንድ ቀን“አንቺ አምሮብሻል፤ እኔ ግን እየተሰቃየሁ ነው” አለኝ፡፡ እኔ ታዲያ ምን አጠፋሁ አልኩት፡፡ “በይ ለማንኛውም 500 ብር አበድሪኝ” አለኝ፡፡• አልጋ የለም ተብዬ እየተመላለስኩ ነው የምታከመው• ለሰርጀሪ ከ60-80 ሺህ ብር ተጠይቄያለሁ• በደረሰብኝ ጥቃት ህዝብና መንግሥት ይፋረደኝአሲዱን የደፋብሽ ማነው?ጥቃቱን ያደረሰብኝ ሰለሞን በላይ የተባለ የቀድሞ ጓደኛዬ (ፍቅረኛዬ) ነው፡፡ ትናንትና (ሰኔ 17) አንድ ወር ሞላኝ፡፡ እንዲሁ እንደተቃጠልኩና እንደተንገበገብኩ አለሁ፡፡ በምን ምክንያት ነው ጥቃቱን ያደረሰብሽ?ለሶስት ዓመታት ያህል በፍቅር አብረን አሳልፈናል፡፡ ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ አብረን መሆናችን ካልቀረ ለምን አንጋባምና ተጠቃልለን አንቀመጥም አልኩት፤ ምላሽ የለም፡፡ በተደጋጋሚ ይህንኑ ጥያቄ አነሳሁ፡፡ እሱ ደግሞ “በጓደኝነታችን እንቀጥል እንጂ ላገባሽ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የፌስቡክ የጥላቻ መልዕክቶች ላይ የተደረገ ጥናት ምን ይላል?

ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፌ ስቡክ የሰመረላቸው የመንግስት ባ ለስልጣናትና ተ ቋማት ጥ ቂት ናቸው ብሏል   ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያውያን የፌስቡክ ማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ላይ ባደረገው የናሙና ጥናት፣ ኢትዮጵያውያን በፌስቡክ በኩል የሚያስተላልፏቸው የጥላቻ መልዕክቶችና አስተያየቶች መጠን፣ ከተጠቃሚዎች ብዛት አንጻር እጅግ አነስተኛ ሆኖ እንዳገኘው አስታወቀ፡፡ዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያውያንን የፌስቡክ አጠቃቀም በተመለከተ ለሁለት አመት ያህል ያከናወነውና ሰሞኑን ይፋ ያደረገው “መቻቻል” የተሰኘ ርዕስ ያለው ይህ ጥናት፤ በናሙናነት ከተወሰዱት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች አስተያየቶች መካከል ብሄርን፣ ዜግነትን፣ ሃይማኖትን ወይም ጾታን መሰረት በማድረግ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን የሚያገልሉ የጥላቻ መልዕክት ያዘሉት 0.7 በመቶ ያህሉ ብቻ እንደሆኑ ገልጿል፡፡በ2007 ዓ.ም ከየካቲት እስከ ሃምሌ በነበሩት ወራት ኢትዮጵያውያን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከሰጧቸው አስተያየቶችና መልዕክቶች ውስጥ 13 ሺህ ያህሉን በናሙናነት ወስዶ የተነተነው ጥናቱ፣ አደገኛ ወይም ጠብ አጫሪ ተብለው ከተመደቡት የፌስቡክ አስተያየቶችና መልዕክቶች መካከል 21.8 በመቶ የሚሆኑት የፖለቲካ ልዩነቶችን መሰረት ያደረጉ እንደሆኑና ሃይማኖትና ብሄር 10 በመቶ እና 14 በመቶ ያህል ድርሻ እንዳላቸውም ገልጧል፡፡በጥናቱ የጥላቻ አስተያየቶችንና
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአዲስ አበባ ኑሮ ከአለማችን ከተሞች ጋር ሲነፃፀር!

ከብራዚልና ከሜክሲኮ ዋና ከተሞች፣ ከካልታና ከኢዝላማባድ … ከሃጋሪና ከፖላንድ እንዲሁም ከዩክሬንና ከማሌዥያ ዋና ከተሞች ይልቅ፣ የአዲስ አበባ የኑሮ ውድነት ይከፋል፡፡ ከካናዳ ኦታዋ እና ጊታሞና ሞንትሪያል፤ ከጀርመን ሊፕዚግ እና ኑርንበርግ ከተሞች ጋር ሊነፃፀርም፣ የኑሮ ውድነት በአዲስ አበባ ይከብዳል፡፡ ሜርሰር የተባለው አለማቀፍ የጥናት ተቋም ከትናንት በስቲያ ይፋ ባደረገው አመታዊው የዓለማችን ከተሞች የኑሮ ውድነት ደረጃ፣ መዲናችን አዲስ አበባ 143ኛ ደረጃን መያዟን አስታወቀ፡፡ተቋሙ ለ22ኛ ጊዜ በ209 የዓለማችን አገራት ላይ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ ይፋ ያደረገው የዘንድሮ ሪፖርት እንደሚለው፣ በአለማችን ከሚገኙ ከተሞች ለመኖር ከፍተኛ ወጪን በመጠየቅ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘቺው ሆንግ ኮንግ ስትሆን የአንጎላ መዲና ሉዋንዳና የስዊዘርላንዷ ዙሪክ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ዝቅተኛ ወጪን የሚጠይቁ የዓለማችን ከተሞች ተብለው የተዘረዘሩት ደግሞ የናሚቢያዋ ዊንድሆክ፣ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታውንና የካይሬጊስታኗ ቢሽኬክ ሲሆኑ በአፍሪካ አህጉር ከሚገኙ ከተሞች የአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያለባት ከተማ ናት ያለው ሪፖርቱ፤ የኮንጎዋ ኪንሻሳና የቻድ ርዕሰ ከተማ ጃሜና ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን መያዛቸውን አብራርቷል፡፡ተቋሙ የከተሞችን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያና በአማራ ክልል በግጭቶች የደረሱ ጉዳቶች በድጋሚ እንዲጣሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠየቁ

ከ”330 በላይ ሰዎች ስለመሞታቸው መረጃ አለኝ” - መድረክየኢሰመኮን ሪፖርት አንቀበለውም ብለዋል   የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተከሰቱ ተቃውሞና ግጭቶችን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶችን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርት እንደማይቀበሉት መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡ ከማንም የማይወግን ነፃ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ የጠፋው ህይወትና የደረሱት ጉዳቶቹ በድጋሚ እንዲጣሩም ጠይቀዋል፡፡ መድረክ በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው ተቃውሞና ግጭት ከ330 በላይ ዜጎች ስለመሞታቸው መረጃ እንዳለው ጠቁሞ የኮሚሽኑ ሪፖርት የሟቾችን ቁጥር በግማሽ ያሳነሰ ነው ብሏል፡፡  በኦሮሚያ ክልል የ292 ሟቾች ስምና ሙሉ መረጃ እንዳለው የገለፀው መድረክ፤ 41 ያህል ማንነታቸው ያልተለዩትን ጨምሮ የሟቾቹ ቁጥር ከ330 በላይ ነው ብሏል፡፡ አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና የፀጥታ ኃይሉም ከመጠን በላይ ኃይል መጠቀሙን የሚገልፅ ሪፖርት ማውጣታቸውን የጠቀሱት ሰማያዊና መድረክ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሟቾች ቁጥር 173 ብቻ ናቸው ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ “በተቃውሞ ወቅት በመንግስት የተወሰደው እርምጃ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” ማለቱም የፀጥታ ኃይሉንና መንግስትን ከተጠያቂነት ነፃ ለማድረግ የተወጠነ ነው” ብለዋል፤ ፓርቲዎቹ ትናንት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኤርትራውያን በመንግሥታቸው ጉዳይ ለሁለት ተከፍለዋል

“የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለፍርድ የመቅረብ እድል በ UN እጅ ላይ ነው”    የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተከሰቱ ተቃውሞና ግጭቶችን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶችን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርት እንደማይቀበሉት መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡ ከማንም የማይወግን ነፃ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ የጠፋው ህይወትና የደረሱት ጉዳቶቹ በድጋሚ እንዲጣሩም ጠይቀዋል፡፡ መድረክ በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው ተቃውሞና ግጭት ከ330 በላይ ዜጎች ስለመሞታቸው መረጃ እንዳለው ጠቁሞ የኮሚሽኑ ሪፖርት የሟቾችን ቁጥር በግማሽ ያሳነሰ ነው ብሏል፡፡  በኦሮሚያ ክልል የ292 ሟቾች ስምና ሙሉ መረጃ እንዳለው የገለፀው መድረክ፤ 41 ያህል ማንነታቸው ያልተለዩትን ጨምሮ የሟቾቹ ቁጥር ከ330 በላይ ነው ብሏል፡፡ አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና የፀጥታ ኃይሉም ከመጠን በላይ ኃይል መጠቀሙን የሚገልፅ ሪፖርት ማውጣታቸውን የጠቀሱት ሰማያዊና መድረክ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሟቾች ቁጥር 173 ብቻ ናቸው ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ “በተቃውሞ ወቅት በመንግስት የተወሰደው እርምጃ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” ማለቱም የፀጥታ ኃይሉንና መንግስትን ከተጠያቂነት ነፃ ለማድረግ የተወጠነ ነው” ብለዋል፤ ፓርቲዎቹ ትናንት በጋራ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች አዲስ ፓርቲ መሰረቱ

የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች፤ “ነፃነት ለአንድነትና ለፍትህ (ነፃነት) የተሰኘ አዲስ ፓርቲ መሰረቱ፡፡ የአዲሱ ፓርቲ መስራች ጠቅላላ ጉባኤ ከረጅም የምስረታ ሂደት በኋላ ግንቦት 27 ቀን 2008 ዓ.ም በሆቴል ዲ.አፍሪክ የተካሄደ ሲሆን በእለቱም የፓርቲው የተለያዩ መተዳደሪያ ሰነዶች በጉባኤው ከፀደቁ በኋላ የቀድሞ የአንድነት አመራር አባል ዶ/ር ንጋት አስፋው ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን በፓርቲው የመስራች አስተባባሪ ኮሚቴው ፀሐፊ፣ አቶ ደምሴ መንግስቱ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ፓርቲውን በማቋቋም ሂደቱ ከሰሞኑ ህይወታቸው ያለፈው አቶ ብሩ ብርመጅ እና አቶ ተመስገን ዘውዴ ጉልህ ድርሻ የነበራቸው ሲሆን በእነ አቶ ብሩ የሚመራው ቡድን በሌላ በኩል ሌላ ፓርቲ እየመሰረተ ከነበረው የእነ አቶ ሽመልስ ሃብቴ ቡድን ጋር በመቀላቀል “ነፃነት” የተሰኘው ፓርቲ እንደተመሰረተ አቶ ደምሴ አብራርተዋል፡፡ አዲሱ ፓርቲ የደቡብ፣ የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችና የአዲስ አበባ ከተማ ውክልና ያላቸው አባላት እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በፓርቲው ምስረታ የተሳተፉት ሁሉም አባላት በአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ውስጥ በከፍተኛ አመራር ደረጃ የነበሩ ግለሰቦች መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ደምሴ፤ 2ሺህ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊላንድ ጋዜጠኞችን ማሰሩ ተዘገበ

የቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭት እንዲቋረጥ አድርጓል ተብሏልየኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ሰኞ ዋጃሌ በተባለቺው የኢትዮ-ሶማሊላንድ የድንበር ከተማ አምስት የሶማሊላንድ ጋዜጠኞችን በቁጥጥር ስር አውሎ ማሰሩንና አራቱ ከቆይታ በኋላ ሲለቀቁ አንደኛው አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ዳስላን ሬዲዮ ከትናንት በስቲያ ዘገበ፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞቹን ከማሰር ባለፈ፣ ሆርን ኬብል የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ በቅርቡ ያስተላለፈው ዘገባ ተገቢ አይደለም በሚል ታይኮም ለተባለው የሳተላይት ተቋም ባቀረበው ቅሬታ፤ጣቢያው በአካባቢው ያሰራጭ የነበረው ፕሮግራም እንዲቋረጥ ማድረጉንም ሶማሊላንድ ኢንፎርመር ዘግቧል፡፡ጋዜጠኞቹ በዋጃሌ ከተማ በተዘጋጀ ሃሰተኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙ በኋላ በመንግስት ልዩ ሃይል ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ወደ ጂግጂጋ ከተማ ተወስደው እንደታሰሩ የጠቆመው ዘገባው፣ አራቱ ሲፈቱ ሆርን ኬብል ቲቪ የተባለው የሶማሊላንድ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ባልደረባ፣ጋዜጠኛ ሙክታር ኑር ግን አሁንም በኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን ያሰረበት ምክንያት ግልጽ አይደለም ያለው ዘገባው፤ሶማሊላንድና ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ረገድ ተባብረው ሲሰሩ እንደነበርና ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ የታሰሩ የአገሪቱ ጋዜጠኞች በሃርጌሳ በፍርድ ሂደት ላይ መሆናቸውን ጠቁሞ ሌሎች
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ሼህ መሐመድ አሊ አላሙዲ ለመቄዶንያ ሁለተኛ አምቡላንስ ሰጡ

ሞሓ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ፣ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል አንድ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ሁለተኛ አምቡላንስ በዕርዳታ ሰጠ፡፡ ርክክቡ የተከናወነው መንግሥት ለመቄዶንያ በነፃ በሰጠውና አያት ኮንዶሚኒየም አጠገብ በሚገኘው 30ሺ ካ.ሜ ቦታ ላይ ሲሆን በስፍራው 5 ብሎክ ቤቶች ተሰርተው ኮተቤ የነበሩ 350 ተረጂዎች ገብተውበታል፡፡ በአያት ኮንዶሚኒየም አጠገብ የሚሰራው የመቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል፤ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ስለሆነ፣ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ሚክሰር፣ ሲኖትራክ፣ የመሳሰሉትን ለተወሰነ ሰዓት ወይም ለአንድ ቀን ይዘው በመምጣት በሕዝብ ድጋፍ የሚሰራው ማዕከል ግንባታ አካል እንዲሆኑ መቄዶንያ ጠይቋል፡፡“አገር በቀሉ መቄዶንያ እስካሁን እየተንቀሳቀሰ ያለውና አዲሱ ማዕከልም የሚሰራው በኢትዮጵያውያን በጎ አድራጎት ስለሆነ ለማዕከሉ ግንባታ ገረጋንቲ፣ የምግብ ማብሰያ እንጨት (የቤት ፍራሽ) ብሎኬት፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ ሚስማር፣ ቆርቆሮ የመሳሰሉትና የሙያ እገዛም በጣም ስለሚያስፈልገን፣ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ወደ ማዕከሉ መጥተው በመጎብኘትና የጎደለውን በማሟላት፣በማዕከሉ ግንባታ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ እንጠይቃለን” ብሏል፡፡ “ይበል ኢንዱስትሪያል፤ለመቶ ሰዎች በነፃ በብረት ተገጣጣሚ ቤት እየሰራ ነው፡፡ ቤቱን፣ በ3 ወር ሰርተው እንደሚያስረክቡን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ለክረምቱ ግብርና በቂ ዝግጅት አልተደረገም” አለማቀፍ ተቋማት

