የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቃጠሎ አልቆመም

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ወደ 400 ሔክታር መሬት አጥፍቷል። ቃጠሎው ዋልያና ጭላዳ ዝንጀሮ በሚገኙባቸው የፓርኩ ክፍሎች መድረሱን ወደ ቦታው የተጓዘው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ተናግሯል። በባሌ እና ሀላይደጌ አሰቦት ተመሳሳይ ቃጠሎ ደርሶ የዜጎችን ትብብር ለመለመን የተገደደችው ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሐብቷን መታደግ ለምን ተሳናት?…