አምስት ፓርቲዎች ሊዋሐዱ ነው

አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊዋሐዱ መሆኑን አስታወቁ። በመጪው ሐሙስ ይፈፀማል በተባለው ውሕደት ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እንደሚቋቋም በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል። አቶ ተሻለ ሰብሮ የሚመሩት የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ በውኅደቱ ተስማምቶ ሒደቱን ቢጀምርም በስተመጨረሻ ግን ኢራፓና ሌሎች ሁለት ፓርቲዎች በውህደቱ አልተገኙም።…