“ከ7 ወር በኋላ ከድርቅና ተረጂነት ዜጎች ይላቀቃሉ” መንግስት   የበልግና የክረምቱ ዝናብ በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ በድርቅ የተጎዱ ዜጎች በመጪው ጥር 2009 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ከተረጂነት ይላቀቃሉ የተባለ ሲሆን በግብርና ላይ የሚሰሩ አለማቀፍ ተቋማት በበኩላቸው፤ መንግስት ለግብርናው በቂ ዝግጅት አላደረጉም ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የክረምቱ ዝናብ በሚፈለገው መጠን እየዘነበ መሆኑን የጠቀሰው በአፍሪካ ግብርና ላይ ትኩረቱን ያደረገው የአርካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት የተሰኘው ተቋም፤ መንግስት እርዳታ በማቅረብ ላይ ብቻ በመጠመዱ የዘር አቅርቦቱን ቸል ብሎታል ብሏል፡፡ የዘር አቅርቦቱ እጥረት እያጋጠመው ነው ያለው ተቋሙ፤ ይህም የድርቁን ችግር ሊያራዝመው ይችላል ብሏል፡፡ የብሄራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ኮሚሽነር በበኩሉ፤ ከ7 ወር በኋላ ሀገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ከድርቅ ተረጂነት ትላቀቃለች ተብሎ እንደሚጠበቅና የድርቁን ወቅታዊ ችግርና የተረጅዎችን ሁኔታ የሚያጠና ቡድን ወደየአካባቢዎቹ መላኩን ጠቁመዋል፡፡ “እስካሁን የድርቅ ተረጂዎች ቁጥር ከ10.2 ሚሊዮን አልዘለለም” ያሉት ኮሚሽነር ምትኩ ካሣ፤ የበልጉ ዝናብ ምን ያህል ተረጅዎችን ከተረጅነት አላቀቀ የሚለውን ቡድኑ ካጠና በኋላ የተረጂዎች ቁጥር አሁን ካለበት ሊቀንስ ይችላል ብለዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት “ብዙ ገድለናል” እያሉ ነው

“የኢሳያስን መንግስት ማስወገድ ያስፈልጋል”የቀድሞ የአየር ሃይል አዛዥ ሜ.ጀ አበበየኢትዮጵያ መንግስት• በከባድ ውጊያ፣ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሻለሁ• ትንኮሳ እንዳይፈጽም ትምህርት ሰጥተነዋል• ካለረፈ ግን፣ በተመጣጣኝ እርምጃ እንቀጣዋለንየኤርትራ መንግስት• ሁለት መቶ ወታደሮችን ገድያለሁ፤ አቁስያለሁ• የአሜሪካ መንግስት ፣ እጁ አለበት፤ ጥቃት አነሳስቶብኛል• የኢትዮጵያ ጦር ወደ ድንበር በብዛት ተሰማርቶብኛልየኢትዮጵያ መንግስት በፆረና ግንባር ከባድ ውጊያ ተካሂዶ እንደነበር ገልፆ፣ ትንኮሳ በፈፀመው የኤርትራ ጦር ላይ ከፍተኛ የህይወት ኪሳራ አድርሻለሁ፤ እርምጃውም ለሻዕቢያ መንግስት አስተማሪ ነው ብሏል፡፡ የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ባልታወቀ ምክንያት የኢትዮጵያ ጦር በብዛት ወደ ድንበር እንደተሰማራና የአሜሪካ እጅ እንዳለበት የተናገረ ሲሆን፤ 200 ወታደሮችን ገድያለሁ ብሏል፡፡ በኤርትራ መንግስት ላይ አስተማሪ እርምጃ መስደናል ያሉት የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፤ “ሌላ ትንኮሳ ያደርጋል ብለን አንጠብቅም፤፡፡  በድንበር አካባቢ ሌላ ግጭት የሚፈጠር ከሆነ ግን፣ የግጭቱ ብቸኛ ተጠያቂ የሚሆነው የኤርትራ መንግስት ነው” ብለዋል፡፡ መንግስት፣ ትንኮሳዎችን ለማስታገስና ለመቅጣት ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የኢያሳያስን መንግስት የማውረድ ኃላፊነት ግን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአለማቀፉ ህብረተሰብም
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“በኦሮሚያ ግጭትና ተቃውሞ ከ400 በላይ ሰዎች ሞተዋል” ሂውማን ራይትስ ዎች

የ314 ሟቾች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል      በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ በነበረው ተቃውሞና ግጭት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የገለፀው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ከ300 በላይ የሚሆኑ የሟቾችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረበው የምርመራ ሪፖርቱ፤ 28 የፀጥታ ኃይሎችና የመንግስት ሹማምንትን ጨምሮ 173 ሰዎች በግጭቱ መሞታቸውን መግለፁ የሚታወስ ሲሆን፤ የፀጥታ ኃይሎች አስፈላጊና ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰዱት ማለቱ አይዘነጋም፡፡ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ፤ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ከመጠን በላይ የኃይል እርምጃ ወስደዋል ብሏል ከትናንት በስቲያ ባወጣው ሪፖርት፡፡ በግጭቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መቁሰላቸውን፣ በ10ሺዎች የሚገመቱ ለእስር መዳረጋቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የደረሱበት አልታወቀም ብሏል፡፡ አብዛኞቹ በግጭቱ የተገደሉት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ሙዚቀኞች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራርና አባላት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና ከፀጥታ ኃይሎች የሚሸሹ ተማሪዎችን ያስጠለሉ ግለሰቦች ለእስር መዳረጋቸውን አመልክቷል፡፡ የተቋሙ የምርመራ ቡድን ሪፖርቱን ለማጠናቀር ከ17 የኦሮሚያ ዞኖች 125 ሰዎችን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት በቴሌኮም ማጭበርበር ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ከስሯል

- 720 ሲም ካርዶችን መጠቀም የሚችል መሳሪያ ተይዟል- በዘጠኝ ወራት ብቻ 165 የሳይበር ጥቃቶች ደርሰዋል       በአራት የአገሪቱ ከተሞች በተፈፀሙ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎች መንግስት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት ተገለፀ፡፡ በጅግጅጋ፣ በአዲስ አበባ፣ በሃረርና ድሬደዋ 400 የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች የተያዙ ሲሆን አንዳንዶቹ 8፣ አንዳንዶቹ ደግሞ እስከ 720 ሲም ካርዶችን የሚጠቀሙ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋዊ ከትናንት በስቲያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል በአገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ሲሆን መንግስትንም ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርጐታል፡፡  ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጅግጅጋ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረርና ድሬደዋ ከተሞች  በተካሄደ አሰሳ፣ 400 የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች የተያዙ ሲሆን መሳሪያዎቹ ከ8 እስከ 720 ሲም ካርዶችን የመጠቀም አቅም ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል፡፡  46  ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ በመንግስት ላይ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“የስንብት ቀለማት” ለንባብ ሊበቃ ነው

- በኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ረጅሙ ልብወለድ ነው    በአንጋፋው ደራሲ አዳም ረታ የተጻፈውና ዘጠነኛ ስራው የሆነው “የስንብት ቀለማት” የተሰኘ የረጅም ልቦለድ መጽሃፍ በቅርቡ ለንባብ እንደሚበቃ ደራሲው ለአዲስ አድማስ  መግለጫ አስታወቀ፡፡ደራሲ አዳም ረታ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሲያስተዋውቀው የነበረውን ‘ሕጽናዊነት’ የተባለ ልዩ የአጻጸፍ ስልት በስፋትና በጥልቀት ያሳየበት “የስንብት ቀለማት”፣ በቅርጹም ሆነ በይዘቱ የተለየ እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጽሃፍት ውስጥ የሚጠቀማቸው ምስሎች፣ ቻርቶች፣ ግራፊክ ዲዛይኖችና ሰንጠረዦች በአዲሱ መጽሀፍም መካተታቸውንና ባለ ሙሉቀለም የግርጌ ስታወሻዎችና ሌሎች አዳዲስ ይዘቶች እንዳሉት ታውቋል፡፡በመጨረሻ ገፆቹ የአንጋፋውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነጽሁፍ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ ዳሰሳ “ድሕረ ቃል” በሚል ርዕስ ያካተተው መፅሀፉ ፤ በ960 ገጾች በኢትዮጵያ የሥነ ፅሁፍ ታሪክ ረዥሙ ልብወለድ ለመሆን በቅቷል፡፡  8 አቢይ ምዕራፎችና 46 ንኡስ ምዕራፎች ያሉት ልብ ወለዱ፤ ዋጋው 350 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ሲኒማና ቲያትር ቤቶች በተመልካች ድርቅ ተመተዋል

“ቃና” 8 ስቱዲዮዎች ገንብቷልበአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘው “የቃና ቴሌቪዥን” ሥርጭትን ተከትሎ ሲኒማ ቤቶችና ቲያትር ቤቶች በተመልካች ድርቅ መመታታቸውን የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለአዲስ አድማስ ተናገሩ፡፡ ባለፉት ሦስት ወራት የፊልምና ቲያትር ተመልካቾች ከግማሽ በላይ መቀነሳቸው ባለሙያዎቹን እንዳስደነገጣቸው ገልፀዋል፡፡ የቲያትር አዘጋጆችና ባለቤቶች እንደተናገሩት፤ በሣምንቱ የእረፍት ቀናት ከሚታዩ ቲያትሮች በስተቀር በስራ ቀናት ምሽት ላይ የሚቀርቡ ቲያትሮች ተመልካች አጥተዋል፡፡ በማዘጋጃ ቤት “እንግዳ” እንዲሁም በብሔራዊ ቲያትር “የፍቅር ማዕበል” የተሰኙ ቲያትሮችን የሚያሳየው አርቲስት ማንያዘዋል እንደሻው፤ ባለፉት ሶስት ወራት የቲያትር ተመልካቾች ከ30 በመቶ በላይ መቀነሳቸውን ገልጿል፡፡ ቀደም ሲል በማዘጋጀ ቤት እየታየ ያለውን ቲያትር እስከ 300 ሰዎች ይመለከቱት እንደነበረ የጠቆመው አርቲስቱ፤ በአሁን ወቅት የተመልካቹ ቁጥር በመቶ እንደቀነሰ ተናግሯል፡፡ “ቃና” ቴሌቪዥን ከመጣ ወዲህ የተመልካቹ ቁጥሩ መቀነሱ የጣቢያው ተፅዕኖ የፈጠረው ነው ብሎ እንደሚያምን የገለፀው ማንያዘዋል፤ በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ቲያትር ቤቶች ባዶአቸውን ሊቀሩ ይችላሉ ብሏል፡፡ ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገ ሌላ የቲያትር ባለሙያ በበኩሉ፤ የተመልካች ቁጥሩ መቀነሱ ኢንዱስትሪውን በእጅጉ እየጐዳው በመምጣቱ፣ በቲያትር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በአዲስ አበባ የአተት ወረርሽኝ ሥጋት ተባብሷል

• በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው• 14 የማከሚያ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል     የኢትዮጵያ መንግስት በፆረና ግንባር ከባድ ውጊያ ተካሂዶ እንደነበር ገልፆ፣ ትንኮሳ በፈፀመው የኤርትራ ጦር ላይ ከፍተኛ የህይወት ኪሳራ አድርሻለሁ፤ እርምጃውም ለሻዕቢያ መንግስት አስተማሪ ነው ብሏል፡፡ የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ባልታወቀ ምክንያት የኢትዮጵያ ጦር በብዛት ወደ ድንበር እንደተሰማራና የአሜሪካ እጅ እንዳለበት የተናገረ ሲሆን፤ 200 ወታደሮችን ገድያለሁ ብሏል፡፡ በኤርትራ መንግስት ላይ አስተማሪ እርምጃ መስደናል ያሉት የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፤ “ሌላ ትንኮሳ ያደርጋል ብለን አንጠብቅም፤፡፡  በድንበር አካባቢ ሌላ ግጭት የሚፈጠር ከሆነ ግን፣ የግጭቱ ብቸኛ ተጠያቂ የሚሆነው የኤርትራ መንግስት ነው” ብለዋል፡፡ መንግስት፣ ትንኮሳዎችን ለማስታገስና ለመቅጣት ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የኢያሳያስን መንግስት የማውረድ ኃላፊነት ግን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአለማቀፉ ህብረተሰብም የሚመለከት ቢሆንም፣ በዋናነት የኤርትራ ህዝብ ጉዳይ ነው ብለዋል -  ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ “ተመጣጣኝ እርምጃ” የሚባለው ሃሳብ እንደማያዛልቅ የተናገሩት የቀድሞ የአየር ኃይል አዛሽ ሜ/ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖት በበኩላቸው፤ ተመጣጣኝ እርምጃ ማለት እነሱ 200 ከገደሉ፣
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ሃያሲ አብደላ እዝራ ሰኞ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይዘከራል

ባለፈው ቅዳሜ ድንገት ባደረበት ህመም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን አንጋፋውን የሥነ ፅሁፍ ሃያሲ አብደላ እዝራን የሚዘክር የኪነ ጥበብ ምሽት ከነገ ወዲያ ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በ“ዝክረ አብደላ” የኪነ ጥበብ ምሽት፣ ሃያሲ አብደላእዝራ ለአማርኛ ስነ ፅሁፍ ያበረከተው አስተዋፅኦ የሚዳስስ ሲሆን “አብደላና ሂስ”፣ “አብደላና ህይወቱ” በመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሥነ ፅሁፍ ባለሙያዎች አስተያየት ይሰጣሉ፡፡የቅርብ ወዳጆቹም ስለ አብደላ የሚያወቁትን ይመሰክራሉ፤ አብደላን የሚያወድሱ፣ ስራውንናሰብዕናውን የሚያወሱ ግጥሞችና ወጎችም ለታዳሚያን ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ይህን የ“ዝክረ - አብደላ” የኪነ ጥበብ ምሽት አዲስ አድማስ ጋዜጣ ያዘጋጀው ሲሆን፣ በምሽቱ አንጋፋና ወጣት ፀሐፍትና ገጣሚያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ከእነዚህም መካከል ነቢይ መኮንን፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፣ አለማየሁ ገላጋይ፣ ደረጀ በላይነህ፣ ኤፍሬም ስዩም፣ ደምሰው መርሻ፣ ምስራቅ ተረፈ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የመምህራን ደሞዝ በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል

