የሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ: መናፍቃንንና ምንደኞቻቸውን ማጥራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፤ የተባረረው ከፍ ያለው ቱፋ ከፍተኛ ውሳኔ እንዲተላለፍበት ተጠይቋል

የኮሌጁ አስተዳደር ጉባኤ ከማታ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት ጋር ተወያይቷል የበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ: በሃይማኖት ድርድርም ኾነ መሸማቀቅ የለም፤ ብለዋል ዘካርያስ ሐዲስ: ለተጠርጣሪዎች በሽምግልና ተልከዋል፤ መባሉን አስተባብለዋል መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን፣ የቤተ ክርስቲያናችን ነባር አስተምህሮ በዘመናዊ አቀራረብ የሚሰጥባቸው የወንጌላውያንና ዘመናውያን ምሁራን መፍለቂያ ምንጮች ናቸው፡፡ የአብነት ትምህርቱን ከዘመናዊው ጋር አዋሕደው በመሠልጠን ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሊቃውንትንም እያፈሩ ቆይተዋል፡፡ …
Post a comment