«ሕክምና ቅዱስ ነው አታርክሱት» ተቃውሞ የወጡ ተለማማጅ ሐኪሞች

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ “ሙያችን ይከበር፤ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ንቃ” ሲሉ ተደምጠዋል። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ከሚያዝያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ተቋማት ውይይት እንደሚደረግ አስታውቋል…