በኮንጎ 700 ለሚሆኑ የፖለቲካ እስረኞች ምህረት ተደረገ

አዲስ ተመራጩ የኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌልክስ ትሲኪዲ በቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ መንግሥት ለታሰሩ ወደ 700 የፖለቲካ እስረኞች ምህረት አደረጉ። ትናንት ከእስር ከተለቀቁት እስረኞች መካከል የሐገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ረብሻችኋል በሚል በካቢላ መንግሥት ታስረዉ የነበሩት ሦስቱ ታዋቂ የመንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ይገኙበታል።  …