በአሜሪካ እና በቻይና የንግድ ጦርነት ማን ያሸንፋል?

ቻይና እና አሜሪካ የዓለም ገበያን መረጋጋት ከነሳው የንግድ ጦርነት የማፈግፈግ ምልክት አላሳዩም። ቻይና 60 ቢሊዮን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካን ሸቀጦች ላይ የምታስከፍለውን ታሪፍ ከፍ አድርጋለች። ታሪፉ ከ10 እስከ 25 በመቶ ይደርሳል። የሁለቱ አገሮች ፍጥጫ መቼ እንደሚረግብ ባይታወቅም በዓለም ምጣኔ ሐብት ላይ የሚያሳድረው ጫና ግን አስግቷል…