5 ቢሊዮን ብር ተመድቧል     የመምህራንን ደሞዝ ለማሻሻል በመንግስት የተመደበው የ5 ቢሊዮን ብር በጀት፣ የመምህራኑን ደሞዝ በእጥፍ ሊያሳድግ የሚችል ከፍተኛ ጭማሪ ነው፡፡ ለአስተማሪዎች “ትርጉም ያለው የደሞዝ ጭማሪ ይደረጋል” በማለት መንግስት በደፈናው መግለጫ ቢሰጥም፤ እስካሁን ዝርዝር መረጃ አላቀረበም፡፡ ጭማሪውም በዝርዝር ተሰልቶ ለትምህርት ተቋማት ገና አልተደላደለም፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት፣ ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመጨመር ውሳኔ ተላልፎ፣ ልዩ በጀት ተመድቦ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ዘንድሮም በተመሳሳይ ሁኔታ ለመምህራን የደሞዝ ማሻሻያ፣ የ5 ቢ. ብር ልዩ በጀት ተመድቧል፡፡ ያኔ ለሁሉም የመንግስት ሰራተኞች፣ ለደሞዝ ማሻሻያ ተብሎ የተመደበው ልዩ በጀት 7 ቢ ብር እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በአማካይ የሰላሳ በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ ውሏል፡፡ ከዚህ ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ ለመምህራን ብቻ የተመደበው የደሞዝ ጭማሪ በጀት 5 ቢሊዮን ብር መሆኑ ጭማሪው ከፍተኛ እንደሚሆን ያሳያል፡፡ የአገሪቱ የመምህራን ብዛት ሩብ ሚሊዮን እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን፣ የወር ደሞዝ ጭማሪው በአማካይ 2500 ብር ገደማ ነው፡፡ ይህም የመምህራንን ደሞዝ በእጥፍ ለማሳደግ ያስችላል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ባለፉት 25 ዓመታት ከ1ሺህ በላይ የህትመት ውጤቶች ከገበያ ውጪ ሆነዋል

ባለፉት 25 አመታት ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑ ጋዜጦችና መጽሔቶች ከህትመት ውጪ የሆኑ ሲሆን በአሁን ወቅት የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው ተብሏል፡፡  ከ1993 ዓ.ም ወዲህ በአጠቃላይ 1400 ያህል የፕሬስ ድርጅቶች የምዝገባ ሠርተፍኬት መውሰዳቸውን የጠቆሙት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ጣፋ፤ በአሁን ወቅት ግን በህትመት ላይ ያሉት ጥቂት ናቸው ብለዋል፡፡ወደ ህትመት ከገቡት ውስጥ ከ2ሺህ በላይ የሚሆኑት ለመረጃ ተደራሽ ባለመሆን፣ በአከፋፋዮች ተፅዕኖ፣ በፋይናንስ አቅምና ኢ-ፍትሐዊ በሆነ የማስታወቂያ ክፍፍል ምክንያት ህትመታቸው መቋረጡን ለአዲስ አድማስ ያስረዱት አቶ ወርቅነህ የብሔር ብሔረሰቦች መብትን፣ የሃይማኖት እኩልነትንና በአጠቃላይ ህገመንግስቱን የሚፃረሩ ተግባራት ላይ ተሠማርተው የተገኙ በጣት የሚቆጠሩ የህትመት ውጤቶችም በህግ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡ “አንዱ የግንቦት 20 ፍሬ የህትመት ኢንዱስትሪው እንደ አሸን የፈላበት ሂደት ነው” ያሉት አቶ ወርቅነህ፤ አብዛኞቹ የህትመት ውጤቶች በራሣቸው ችግር ከገበያ የወጡ ናቸው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ሆነው በሣተላይት አማካኝነት የሚሠራጭ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፍቃድ ለመስጠት ባለስልጣኑ ያወጣውን የውድድር ማስታወቂያ ተከትሎ እስካሁን 27 ድርጅቶች ፍላጐት አሳይተዋል ተብሏል፡፡ ባለስልጣኑ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ህዳሴ ግድብ፤ በ5 ዓመት ወጪውን ሊመልስ ይችላል

• “በአመት 1 ቢ.ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል”• ግድቡ የአፄ ኃይለስላሴ ህልም ነበረ - ታይም መጽሔትህዳሴ ግድብ ከአመት በኋላ ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንደሚጀምር የዘገበው ታይም መጽሔት፣ ግንባታው፣ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጅ ቢሆንም፣ በየዓመቱ 1. ቢ ዶላር ገቢ ሊያስገኝ እንደሚችል ገለፀ፡፡ የአገሪቱ የኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ የህዳሴ ግድብ ሲጨመርበት፣ አራት እጥፍ እንደሚሆን መጽሔቱ ጠቅሶ፤ የአገር ውስጥን የኤሌክትሪክ እጥረት ያቃልላል፤ ከሱዳንና ከግብጽ ማሰራጫ መስመሮች ጋር ሲገናኝም፣ በየዓመቱ 1 ቢ.ዶላር የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስገኝ የኤምአይቲ ጥናት ያሳያል ብሏል፡፡አፄ ኃይለስላሴ፣ ግድቡን የመገንባት ህልም እንደነበራቸውና የዛሬ ሃምሳ ዓመት ግንባታውን ለማካሄድ ወስነው እንደነበር አስታውሷል - መጽሔቱ፡፡ የገንዘብ እጥረት፤ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ከባድ የድርቅ አደጋ፣ የደርግ መፈንቅለ መንግስት…ሌሎችም በርካታ ችግሮች ተደራርበው፣ የግድቡ ዕቅድ ለግማሽ ምዕተዓመት ዘግይቷል፡፡በ2003 ዓ.ም በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ይፋ የተደረገው የግድብ ግንባታ፣ አሁን እንደተጋመሰና በግዙፍነቱ በአፍሪካ ቀዳሚ እንደሆነ መጽሔቱ ጠቅሶ፤ በግድቡ የሚፈጠረው ሃይቅ የወንዙን ውሃ ሙሉ ለሙሉ የማጠራቀም አቅም አለው ብሏል። በሚቀጥለው አመት ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንደሚጀምርም መጽሔቱ በሰሞኑ እትሙ ገልጿል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“በኦሮሚያ በተከሰቱ ግጭቶች 173 ነዋሪዎችና 14 ፖሊሶች ሞተዋል”

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ ተከስቶ በነበረው ተቃውሞና ግጭት 173 ሰዎች መሞታቸውንna 14 የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ገልፆ የመንግስት ፀጥታ አካላት የወሰዱት እርምጃ ተመጣጣኝ ነበር ብሏል፡፡ ሪፖርቱን ትናንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀረቡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር፤ በተለይ ግጭቱ ጠንካራ በነበረባቸው ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ሠፊ ምርመራ መካሄዱን ጠቅሰዋል፡፡ ተቃውሞና ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ከህዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የደረሱ ጉዳቶችን መመርመሩን የገለፀው ኮሚሽኑ፤ ወደ ክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች 23 ባለሙያዎችን የያዘ 9 የምርመራ ቡድን ተንቀሳቅሶ በአካል ምልከታ፣ በቃለ መጠይቅ፣ በቡድን ውይይት፣ የተለያዩ ሰነዶችን በመፈተሽ ማስረጃ ተሰባስቧል ተብሏል፡፡ የግጭቱና ተቃውሞው መነሻም የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ስራ አጥነት፣ የፍትህ እጦት መሆናቸው የተጠቀሱ ሲሆን የመንግስት ፖሊሲዎችና አፈፃፀሞች ላይ ክፍተት መኖሩም ለተቃውሞው ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ፖሊሶችና የህግ አካላት አላግባብ ድብደባን የሚፈፅሙ ሲሆን ፍትህን በሙስናና በጥቅማጥቅም እንደሚለውጡም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ በደጀንነት የተፈረጀው ኦነግና ህጋዊ እውቅና ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግጭቱን በማባባስ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላላ የፌደራል በጀት 275 ቢሊዮን ብር፣ ለፌደራል ባጀት 175 ቢሊዮን ብር፣ ለክልሎች 100 ቢ. ብር

በግንባታ ስራ ላይ መሰማራት ሳያዋጣ አይቀርም፡፡ ከፌደራል በጀት ውስጥ 75 ቢ. ብር ለግንባታ የተመደበ ነው፡፡ በትልቅ በጀት ቀዳሚነቱን የያዘው፣ የመንገድ ግንባታና ጥገና ነው - 46 ቢ. ብር፡፡ 38 ቢ. ብር የተመደበላቸው ዩኒቨርስቲዎች፣ ሁለተኛ ደረጀ ላይ ተቀምጠዋል - በገንዘብ ብክነትና በዝርክርክነት ግን አንደኛ ሆነዋል፡፡ 26 ቢ. ብር - መጠባበቂያ እህል ለማከማቸት ይውላል ተብሏል፡፡ 14 ቢ. ብር ለእዳ ክፍያ (10 ቢ. ብሩ ለወለድ ክፍያ ነው)11 ቢ. ብር ለመከላከያ፣ 2.3 ቢ. ብር ለፌደራል ፖሊስ፣ 1.2 ቢ. ብር ለብሔራዊና ለመረጃ ደህንነት የእርሻ በጀት 8.6 ቢ ብር ቢሆንም፣ እንደ ድሮው ለምርት እድገት ሳይሆን፣ በአብዛኛው ለችግረኞች ድጐማ ተመድቧል፡፡ 8.8 ቢ. ብር ለውሃ የተመደበ ነው፡፡ ግን በሃብት ብክነቱም ቀላል አይደለም፡፡ ከአስር ዓመት በፊት ይጠናቀቃሉ የተባሉ፣ ግድቦች ዘንድሮም ብዙ መቶ ሚሊዮን ብር ተመድቦላቸዋል ለጤና አገልግሎት የሚውለው ገንዘብ 8.2 ቢሊዮን ይሆናል፡፡ ከዚህ ውስጥ 6 ቢ. ብር በውጭ አገር እርዳታ የሚሸፈን ነው - በአብዛኛውም በአሜሪካ መንግስት እርዳታ፡፡ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ በቀን 10 ሰዎች በመኪና አደጋ ይሞታሉ

• በመንጃ ፈቃድ አሰጣጡ ላይ ማስተካከያ ሊደረግ ነው• በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የሚቀመጥና የመንጃ ፈቃዶችን በማዕከላዊነት የሚመዘግብ ሰርቨር ሥራ ጀምሯል• ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እየደረሰ ያለው በዘመናዊና አዳዲስ መኪኖች ነው     በኢትዮጵያ በከፍተኛ ቁጥር በጨመረው የትራፊክ አደጋ፤ በቀን 10 ሰዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡና 31 ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት እንደሚዳረጉ ተገለፀ፡፡የትራንስፖርት ባለስልጣን በመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ዙሪያ ለብዙኃን መገናኛ  ባለሙያዎች አዘጋጅቶት በነበረው ስልጠና ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ የግንዛቤ ትምህርት ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ድል አድርጋቸው ለማ እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ በየጊዜው እየጨመረ በሄደው የትራፊክ አደጋ ቁጥር፣ ባለፈው ዓመት ብቻ 3ሺ847 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። 5ሺ918 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ 6ሺ508 ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚሁ ዓመት ከ668 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት መውደሙንም አቶ ድል አድርጋቸው ተናግረው፤ በቀን በአማካይ 10 ሰዎች ከትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን እንደሚያጡና 31 ለአካል ጉዳት እንደሚዳረጉ አቶ ድል አድርጋቸው ገልፀዋል፡፡ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እያደረሱ ያሉት ከ5-10 ዓመት ብቻ ያገለገሉ አዳዲስ መኪናዎች
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የላሊበላ ቤተ ሩፋኤል እና ቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደሶች በ15 ሚ. ብር ወጪ ተጠገኑ

በዩኔስኮ የዓለም አስደናቂ ቅርሶች ከተመዘገቡትና የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አካል የኾኑት የቤተ ሩፋኤልና ቤተ ገብርኤል አብያተ መቅደሶች፤ በረጅም ጊዜ አገልግሎትና በተፈጥሮ በደረሰባቸው የመሠንጠቅና የማፍሰስ ጉዳት የተነሣ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ የነበሩ ሲኾን፤ በ15 ሚሊዮን ብር ወጪ ውጤታማ ጥገና እንደተደረገላቸው ተገለጸ፡፡ከዩኔስኮ፣ ከዓለም ቅርስ ፈንድ(World Monument Fund) እና ከአሜሪካ መንግሥት(American Ambassador’s Fund) በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ የተካሔደውን የጥገና ፕሮጀክት በሓላፊነት ያሠራው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የቅርስ ጥበቃ መምሪያም፤ ከፕሮጀክቱ ጥናት እስከ ፍጻሜው ድረስ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በባለቤትነት መሳተፏ ታውቋል፡፡አምስት ዓመት በወሰደው የፕሮጀክቱ ጥናት መሠረት፣ ኦልሚ ኦሊንዶ የተባለ አገር በቀል ደረጃ አንድ ኮንትራክተር የአብያተ መቅደሶቹን ጥገና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሲያካሔድ የቆየ ሲኾን፤ የፌደራል ሳይንቲፊክ ኮሚቴ ያስተባበራቸው ኢትዮጵያውያን አርክቴክቸሮችና ጂኦሎጂስቶች ከታዋቂ የእንግሊዝና የጣሊያን ባለሞያዎች ጋር መሳተፋቸው ተጠቅሷል፡፡የውቅር አብያተ ክርስቲያናቱን አካባቢ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈ ኮሚቴም ለፕሮጀክቱ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንደተወጡና፤ የደብሩ አስተዳደርና ማኅበረ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የፌስቱላ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው

በየዓመቱ ከ3500 በላይ አዳዲስ የፌስቱላ ተጠቂ እናቶች ይኖራሉ    ዕድሜዋ ገና በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ ነው፡፡ ልጅነቱን በቅጡ አጣጥማ ሳትጨርስ ገና በለጋ ዕድሜዋ የገጠማት ችግር ከእሷም አልፎ ለቤተሰቦቿ ዱብዕዳ ሆኖባቸዋል። ተወልዳ ካደገችበት የሰሜን ጐንደር ዞን፣ ጃን አሞራ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ትንሽ መንደር ብዙም ባልራቀ ት/ቤት ውስጥ ትምህርቷን እየተከታተለች 6ኛ ክፍል ላይ ደርሳለች፡፡ ትምህርቷን ተምራ ዶክተር የመሆን ህልሟን እውን ለማድረግ በምትታትርበት የለጋነት ዕድሜዋ፣ ተስፋዋን የሚያጨልም፣ ነገዋን የሚያደበዝዝ ችግር ገጠማት፡፡ ገና በ15 ዓመት ዕድሜዋ እስከ አሁን ድረስም ስሙን ለመጥራት አብዝታ በምትፈራው ሰው ተደፈረች። ወቅቱ ትምህርት ቤቶች ለእረፍት የተዘጉበት ነበርና የመደፈር መራራ እውነት በእሷና በደፋሪዋ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር አደረጉት፡፡ በዕድሜ እጅግ በሚበልጣት ሰው የተፈፀመባት የአስገድዶ መድፈር ተግባር የፈጠረባትን የአካልና የሥነልቡና ህመም ብቻዋን ቤቷ አስታማ ተነሳች፡፡ የክረምቱ ወራት አልቆ ት/ቤቶች ሲከፈቱ የደበዘዘ ተስፋዋን ይዛ ወደትምህርት ቤቷ ገባች፡፡ ታዳጊዋ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ  የነበረች ብትሆንም በሰውነቷ ላይ የሚታዩትን ተፈጥሮአዊ ለውጦች የምታስተውልበት ምንም ዓይነት ዕውቀት አልነበራትም፡፡ የአመቱ አጋማሽ ላይ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

እዝራ አብደላ – የጥበብ አድማስ !!!

