የብሪታንያ ፓርላማ የብሬግዚት ውልን ዳግም ተቃወመ  

ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ከአውሮጳ ሕብረት ጋር የተስማሙበትን ሀገራቸው ከሕብረቱ የምትወጣበትን ውል ለሁለተኛ ጊዜ ትንናት ማታ ውድቅ አድርጎታል። ፓርላማው በተለይ ብሪታንያ ከሕብረቱ አባልነት ከለቀቀች በኋላ በሰሜን አየርላንድ እና በአየርላንድ መካከል ያለው ድንበር ክፍት ሆኖ እንዲቆይ የሚጠይቀውን የውሉን ክፍል ነው የተቃወመው።…