የሕዝቡ ጥያቄ እና የልኂቃኑ መልስ

ምርጫ 97 በውዝግብ ከተጠናቀቀ በኋላ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተስፋ እንደገና ወደኋላ ተመልሷል። የተቃዋሚ ቡድኖች የትግል ስልትም እንደዚሁ ተቀይሮ ከፊሉ በስደት፣ከፊሉ ነፍጥ አንስቶ፣ ቀሪው ተበታትኖ ስርዓቱን በብዙ አቅጣጫ ሲታገሉት ከርመዋል። ገዢው ፓርቲም ይህንን የተቃዋሚዎቹን ጥረት ለማደናቀፍ በአዋጅ እና በአሠራር ጠብ እርግፍ ሲል ከርሟል።…