የመጤ እና ተዛማች አረሞች ስጋት

አንዳንድ እፅዋት በተፈጥሮ ከሚገኙባቸው አካባቢዎች ወደ ስፍራ በየትኛውም አጋጣሚ ተዛውረው ሲስፋፉ በመጤነት እንደሚፈረጁ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የምርምር ጽሑፎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆን ተብለውም ሆነ በአጋጣሚ ወደ ሀገር የገቡ መጤ ተክሎች ወይም አረሞች ውለው አድረው ለመሬቱም ሆነ ለውኃ አካላት ስጋት መሆን መጀመራቸው እየተነገረ ነው።…