የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የምልአተ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር፤ “የመሪ ዕቅድ ጥናቱ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ሊነጋገርበት ይገባል”

መሠረታዊ ችግር ሊኾን የሚችለው፣ ክፍተት ለምን ተፈጠረ የሚለው ሳይኾን ክፍተት መኖሩ እየታወቀ ዝም ብሎ መኖሩ ነው፤ ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ ቤተ ክርስቲያኑን ለመደገፍና ለማልማት የሚያደርገው ቀና ትብብር ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ተሰፋ ሰጪ ኾኖ ይታያል፤ ሐዋርያዊ ተልእኮን ለማስፋፋት በተደረገው እንቅስቃሴ÷ ከምዕራብ አሜሪካ እስከ ጃፓን፤ ከአየርላንድ እስከ አውስትራልያ ቤተ ክርስቲያናችን ክንፎቿዋን የዘረጋችበት ኹኔታ በመፈጠሩ ዓለም አቀፋዊት ወደ መኾን አድጋለች […]
Post a comment