ዝክረ-አሌክሳንደር ፎን ሑምቦልት፤ 250ኛ ዓመት

መስከረም በጠባ የመጀመሪያው ቅዳሜ ነበር ወደዚህ ዓለም ብቅ ያለው። ሣይንቲስት ብቻም አልነበር። መጻዒውን ተንባይ፤ ሀገር አሣሽ፤ ተመራማሪ እና ገድለኛም ጭምር እንጂ፤ ጀርመናዊው የተፈጥሮ ሳይንስ ጠቢብ አሌክሳንደር ፎን ሑምቦልት። የተፈጥሮ አሳሹ ሳይንቲስት እነሆ! ቅዳሜ መስከረም 3 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ከተወለደ 250ኛ ዓመቱ ይታሰባል።…