ሦስትም አንድም ሆኑ

ቃዛፊ እንደ ጦር ኃይሎች ጠቃላይ አዛዥ ያዋጉትን ጦርነት፣ አብዱል አዚዝ ቡተፈለቃ እንደ እዉቅ ዲፕሎማት ሲዘዉሩት ነበር።የአረቦችን ዉጊያ ዲፕሎማሲ ቃዛፊ ከትሪፖሊ-ካይሮ-ደማስቆ፣ ቡተፈሊቃ ከአልጀርስ፣ፓሪስ፣ኒዮርክ  ሲያሾሩት የ29ኝ ዓመቱ ወጣት የጦር መኮንን ሲና ግንባር ከእስራኤል ጦር ጋር ይፋለም ነበር።…