ኢትዮጵያ የልዑል ዓለማየሁ አፅም እንዲመለስ ግፊት እያደረገች ነው

ኢትዮጵያ የልዑል ዓለማየሁን አፅም ጨምሮ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ቅርሶቿን ከብሪታኒያ ለማስመለስ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች። ከ150 አመታት ገደማ በፊት ከኢትዮጵያ ተወስዶ በብሪታኒያ ሕይወቱ ያለፈው የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ አፅም እንዲመለስ የመጀመሪያውን ጥያቄ ያቀረቡት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ነበሩ።…