ስፖርት፤ ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2011 ዓ.ም

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ዋንጫውን ለማንሳት በማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል መካከል ትንቅንቁ ቀጥሏል። የኹለቱም ቡድን አሰልጣኞች ከእንግዲህ መሸነፍ የለም ሲሉ ፎክረዋል። ኹለቱም በአሸናፊነታቸው ከቀጠሉ ሊቨርፑል የዓመታት ሕልሙ መክኖ ይቀራል። ማንቸስተር ሲቲ በአንድ ጨዋታ ከተዘናጋ ነገር ይበላሽበታል። …