ሰው በሀገር ይወለዳል ይባላል። ግን ደግሞ ሀገርን የሚወልዱ ሰዎች አሉ።   አብደላ እዝራ ጥበብና ፍቅር የተቃቀፉበት ሀገር በውስጡ ተሸክሟል።አብሮም ኖሯል።  የምናውቀው በተባ ብዕሩ፣በሰላ ሂሱ፣ስለ ጥበብ ሲል ሁሉንም በሚተው ኪናዊ ፍቅሩ ነው።  የአንጋፋ ደራስያንን ሥራ ፈትኗል፤የረገበውን የሀገር ጥበብ ቆንጠጥ አድርጎ በከፍታ አጉልቶ ለማሳየት።  ጠቢባን የሚያደንቁ ውብ ዓረፍተ ነገሮችን ዘክሯል። እምቡጥ አበቦቹን ወጣት ደራሲያንን በሚሳሳ እጁ ኮትኩቷል።  ቸርነቱ በጥበብም በቁስም ነው።   አብደላ እዝራ ጭው ባለ በረሃ ውስጥ ዕድሜውን ሙሉ ለጥበብ ንጽህና እንደ ምንጭ የፈሰሰ ጅረት ነበር!   በፈረሰው  ቅጥር -----     የቆመ የጥበብ ዘብ!!                                   *********           አንጋፋው የጥበብ ሃያሲና የአዲስ አድማስ ጸሐፊ እዝራ አብደላ፣ ቅዳሜ ግንቦት 28  ቀን 2008  ከዚህ ዓለም በሞት  ተለይቶናል። የቀብር ሥርዓቱ እሁድ ተፈጽሟል።  ለቤተሰቡ፣ለወዳጆቹ፣ለአድናቂዎቹና ለጥበብ አፍቃሪያን መጽናናትን እንመኛለን።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሽብር የተከሰሱ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ

“መንግስት የፀረ - ሽብር አዋጁን ተቃውሞን ለማፈን እየተጠቀመበት ነው”   በሽብርተኝነት ተጠርጥረውና ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስትን የጠየቁት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፤ መንግስት የፀረ ሽብር አዋጁን ተቃውሞዎችን ለማፈን እየተጠቀመበት ነው ብለዋል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ 9 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አባል የሆኑበት ማህበር ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግስት የፀረ ሽብር አዋጁን ጋዜጠኞችን፣ ፖለቲከኞችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ለማሳደጃነት እየተጠቀመ ነው ብሏል፡፡ በተለይ በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን ግጭትና ተቃውሞ ተከትሎ ያለአግባብ በፀረ ሽብር ህጉ ተከሰዋል ሲል ከጠቀሳቸው መካከል የ “ነገረ ኢትዮጵያ” ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው፣ የኦፌክ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ይገኙበታል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማህበሩን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ፓርላማ፣ የአሜሪካ መንግስትና ሌሎች ሀገራት የኢትዮጵያ መንግስት የፀረ ሽብር ህጉን ያለ አግባብ እንዳይጠቀም ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርቡም እስካሁን ተቀባይነት አላገኙም ብሏል -
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

እነ አቶ በቀለ ገርባ ባዶ እግራቸውን፣ ባልተለመደ አለባበስ ፍ/ቤት ቀረቡ

• የክስ መቃወሚያቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል    በኦሮሚያ ከተፈጠረው ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት የኦፌኮ ተ/ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ተከሳሾች ባልተለመደ አለባበስ ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን በአቃቤ ህግ ለቀረበባቸው ክስ መቃወሚያቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ትናንት ጠዋት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 19ኛ ወ/ችሎት መቃወሚያቸውን ይዘው ከቀረቡት  22 ተከሳሾች መካከል አቶ በቀለን ጨምሮ ግማሽ ያህሉ፣ በቁምጣ፣ በካኒቴራና ባዶ እግራቸውን የተገኙ ሲሆን፤ ይህን ያደረጉት ሃሙስ እለት በማረሚያ ቤት በተደረገባቸው ፍተሻ፣ ለችሎት ሊለብሱ ያዘጋጁት ልብስ ስለተወሰደባቸው መሆኑን ለፍ/ቤቱ ተናግረዋል፡፡ በማረሚያ ቤቱ በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን ለፍ/ቤት ያመለከቱት አቶ በቀለ ገርባ፤ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ፍ/ቤት እስኪቀርቡ ምግብ አለመመገባቸውን ጠቁመው ማረሚያ ቤት እንዲቀየርላቸው ጠይቀዋል፡፡ የተከሣሾቹን አቤቱታ ያዳመጠው ፍ/ቤቱ ማረሚያ ቤቱ የራሱ ደንብና ስነ ስርአት ሊኖረው እንደሚችል ጠቅሶ፤ ተከሳሾች የተለየ ትኩረት የሚስብ አለባበስ መልበስ እንደሌለባቸው፤ በአንፃሩም ማረሚያ ቤቱ “ይሄን ልበሱ፤ ያንን አትልበሱ” ማለት አልነበረበትም ብሏል፡፡ማረሚያ ቤቱ ይቀየርልን ለሚለው የተከሳሾቹ ጥያቄ፤ ፍ/ቤቱ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በላይ የትም መሄድ እንደማይቻል ጠቅሶ በደል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጠበቃ እንዲያቆሙ መንግስት መፍቀዱን እንግሊዝ አስታወቀች

ሰሞኑን ኢትዮጵያን የጎበኙት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃሞንድ፣ በሽብር ወንጀል ተከስሰው ሞት የተፈረደባቸውና በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ የህግ ድጋፍ የሚያደርግላቸው ጠበቃ ማቆም ይችላሉ የሚል ማረጋገጫ ከኢትዮጵያ መንግስት እንዳገኙ ተገለጸ፡፡ሪፕራይቭ የተባለው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም በበኩሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ አንዳርጋቸው ከእስር ተፈትተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ የኢትዮጵያን መንግስት አልጠየቁም በሚል ትችት ሰንዝሮባቸዋል፡፡ባለፈው ረቡዕ ኢትዮጵያን የጎበኙት ፊሊፕ ሃሞንድ፤ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ በጉብኝታቸው ዋና አጀንዳ እንዳደረጉት የጠቆመው የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ዙሪያ መምከራቸውንና አቶ አንዳርጋቸው ጠበቃ ማቆም እንደሚችሉ ማረጋገጫ እንደተሰጣቸውም ገልጧል፡፡ፊሊፕ ሃሞንድ ምንም እንኳን አቶ አንዳርጋቸውን የእንግሊዝ ቆንስላ እንዲጎበኛቸው መፈቀዱና ወደ ፌደራል እስር ቤት እንዲዛወሩ መደረጋቸው አንድ እርምጃ ቢሆንም፣ ሌሎች ቀጣይ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ ማርያም መግለጻቸውንና፣ የህግ አማካሪ እንዲኖራቸው መፈቀዱን ተናግረዋል፡፡እንግሊዝ በሌሎች አገራት የፍትህ ስርዓት ጣልቃ እንደማትገባ የገለጹት ፍሊፕ ሃሞንድ፤ የአገሪቱ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፤ የግድቡን ህልውና መካድ አያዋጣንም አሉ

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜን ሹክሪ፤ “የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እውን ሆኗል፣ ህልውናውን ለመካድ መሞከር ራስን መሸንገል ነው፤ በተጨባጭ የምናየውን ግድብ ህልውና ለመካድ መሞከር አያዋጣንም” ማለታቸውን አሃራም የተባለው የአገሪቱ ድረገጽ ዘገበ፡፡ሚኒስትሩ ባለፈው ማክሰኞ አል-ሃያት በተባለው የአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባደረጉት ንግግር፣ አገሪቱ የግድቡን ጉዳይ በተመለከተ የምታደርገው እንቅስቃሴ በጥርጣሬ፣ ባለመተማመንና በተጋነኑ አደጋዎች ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን ጠቁመው፣ ይሄም ሆኖ ግን ከግድቡ ጋር በተያያዘ ለአገሪቱ አስጊ የሆኑ አደጋዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡መንግስታቸው እነዚህ አደጋዎች በአገሪቱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት የማያደርሱበትን መላ ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም ከኢትዮጵያና ከሱዳን ጋር ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ቢናገሩም፣ የአደጋዎቹን ባህሪና ምንነት በተመለከተ ግን ግልጽ ማብራሪያ አለመስጠታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አቃቤ ህግ በሽብር ለተከሰሱት አቶ ዮናታን ተስፋዬ መቃወሚያ ምላሽ ሰጠ

የኦነግን አላማ ለማስፈፀም ተንቀሳቅሷል፤ በፌስ ቡክ አመፅና ብጥብጥ ቀስቃሽ ፅሁፎች አሰራጭቷል የሚል ክስ የተመሰረተበት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ላቀረበው የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ ምላሽ ሰጠ፡፡ ተከሳሹ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፤ የክስ መቃወሚያቸውን በዝርዝር ባቀረቡበት ወቅት ህገ መንግስቱ በሰጣቸው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጠቀም ሃሳባቸውን መግለፃቸው ሊያስከስሳቸው እንደማይገባና በኦሮሚያ የተነሳው ብጥብጥ ጠ/ሚኒስትሩ የመልካም አስተዳደር ችግር የፈጠረው መሆኑን ማረጋገጣቸውን በመጥቀስ “ልጠየቅበት አይገባም” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ መቃወሚያ ምላሹን በ5 ነጥቦች ከፋፍሎ በፅሁፍ አቅርቧል፡፡ አቃቤ ህግ፤ አቶ ዮናታን በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ፅፈውታል ያለውን አንድ ፅሁፍ በመጥቀስ፤ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረውን ግጭት ለማስቀጠልና ሌሎችን ለአመፅ ለማነሳሳት አስቦ በፃፈው ቀስቃሽ ፅሁፍ፤ የአሸባሪውን ድርጅት አላማ ለማሳካትና ለማስቀጠል በማለም የፃፈው ፅሁፍ ነው ብሏል፡፡ በተከሳሹ ላይ የቀረበው ክስ በተገቢው መንገድ ህጉ በሚያዘው ተሟልቶ የቀረበ ነው ያለው አቃቤ ህግ፤ መቃወሚያው ውድቅ እንዲደረግለት ፍ/ቤትን ጠይቋል፡፡ ተከሳሹ፤ “የመልካም አስተዳደር እጦት ችግር እንጂ የኦነግ ተግባር አለመሆኑ የህግ ግምት ሊወሰድበት ይገባል” ብለው
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በፈተና ስርቆት ላይ ፖሊስ ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሏል

ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቋረጥ ምክንያት የሆነውን የፈተና መሰረቅ ጉዳይ ፖሊስ እየመረመረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ለድጋሚ ፈተና የህትመትና የመጠረዝ ስራ እየተከናወነ ነው ተብሏል፡፡ በስርቆቱ ጉዳይ የሚደረገው ምርመራ በተጠናከረ መልኩ ሙሉ ለሙሉ በፀጥታ ኃይሎች መያዙን ያስታወቁት በትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አህመድ ሲራጅ፤ ጉዳዩን ተከታትሎ ለህግ የማቅረብ ስራ የፖሊስ መሆኑን ጠቁመው ጉዳዩ የፀጥታ አካላት የሚፈትኑበት ነው ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የህግ ባለሙያ፤ በመንግስት ከፍተኛ መስሪያ ቤት እንዲህ ያለው ወንጀል ሲያጋጥም ፖሊስ በሁለት መንገድ ምርጫ ሊያደርግ እንደሚችል ጠቅሰው አንደኛ ቀጥታ ጥቆማ ከመስሪያ ቤቱ ሲደርሰው፣ ጥቆማ ካልደረሰው ያገኘውን ፍንጭ መነሻ አድርጎ ምርመራ እንደሚያደርግ አብራርተው፤ ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ “ፈተናው ተሰርቋል” ተብሎ ይፋ በተደረገ ጊዜ ፖሊስ ምን ህል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ምርመራ ለማድረግ እንደሞከረ መጠየቅ አለበት ብለዋል፡፡ ትምሀርት ሚኒስቴር በበኩሉ፤ በአሁን ወቅት በዋናነት ትኩረት የሰጠው ፈተናው በድጋሚ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በጥንቃቄ ማካሄድ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለአዲስ አድማስ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“ሀገሪቱ በዲሞክራሲና በፍትህ ወደፊት አልተራመደችም”

“ሀገሪቱ በዲሞክራሲና በፍትህ ወደፊት አልተራመደችም”ባለፉት 25 ዓመታት ሀገሪቱ በዲሞክራሲ፣ በሰብአዊ መብትና በፍትህ የሚጠበቅባትን ያህል ወደፊት አልተራመደችም ሲሉ አንጋፋ የህግ ባለሙያዎች የተቹ ሲሆን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፤ በአሁኑ መንግስት ከምንግዜውም የተሻለ የዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብትና የፍትህ ስርአት ተዘርግቷል ብለዋል፡፡ አንጋፋው የህግ ባለሙያ አቶ አብዱ አሊ ሂጅራ ለአዲስ አድማስ በሰጡት አስተያየት፤ “ዲሞክራሲ ማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ነው፤ በአሁን ወቅት ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ የሚችል ስርአት አልተፈጠረም” ብለዋል፡፡ “ዲሞክራሲ በሌለበት ነፃ ፍ/ቤት ሊኖር አይችልም” ያሉት ዓለምአቀፉ የህግ ባለሙያ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም በበኩላቸው፤ ወንጀል የሰሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት በህግ አለመጠየቃቸውን ጠቅሰው የህግ የበላይነትም እየተከበረ አይደለም ብለዋል፡፡ “ለፍትህ ስንቅ የሆኑ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን የሚንዱ አዋጆች መፅደቃቸው የፍትህ ስርአቱ ወደፊት እንዳይራመድ አድርጎታል” ሲሉም ተችተዋል፤ ዶ/ር ያዕቆብ፡፡ ሌላው የህግ ባለሙያ አቶ ተማም አባቡልጉ፤ የፍትህ ስርአቱ በሚፈለገው መጠን ገና እንዳልተመሰረተ ገልፀው፤ የፍትህ ተቋማት መኖር ብቻውን ፍትህ አለ አያስብልም ብለዋል፡፡ “የህግ የበላይነት ሠፍኗል ብዬ አላምንም” ያሉት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢንተርኔት ጽሑፎችን ለመቆጣጠር ህግ ሊወጣ ነው

