በኢትዮጵያ ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት

ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በነገው ትውልድ ላይ ሰፊ አደጋ «የጋረጠ» ያሉት ይህ ችግር ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ አሳስበዋል። የሴቶች ግርዛት በስፋት ይካሄድባቸው የነበሩት የአፋርና ከሐረሪ ክልል ተወካዮች፣ በአሁኑ ጊዜ የሴቶች ግርዛት በጣም መቀነሱን ተናግረዋል። በገጠር አካባቢዎች ግን የተፈለገውን ያህል ውጤት አለመገኘቱንም ገልጸዋል።…