ናይጄሪያ ቸል ያለችው የአፍሪቃ ነጻ የንግድ ቀጠና ምሥረታ

አዲስ አበባ በሽር ጉድ እንግዶቿን እየተቀበለች ትገኛለች። የከተማይቱ ዋና ዋና መንገዶች በተለይ የአፍሪቃ መሪዎች እና ከፍተኛ ፖለቲከኞች የሚዘዋወሩባቸው ጸድተዋል። ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥርም በከተማዋ ይታያል። በሒደት ላይ የሚገኘው የአፍሪቃነፃ የንግድ ቀጠና ምሥረታ በ32ኛው የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ቁልፍ ቦታ እንደሚኖረው ይጠበቃል።…