በኢንተርኔት የሚሰራጩ ጽሑፎችን፣ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለመቆጣጠር፣ መንግስት አዲስ ህግ እያዘጋጀ ነው፡፡ ህጉ የሚዘጋጀው በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲሆን፤ በኢንተርኔት የሚሰራጩ መረጃዎችንና በኢንተርኔት የሚከናወኑ ስራዎችን በሙሉ የመቆጣጠር ስልጣን እንዳለው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ገልጿል፡፡ የኢንተርኔት መረጃዎችን ለመቆጣጠር የህግ ሰነድ ለማዘጋጀትም፣ ከሁለት ኩባንያዎች ጋር ጥናት ለማካሄድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ተፈራርሟል፡፡ “Grail Consulting and Project Management Services” የተባለ የውጭ አገር ኩባንያ ጥናቱን ሲያካሂድና፤ “Perago Information Systems” የተባለ የሀገር ውስጥ ኩባንያ በአጋርነት ይሰራል ብሏል፡፡ የመንግስት አካላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማነጋገርና መረጃ በመሰብሰብ ጥናቱ ይካሄዳል ብሏል - ሚኒስትሩ፡፡ የኢንተርኔት የመረጃ ጠለፋንና ተመሳሳይ ድርጊቶችን፤ እንዲሁም የመንግስት መርማሪዎች ስልጣንን በሚመለከት በቅርቡ አዲስ ህግ ተዘጋጅቶ የወጣ ሲሆን፤ በኢንተርኔት የሚሰራጩ መረጃዎችን ላይ የሚደረጉ ቁጥጥሮችንም ያካተተ እንደነበር ይታወቃል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ቴዎድሮስ ከቀናቸው፣ የ600ሺ ብር ደሞዝተኛ ይሆናሉ

ከኢትዮጵያ መንግስት በፊት፣ 31 አገራት ለዶ/ር ቴዎድሮስ ድጋፍ ሰጥተዋልየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ከአመት በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለመሆን በምርጫ ካሸነፉ፣ በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ የያዙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ይሆናሉ፡፡ ለዓለም ጤና ድርጅት መሪነት ድጋፍ ሲያሰባስቡ የቆዩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ከ31 የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ እንዳገኙ መረጃዎች አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፉን የገለፀው፣ ገና በዚህ ሳምንት እንደሆነም፣ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ዶ/ር ቴዎድሮስን ጨምሮ አምስት ሰዎች በየፊናቸው ድጋፍ ለማግኘት ሲጣጣሩ የቆዩ ቢሆንም በመጪው ሐምሌ ወር ለሚካሄደው ምርጫ በተወዳዳሪነት የሚቀርቡት ግን ሶስት እጩዎች ብቻ ናቸው፡፡ የአለም አገራት በሚሰጡት ድምጽ ቀዳሚውን ደረጃ ያገኘ ተወዳዳሪ፣ የአለም ጤና ድርጅት ዳሬክተር ይሆናል፡፡ ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሸነፉ፣ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይሆናሉ ተብሏል፡፡ የዳሬክተሩ የወር ደሞዝ 31ሺ ዶላር ገደማ ነው (ከ600ሺ ብር በላይ)፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የእንግሊዝን መንግስት ልትከስ ነው

በየመን በኢትዮጵያ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉትና በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የሆነቺው የ9 አመቷ ታዳጊ ምናበ አንዳርጋቸው፤ አባቴ ከእስር የሚፈታበትን መንገድ አላመቻቸም በሚል የእንግሊዝን መንግስት ልትከስ እንደሆነ ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡ የታዳጊዋ የህግ ባለሙያዎች የእንግሊዝ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚገባውን ያህል አለመከታተሉና ከእስር የሚፈቱበትን መንገድ ለመፈለግ እስከመጨረሻው አለመግፋቱ በህግ ያስጠይቀዋል ማለታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የእንግሊዝን መንግስት በህግ መጠየቁ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከእስር የሚፈቱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያስችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው መናገራቸውን ገልጧል፡፡በእንግሊዝ የውጭና የኮመንዌልዝ ቢሮ ፤የአቶ አንዳርጋቸው እስርና አያያዝ ተቀባይነት የሌለው ነው ቢልም፣ ከእስር ተፈትተው እንዲወጡ ግፊት አላደረገም ያለው ዘገባው፣ ልጃቸው ምናበ፤ አባቷ የሚፈቱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ተጨማሪ ጥረት ያደርጋል በሚል ተስፋ መንግስትን ለመክሰስ መዘጋጀቷን ጠቁሟል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዲቢኤል ግሩፕ በ2 ቢ. ብር የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

ዲቢኤል ግሩፕ የተባለው ታዋቂ የባንግላዴሽ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራች ኩባንያ በትግራይ ክልል ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን ዴይሊ ስታር ድረገጽ ትናንት ዘገበ፡፡በቀጣዩ አመት የካቲት ወር ላይ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ የማምረት ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው የጨርቃ ጨርቅና የአልባሳት ፋብሪካው፤ ለ3 ሺህ 500 ሰራተኞች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር የኩባንያው ከፍተኛ የስራ ሃላፊ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ኩባንያው ለፋብሪካው ግንባታ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካገኘው 55 ሚሊዮን ዶላር ብድር በተጨማሪ የ15 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከስዊድን መንግስት የልማት ፈንድ ማግኘቱን የጠቆመው ዴይሊስታር፣ ምርቶቹን ወደተለያዩ የአውሮፓ፣ የአፍሪካ፣  የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራትና ወደ አሜሪካ ኤክስፖርት ለማድረግ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የፓትሪያሪኩን ስም በማጥፋት የተከሰሰው የ“ሰንደቅ” ዋና አዘጋጅ በዋስ ተለቀቀ

የ100ሺ ብር የፍትሃብሔር ክስም ቀርቦበታልየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት፣ የፓትሪያርኩን ስም በማጥፋት ወንጀል የተከሰሰው የ“ሰንደቅ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ፍሬው አበበ ፍ/ቤት ቀርቦ በ5ሺህ ብር ዋስ ተለቀቀ፡፡ ቤተ ክህነት ከወንጀል ክሱ በተጨማሪ ላይ የ100 ሺህ ብር ካሳ እንዲከፈላትም በጋዜጠኛው ላይ የፍትሃ ብሄር ክስ አቅርባለች፡፡ መጋቢት 25 ቀን 2008 ዓ.ም በ“ሰንደቅ” ጋዜጣ ዕትም ላይ “ፓትርያርኩ ለኢትዮጵያ የደህንነት ስጋት ለምዕመናን የድህነት ስጋት” በሚል ርዕስ የተፃፈውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፅሁፍ በማተሙ ነው ቤተ ክህነት ክሱን የመሰረተችው፡፡ ቤተክህነት ያቀረበችው የቀረበው የክስ ዝርዝር እንደሚያስረዳው፤ ለክሱ ምክንያት የሆነው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፅሁፍ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋዋማዊ አሰራር ጥላሸት የሚቀባና የፓትርያርኩን ስም የሚያጠፋ እንዲሁም በመልካም ስምና ዝናቸው ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ህዝበ ክርስቲያኑ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ አሰራር እንዳይቀበል የሚያደርግ ፅሁፍ በጋዜጣው ታትሞ እንዲወጣ ያደረገ በመሆኑ በፈፀመው ስም የማጥፋት ወንጀል መከሰሱን ይጠቁማል፡፡ ቤተ ክህነቷ ከዚሁ የክስ ጭብጥ ጋር በተያያዘ ጋዜጠኛው አድርሶብኛል ላላቸው የህሊና ጉዳት የ100 ሺህ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ማህሙድ አህመድ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀበለ

አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ፤የክብር ዶክትሬቱን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትላንት ተቀበለ፡፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አርቲስቱ ላበረከተው ድንቅና የረጅም ጊዜ የኪነ ጥበብ ስራ በ2007 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ፣ የክብር ዶክትሬት ከሰጣቸው አራት ሰዎች አንዱ አንደነበር የሚታወስ ሲሆን ማህሙድ በወቅቱ በአገር ውስጥ ባለመኖሩ ተወካዩ በሥነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደነበረ የዩኒቨርሲቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሴ ደስታ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በትላንትናው እለት አርቲስቱ ራሱ በአካል ተገኝቶ ከዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬቱን ተቀብሏል፡፡ በዚህ ሥነ ስርዓት ላይ የቀድሞው የጎንደር ፋሲለደስ የኪነት ቡድን ዳግም  ምስረታም ተካሂዷል፡፡ ማህሙድ አህመድ፤ በቅርቡ 75ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ሲያከብር በማሪዮት ሆቴል ለእይታ ከቀረቡት 75 ፎቶዎቹ መካከል 40 ያህሎ በጎንደር ሥነ ሥርዓቱን ምክንያት በኤግዚቢሽን መልክ ለእይታ የቀረቡ ሲሆን ለአንድ ሳምንት ለተመልካች ክፍት ሆነው እንደሚቆዩም አቶ ደምሴ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በርካታ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ሸገር የከተማ አውቶቡስ ሥራ ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ችግር እንደሚፈታ የተነገረለት ሸገር የከተማ አውቶቡስ ትናንት ስራ የጀመረ ሲሆን ለአንድ አውቶቡስ 3.61 ሚ. ብር ፣ ለ50 አውቶብሶች 180 ሚ. ብር ወጪ መደረጉ ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ብረታ ብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን እንዲሰራለት ካዘዛቸው 300 አውቶቡሶች ውስጥ 50ዎቹን ተረክቦ ሥራ ማስጀመሩን የአስተዳደሩ የትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ካፓሲቲ ኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን አማረ ገልጸዋል፡፡ አውቶብሶቹ ከአንድ ኪሎ ሜትር በታች የሚቆሙ ስላልሆነ፣ የረዥም ርቀት ፍላጎት የሚያሟሉ ናቸው ያሉት አቶ ሙሉቀን፤ ታሪፋቸውም ኪስ አይጎዳውም ብለዋል፡፡ እስከ 4 ኪሎ ሜትር 1.50፣ ከ4-6 ኪ.ሜ 2 ብር፣ ከ6-9 ኪ.ሜ 3 ብር፣ እስከ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት 3.50 እንደሚያስከፍሉ በመግለፅ፡፡ አውቶብሶቹ ለጊዜው የሚጓዙባቸውና የተመረጡ መስመሮች፡- ከሜክሲኮ ቦሌ፣ ከቦሌ ፒያሳ፣ ከፒያሳ መገናኛ፣ ከሜክሲኮ ዓለም ባንክ፣ ከሳሪስ አቦ መገናኛ እንደሆኑ የጠቀሱት ኃላፊው፤ ከ3ወር በኋላ 150 አውቶብሶች ሲረከቡ የመስመሮቹ ቁጥር 21 እንደሚደርስና የቀሩትን አውቶቡሶች አጠናቀው አጠናቀቁ ሲረከቡ እንደየአስፈላጊነቱ ሌሎች መስመሮች እንደሚከፈቱ አስረድተዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዛምቢያ ለ40 ኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት አደረገች

554 እስረኞች እንዲለቀቁ ወስኗልየዛምቢያ ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ 40 ኢትዮጵያውያን ወጣት ጥፋተኞችን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ተከስሰው ለተቀጡና በእስር ላይ ለሚገኙ 554 እስረኞች ባለፈው ማክሰኞ ምህረት ማድረጋቸውን ዛምቢያን ናሽናል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገበ፡፡ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ረቡዕ የተከበረውን የአፍሪካ የነጻነት ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት የምህረት ውሳኔ፣ ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣት ጥፋተኞች መቼና በምን ወንጀል ተከስሰው ለእስር እንደተዳረጉ የታወቀ ነገር የለም ያለው ዘገባው፣ ከ2015 አንስቶ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን በዛምቢያ እንደታሰሩ ጠቁሟል፡፡ምህረት የተደረገላቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁሉም በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ የጠቆመው ዘገባው፣ ታስረውበት የነበረው እስር ቤት ግን የአዋቂዎች እንደሆነና፣ መንግስት ባወጣው የምህረት ውሳኔ ኢትዮጵያውያኑን ማካተቱ ትርጉም ያለው ነገር ነው መባሉን ገልጧል፡፡በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዛምቢያ ሉዋንጉዋ ድንበር በኩል አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር እንደሚሞክሩ የገለጸው ዘገባው፣ የአገሪቱ ፖሊሶችና የኢሚግሬሽን ሰራተኞችም በህገወጥ መንገድ ድንበር የሚያቋርጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እየተከታተሉ በቁጥጥር ስር ማዋል መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የግንቦት 20 ስኬቶችና ጉድለቶች በፖለቲከኞች ተገምግሟል

የዘንድሮ የግንቦት 20፣ ሃያ አምስተኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዮ በአል - ባለፉት ዓመታት የተገኙ ስኬቶችንና ፈተናዎችን በመገምገም እንደሚከበር መንግስት የገለፀ ሲሆን አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው ፖለቲከኞች የግንቦት 20ን ትሩፋቶች በመተቸትና በማወደስ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡ የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ በሰጡት አስተያየት፤ በ1983 ዓ.ም ለውጡ ሲመጣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉበት አመራር ተፈጥሮ፤ ሀገሪቱ ለውጥ ታመጣለች የሚል ተስፋ ሰንቀው እንደነበር ጠቁመውና ዛሬ ላይ ሆነው ያለፈውን 25 አመት ሲገመግሙት ግን ያንን ተስፋቸውን በተግባር እንዳላዩት ይናገራሉ፡፡ የአንድ መንግስት ስኬታማነት በመሠረተ ልማትና በኢኮኖሚ እድገት ብቻ አይመዘንም ያሉት አቶ ግርማ፤ ዋናው ስኬት የሰው ልጅ ሠብአዊ መብትና ነፃነት ሲከበር ነው ብለዋል፡፡ የኢኮኖሚው እድገትም ቢሆን ከሀገሪቱ ህዝብ 20 ሚሊዮን ያህሉን ከእለት ተረጅነት አላወጣም ሲሉ ተችተዋል- አቶ ግርማ፡፡ “ባለፉት 25 ዓመታት ቃልና ተግባር አልተገናኙም” ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው፤ የግንቦተ 20 ትልቁ ትርፍ የደርግ መንግስት መወገዱ ነው ብለዋል፡፡ የመንግስት ለውጡ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አንድምታዎች ላይ ለውጥ ያመጣል የሚል ተስፋ እንደነበራቸው የጠቆሙት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች በተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል ተባለ

አደጋዎቹ 100 ያህል ሰዎችን ለሞት ዳርገዋልጎርፉ ተጨማሪ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያፈናቅል ይችላል   በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸው እንደተፈናቀሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስታወቁንና መንግስትም 100 ያህል ዜጎች በአደጋዎቹ ለሞት ተዳርገዋል ማለቱን አልጀዚራ ዘገበ፡፡ በአገሪቱ በመከሰት ላይ ያሉት የጎርፍ አደጋዎች ዜጎችን ከማፈናቀል ባለፈ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች እርዳታን በማከፋፈል እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን የጠቆመው ዘገባው፤ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ትብብር የኢትዮጵያ ተወካይ ፖል ሀንድሊም የተፈጥሮ አደጋዎቹ በቀጣይ ሰብሎችንና እንስሳትን ከማውደም ባለፈ ዜጎችን ለከፋ ችግር ሊያጋልጡ ይችላሉ ማለታቸውን ገልጧል፡፡የእርዳታ ድርጅቶችም የጎርፍ አደጋዎቹ ቀጣይ እንደሚሆኑና ሌሎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያፈናቅል እንደሚችል ግምታቸውን መስጠታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የተፈጥሮ አደጋዎቹ የተከሰቱባቸው አንዳንዶቹ አካባቢዎች የድርቅ ተጎጂ መሆናቸውንና ዜጎችን ለተጨማሪ ችግር መዳረጋቸውን አስረድቷል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በገርጂ ወረገኑ ቤታቸው የፈረሰባቸው፣ ከፖሊስ ጋር በፈጠሩት ግጭት ሰዎች ተጐድተዋል

