ቋሚ ሲኖዶስ: ለደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስን በሥራ አስኪያጅነት ሾመ፤ አባ ጥዑመ ልሳን አዳነ ወደ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተጠርተዋል

ቋሚ ሲኖዶስ፥ በዛሬ ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ በአስተዳደራዊ ውዝግብ ሲታመስ በቆየው የደቡብ አፍሪቃ አህጉረ ስብከት እና የጆሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ደብር ጉዳይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔው መሠረት፣ ላለፉት ዓመታት አህጉረ ስብከቱን በሥራ አስኪያጅነት ደብሩንም በአስተዳዳሪነት ሲመሩ ከሰበካ ጉባኤው ጋር በፈጠሩት ውዝግብ፣ ለምእመናኑ አንድነትና ከሀገሪቱ ሕግም አንፃር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ህልውና ከፍተኛ ስጋት …
Post a comment