ስፖርት፤ ሚያዝያ  14 ቀን፣ 2011 ዓ.ም

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ የዋንጫ ትንቅንቃቸው ተጠናክሯል። ኹለቱ ቡድኖች የደረጃ ሰንጠረዡን ተራ በተራ በበላይነት እየተፈራረቁበት ነው። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ በሳምንቱ ማሳረጊያ በግብ የተንበሸበሸው ቦሩስያ ዶርትሙንድ ከኃያሉ ባየር ሙይንሽን  ጋር ያለው ልዩነት የአንድ ነጥብ ብቻ ነው።…