የባህርዳሩ አማራ ክልል ምሁራን መማክርት ጉባዔ 

መንግስት ከምሁራን ጋር ተባብሮ ባለመስራቱ ችግሮችን የማቃለል እድል ሳይኖረው መቆየቱ ተነገረ። ይህ የተገለፀዉ በባህር ዳር ዛሬ በተጀመረው የአማራ ክልል ምሁራን መማክርት ጉባዔ ላይ ነዉ። ከመክፈቻ ንግግሮች በኋላ ዉይይቱ ለጋዜጠኞች ዝግ በመሆኑ የዉይይቱ ይዘት በርግጥ ምን ላይ መሆኑ ለማወቅ አለመቻሉ ተመልክቶአል። …