• ከ2 ሺህ በላይ ቤቶች እየፈረሱ መሆኑ ታውቋል• ግጭቱን ተከትሎ ለ3 ቀናት ት/ቤቶች ተዘግተዋል    በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ገርጂ ወረገኑ በተባለ አካባቢ በህገ ወጥ የመሬት ወረራ ተገንብተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በተሰማራ የደንብ ማስከበር ግብረ ኃይልና በነዋሪዎች መካከል  ውዝግብ ተነስቶ ከፖሊስ ጋር በተከሰተ ግጭት በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በግርግሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ሲናገሩ የፖሊስ ምንጮች በበኩላቸው፤ 3 ፖሊሶችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ከመድረሱ በቀር የሞተ ሰው ስለመኖሩ አልተረጋገጠም ብለዋል፡፡ የዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታልም ከግርግሩ ጋር በተገናኘ ያስተናገደው አስክሬን አለመኖሩን አስታውቋል፡፡ በቦታው ላይ በህገ ወጥ የመሬት ወረራ የተሰሩ ናቸው ያላቸውን ከ2 ሺህ በላይ ቤቶች ለይቶ በማፍረስ ላይ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊዎች ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን ቤት የፈረሰባቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ “ከገበሬው ላይ በውድ ዋጋ የገዛነው መሬት ላይ ጥሪታችንን አሟጠን የሰራነው ቤታችን አማራጭ ሳይሰጠን በኃይል በመፍረሱ ሜዳ ላይ ተበትነናል” ሲሉ አማረዋል፡፡ ባለፈው ረቡዕ ከሌሊቱ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ረብሻ ተቀሰቀሰ

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ረቡዕ የተቀሰቀሰው ረብሻ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲው ቬተርናሪ እና IOT ካምፓሶች የተጀመረው ረብሻ ወደ ዋናው ካምፓስ ተሸጋግሮ፣ ተማሪዎች የመማሪያ ክፍሎችንና በግቢው ውስጥ የሚገኙ ህንፃዎችን መስታወቶች በድንጋይ እየሰባበሩ ነው፡፡  ከዩኒቨርሲቲው ምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ መሰረት፤ ባለፈው ረቡዕ ተማሪዎች ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እንሻለን በሚል ምክንያት የቀሰቀሱት ረብሻ በዩኒቨርሲቲው በሚገኙ ሁሉም ካምፓሶች ተዳርሶ ረብሻው እንደቀጠለ ታውቋል፡፡ በረብሻው ወቅት ከየት እንደመጣ  ያልታወቀ ቦምብ ፈንድቶ ፍንጥርጣሪው በተማሪዎች ላይ ጉዳት በማድረሱ ምክንያት ተማሪዎቹ በህክምና ተቋማት ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ምንጮቻችን ጠቁመውናል፡፡ በጉዳቱ ህይወቱ ያለፈ ሰው ባይኖርም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች እንዳሉ እነዚሁ ምንጮች ገልፀውልናል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ትግሉ መለሰ እንደገለፁልን፤ በዩኒቨርሲቲው፤ ካለፈው እሮብ ጀምሮ የተቀሰቀሰው ረብሻ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ጠቁመው የረብሻው መነሻ ምክንያት ግን እስካሁን አለመታወቁን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዎቹ ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ በኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ለተቀሰቀሰው ረብሻ ጥያቄያቸው በመንግስት ምላሽ በማግኘቱ  ተቋርጦ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የቀዳማዊ ኃ/ ስላሴ የወርቅ ሰዓት ዳግም ለጨረታ ሊቀርብ ይችላል

ንብረትነቱ የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የነበረውና ባለፈው ህዳር ወር ላይ በታዋቂው ዓለምአቀፍ አጫራች ኩባንያ ክርስቲ አማካይነት በጨረታ ሊሸጥ በዝግጅት ላይ ሳለ፣ የንጉሱ ቤተሰቦች ባሰሙት ተቃውሞ ሳቢያ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታግዶ የቆየው 1 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የወርቅ ሰዓት በቅርቡ ዳግም ለጨረታ ሊቀርብ እንደሚችል ብሉምበርግ ዘገበ፡፡ንጉሱ ከአንድ ጣሊያናዊ ባለሃብት በስጦታ እንዳገኙት የተነገረለትና ፓቴክ ፊሊፒ የሚል ስያሜ ያለው ይህ እጅግ ውድ የወርቅ ሰዓት፣ ጄኔቫ ውስጥ ለጨረታ ሊቀርብ ሲል የንጉሱ ቤተሰቦች “ሰዓቱ ከንጉሱ የተዘረፈ ነው፤ ሊመለስልን ይገባል” በማለት ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ተከትሎ፣ የጄኔቫ ፍርድ ቤት ሽያጩ ለጊዜው እንዲሰረዝ በመወሰን ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቷል፡፡ፍርድ ቤቱ በመጨረሻም ሰዓቱ የንጉሱ ቤተሰቦች እንዳሉት ተዘርፎ የተወሰደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ማስረጃ አለማግኘቱንና በመጪዎቹ ሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥም ሰዓቱን ለሽያጭ እንዳያቀርብ በአጫራቹ ድርጅት ላይ የጣለውን ጊዚያዊ እግድ ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ ኦሊቨር ጆርኖት ተናግረዋል፡፡ጊዚያዊ እግዱ የሚነሳ ከሆነ አጫራቹ ድርጅት ሰዓቱን ዳግም ለጨረታ ሊያቀርበው እንደሚችል የጠቆመው ዘገባው፣ ይህም በንጉሱ ቤተሰቦች፣ በአጫራቹ ድርጅትና
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ ሽልማት”ን አገኘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካን አቪየሽንን የ2016 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማት ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደ ስነ-ስርዓት መቀበሉን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡አየር መንገዱ በፋይናንስ እንቅስቃሴና ትርፋማነት፣ በረራን በማዘመን፣ የበረራ መስመር ትስስርን በማስፋፋት፣ በአጠቃላይ የደንበኞች እንክብካቤና በአህጉሪቱ የአቪየሽን ኢንዱስትሪ ልማት አስተዋጽኦ በማበርከት ረገድ በአመቱ ባስመዘገበው የላቀ ውጤት ለሽልማት መብቃቱ ተነግሯል፡፡በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ሽልማቱን የተቀበሉት የአየር መንገዱ ቺፍ ኦፐሬቲንግ ኦፊሰር አቶ መስፍን ጣሰው፤ ሽልማቱ አየር መንገዱ ላለፉት 70 አመታት አፍሪካን አንድ ለማድረግና ከተቀረው አለም ጋር ለማቀራረብ በቁርጠኝነት መስራቱን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡ ሽልማቱን ያበረከቱት የአፍሪካን አቪየሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኒክ ፋዱግባ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨባጭ ውጤቶችን በማስመዝገብ መሪነቱን ይዞ መቀጠሉንና ለአፍሪካ ትልቅ የኩራት ምንጭ መሆኑን በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

“በስኳር ፕሮጀክቶች ላይ “ሜቴክ” ምላሽ ሰጠ

የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፉ ዳኘው የሜቴክፕሮጀክቶችን የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም ከትናንት በስቲያ በተመረቀበት ወቅት ስኳር ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ በተለይ በአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ዘጋቢ ፊልም መስራት ያስፈለገበት ምክንያት መነሻው ምንድነው?ጥናት ሰርቼ ነበር፡፡ የታገልኩለት ስለሆነ ጥናት ሰርቼ ጽሑፍ ያዘጋጀሁት፡፡ ጽሑፉ፣ ከጋዜጠኛዋ ፍፁም የሺጥላ የዘጋቢ ፊልም መነሻ ሀሳብ ጋር በጣም የተቀራረበ ስለነበር ጽሑፉን ሰጠኋት ያንን የማዳበር ስራ፤ ከመስራት በስተቀር ተነሳሽነቱ የጋዜጠኛዋ ነው፡፡ዘጋቢ ፊልሙ ለመስራት ምን ያህል ጊዜና ገንዘብ ወሰደ? ፊ ልሙን ላይ፤ የብረታብረት ኮርፖሬሽን ስራዎች ሁሉውጤታማ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ ሁሉም ነገር ጥሩ ነው ተብሏል፡፡ ግን በፓርላማ እና በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ደግሞ፣ በተለይ ከስኳር ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ አገሪቱ ለብዙ ወጪ ተዳርጋለች ተብላችሁ ተተችታችኋል፡፡ የመጀመሪያውን ጥያቄ ስንመለከት፣ ፊልሙን ያዘጋጁዜጐች፣ ከፊልሙ የጽሑፍ ዝግጅት ጀምሮ፣ በቀረፃ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ ሲሰሩ ከሶስት  ወር በላይ ሳይወስድ አይቀርም፡፡ መነሻ ሃሳቦቹ ከዚያ ቀደም ይላሉ፡፡ ብዙም ደክመውበታል፡፡ሁለተኛ ጥያቄሽን በተመለከተ፣ በዋናነት ማለት የምፈልገው፣ ምንም ክስ ቢነሳም፣ ለእኔ ትልቁ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የስኳር ፕሮጀክቶች እንዳልተሳኩና አገሪቱን ለእዳ እንደዳረጉ በይፋ ተነገረ

2   ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ፤ ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ የአገር ውስጥ እዳየስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች፤ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ተጠያቂ አድርገዋል - ክፍያ ወስዶ የፋብሪካ ግንባታዎችን በእንጥልጥል አስቀርቷል በማለት፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት ደግሞ፤ የስኳር ኮርፖሬሽንን ኃላፊዎች ለከሰምና ለተንዳሆ ግድቦች መጓተት የፌደራል የውሃ ስራዎች ድርጅትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ አዲስ አድማስ፤ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የስኳር ፕሮጀክቶች እንደማይሳኩ ተጨባጭ መረጃዎችንና ትንታኔዎችን በማቅረብ በተደጋጋሚ ዘግቧል፡፡ “ውሎ አድሮ ወደ ቀውስ ማምራቱ አይቀርም”…አዲስ አድማስ 2003 ዓ.ም“የስኳር ፋብሪካዎችን እቅድ ማሳካት ፈጽሞ አይቻልም” 2005 ዓ.ም“መንግስት …10 አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች መገንባት ይችላል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ፣ ‹ተአምር› የማየት ረሃብ ይዟችኋል”…2006 ዓ.ም የስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች ሰሞኑን ለፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት፤ የመንግስት ነባር የስኳር ፋብሪካዎች ውጤታማ አለመሆናቸውን ገልፀው፤ አዳዲሶቹ ፕሮጀክቶች ክፉኛ ተዝረክርከው የብዙ ቢሊዮን ብር ኪሳራ እያስከተሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የፕሮጀክቱ የሀብት ብክነት፣ ህሊናን የሚያቆስል የአገር ጉዳት እንደሆነ ሃላፊዎቹ ጠቅሰው፤ 2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ እንደተጠራቀመ ገልፀዋል፡፡ ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ የአገር ውስጥ ሀብት በፈሰሰባቸው ፕሮጀክቶች፤
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ዘንድሮ 1.5 ሚ. ኢትዮጵያውያን ለድንገተኛ አደጋዎች ይጋለጣሉ ተባለ

መነሻውን ከምስራቃዊው የአገሪቴ ክፍል ባደረገውና በቀጣይነት መላውን የአገሪቱን አካባቢዎች ያዳርሳል በተባለው የጎርፍና ሌሎች ቅፅበታዊ የተፈጥሮ አደጋዎች ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ተጋላጭ ናቸው ተባለ። በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ እስካን ከ100 በላይ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ የአማራ ክልል፣ ደቡብ ክልል፣ ኦሮሚያ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች ለአደጋው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ መሆናቸውን ለአዲስ አድማስ የገለፁት የብሔራዊ አደጋ መከላከል ብሔራዊ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ፤ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ዜጎችን በዘላቂነት ሰላማዊ ወደሆኑ አካባቢዎች ለማዛወር እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት የጎርፍና የመሬት ናዳ አደጋዎች በደረሱባቸው አካባቢዎች ያሉ ዜጎችን በፕላስቲክ መጠለያ ውስጥ ለማስፈር ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አደጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች የምግብና ጊዜያዊ የመጠለያ እርዳታዎች እየተደረጉ እንደሆነ የተናገሩት ኮሚሽነሩ፤ ዝናቡ ባለማቋረጡ ምክንያት የእርዳታ አሰጣጡ ላይ ችግር መፈጠሩንና ጎርፍ የተረጂዎችን ምግብና አልባሳት ጠራርጎ እንደወሰደው ጠቁመው ተጎጂዎቹ በሚደረግላቸው እርዳታ መጠቀም እንዳይችሉ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ደሴ፣ ወልዲያ፣ ሸዋሮቢት ጣና ዙሪያ፣ በኦሮሚያ ክልል በተለይም ከአዋሽ ተፋሰስ ጋር ያሉ እንደ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በደል እየተፈፀምብን ነው ያሉ አባወራዎች ለአማራ ክልል አቤቱታ አቀረቡ

“በአማራ ተወላጅነታችን የብሔር ጭቆና ደርሶብናል” ያሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ ከ400 በላይ አባወራዎች ለአማራ ክልል አመራሮች አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ለአሶሣ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ በሚል ከ6 አመት በፊት ለተወሰደባቸው 163ሺህ ሄክታር መሬት ካሣ እንዲከፈላቸው አሊያም ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው በፍ/ቤት የጠየቁት አባወራዎቹ፤ ከሰሞኑ “በአማራ ተወላጅነታችን በደል እየተፈፀመብን ነው” ሲሉ የአማራ ክልል መፍትሔ እንዲሰጣቸው አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ አባወራዎቹ ለልማት ተብሎ ቦታችን ያለአግባብ ተወስዷል፣ ካሣ አልተከፈለንም፤ ከክልሉ ነባር ተወላጆች እኩል የአስተዳደር አገልግሎት እያገኘን አይደለም” የሚሉ አቤቱታዎችን ለአማራ ክልል አመራሮች በማቅረብ ክልሉ መብታቸውን እንዲያስከብርላቸው ጠይቀዋል፡፡ የመኖሪያና በግብርና የሚተዳደሩበት ቦታቸው ያለ ምንም ካሣ እንደተወሰደባቸው የሚገልፁት አባወራዎቹ፤ የመኖሪያ ቦታ ከሌለንና ተሠማርተንበት በነበረው ግብርና ልጆቻችንን ማሳደግ ካልቻልን የኛ በክልሉ መኖር ትርጉም የለውም ብለዋል፡፡አባወራዎቹ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን አግኝተው ለማነጋገር በማሰብ ከአሶሣ ወደ ባህርዳር ሄደው የነበረ ቢሆንም የክልሉ መንግስት የፕሬዚዳንት ልዩ ረዳት አቶ ሰማ ጥሩነህን ማነጋገራቸውንና ሃላፊውም በፍርድ ቤት የተያዘውን ጉዳይ በሚገባ ተከታተሉ፤ እኛም ይሄን ጉዳይ ሃላፊነት ወስደን በትኩረት እንከታተላለን”
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

