በፓትርያርኩ እንደራሴ አስፈላጊነት ከስምምነት ተደረሰ፤ “ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ቅ/ሲኖዶሱ ተስማምቶ ካልወጣ ለሕዝብም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ብለዋል

በምልዓተ ጉባኤው ውሎ በተደረሰው መግባባት፤ የእንደራሴው መመዘኛ፣ ፓትርያርኩን የማገዝ ተግባሩና ሓላፊነት ደንቡ በቀጣዩ ጉባኤ ይታያል፤ በልዩ ጽ/ቤቱ፣ ለሥራ ዕንቅፋት የኾኑ ሰዎች ተነሥተው፣ እንዲስተካከልና እንዲረጋጋ ይደረጋል፤ የገዘፈ ችግር ያለበት የአ/አበባ ሀ/ስብከት፣ በረዳት ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ሕጉ የሚሻሻል ይኾናል፤ ፓትርያርኩ፣ ስለወቅታዊ ኹኔታዎች ያላቸው አረዳድ ውስንነት ምደባውን አስፈላጊ አድርጎታል፤ ተግባር የሚሻው የልዩ ጸሐፊውና የጨለማ አማካሪዎች ግፍና አውዳሚነት አጽንዖት አግኝቷል፡፡ …




Post a comment