የኑሮ ውድነት በባሕር ዳር

የኑሮ ውድነት የየዕለቱ የሕይወት ፈተና እንደሆነባቸው የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች አመለከቱ።  በተለይ የሽንኩርትና የጤፍ ዋጋ  ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በመጨመሩ በልቶ ማደር አስቸጋሪ መሆኑን ነው የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች የሚናገሩት። ዘይት እና ሥጋ ለመመገብ ዋጋው በመወደዱ ቅንጦት ሆኗል እና አልቻልንምም ይላሉ። …