አሜሪካ ለድርቁ ተጎጂዎች የ128 ሚ. ዶላር ተጨማሪ እርዳታ ልትሰጥ ነው

የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤአይዲ፣ በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ተጎጂ ለሆኑ ዜጎች 128 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ተጨማሪ የሰብአዊ እርዳታ ለመስጠት መወሰኑን ከትናንት በስቲያ አስታወቀ፡፡በዩኤስኤአይዲ የዲሞክራሲ፣ የግጭትና የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ቶማስ ኤህ ስታል፣ ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ እርዳታው ምግብ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ የስነምግብ አገልግሎቶችና ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድኖችን የሚያጠቃልል መሆኑንና ለአርሶ አደሮችም የተለያዩ የእህል ዘሮች እንደሚከፋፈሉ ተናግረዋል፡፡ተጨማሪ እርዳታው አሜሪካ ድርቁ አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳያስከትል ለመከላከል ስታደርገው የቆየቺውን ጥረት አጠናክራ ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ያሉት ስታል፣ አሜሪካ ከጥቅምት ወር 2014 አንስቶ፣ ለኢትዮጵያ 705 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓንም አስታውሰዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያዊው ወጣት በደቡብ አፍሪካ ዘራፊዎች ተገደለ

በደቡብ አፍሪካ ምስራቃዊ ኬፕታውን በሚገኘው ሴንት ፍራንሲስ ቤይ የተባለ አካባቢ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ባለፈው ሳምንት በዘራፊዎች መገደሉንና ይህን ተከትሎ በአካባቢው የሚገኙ የውጭ አገራት ዜጎች መደብሮች በአገሬው በመዘረፍ ላይ እንደሚገኙ ተዘገበ፡፡ኢዮብ ማዴሞ የተባለው ኢትዮጵያዊ የ27 አመት ወጣት ከ9 ቀናት በፊት ክዋኖምዛሞ በተባለው አካባቢ በሚገኘው መደብሩ ውስጥ እያለ በአንድ ዘራፊ መገደሉን ያስታወሰው ዘገባው፣ ወጣቱን በመግደል የተጠረጠረው ዘራፊ የሌላን ኢትዮጵያዊ መደብር ዘርፎ ካመለጠ በኋላ፣ ባለፈው እሁድ ኢትዮጵያውያን ናቸው በተባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በደረሰበት ድብደባ ህይወቱ ማለፉን ገልጧል፡፡ይህም በአካባቢው በሚገኙ ደቡብ አፍሪካውያን ላይ ቁጣ መቀስቀሱንና የተደራጁ ዘራፊዎች ሲ ቪስታ በተባለው አካባቢ የሚገኙ የውጭ አገራት ዜጎችን መደብሮች መዝረፍ መጀመራቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የአካባቢው የፖሊስ ቃል አቀባይም ስምንት ያህል የውጭ አገራት መደብሮች መዘረፋቸውን እንዳረጋገጡ ገልጧል፡፡ፖሊስ ዝርፊያውን ለማስቆም በአካባቢው መሰማራቱን የጠቆመው ዘገባው፣ በዘረፋው ላይ ተሰማርተዋል በሚል የተጠረጠሩ ሶስት ደቡብ አፍሪካውያንም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ከትናንት በስቲያ በሁማንስ ድሮፕ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታውቋል፡፡በሌላ ዜና ደግሞ የሉዋንግዋ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በገርባ ከተማ በፋሲካ እርድ ሳቢያ ሁከት ተፈጠረ

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገርባ ከተማ፣ ከሑዳዴ ጾም እና የፋሲካ እርድ ጋር በተያያዘ ከበዓሉ ቀን ጀምሮ ሁከት ተፈጥሮ እንደነበር የተገለጸ ሲኾን፤ በቡድን ተደራጅታችሁ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል የታሰሩ ከኻያ ያላነሱ ሰዎችም ፍ/ቤት ቀርበው በነፃ እና በዋስ ተለቀዋል፡፡ በጾም ወቅት የከተማዋ ሉካንዳ ቤቶች እንዳይዘጉ ሲከላከሉ ነበር በተባሉ ግለሰቦች ስጋት ተፈጥሮ መቆየቱን የተናገሩ የከተማዋ ነዋሪዎች፤ በበዓሉ ዕለት በተከፈተ አንድ ሉካንዳ ቤት ደግሞ ሕገ ወጥ እርድ ተካሒዷል በሚል ሁከቱ መቀስቀሱን ጠቁመዋል፡፡ በሁከቱ በሉካንዳው ላይ ጉዳት የደረሰ ሲኾን ባለቤቱን ጨምሮ የከብቱን ቆዳ ገዝቷል የተባለ ነዋሪና ሥጋም ለመሸመት ሞክሯል የተባለ ሌላ ሰው በማዘጋጃ ቤቱ ታስረው መዋላቸው ተገልጧል፡፡በበዓሉ ማግሥት፣ የሉካንዳው ባለቤት ይቅርታ ጠይቆ የከብቱ ሥጋ ከተወገደ በኋላ ሉካንዳው ሥራውን ቀጥሎ የዋለ ሲኾን፤ ከቀትር በኋላም የከተማው አስተዳደር ሓላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በጉዳዩ የምክክር ስብሰባ ተካሒዶ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ስብሰባው ምሽቱን መጠናቀቁን ተከትሎ ግን፣ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች የወረዳውን ሊቀ ካህናት እና በከተማው የሚገኘውን የገርባ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ለወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያው ሎጅ ዛሬ ይመረቃል

በጉራጌ ዞን፣ በዕዣ ወረዳ ከአዲስ አበባ 189 ኪ.ሜ ላይ የተገነባውና ለወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያው ነው የተባለው “ደሳለኝ ሎጅ” በዛሬው ዕለት ይመረቃል፡፡   ምስራቅና ምዕራብ ጉራጌን በእኩል ቦታ ላይ የሚያገናኘው ሎጁ፤ 30ሺ ካ.ሜ መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ግንባታው 7 ዓመት እንደፈጀ ተገልጿል፡፡ሎጁ፤ በጉራጌ ባህላዊ የቤት አሰራር የተገነቡ ሁለት የባህል አዳራሾች፣ ዘመናዊ የምግብ አዳራሽ፣ 300 ሰዎችን የሚይዝ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ 600 ሰዎች የማስተናገድ አቅም ያለው የሚይዝ ሁለገብ አዳራሽ እንዲሁም በ3 ደረጃ የተዘጋጁ 50 የመኝታ ክፍሎች እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡  ቱሪስቶችን በመሳብ መዳረሻዎችን ለማስፋት ታስቦ የተገነባ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ነው መሆኑ የተነገረለት “ደሳለኝ ሎጅ”፤ ለ60 ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ተብሏል፡፡ በቀጣይም በሎጁ ዙሪያ የሚገኘውን ከ20ሺህ ካሬ ሜትር የሚበልጥ ቦታም የዱር አራዊትና የተለያዩ አእዋፋት የሚጠበቁበት ሥፍራ በማድረግ የሎጁ ማስፋፊያ ስራዎችን ለማከናወን መታቀዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡  ሎጁን ያስገነቡት ባለሀብት በአዲስ አበባ የሚገኘው የደሳለኝ ሆቴል ባለቤት ሲሆኑ ለረጅም አመታት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያካተበቱትን የዘመናዊ ሆቴል አገልግሎት ተሞክሮ በመጠቀም፣ ደረጃውን የጠበቀ ስራ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የሚዲያ ብዝሃነት ተከብሯል የሚለው እያነጋገረ ነው

አለማቀፉ የፕሬስ ቀን ባለፈው ማክሰኞ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት አዘጋጅነት፤ “የሚዲያ ብዝሃነትን  ያከበረች ሀገር-ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን ምሁራንና ጋዜጠኞች የሚዲያ ብዝሃነት አልተከበረም ሲሉ ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል፡፡ መሪ ቃሉ መሬት ያለውን ተጨባጭ እውነታ የሚገልጽ አይደለም ብለዋል - አስተያየት ሰጪዎቹ፡፡ የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር (ኢነጋማ) ፕሬዚዳንት አቶ ወንድወሰን ተሾመ በሰጡት አስተያየት፣ ቀኑ የሚከበረው በሙያቸው ምክንያት የታሰሩ፣ የተሰደዱና ጫና እየደረሰባቸው ያሉ ጋዜጠኞችን ለማሰብ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት ሌላ ወንጀል አግኝቼባቸዋለሁ ብሎ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በዚህ አጋጣሚ ከእስር ቢለቅ የሚጎዳው ነገር የለም ብለዋል፡፡ በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ የሚዲያ ሞኖፖሊ እየተስፋፋ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ የሀሳብ ብዝሃነትና የሚዲያ ብዝሃነት አለ ለማለት ያስቸግራል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ህብረት ፕሬዚዳንት አቶ አንተነህ አብርሃም በበኩላቸው፤ ሁሉም ሰው እኩል የመናገር፤ የመደመጥና ሃሳቡን የማንፀባረቅ እድል ያገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ጠቅሰው፤ በመንግስት በኩል ዜጎች ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ክልከላ ባይኖርም የበለጠ እድሎች ሊከፈቱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የ “አዲስ ገፅ” መፅሄት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በሰጠው አስተያየት፤
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ጐርፍ በድሬደዋ ለሦስተኛ ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ

የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል ከተማዋ አሁንም የጎርፍ አደጋ ያሰጋታል፤ ተባለ    በድሬደዋ ከትናንት በስቲያ ለሦስተኛ ጊዜ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በከተማዋ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ጠቆመ፡፡ ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ እስከ ንጋቱ 1 ሰዓት ድረስ በተከታታይ በድሬደዋና አካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ፤ ገንደጋራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ሰው ሲወስድ፣ ሃሉቡሳ በተባለ አካባቢም አንድ የ10 ዓመት ህፃን ልጅ በጎርፉ ተወስዶ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል፤ በ“ሃርላ” አካባቢ በጎርፍ ምክንያት የኤሌክትሪክ ምሰሶ ወድቆ አንድ ሰው በኤሌክትሪክ አደጋ መሞቱንና 7 ያህሉ መቁሰላቸውን የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኢንስፔክተር ገመቹ ካቻ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በእለቱ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በሰዎች ላይ ካስከተለው ጉዳት በተጨማሪ  ድሬደዋን ከመልካ ጀብዱ የሚያገናኘው ድልድይ ሙሉ ለሙሉ መፍረሱንና የሁለቱ አካባቢዎች ግንኙነት መቋረጡን ኢንስፔክተሩ ጠቁመው፣ ከከተማዋ ወደ አዲስ አበባ የሚያስወጣው መንገድም በጎርፍ ክፉኛ በመቦርቦሩ አደጋው የሚቀጥል ከሆነ መንገዱ ሙሉ ለሙሉ ሊዘጋ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ የቤት
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የመዝገቡ ተሰማ ሥዕሎች ለዕይታ ይቀርባሉ

ታዋቂው ሰዓሊ መዝገቡ ተሰማ የሰራቸው ትልልቅና አዳዲስ ስዕሎች፣ “የአዲስ አባ ልጅ” በሚል ስያሜ፣ ሐሙስ  በብሔራዊ ሙዚየም ለተመልካቾች ይታያሉ፡፡ምናባዊ ፈጠራንና ተዓማኒነትን ባጣጣመ ድንቅ የስዕል እውቀትና ክህሎት የላቀ የጥበብ ደረጃ ያሳየ አርቲስት እንደሆነ የሚነገርለት ሰዓሊ መዝገቡ፤ “ንግስ” በተሰጥኦ ትርኢት ያቀረባቸው  ስዕሎች ከፍተኛ አድናቆት አትርፈውለታል፡፡ በታሪክ ተጠቃሽ የሆኑ የስዕል ስራዎቹንና ምርጥ ችሎታውን ማሳየት የጀመረው ከ20 ዓመታት በፊት ቢሆንም፤ በየጊዜው የፈጠራና የችሎታ ምጥቀትን የሚመሰክሩ ስራዎች በማበርከት ይታወቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት “ንግስ” በሚል ስያሜ ያቀረባቸው ስዕሎች በበርካታ የሚዲያ ተቋማት መነጋገሪያ  ርዕስ ለመሆን የበቁትም፤ ስዕሎቹ በፈጠራ ሃሳብና በስዕል ችሎታ አዲስ ደረጃን ያሳያሉ በሚል ነበር፡፡ በርካታ ተመልካቾችን የማረከው ይሄው “ንግስ” የስዕል ትርዒት፣ እንደገና ለእይታ እንዲከፈት በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የነበረ ሲሆን፤ የተወሰኑት ስዕሎች በአሁኑ ትርዒት እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ “የአዲስ አባ ልጅ” ለተሰኘው ትርዒት የተሰሩ  አዳዲስ የመዝገቡ ስዕሎች፤ ከወትሮው የተለዩ አይደሉም፤ እንደ ወትሮው በአዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችና በጥበብ ክህሎት  የተሰሩ ስዕሎች ናቸው፡፡ የፊታችን ረቡዕ ምሽት ተመርቆ ሐሙስ ለተመልካች የሚከፈተው ትርኢት 20 ስዕሎችን
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በአዲስ ከተማ አንድ ጎልማሳ ራሱን አቃጥሎ ገደለ

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 2፣ ልዩ ቦታው ጭላሎ ሆቴል ገባ ብሎ እድሜው  55 ዓመት ገደማ ይሆናል የተባለ ጎልማሳ ራሱን አቃጥሎ ገደለ፡፡ ይሄይስ ደምሴ የተባለው ይኸው ጐልማሳ፣ ሐሙስ ጠዋት 12 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያ ቤቱ በረንዳ ላይ ሰውነቱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ እሳት በመለኮስ፣ ራሱን አቃጥሎ እንደገደለ የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ሟች ራሱን ሲያቃጥል የተመለከተች የግቢው ተከራይ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ተጐጂውን ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ቢሞከርም ህክምና ቦታ ሳይደርስ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡ ግለሰቡ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ሰላማዊ የወዳጅነት ግንኙነት ያለውና ከሁሉም ጋር ተግባቢ እንደነበር የጠቀሱት የቅርብ ወዳጆቹ፤ እነሱ እስከሚያውቁት ድረስ ምንም ዓይነት ለዚህ አሰቃቂ ድርጊት የሚያደርስ እክል እንዳልነበረበት ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በዚህ መንገድ ህይወቱ ማለፉ የአካባቢውን ህብረተሰብ ማስደንገጡንም ምንጮቻችን አክለዋል፡፡ ሟች ይሄይስ ደምሴ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን እያከራየ በሚያገኘው ገቢ ይተዳደር የነበረ ሲሆን ትዳርም እንዳልመሰረተ የአካባቢው ምንጮቻችን ጠቅሰው፤ ለረጅም አመታት በብቸኝነት ይኖር እንደነበር አስረድተዋል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በዚያው ዕለት 9 ሰዓት ላይ በአማኑኤል ቤተ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

