የኢራን አብዮት ምክንያት፣ዉጤትና መዘዙ

 ሻሁ የዘመናት አንፀባሪቂ ጀንበራቸዉ በ38ኛዉ ዓመት ከምዕራብ አድማስ ጥግ መድረሷን የተረዱት መሠለ።ጥር 1979 «ለዕረፍት» በሚል ሰበብ ጓዛቸዉን ጠቅልለዉ ከቴሕራን ዉልቅ አሉ።በወሩ የአመፁ በተለይ እስልምናን እንደ ርዕዮተ ዓለም አንግበዉ የሚታገሉ ወገኖችን— ይመሩ የነበሩት ታላቁ አያቱላሕ ሩሆላሕ ኾሚኒ ከ16 ዘመን ስደት በኋላ ቴሕራን ገቡ…