ቅ/ሲኖዶስ: በመላው ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ዐወጀ፤“ባሳለፍናቸው ሳምንታት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በመሪር ሐዘንና በጸሎት እናስባቸዋለን”

የካቲት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚአሃ ይከውን ሰላምክሙ፤ (የአገርን ሰላም እሹ ፈልጉ የአገራችኹ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና)  የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ የሀገርና የወገን ፍቅር ያለው ሕዝብ፥ ሰላም ከእግዚአብሔር መኾኑን ያውቃል፤ ሰላም ለሰው ልጆች ከማናቸውም መሠረታውያን …
Post a comment