ስም ከመቃብር በላይ ነው

አዲሷን የብራዚል ዋና ከተማ ትናንት ጎበኘናት፡፡ ገና 59 ዓመቷ ነው፡፡ አሠራሯ ግን የሚያስደንቅ ነው፡፡ ጽድት ያለች ከተማ፡፡ ወደ ታች እንጂ ወደ ላይ ፎቅ መደርደር የማይፈቀድባት፡፡ በዛፎች የተሞላች የጫካ ውስጥ ከተማ፡፡ እንደ ሰላሌ መስክ የተንጣለሉ፣ እንደ ቶራ መስክ የሚያማልሉ፣ እንደ ደንቢያ መስክ የማዕበል ቅርጽ ያላቸው ፓርኮች የሞሉባት ከተማ፡፡ ከተማዋን ለመሥራት የታሰበው እኤ…