በደቡብ አፍሪቃ የብዙኀን ነፍሳት መጥፋት: በሊቀ ጳጳሱ ላይ አቤቱታው ተጠናክሯል፤ ምእመናን፥ የታዳጊ ያለኽ እያሉ ነው፤ ኮሚዩኒቲው አስጠነቀቀ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ እያጣራ ነው

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ለደቡብ አፍሪቃውያን፥ የነፃነት አርኣያ፣ የማንነት መለዮ እና የድኅነት ተስፋ ነበረች፤ በነጋዴው ብፁዕ አባ ያዕቆብ የጋንጎችና አፋኞች አመራር ግን የማያባራ ትርምስና የምእመናን ልቅሶ ማዕከል ኾና ትገኛለች፡፡” ˜˜˜ ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አባ ያዕቆብ፣ የኖላዊነት አደራቸውን ዘንግተው ከቻይና ሸቀጥ እያስመጡ የሚነግዱ ኾነዋል፤ በቤተ ክርስቲያን ስምና በአገልግሎት ሽፋን ግለሰቦችን(ኢአማንያንን ሳይቀር) ወደ ደቡብ አፍሪቃ በማስገባት ከፍተኛ …