በብሔራዊ ስቴዲየም ግንባታ አፈር ተደርምሶ 2 ሰዎች ሞቱ

በግንባታ ወቅት በደረሱ አደጋዎች 11 ሰዎች ሞተዋል     በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው ብሄራዊ ስቴዲዬም የመሰረተ ጉድጓድ ቁፋሮ ላይ የነበሩ ሁለት የቀን  ሰራተኞች አፈር ተደርምሶባቸው ከትናንት በስቲያ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ዘንድሮ በተመሳሳይ አደጋ የ11 ሰዎች  ህይወት ማለፉን ለማወቅ ተችሏል፤ በግንባታ ሥራ ላይ እየደረሱ ያሉ አደጋዎችም አሳሳቢ ሆነዋል፤ ተብሏል፡፡ በቀን  ሠራተኞቹ ላይ አደጋው ሊደርስ የቻለው፣ 10 ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ 18 ወጣቶች ገብተው እየቆፈሩ፣  የሚያወጡትን አፈር ከጉድጓዱ ጫፍ ብዙም ሳይርቁ በመቆለላቸው አፈሩ ወደ ጉድጓዱ ተመልሶባቸው በመናዱ  መሆኑን ከአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ያገኘነው መረጃ  ያመለክታል፡፡  ከትናንት በስቲያ አመሻሽ ላይ አደጋው በደረሰበት ወቅት፣ የ25 እና የ28 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወጣቶች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሌላው ወጣት በእሳትና ድንገተኛ አደጋ መካከል ሰራተኞች ትብብር ከተደረመሰው አፈር ውስጥ ወጥቶ ህይወቱ ሊተርፍ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡ በወቅቱ ወቅት በጉድጓዱ ውስጥ ከነበሩት 18 የቀን ሰራተኞች 11 ያህሉ መጠነኛ ጉዳቶች እንደደረሰባቸውና ቀሪዎቹም ከአደጋው
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

ከቦሌ መድኃኔዓለም በስጦታ ተበረከተ የተባለው 104 ሺሕ ብር እያነጋገረ ነው

“ለምስጋና የተደረገ ነው” (የካቴድራሉ ዋና ጸሐፊ)   የደመወዝ ጭማሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስለተደረገላችሁ የአንድ ወር የደመወዝ ጭማሬአችሁን ለስጦታ አዋጡ ተብለን  በግዳጅ ሰጠን፤ ሲሉ አንዳንድ የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ካህናትና ሠራተኞች አስታወቁ፡፡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የካቴድራሉ ካህናት ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ የደመወዝ ጭማሬው በሀገረ   ስብከቱ ሲጸድቅ እንዲከፈላቸው የተወሰነው ካሳለፍነው ጥር ወር ጀምሮ ነበር፡፡ ክፍያውን ሳይፈጽም እስከ የካቲት  ወር የቆየው አስተዳደሩ ግን፣ ካህናትንና ልዩ ልዩ ሠራተኞችን ሰብስቦ፣ “ይህን ያደረጉልንን የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ እና የሒሳብ እና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊ ልናመሰግናቸው ይገባል፤” በማለት ኮሚቴ ማዋቀሩን ይገልጻሉ፤ ኮሚቴውም ካህናቱን ሳያወያይ የጥር ወር ጭማሬን በፈቃዳቸው ለመተው እንደወሰኑ አድርጎ በግቢው ፊርማ ማሰባሰብ ይጀምራል፤ ያልፈረሙ ጥቂት ሠራተኞች ቢኖሩም ደመወዛቸው ግን ለስጦታው በሚል ተቆርጧል፡፡  ለ164 ያህል ካህናትና ሠራተኞች ከጥር ወር አንሥቶ የተደረገው የደመወዝ ጭማሬ ከ450 እስከ 880 ብር እንደሚደርስ የጠቆሙት ምንጮቹ፤ 104 ሺሕ 90 ብር ከፈረሙትም ካልፈረሙትም ደመወዝ ተቆርጦ ለምስጋና በሚል ለሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች በስጦታ መልክ ተሰጥቷል፤ ብለዋል፡፡“ሙስና
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የቤንሻንጉል ክልል መንግስት እና ትምህርት ሚኒስቴር ተከሰሱ

ለአሶሳ ዩኒቨርስቲ ግንባታ ሲባል ከ6 አመት በፊት ለተወሰደብን የእርሻ መሬት ካሣ ወይም ምትክ መሬት አልተሰጠንም ያሉ ከ400 በላይ አርሶ አደሮች የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስትንና ትምህርት ሚኒስቴርን ከሰሱ፡፡ አርሶ አደሮቹ በወኪላቸው አቶ በለጠ አባተ በኩል ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት የፍትሃ ብሄር ክስ የ63 ሚሊዮን 445ሺ 371 ብር ካሣ ጠይቀዋል፡፡ 402 የሚሆኑት ከሳሾች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት አሶሳ ወረዳ ውስጥ በግብርና ይተዳደሩ እንደነበር ጠቅሰው በ2001 ዓ.ም ለልማት ተብሎ 163 ሄክታር የእርሻ መሬታቸው ምንም አይነት ካሣ ሳይከፈል ወይም ምትክ መሬት ሳይሰጣቸው ስለተወሰደባቸው ላለፉት 6 አመታት ከግብርና ያገኙት የነበረው ገቢ ተቋርጦ፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለውና ለችግር ተዳርገው እንደሚገኙ በክስ አቤቱታቸው አስታውቀዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ በመሬቱ ላይ ከሚያበቅሉት የተለያዩ ሰብሎች በአመት በአማካይ ያገኙ የነበረውን ገቢ በማስላትና እንዲሁም ቀደም ሲል ጫካ የነበረውን ይህን መሬት ለመመንጠር ያወጡትን ወጪ በመደመር ካሣው እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ላለፉት 6 አመታት የክልሉ መንግስት ካሳውን እንዲከፈላቸው ወይም ምትክ የከተማ ቦታ እንዲሠጣቸው በሠላማዊ ሠልፍ ጭምር
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የዘንድሮ የትንሳኤ በአል ገበያ ምን ይመስላል?

በተለያዩ የአዲስ አበባ የገበያ ስፍራዎች ተዟዙረን የበዓል ገበያ ዋጋን ለመቃኘት እንደሞከርነው፤ በአብዛኛው ከዓምና ተመሳሳይ የበዓል ገበያ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ በአቃቂ ቄራ ገበያ የበሬ ዋጋ ከ5 ሺህ እስከ 22 ሺህ ብር ድረስ ሲሆን ዓምና በተመሳሳይ በዓል የበሬ ዋጋ ከ8 ሺህ ብር እስከ 25 ሺህ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በአቃቂ ቄራ፡- የበግ ዋጋ ከ700 ብር እስከ 3500 ብር ሲሆን በዓምና የፋሲካ ገበያም በግ ከ900ብር እስከ 3500 ብር ተሸምቷል፡፡ በአቃቂ የቁም እንስሳት ቄራ ገበያ፣ ከፍተኛው የፍየል ዋጋ 7ሺህ ብር መሆኑን ከነጋዴዎች የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ በገበያው ቋሚ የበግና የፍየል ነጋዴ የሆነው ወጣት መስፍን ይልማ፤ በግና ፍየሎችን ከአዳማና አርሲ አካባቢ አምጥቶ እንደሚሸጥ ገልፆ፤ ዘንድሮ ገበሬው በግና ፍየል ለነጋዴው እየሸጠበት ያለው ዋጋ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በአማካይ እስከ 200 ብር ቅናሽ ማሳየቱን ተናግሯል፡፡ ገበሬው ለመጪው ክረምት የሰብል ምርት የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት የትንሳኤ በዓል የከብት ገበያን እንደመልካም አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ይኸው ነጋዴ ገልጿል፡፡ በአዲስ አበባ ዋናው ቄራ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የዶ/ር ነጋሶ “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” መፅሐፍ ዛሬ ይወጣል

አንጋፋው የታሪክ ምሁርና ፖለቲከኛ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ የፃፉትና በአዳዲስ የምርምር ውጤቶች ላይ ተመስርቶ እንደተዘጋጀ የተነገረለት “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” የተሰኘ አዲስ መፅሃፍ ዛሬ በገበያ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡ መፅሃፉ የኦሮሞ ህዝብ አመጣጥ ታሪክ ላይ ከዚህ ቀደም የሚታወቁ እውነታዎችን የሚሞግት ሲሆን የኦሮሞ ታሪክ በኢትዮጵያ የሚጀምረው በ16ኛው ክ/ዘመን እንደሆነ ሲገለፅ የቆየው የተሳሳተ መሆኑን ይጠቁማል፡፡በኢትዮጵያ ታሪክ ማስተማሪያ መፃህፍት ላይ ሳይቀር የኦሮሞ ህዝብ በ16ኛው ክ/ዘመን መነሻውን ከባሌ መደወላቡ አድርጎ ወደ ሰሜን መስፋፋቱ ተተርኳል የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ የኦሮሞ ህዝብ ከ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በፊት፣ ከላሊበላ የስልጣኔ ዘመን ጀምሮ በሰሜኑና መካከለኛው የሀገሪቱ ክልል የኖረ ህዝብ ነው፤ ብለዋል፡፡ ማህበረሰቡ ከሰሜን ወደ ደቡብ የተስፋፋ እንጂ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተስፋፋ አለመሆኑን ዶ/ር ነጋሶ በመጽሐፋቸው ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ ሲማሩ፣ መምህራቸው ፕ/ር ዶ/ር ታደሰ ታምራት፤ “የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖትና የክርስቲያን ዐፄ አገዛዝ ወደ ደቡብ መስፋፋት” የሚለውን የታሪክ ክፍል ሲያስተምሯቸው፣ በ13ኛው ክ/ዘመን በሰሜን ሸዋ ገላና እና ያያ የሚባሉ ህዝቦች ቆርኬ ለሚባል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የጋምቤላ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 7 ሰዎች በእስራት ተቀጡ

ክልሉን ከፌደሬሽኑ ለመገንጠል ተንቀሳቅሰዋል ተብሏል     የጋምቤላን ክልል ከፌደሬሽኑ በኃይል ለመገንጠል ሙከራ አድርገዋል የተባሉት የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 7 ግለሰቦች ከ7 ዓመት እስከ 9 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው፡፡ የክልሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ ኦኳይ፤ ከዚህ በፊት በምንም ወንጀል ተከሰው እንደማያውቁ፣ ከ1978 እስከ 1992 ለ13 ዓመታት በጤና ቢሮ የተለያዩ ኃላፊነቶች ማገልገላቸውንና ክልሉን በፕሬዚዳንትነት መምራታቸውን በመግለፅ የቅጣት ማቅለያ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ በ9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡  በተመሳሳይ ዴቪድ ኡጁሉ የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነው በድርጊቱ ከፍተኛ ተሳትፎ እንደነበራቸው በመረጋገጡ ፍ/ቤቱ በ9 ዓመት እስራት ይቀጡ ብሏል፡፡ ቀሪዎቹ ኦታካ ኡዋራ፣ ኡማንኤው፣ ኦቦንግ አሞኮ፣ ኡጁሉ ቻም እና ኦቻን ኦፒዮ በንቅናቄው ውስጥ በአባልነት በመሳተፋቸውና የቡድኑን አላማ አውቀው ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ ጥቃት ለመፈፀም በዝግጅት ላይ ስለነበሩ፣ በ7 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡   
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓቱን ከሙስና ለማጽዳት

የ33 ሚ. ዶላር ብድር ፀደቀ    የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ስርአቱን ከሙስና የፀዳ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት የሚደግፍ የ33 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰሞኑን አፀደቀ፡፡ ከአለም አቀፉ የልማት ማህበር የተገኘው ይኸው ብድር፤በክልልና በፌደራል ደረጃ የወጭ አስተዳደር ስርአቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖረው ያስችላል ብሏል፤ምክር ቤቱ፡፡ ብድሩ የኦዲት የሶፍትዌር ግዢን ለመፈፀም፣ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ስርአት በአግባቡ መዘርጋቱን የሚያረጋግጥ ኩባንያ ለመቅጠርና ሌሎች መሰል ተግባራትን ለማከናወን ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡ ከጠቅላላ የብድር ገንዘብ ውስጥ የተቋማት የተጠያቂነት ስርአትን ለማጠናከር 9.1 ሚሊዮን ዶላር፣ የወጪ ቁጥጥር የመረጃ ስርአቱን ለማዘመን 22.4 ሚሊዮን ዶላር የሚመደብ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀሞች ለመገምገምና የግዥ ስርአት ለመዘርጋት ይውላል ተብሏል፡፡  ብድሩ ከወለድ ነፃ ሲሆን የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 አመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል፡፡ ብድሩ በረጅም ዓመታት መከፈሉ ከሀገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣምና ጫናውም ያልበዛ መሆኑን የጠቆመው ምክር ቤቱ፤መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተጀመረውን ሰፊ እንቅስቃሴ ከግብ ለማድረስ እንደሚረዳ ጠቁሟል፡፡  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News

የቻይናው ቲቢኢኤ፤ ከፍተኛ የሃይል ማስተላለፊያ መስመር ይዘረጋል

ፕሮጀክቱ በ12 ወራት ይጠናቀቃል ተብሏል     የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአቃቂ ቦኮየ አቦ፣ በቂልንጦና በቦሌ ለሚ ለሚያሰራው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከቻይናው ቲቢኢኤ ጋር ኮንትራት ተፈራረመ፡፡ ባለፈው ማክሰኞ በሂልተን ሆቴል የተደረገውን የፊርማ ሥነ-ስርዓት፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀና የቲቢኢኤ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሽ ፋን ፈርመዋል፡፡ ኮንትራቱ ሁለት ንዑስ ማስተላለፊያ ጣቢያዎችና የትራንስሚሽን መስመር ተከላ ሲኖረው የንዑስ ጣቢያው ኮንትራት፣ የኮየ አቦ 400 ኪሎ ቮልት፣ የቅሊንጦ 230 ኪሎ ቮልትና የቦሌ ለሚ 230 ኪሎ ቮልት ዲዛይን፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አቅርቦት፣ መልሶ ተከላና ሥራ ማስጀመርን ያጠቃልላል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባን የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን የሪል እስቴትና በኮየ አቦ፣ በኮየ ፍቸ፣ ቂሊንጦና በቦሌ ለሚ አካባቢ ለሚቀርበ አዳዲስ የኃይል ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል ተብሏል፡፡ የትራንሚሽን መስመር ኮንትራቱ ደግሞ በሦስቱ ንዑስ ጣቢያዎች መካከል ያለውን 26 ኪ.ሜ 400 ኪሎ ቮልትና 230 ኪሎ ቮልት  ዲዛይን፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ምሰሶ ማቆምና ሥራ ማስጀመርን ያካትታል፡፡ የሁለቱም ፕሮጀጅቶች ማጠናቀቂያ ጊዜ 12 ወራት ሲሆን የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 82
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News