አደጋ ላይ የወደቀዉ የኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዓመት በመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ላይ ባደረገው ከፍተኛ መሻሻል የኋሊት የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦበታል ሲል የዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አሳሰበ። ሰሞኑን ጋዜጠኞችን ማሰሩና የሐገሪቱን መከላከያ ሚንስቴር ወታደራዊ ሚስጥር አወጡ ያላቸዉን ጋዜጠኞች እንደሚከስ ማስታወቁ ለፕረስ ነፃነት አደገኛ ነዉ።…