ሰበር ዜና – ዐውደ ርእዩ በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዳይካሔድ የተከለከለው በመንግሥት ትእዛዝ ነው፤ “ላልተሟሉት ቅድመ ኹኔቻዎች” ማዕከሉ ሓላፊነቱን ወስዷል

ፈቃዱን ለመስጠት ይመለከተዋል የተባለው የአዲስ አበባ አስተዳደር፣ “ለዐውደ ርእይ ፈቃድ የመስጠት አሠራር የለኝም፤ በእንግዳ ሕግ ፈቃድ ለመስጠት አልችልም፤” ብሏል፡፡  “ዝግጅቱን ለማካሔድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ኹኔታዎችን በተሟላ መልኩ ኤግዚቢሽን ማዕከሉ ለአዘጋጆች ባለመግለጹና እንዲያሟሉ ባለማስቻሉ ዝግጅቱ በተያዘለት ፕሮግራም ሊካሔድ አልቻለም፡፡”/ማዕከሉ/ በተፈጠረው ክፍተት ላይ ከማኅበሩ ጋር ተከታታይና ሰላማዊ ውይይት ማድረጉን የገለጸው ማዕከሉ፥ “ለማኅበረ ቅዱሳን፣ ለተሳታፊዎችና ለተመልካቾች ከፍተኛ ይቅርታ ይጠይቃል፤” …
Post a comment